Вы находитесь на странице: 1из 65

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

የአካባቢ፣ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን

የአካባቢ ተ ፅዕኖ ግምገማ መመሪያ

ቁጥር 001/2010

ሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም


ባህር ዳር
ማውጫ ገጽ

1 መግቢያ.............................................................................................................................................1
2 ዓላማዎች...........................................................................................................................................2
3 አጭር ርዕስ........................................................................................................................................2
4 ትርጉም.............................................................................................................................................2
5 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርት ዝግጅት..................................................................................................6
5.1 አጠቃላይ መግለጫ (Executive Summary)...........................................................................6
5.2 መግቢያ (Introduction).........................................................................................................7
5.3 የአካባቢ ተጽእኖ ጥናቱ ዓላማ..........................................................................................................7
5.4 የጥናቱ ወሰን...............................................................................................................................7
5.5 የጥናቱ ስልት ወይም ዘዴ...............................................................................................................8
5.6 በጥናቱ ወቅት የተወሰዱ ታሳቢዎች እና የነበሩ የእውቀት ክፍተቶች............................................................8
5.7 የፖሊሲ፣ የህግና የአስተዳደር ማዕቀፎች..............................................................................................9
5.8 የፕሮጀክቱ ገለፃ............................................................................................................................9
5.9 የባዮፊዚካልና ማህበረ-ኢኮኖሚ መሰረታዊ መረጃዎች ትንተና...................................................................9
5.10 የአካባቢ ተጽዕኖ ትንተና ማካሄድ...................................................................................................10
5.11 የተፅዕኖ ማቅለያ እርምጃዎች.........................................................................................................11
5.12 የአካባቢ አያያዝ እቅድ.................................................................................................................11
5.13 የአካባቢ ክትትል/ምርመራ እቅድ....................................................................................................12
5.14 በፕሮጀክቱ ትግበራ ተጽእኖ የሚደርስባቸውና የሚመለከታቸው አካላት ምክክር ማካሄድ...............................13
5.15 ማጠቃለያና ምክረ-ሃሳብ..............................................................................................................14
5.16 ዋቢ መፃህፍት/ማጣቀሻዎች..........................................................................................................14
5.17 እዝሎች...................................................................................................................................14
5.18 የነባርና ማስፋፊያ ፕሮጀክት የአካባቢ አያያዝ እቅድ ዝግጅት..................................................................15
6 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርትን ስለመገምገም........................................................................................15
6.1 በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርት ግምገማ ወቅት ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች.....................................15
6.2 የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሪፖርት ተቀባይነት ላይ ውሳኔ ስለመስጠት.......................................................18
6.3 ስለ አካባቢ ይሁንታ ፈቃድ የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ...........................................................................19
7 የፕሮጀክት ትግበራ ስለሚከለከልባቸዉና ስለሚሰረዝባቸው አግባቦች................................................................20
8 የአካባቢ ህግ ማስከበር ግብረ-ሀይል ስለማቋቋም፣ተግባርና ኃላፊነት.................................................................22
9 ለአካባቢ አማካሪ ድርጅቶችና ባለሙያዎች የአማካሪነት የሙያ ፈቃድ ስለመስጠት...............................................24
9.1 የአካባቢ ተጽዕኖ ዘገባ የማዘጋጀት ስልጣን.........................................................................................24
9.2 በአካባቢ አማካሪነት ስራ ለመሰማራት መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች...................................................24
9.3 የሙያ ብቃት ማስረጃ በአዲስ ለማውጣትና ለዕድሣት አገልግሎት ክፍያ....................................................25
9.4 የአካባቢ አማካሪ ድርጅቶችና ባለሙያዎች ተግባርና ኃላፊነት..................................................................26
9.5 ለምዝገባ መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች...............................................................................................28
9.6 የአማካሪ ድርጅት ወይም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አሰጣጥ ሂደት.............................................29
9.7 ስለምስክር ወረቀት አሰጣጥና ይዘት.................................................................................................30
9.8 ስለቅሬታ አቀራረብ.....................................................................................................................30
10 የይሁንታ ፈቃድ ሳይዙ ወደ ተግባር የገቡና የሚገቡ ፕሮጀክቶችን አሰራር ስለመወሰን........................................31
11 ስለአካባቢ ወሰን ልየታ ሪፖርት ዝግጅት...............................................................................................33
11.1 የወሰን ልየታ አሰራር ቅደም ተከተል................................................................................................33
11.2 የወሰን ልየታ ዘገባ ስለሚይዛቸው ዝርዝር ሃሳቦች.................................................................................34
11.3 የወሰን ልየታ ሪፖርትን በተመለከተ የባለሙያዎች ተግባርና ኃላፊነት.........................................................37
12 ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ህጎች.......................................................................................................38
13 መመሪያ ስለማሻሻል........................................................................................................................38
14 መመሪያዉ የሚጸናበት ጊዜ...............................................................................................................38
15 ዕዝሎች.......................................................................................................................................39
15.1 የአካባቢ አያያዝ እቅድ ፎርማት......................................................................................................39
15.2 የአካባቢ ክትትል እቅድ ፎርማት.....................................................................................................40
15.3 የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሪፖርት ግምገማ ማጠቃለያ ቅፅ....................................................................41
15.3.1 የአካባቢ ተጽእኖ ጥናት ዘገባ መገምገሚያ ዝርዝር መመዘኛ ቅፅ.......................................................42

15.3.2 የተፅዕኖ ግምገማ ሪፖርቱን ለመገምገም የሚጠቅሙ ማብራሪያዎች..........................................54

15.4 የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ ያገኘ ፕሮጀክት የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ....................55
15.5 የአካባቢ አማካሪ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ምልመላ፣ መመዘኛና ማወዳደሪያ መስፈርት..................................56
15.6 በአካባቢ ዘርፍ የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናትና ኦዲት አገልግሎት የሚሰጡ አማካሪ ባለሙያዎች መስፈርት.................59
15.7 በአካባቢ ዘርፍ የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናትና ኦዲት አገልግሎት የሚሰጡ አማካሪ ድርጅቶች መስፈርት....................60
15.8 ማመልከቻ ቅጾች........................................................................................................................61
15.8.1 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ባለሙያ የሚሞላ የአገልግሎት
መጠየቂያ ቅጽ አዲስ ለሚጠየቁ..............................................................................................................61

15.8.2 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ባለሙያ የሚሞላ
የአገልግሎትመጠየቂያ ቅጽ ደረጃ ለማሳደግ................................................................................................63

15.8.3 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ባለሙያ የሚሞላ የአገልግሎት
መጠየቂያ ቅጽ እድሳት ለሚጠይቁ..........................................................................................................65

15.8.4 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ባለሙያ የሚሞላ
የአገልግሎትመጠየቂያቅጽ ለጠፈ ምስክር ወረቀት ምትክ ለሚጠይቁ.................................................................67

ii
15.8.5 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ድርጅት የሚሞላ የአገልግሎት
መጠየቂያ ቅጽ የምስክር ወረቀት ለሚጠይቅ..............................................................................................68

15.8.6 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ድርጅት የሚሞላ የአገልግሎት
መጠየቂያ ቅጽ ደረጃ ለማሰደግ...............................................................................................................70

15.8.7 በአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ድርጅት የሚሞላ የአገልግሎት መጠየቂያ
ቅጽ የብቃት ማረጋገጫን ለማሳደስ..........................................................................................................72

15.8.8 በአማካሪ ድርጅት የሚሞላ የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ ለጠፋ የምስክር ወረቀት ምትክ ለሚጠይቁ...........74

15.9 የፕሮጀክት ባለቤቱ የውል ስምምነት................................................................................................75

iii
1 መግቢያ

ቀጣይነትና ዘለቄታ ያለው ልማት ለማምጣት የአካባቢ ደህንነትን ማረጋገጥ አንዱና ዋነኝው ተግባር ሲሆን ይህንን
ለማረጋገጥ ደግሞ ወደ ትግበራ የሚገቡ ፕሮጀችቶች ከመተግበራቸው በፊት በአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሂደት
እንዲያልፉ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በሌላ መልኩ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሪፖርት ሳያቀርቡና የይሁንታ ፈቃድ ሳይዙ ወደ ትግበራ የገቡ
በርካታ ፕሮጄክቶች በመኖራቸው በአካባቢ ላይ ተፅዕኖ እያደረሱ በመሆኑና ይህንን ችግር የሚያስተካክል
ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤ የሚዘጋጀውም ሪፖርትም ደረጃዉን የጠበቀ እንዲሆን ብቃት ባላቸዉ
ባለሙያዎች እንዲዘጋጅ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በአካባቢና በማህበረሰቡ ላይ የሚያደርሱትን የተጽዕኖ ደረጃዎች በመለየት የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ


ሪፖርት እንዲያቀርቡ የሚገደዱና የማይገደዱ ፕሮጀክቶችን መለየት አስፈላጊ በመሆኑ፤

የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርት ወጥነት ያለውና ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል በቂ መረጃ እንዲይዝ ለማድረግ
ሪፖርቱ የሚያካትታቸውን ይዘቶች ለመወሰንና የቀረበውን ሪፖርት ለመገምገም የሚያስችሉ ወጥነት ያላቸው ዝርዝር
መስፈርቶችን ማዘጋጀት በማስፈለጉ፤

ይህንንም ተከትሎ በክልሉ ውስጥ የሚካሄደውን የአካባቢ ብክለትና ብክነት የመቆጣጠር ስልጣን የተሰጠው
የክልሉ የአካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ በቁጥር 232/2008 አንቀጽ
6 ንዑስ አንቀጽ 14 እና አንቀጽ 18 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት መመሪያ የማውጣት ስልጣን የተሰጠው በመሆኑና
የክልሉ ምክር ቤት ያወጣው የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ አዋጅ ቁጥር 181/2003 ድንጋጌዎች የአፈጻጸም መመሪያ
እንደሚወጣላቸው የተመላከተ በመሆኑ፤ ይህ የአፈጻጸም መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

መመሪያውም ለክልሉ አካባቢ ምክር ቤት ቀርቦ የጸደቀ ሲሆን ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ተወስኗል፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በፊት ሲሰራበት የነበረው የአካባቢ አማካሪዎች የሙያ ፍቃድ ለመስጠት የወጣ
መመሪያ ቁጥር 01/2006 ዓ.ም በዚህ መመሪያ ተሽሯል፡፡

2 ዓላማዎች

1) የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርት ለማዘጋጀትና ሪፖርቱን ለመመርመር የሚያግዙ ዝርዝር


አሰራሮችን ለመወሰን፤

2) የአካባቢ አማካሪዎች የሙያ ፈቃድ እና የአካባቢ አማካሪ ድርጅቶች ፈቃድ አሰጣጥን ለመወሰን፣
3) የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት የሚያስፈልጋቸውንና የማያስፈልጋቸውን ፕሮጀክቶች ምድብ ለመለየት፣

4) የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሪፖርት ሳያቀርቡና የይሁንታ ፈቃድ ሳያገኙ ወደ ተግባር የገቡና የሚገቡ
ፕሮጀክቶችን አሰራር ለመከታተልና የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ፣

5) የፕሮጀክት ትግበራ የሚከለከልባቸዉን አግባቦች ለመለየት

6) የአካባቢ ተጽእኖ ጥናት የወሰን ልየታ (scoping) ሪፖርት ይዘትን የሚመለከቱ ዝርዝር
አሰራሮችንና የሪፖርት አቀራረብ መመሪያ ለማዘጋጀት፡፡

3 አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ መመሪያ ቁጥር 001/2010 ዓ.ም” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

4 ትርጉም

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፣

1) “ባለስልጣን” ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት


ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ማለት ነው፡፡
2) “አካባቢ ” ማለት በመሬት፣ በከባቢ አየር፣ በአየር ሁኔታ እና በአየር ንብረት፣በውኃ፣ በሕያዋን፣
በድምፅ፣ በሽታ፣ በጣዕም፣ በማሕበራዊ ጉዳዮች እና በሥነ ውበት ሳይወሰን በተፈጥሯዊ
ሁኔታቸው ወይም በሰው አማካኝነት ተሻሽለው ወይም ተለውጠው የሚገኙ ነገሮች በሙሉ
ያሉበት ቦታ፣ እንዲሁም መጠናቸውን ወይም ሁኔታቸውን ወይም ደግሞ የሰው ወይም
የሌሎች ሕያዋን በጎ ሁኔታን የሚነኩ መስተጋብሮቻቸው ድምር ነው ፡፡
3) “የአካባቢ ጥበቃ ” ማለት የሰው ልጅን ጨምሮ የማንኛውም ሕይዎታዊ አካልና እድገት
የሚወስኑ የመሬት፣ የውኃና የአየር እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ የአካባቢ ሀብቶች፣
ክስተቶችና ሁኔታዎች እንዳይጠፉ፣እንዳይቀንሱ ወይም ባህሪያቸዉ እንዳይለወጥ የመንከባከብ
ተግባር ነው፡፡
4) “የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ” ማለት ኘሮጀክት፣ ፖሊሲ፣ እቅድ ወይም ፕሮግራም ተግባራዊ
ሲሆን፣ ሲስፋፋና ሲቋረጥ በአካባቢ ላይ የሚያስከትለውን ጠቃሚም ሆነ ጎጅ ዉጤትን ለይቶ
የማወቂያና ለችግሮችም ማቃለያ ወይም ማስወገጃ ዘዴን የሚያመላክት ሂደት ነው፡፡
5) “ተፅዕኖ ” ማለት በአካባቢ ወይም በንዑሳን ክፍሎች ላይ በሚፈጠር ለውጥ ምክንያት
ማንኛውም በሰው ጤና ወይም ደህንነት፣ በዕፅዋት፣ በእንስሳት፣ በአፈር፣ በአየር፣ በውኃ፣
በአየር ንብረት፣በተፈጥሮአዊ ወይም በባሕላዊ ቅርስ፣ በሌላ ቁሳዊ አካል ወይም በአጠቃላይ
ሲታይ በአካባቢያዊ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ ወይም በባሕላዊ ገጽታዎች ላይ የሚከሰት
ተከታይ ለውጥ ነው፡፡

2
6) “ብክለት ” ማለት በዚህ አዋጅ ወይም አግባብ ባለዉ ሌላ ህግ የተደነገገን ማንኛዉም ግዴታ፣
ማዕቀብ ወይም ገደብ ጥሶ የማንኛዉንም አካባቢ ክፍል ቁሳዊ፣ ጨረራዊ፣ ሙቀታዊ፣ ንጥረ
ነገራዊ፣ ስነ ህይወታዊ፣ ወይም ሌላ ባህርይን በመለወጥ የተፈጠረ በሰዉ ጤና ወይም በጎነት
ወይም ደግሞ በሌሎች ህያዋን ላይ አደገኛ የሆነ ወይም አደገኛ ሊሆን የሚችል ሁኔታ ነዉ፡፡
7) “በካይ ” ማለት ፈሳሽ፣ ጠጣር ወይም ጋዝ የሆነ በቀጥታም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ፡-
ያረፈበትን የአካባቢ ክፍል ጥራት በመለወጥ ጠቀሜታ የመስጠት አቅሙን የሚያጓድል ወይም፣
በሰው ጤና ወይም በሌሎች ሕያዋን ላይ ጉዳት የሚያደርስ ወይም ሊያደርስ የሚችል
መርዝን፣ በሽታን፣ ክርፋትን፣ ጨረርን፣ ድምፅን፣ ንዝረትን፣ ሙቀትን፣ ወይም ሌላ ክስተትን
የሚያመነጭ ማንኛውም ነገር ነው፡፡
8) “ፕሮጀክት ” ማለት ማንኛውም አዲስ የልማት እንቅስቃሴ፣ ወይም በነባር ድርጅት ላይ
የሚደረግ ጉልህ መስፋፋት ወይም ለውጥ፣ ወይም ተቋርጦ የነበረ ሥራን መልሶ ለመጀመር
የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡
9) “ነባር ፕጀክቶች ” ማለት የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ አዋጅ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊትና
ከዚያም በኋላ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሳያካሂዱ ወደ ትግበራ የገቡ ፕሮጀክቶች ማለት
ነዉ፡፡
10) “የፕሮጀክት ባለቤት ” ማለት የልማት ተግባሩ በመንግሥት የሚካሄድ ሲሆን የሚመለከተው
የመንግሥት አካል፣ ወይም በግሉ ዘርፍ የሚካሄድ ሲሆን ባለሀብት የሆነው ሰው ወይም
በሁለቱም የሚካሄድ ሲሆን የሚመለከተዉ የመንግስት አካልና ባለሀብት የሆነዉ ሰዉ ነዉ፡፡
11) “ፈቃድ ሰጭ መስሪያ ቤት ” ማለት እንደሁኔታዉ የኢንቨስትመንት፣ የንግድ ወይም የስራ
ፈቃድ ለመስጠት ወይም የንግድ ድርጅት ለመመዝገብ በህግ ስልጣን የተሰጠዉ ማንኛዉም
የመንግስት አካል ነዉ፡፡
12) “ተሻጋሪ ” ማለት ከአንድ ቀበሌ ወደ ሌላ ቀበሌ ወይም ከወረዳ ወደ ሌላ ወረዳ ወይም ከዞን
ወደ ሌላ ዞን ኘሮጀክቱ የሚያስከትለው ወይም ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት መተላለፍ
ወይም መዛመት ማለት ነው፡፡
13) “የይሁንታ ፈቃድ ” ማለት ማንኛውም ሰው ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት ለቢሮዉ ወይም
ለሚወክለው አካል የሚያቀርበው ፕሮጀክት ወይም ሰነድ ወይም ፕሮግራም ወደ ሥራ ቢገባ
የጎላ ችግር የሌለበት መሆኑን በአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ መመዘኛ መሠረት ተረጋግጦ ሥራውን
እንዲሠራ የሚሰጥ ፈቃድ ነው፡፡
14) “መንግሥታዊ ሰነድ ” ማለት ፖሊሲ፣ ስልት፣ የረጅም ጊዜ መርኃ ግብር፣ ሕግ ወይም ዓለም
አቀፍ ስምምነት ነው፡፡
15) “ክልል ” ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልል ነዉ፡፡
16) “በተዋረድ ያለ የአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤት ” ማለት የዞን፣ የወረዳ ወይም የቀበሌ አካባቢ
ጥበቃ መስሪያ ቤት ማለት ነዉ፡፡
17) “የአካባቢ ተቆጣጣሪዎች ” ማለት ለቁጥጥር ስራ በባለስልጣኑ ወይም በተዋረድ በባለስልጣኑ
ስር ባለ መስሪያ ቤት የሚሰየሙ ባለሙያዎች ማለት ነዉ፡፡
18) “ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው::

3
19) “ምድብ 1 ወይም ሙሉ የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት የሚያስፈልገው ፕሮጀክት” ማለት የፕሮጅከቱ ትግበራ
በአካባቢና ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያደርስና ተጽዕኖውን ለመቀነስ (ለማስቀረት) ጥልቅ
የአካባቢ ተጽእኖ ጥናት ዘገባ እንዲቀርብባቸው ከሚገደዱ ፕሮጀክቶች ምድብ ውስጥ የሚካተት ፕሮጀክት ነው፡፡
20) “ምድብ 2 ወይም ከፊል የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት የሚያስፈልገው ፕሮጀክት” ማለት በፕሮጀክቱ ትግበራ
የሚከሰቱ የአካባቢና ማህበራዊ ተጽእኖዎች ስፋት መለስተኛ የሆነ (ዉስብስብ) ያልሆነና ተጽዕኖው በማቃለያ
እርምጃዎች የሚቀረፍ ፕሮጀክት ምድብ ሲሆን መካከለኛ ጥልቀት ያለው የተጽዕኖ ጥናት ዘገባ እንዲያቀርብ
ይገደዳል፡፡
21) “ምድብ 3 ወይም የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት እንዲያካሂዱ የማይገደዱ ፕሮጀክቶች” ማለት ፕሮጀክቶች
በሚያከናውኗቸው ተግባራት ምክንያት በተናጠልም ሆነ በተደማሪነት በአካባቢ ላይ የጎላ ተጽዕኖ የሌላቸው
ወይም በአካባቢ ላይ አወንታዊ ተጽእኖ የሚኖራቸው ፕሮጀክቶች ምድብ ሲሆን በዚህ ምድብ ውስጥ የሚካተቱ
ፕሮጀክቶች የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ማካሄድ አያስልጋቸውም፡፡
22) “የመጀመሪያ ደረጃ የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት” ማለት ፕሮጀክቶች በሚያከናዉኗቸዉ ተግባራት የተነሳ የሚከሰቱ
የአካባቢ ተጽእኖዎችን ደረጃና የጥናት አይነት ለመለየት አስቸጋሪ ሲሆን የተጽዕኖዎችን ደረጃና የሚያስፈልገውን
የጥናት አይነት ለመለየት የሚካሄድ የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት አይነት ነው፡፡
23) “በቀላሉ ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ ወይም ልዩ ጥንቃቄ የሚሹ አካባቢዎች” ማለት በተፈጥሮ አደጋ ወይም ሰዎች
በሚያካሂዱት የዕለት ተዕለት የልማት እንቅስቃሴ ምክንያት የጎላ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊደርስባቸው እና በቀላሉ
ሊጠፉ የሚችሉ ወይም አንዴ ከጠፉ መልሰው ሊተኩ የማይችሉ ነገር ግን ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣
ባህላዊ፣ ታሪካዊና አካባቢያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብቶች ናቸው፡፡
24) “ተዳማሪ ተፅዕኖ” ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶች በአንድ አካባቢ ሲተገበሩ የሚያስከትሉት የአሉታዊ
ተፅዕኖ ድምር ወይም የሁለትና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶች መስተጋብር ውጤት በአካባቢው ካሉ ፕሮጀክቶች ድምር
ተጽዕኖ በላይ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲፈጠር ነው፡፡
25) “የአካባቢ ክትትል” (monitoring) ማለት በአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ሪፖርት ውስጥ በአካባቢ አያያዝ
ዕቅድ ላይ የታቀዱ የማቅለያ ተግባራት ስለመፈፃመቸው፣ ከተተነበዩ ተጽዕኖዎች በተጨማሪ ሌሎች አዳዲስ
ተፅዕኖዎች ስለመከሰታቸው፣ በመሰረታዊ የአካባቢ መረጃ ላይ የተለዩ የአካባቢ ጉዳዮች በትግበራ ጊዜ ምን ያህል
እንደተለወጡ፣ የፕሮጀክት ትግበራ ከወጡ የአካባቢ ህጎች ጋር ምን ያህል ተጣጥሞ እየተተገበረ እንደሆነና
የማቅለያ ተግበራት አፈጻጸም ውጤታማነትን ለመገምገምና ወቅቱን የጠበቀ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ
የሚያስችል ስልታዊና ተከታታይነት ያለው መረጃን የመሰብሰብ፣ የመለካት፣ የመተንተንና የማስተካከያ እርምጃ
የመውሰድ እና የመደገፍ ሂደት ነው፡፡
26) “የአካባቢ ምርመራ” (Auditing) ማለት አጠቃላይ የፕሮጀክቱን አፈፃፀም ከወጡ የአካባቢ ህጎችና
ደረጃዎች ጋር ምን ያህል ተጣጥሞ እየሄደ እንደሆነ ለመገምገም፣ በአካባቢ ተጽዕኖ ጥናቱ የተለዩ ተጽዕኖዎችን
ለመቀነስ (ለማቃለል)፣ የታቀዱ ተግባራትን አፈፃፃምና ውጤታማነት ለማረጋገጥ፣ እየተተገበረ ያለው የአካባቢ
አያያዝ እቅድ ያመጣውን ለውጥ ለመገምገም ወይም ፕሮጀክቱ ከአንዱ አካል ወደሌላ አካል ከመዛወሩ በፊት
ያለውን አጠቃላይ የአካባቢ አያያዝ ሁኔታ ለማወቅ እንዲሁም ሊደርሱ የሚችሉ የአካባቢ ተጽዕኖዎችና አደጋዎችን
ለመለየት እና ለችግሮቹ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችል የአካባቢ መረጃን በተወሰነ የጊዜ ክፍተት የመሰብሰብ፣
የመለካት፣ ያሉ ሰነዶችንና ሪፖርቶችን የመመርመርና የመተንተን ሂደት ነው፡፡
27) “የአካባቢ ቁጥጥር” (Inspection) ማለት ጥርጣሬ ሲኖር ወይም ጥቆማ ሲደርስ የሚካሄድ ድንገተኛ
የአካባቢ ፍተሻ ወይም ቀደም ሲል በተካሄደ የአካባቢ ክትትልና ምርመራ ላይ የተሰጠ ግብረመልስን የአፈፃፀም

4
ደረጃ ለማረጋገጥ ወቅቱን ባልጠበቀ ምልከታ የምናረጋግጥበትና በቁጥጥሩም መሰረት የተለያዩ ህጋዊና
አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃዎችን የምንወስንበት ሂደት ነው፡፡
28) “የአካባቢ ወሰን ልየታ” ማለት የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት በሚካሄድበት ወቅት በትኩረት (በጥልቀት) መታየት
ያለባቸው ዋና ዋና ጉዳዮችና ተፅዕኖዎች የሚለዩበትና የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ለማካሄድ የሚያገለግል የጥናት
እቅድ የሚዘጋጅበት የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ሂደት ክፍል ነው፡፡
29) “የተፅዕኖ ማቅለያ እርምጃዎች” ማለት በፕሮጀክት ትግበራ ወቅት በአካባቢና በማህበረሰብ ላይ የሚደርሱ
አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ለመቀነስ ወይም በተወሰነ ደረጃ ለማስቀረት ካልሆነም ደግሞ ለማካካስ የሚከናወኑ
የተጽዕኖ ማቃለያ ተግባራት ናቸው፡፡

5 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርት ዝግጅት

የሚዘጋጀው የአካባቢ ተፅእኖ ግምገማ ሪፖርት የኘሮጀክቱን አሉታዊና አወንታዊ ተጽዕኖዎች የለየ፣ ፕሮጀክቱ
ሲተገበር ስለሚወሰዱ የአካባቢ ተጽዕኖ ማቃለያ እርምጃዎች በቂ መረጃ የያዘ መሆን አለበት፡፡ የፕሮጄክቱ
ባህሪ የሚያስገድድ ካልሆነ በቀር ሪፖርት የሚቀርበው በአማርኛ ቋንቋ ይሆናል፡፡ የፕሮጄክቱ
ባለቤት የውጭ አገር ዜግነት ያለው ከሆነ በእንግሊዝኛ ሪፖርት ሊቀርብ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን
ከሚቀርበው ሪፖርት ውስጥ የአካባቢ አያያዝና የክትትል እቅዱ ክፍል በአማርኛ ተተርጉሞ የሪፖርቱ
አካል ሆኖ ይቀርባል፡፡ የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ዘገባ ሲዘጋጅ መካተት የሚገባቸዉ ዝርዝር ጉዳዮች የሚከተሉት
ይሆናሉ፡-

5.1 አጠቃላይ መግለጫ (Executive Summary)

ይህ ክፍል ከሁለት ገጽ ያልበለጠ ሆኖ የፕሮጀክቱ ገምጋሚዎችና ውሳኔ ሰጭ አካላት የፕሮጀክቱን ምንነት፣


ተጽዕኖዎችንና የተጽእኖ ማቃለያ መንገዶችን በቀላሉ እንዲረዱት የሚያስችል ክፍል ነው፡፡ በመሆኑም አጠቃላይ
መግለጫው ስለፕሮጀክቱ ግልፅ፣ ትክክለኛና የማይጣረስ መረጃ ሊይዝ ይገባል፡፡ ይህ ክፍል ገምጋሚዉ የውሳኔ ሀሳብ
ለመስጠት የሚያግዙትን ዋና ዋና ግኝቶችና ምክረ-ሀሳቦች የሚዳስስበት ክፍል ነው፡፡ በዚህ ክፍል የሚከተሉት ጉዳዮች
መካተት ይኖርባቸዋል፡- የፕሮጀክቱ ስምና አድራሻ (መገኛ ቦታ)፤ የፕሮጀክቱ ባለቤት ስም፤ ጥናቱን ያጠናው አማካሪ
ድርጅቱ ስም፤ የፕሮጀክቱ ምንነት አጭርና ግልጽ ማብራሪያ፤ የፕሮጀክቱ ቦታ አጭርና ግልጽ የመነሻ መረጃ፤
የፕሮጀክቱ አማራጮች፤ በፕሮጀክቱ ምክንያት ይከሰታሉ ተብሎ የሚገመቱ ዋና ዋና የአካባቢ ተፅእኖዎች፤ የተለዩ
የተጽእኖ ማቅለያ ዘዴዎች (የገንዘብ ወይም በአይነት ካሳን ጨምሮ)፣ የአካባቢ ክትትል ስራዎችና የማስተግበሪያ
ስልት፡፡

5.2 መግቢያ (Introduction)

ይህ ክፍል የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የመነሻ ሀሳብ የሚገለጽበትና የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናቱ አደረጃጀት የሚመላከትበት
ክፍል ሲሆን ጽሁፉ ከሁለት ገጽ መብለጥ የለበትም፡፡ የጥናቱም መግቢያ የሚከተሉትን ነጥቦች በግልፅ ማሳየት
ይኖርበታል፡፡
1) የፕሮጀክቱ ወይንም የጥናቱ መነሻ ሀሳቦች፤

5
2) የፕሮጀክቱ ፕሮፖዛል መግለጫ ባጭሩ (ዓላማ፣ የፕሮጀክቱ መገኛ ቦታ፣ የተለዩ አማራጮች ለምሳሌ ከቦታ፣
ከዲዛይን፣ ከአሰራር ሂደት፣ ከሚጠቀምበት ቴክኖሎጂ፣ ከግብዓትና ጥሬ ዕቃ አንጻር ወዘተ፣ የሚጠይቀውን
የኃይል ዓይነት፣ ፍጆታና ምንጭ እንዲሁም የሌሎች ሃብቶችን ፍላጎትና የፕሮጀክቱን የቆይታ ጊዜ)፤
3) የአካባቢ ተጽእኖ ጥናት ዘገባው አደረጃጀት፤
4) የጥናት ዘገባው አላማ፣ የባለሀብቱን ግዴታ፣ የህግ ተጠያቂነትንና በቀጣይ የሚከናዎኑ ተግባራትን የሚያገልጽ
መሆን አለበት፡፡

5.3 የአካባቢ ተጽእኖ ጥናቱ ዓላማ

ከፕሮጀክቱ ትግበራ በፊት የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ማካሄድ ያስፈለገበት ጥቅል አላማና የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናቱ
የሚያረጋግጣቸው ዝርዝር አላማዎች በዚህ ክፍል በአግባቡ ሊገለጹ ይገባቸዋል፡፡ የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናቱ በዚህ ክፍል
ለተለዩት ዝርዝር አላማዎች ምላሽ የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡

5.4 የጥናቱ ወሰን

ፕሮጀክቱ የአካባቢ ተጽእኖ ጥናት የሚያስፈልገዉ ከሆነና የአካባቢ ወሰን ልየታ ጥናት የተካሄደለት ከሆነ በዚህ ጥናት
በተካተተዉ ቢጋር ውስጥ የጥናቱ ጥልቀትና ስፋት በግልጽ መጠቀስ ይኖርበታል፡፡ ፕሮጀክቱ የአካባቢ ተጽእኖ ጥናት
ማካሄድ የሚያስፈልገው ከሆነ የጥናቱ ወሰን እንደ ፕሮጀክቱ አይነትና ፕሮጀክቱ እንደሚተገበርበት አካባቢያዊ፣
ማህበራዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ተለይቶ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡ የጥናት ወሰኑ የፕሮጀክቱን የጥናት ክልል
የሚያሳይ ካርታ ሊያካትት ይገባዋል፡፡

5.5 የጥናቱ ስልት ወይም ዘዴ

በዚህ ክፍል አወንታዊና አሉታዊ የአካባቢ ተፅእኖዎችን ለመለየት፣ ለመተንበይና ለመተንተን፣ እንዲሁም ያሉ
አማራጮችንና የማቃለያ እርምጃዎችን ለመለየትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማሳተፍ ጥቅም ላይ የሚውሉ
ዘዴዎች የሚገለጽበት የዘገባ ክፍል ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ክፍል የሚከተሉትን ነጥቦች በግልፅ ማስቀመጥ ይገባል፡-
1) ጥናቱን ለማካሄድ ጥቅም ላይ የሚውል የጥናት ስልት፣ የሚያስፈልግ ግብዓት፣ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎችና
የትንተና ዘዴዎች (ለምሳሌ የባለሙያዎች ሙያዊ አስተያየት፣ የአዋጭነት ትንተና፣ የመገምገሚያ ቅፆች፣ ከአሁን
በፊት ያሉ ልምዶች፣ የቦታ ሽፋን፣ ወዘተ)
2) የሚመለከታቸውን አካላት ለማሳተፍ ጥቅም ላይ የሚውል የማሳተፊያ ዘዴ ወይም ስልትና የተሳትፏቸው ደረጃ
3) በጥናቱ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ብዛት፣ የሙያ ስብጥር፣ ኃላፊነትና ሙሉ አድራሻ

5.6 በጥናቱ ወቅት የተወሰዱ ታሳቢዎች እና የነበሩ የእውቀት ክፍተቶች

በቂ የመረጃ ምንጭ ባለመገኘቱ የተነሳ ሊተገበር በታሰበው ፕሮጀክት ዙሪያ የሚሰበሰቡ መረጃዎች ከአጠራጣሪ
ምንጮች ሊሰበሰቡ ይችላሉ፡፡ በዚህ ምክንያት አንዳንድ የጥናት ዳሰሳዎች በግምት ወይም በመላምት ላይ ተመርኩዘው
ሊሰሩ ስለሚችሉ ተፅእኖዎችን ለመተንበይና ለመተንተን ክፍተት ሊገጥም ይችላል፡፡ ስለዚህ ጥናቱን የሚያዘጋጀው

6
አካል የሚከተሉትን ነጥቦች በማካተት የዳሰሳ ጥናቱን የእርግጠኛነት ደረጃ በግልፅ ማመላከት ይኖርበታል፡፡ በዚህ
ክፍል፡-
1) በጥናት ሂደት ያጋጠሙ የእውቀት ክፍተቶችን፣ በይሆናል የተወሰዱ መረጃዎችንና የመረጃ ምንጭ ያልተገኘላቸውን
ጉዳዮች ይለያሉ፣
2) መላምቶች ያልተሟሉ የሆኑበትን ምክንያት ይዘረዘራል
3) የተለዩት የእውቀት ክፍተቶችና መላምቶች በውሳኔ አሰጣጥ ላይ የሚኖራቸው እንድምታ
4) ያጋጠሙ እጥረቶችንና ውስንነቶችን ለማስወገድ የተወሰዱ መፍትሄዎች መገለጽ ይኖርባቸዋል፡፡

5.7 የፖሊሲ፣ የህግና የአስተዳደር ማዕቀፎች

ይህ ክፍል ፕሮጀክቱ ሲተገበር ሊፈጽማቸውና ሊመራባቸው የሚገቡ የፖሊሲና ህጋዊ ማዕቀፎችን የሚዘረዝር የአካባቢ
ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርት ክፍል ሲሆን ፕሮጄክቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የፖሊሲ፣ የህግና የአካባቢ ደረጃ
ማዕቀፎች በጥናቱ ይዳሰሳሉ፡፡ ከቦታውና ከፕሮጀክቱ ጋር ተገቢነትና ተያያዥነት ያላቸው ተጨማሪ የህግ ክፍሎች
በዕዝል ይያያዛሉ፡፡

5.8 የፕሮጀክቱ ገለፃ

በዚህ ክፍል የሚከተሉት ነጥቦች መካተትና መገለፅ አለባቸው፡-


1) የፕሮጀክቱ ስፋትና ባህሪ፣
2) ለፕሮጀክቱ የተለያዩ አማራጮች ግልፅ ማብራሪያ፣
3) የጥሬ እቃዎች ምንጭ፣ አይነት፣ ባህሪና መጠን፣
4) በምዕራፎች የተከፋፈለ የፕሮጀክቱ የትግበራ የጊዜ ሰሌዳ፣
5) የቴክኖሎጂ አይነትና የቴክኖሎጅ አጠቃቀም ገለጻ፣
6) የአመራረት ሂደት፣ የተረፈ-ምርቶችና ዋና ምርቶች አይነትና መጠን
7) የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ የማፅዳትና የማስወገድ ስርዓት፣
8) የሰውና የግብዓት ፍጆታ ወጪዎች፣

5.9 የባዮፊዚካልና ማህበረ-ኢኮኖሚ መሰረታዊ መረጃዎች ትንተና

በዚህ ክፍል የፕሮጀክቱን አካባቢዊ ሁኔታ የሚገልፅ መሰረታዊ መረጃ በመሰብሰብ አካባቢውን በትክክል የሚያሳይ
ዘገባ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ክፍል በፕሮጀክቱ ምክንያት ጉዳት ወይም ተጽዕኖ ስለሚደርስባቸው አካባቢዎች
ትኩረት በመስጠት ግልፅ ማብራሪያ ማካተት/መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ በመሆኑም መካተት የሚገባቸው መረጃዎች፡-
1) ፕሮጀክቱ የሚተገበርበትን ልዩ ቦታ የሚመለከት መረጃ (ለምሳሌ የአካባቢውን የመሬት ስሪት ወይም የይዞታ
ሁኔታ፣ በዙሪያው ስለሚገኝ የመሬት ሁኔታ፣ በአካባቢው ላይ ያሉና በግልፅ የሚታዩ ተግዳሮቶች፣ በፕሮጀክቱ
ውስጥና በአካባቢዉ ያለው የመሰረተ-ልማት አገልግሎት ሁኔታ ወዘተ)፣
2) አሃዛዊና አሃዛዊ ያልሆኑ ፊዚካላዊና ስነ-ህይወታዊ የአካባቢ መረጃዎች (ለምሳሌ፡- የአየር ንብረት፣ የአፈር፣ የውሃ
ሀብት፣ የስርዓተ ምህዳር፣ የመሬት አቀማመጥ፣ የዕፅዋትና የእንስሳት አይነት ስርጭትና ብዛት ወዘተ…….)፣

7
3) አሃዛዊና አሃዛዊ ያልሆኑ የማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ መረጃዎች (ለምሳሌ የህዝብ ቁጥርና ስርጭት፣ የዕድሜ
ስብጥር፣ የኢኮኖሚ እድገት ሁኔታ፣ የውልደትና የጤና ሁኔታ፣ የቤተሰብ የገቢ ሁኔታ መረጃ፣ የኑሮ ሁኔታ፣
የመሰረተ-ልማት አገልግሎት፣ የቤቶች ሁኔታ፣ የሃይል ፍጆታ፣ የውሃ አቅርቦት ወዘተ…..)
4) የባህላዊና ታሪካዊ ቦታዎች ገለጻ (ለምሳሌ ብሄራዊ ፓርኮች፣ የዱር እንስሳት መጠለያ ቦታዎች፣ የመስህብ
ቦታዎችና ሃውልቶች፣ በሰውና በእንስሳት ምስል የተሰሩ ሀውልቶች፣ ትኩረት የሚሰጣቸው ሃይማኖታዊ ቦታዎች
ወዘተ…..)፣
5) ተጽዕኖ የሚደርስበትን ቦታ የሚያመለክቱ ኮኦርድኔቶች፣ ከለር ፎቶግራፎች፣ ሰንጠረዥና ሌሎች ገላጭ መረጃዎች፣
6) የፕሮጀክቱ የትግበራ ቦታ ካርታና የፕሮጀክት ሳይት ፕላን፣
7) ፕሮጀክቱ ድንበር ተሻጋሪ ተፅዕኖ የሚያደርስ ከሆነ ተጽእኖ የሚደርስበት አካባቢ የፊዚካላዊና ስነ-ህይወታዊ
እንዲሁም የማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ መረጃዎች ናቸው፡፡

5.10 የአካባቢ ተጽዕኖ ትንተና ማካሄድ

ይህ ክፍል አዎንታዊና አሉታዊ የአካባቢ ተፅእኖዎች የሚለይበት፣ የሚተነበይበትና የሚተነተንበት ወሳኝ ክፍል ነው፡፡
የእያንዳንዱ ተፅእኖ ትንተና የሚከተሉትን ነጥቦች ሊያካትት ይገባል፡-
1) የእያንዳንዱ ተጽእኖ ግልጽ ማብራሪያና ትንታኔ (ምሳሌ የተፅዕኖው መጠን፣ የቦታ ስፋት፣ የሚቆይበት ጊዜ፣
ድግግሞሽ፣ ደረጃ፣ ተጽእኖ የደረሰበት አካባቢ ወደነበረበት መመለስ የሚቻል መሆኑና አለመሆኑ፣ ስጋትና
ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ክስተት፣ ተጽዕኖ የሚደርስባቸው ክፍሎች መጠን ወዘተ) መለየት፣
2) በፕሮጀክቱ ውስጥና አካባቢ የሚገኙ ተጽዕኖ የሚደርስባቸው አካላት ትንተና፣
3) ፕርጀክቱን ለመተግበር የተለዩ አማራጮች ንጽጽር (ስፋት/መጠን፣ መገኛ ቦታ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፕላን፣ የሃይል
ምንጭ፣ የጥሬ እቃዎች ምንጭ፣ ቴክኒካዊ ተፈጻሚነት፣ የአካባቢዊና ማህበራዊ ችግሮች/እጥረቶች)፣
4) አዲሱ ፕሮጀክት ከነባር ፕሮጀክቶችና ወደፊት ሊሰሩ ከታቀዱ ፕሮጀክቶች ጋር ሲዳመር ሊደርስ የሚችለውን
ተዳማሪ የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖ፣
5) የተጽዕኖ ትንበያ የእርግጠኛነት ደረጃ፣
6) የተሻሉ አማራጮችን ለመምረጥ የተሰበሰቡ መረጃዎች ምዘና ናቸው፡፡

5.11 የተፅዕኖ ማቅለያ እርምጃዎች

በፕሮጀክት ትግበራ ወቅት ጉዳት የሚያስከትሉ የፕሮጀክቱን ተግባራት ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ቀዳሚ አማራጭ
ተደርጎ መወሰድ ሲኖርበት ይህን ማድረግ ካልተቻለ ግን የተፅእኖ ማቃለያ ተግባራት በሚከተለው መልኩ ተዘርዝረው
መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
1) ለእያንዳንዱ ተፅእኖ በእያንዳንዱ የፕሮጀክት የትግበራ ደረጃ ሊተገበሩ የሚገባቸው የተጽዕኖ ማቅለያ እርምጃዎች
በአግባቡ ሊዘረዘሩና የሚያስፈልጋቸውም ወጪ (ገንዘብ) በበቂ ሁኔታ ሊመደብ ይገባል፡፡
2) የተለያዩ የማቃለያ እርምጃዎችን በመለየትና በማደራጀት ከተዘረዘሩት አማራጮች ውስጥ ምክንያታዊ በመሆን
የተሻሉ የማቅለያ እርምጃዎችን በመምረጥ ማሳየት ያስፈልጋል፡፡
3) አዎንታዊ ተፅእኖዎችንም እንዴት የበለጠ ማሳደግ ወይም ማሻሻል እንደሚቻል በዚህ ክፍል መገለጽ አለበት፡፡

8
5.12 የአካባቢ አያያዝ እቅድ

1) ይህ እቅድ ከተጽዕኖ ማቃለያ እርምጃዎች የሚቀዳ ሲሆን የሚከናወኑ ተግባራትን በአግባቡ የለየ፣ ፈጻሚ
ባለቤት ያለው፣ ሊተገበር የሚችል፣ አፈጻጸሙ የሚለካ፣ ግልጽ የሆነ የአሰራር ስርዓት ያለው፣ በቂ በጀት ያለውና
በጊዜ የተገደበ ሆኖ በተለያዩ የፕሮጀክት የትግበራ ምዕራፎች ወቅት አካባቢውን ለመጠበቅ የሚያስችል ዝርዝር
አቅድ የሚዘጋጅበት የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርት ክፍል ነው፡፡

2) በእቅዱ ውስጥ የሚካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ሊሆኑ ይገባል፤


1) የተጽእኖዎች ዝርዝር
2) ለእያንዳንዱ ተጽእኖ የታቀዱ የተጽእኖ ማቅለያ ተግባራት ዝርዝር
3) የታቀዱ የተጽእኖ ማቅለያ ተግባራት መለኪያ
4) የታቀዱ የተጽእኖ ማቅለያ ተግባራት መጠን
5) ለእያንዳንዱ ተጽእኖ ማቅለያ ተግባራት የተመደበ ገንዘብ መጠን
6) የታቀዱ የተጽእኖ ማቅለያ ተግባራት የሚተገበሩበት የጊዜ ሰሌዳ
7) የታቀዱ የተጽእኖ ማቅለያ ተግባራትን የሚፈፅሙ አካላት ዝርዝር

3) አንድ የአካባቢ አያያዝ እቅድ የቆያታ ጊዜ ጣሪያ 10 ዓመት ሆኖ በጸደቀ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ
መተግበር መጀመር አለበት፡፡ በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ካለተጀመረ ጥናቱ ውድቅ ሆኖ
እንደገና እንዲጠና ይደረጋል፡፡ አንድ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርት ሲዘጋጅ የፕሮጀክቱን ቅድመ ግንባታ፤
ግንባታ፤ ትግበራና መዝጊያ ወቅት ታሳቢ ያደረገ መሆን ይገባዋል፡፡ ከአስር አመት የጊዜ ቆይታ በኋላ የአካባቢ
ጥናት ዘገባው መከለስ ወይንም ደግሞ በአዲስ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
4) የአካባቢ አያያዝ እቅድ ፎርማት በእዝል 15.1 የተያያዘ ሲሆን የሚዘጋጀው የአያያዝ እቅድ ከላይ
የተጠቀሱትን ዝርዝር መረጃዎች መያዝ ይኖርበታል፡
5) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮና ሌሎች የሚመለከታቸው የስራና የግንባታ ፈቃድ ሰጭ አካላት በምድብ
አንድና ሁለት ለተካተቱ የልማት ፕሮጀክቶች (በአብክመ የተሻሻለውን የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ የአሰራር መመሪያ
ዕዝል አንድን ይመልክቱ) የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሪፖርት ካልተዘጋጀላቸውና የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ
ካልተሰጣቸው በስተቀር የግንባታ/ የስራ ፈቃድ መስጠት የለባቸውም፡፡
6) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮና ሌሎች የሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጭ አካላት በምድብ አንድና ሁለት
ለተካተቱና የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ ለተሰጣቸው ፕሮጀክቶች የግንባታ/የስራ ፈቃድ በሚሰጡበት ጊዜ በተጽዕኖ
ጥናት ዘገባው ውስጥ የተካተቱ የተጽዕኖ ማቃለያ ተግባራት በቀረበው ዲዛይን/የትግበራ ሂደት ውስጥ መካተቱን
የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው፡፡
5.13 የአካባቢ ክትትል/ምርመራ እቅድ

ይህ ክፍል ዝርዝር የአካባቢ ክትትል እቅድ የሚቀርብበት ክፍል ሲሆን የተጽእኖ ማቃለያ ተግባራት በአግባቡ
መከናወናቸውን ለማረጋገጥ የሚዘጋጅ የእቅድ አካል ነው፡፡ በዚህ መመሪያ መሰረት በምድብ አንድ ስር ለተካተቱ
ትልልቅ ፕሮጀክቶች የፕሮጀክቱ ባለቤት ቋሚ የውስጥ የአካባበቢ ክትትል ባለሙያ የመቅጠር ግደታ አለበት፡፡ ሁሉም

9
ፕሮጀክቶች የአካባቢ አያያዝ እቅድ አተገባበራቸውን በዓመት ሁለት ጊዜ በየደረጃው ላለ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም
ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የአካባቢ ክትትል እቅዱ ፎርማት በእዝል 15.2 ቀርቧል፡፡ የአካባቢ ተፅዕኖ ዘገባ
ተገምግሞ ከጸደቀ በኋላ የፕሮጀክት የዲዛይን ለዉጥ ከተከሰተና የተወሰኑ ዝርዝር ተግባራት ከተቀየሩ፤ እነዚህ ለውጦች
ለሚመለከተው የአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤት መቅረብና መፅደቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ እቅድ የሚከተሉትን አንኳር
ነጥቦች ሊይዝ ይገባል፡፡
1) ክትትል የሚደረግባቸው የማቃለያ ተግባራት ዝርዝር
2) ክትትሉን የሚያደርገው ተቋም
3) ክትትሉን የሚያደርገው ተቋም የክትትል ስራውን ለማከናወን የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች/ስልቶች፣
4) ክትትል የሚደረግባቸው የተግባራት አመላካቾችና ጥቅም ላይ የሚዉሉ ደረጃዎች (ስታንዳርድ) ወይም የአሰራር
መመሪያዎች፣
5) ክትትል የሚካሄድበት የድርጊት መርሃ ግብር፣

5.14 በፕሮጀክቱ ትግበራ ተጽእኖ የሚደርስባቸውና የሚመለከታቸው አካላት ምክክር ማካሄድ

የአካባቢ ተጽእኖ ግመገማ ሪፖርት ለማዘጋጀት መካሄድ ካለባቸው ተግባራት መካከል በፕሮጀክቱ ትግበራ ተጽእኖ
የሚደርስባቸውና የሚመለከታቸው አካላት በጥናት ሂደቱ ውስጥ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ማወያየት ሲሆን
በተለይም በወሰን ልየታና በረቂቅ የአካባቢ ተጽእኖ ሪፖርቱ ላይ የሚካሄዱ ውይይቶች ወሳኝ ናቸው፡፡ በረቂቅ ሰነዱ
ላይ ውይይት ሲደረግ በፕሮጀክቱ ተጎጂ ወይም ተጠቃሚ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ በየደረጃው ያሉ የአካባቢ
ጥበቃ ተቋማትና የሚመለከታቸዉ አጋር አካላት መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በሚተገበርበት ቀበሌ/ወረዳ ውስጥ
ያሉ አመራሮች፣ ፕሮጀክቱ የሚተገበርበት ጎጥ መሪዎች፣ የሴቶች/የወጣቶች ተወካዮች፣ በፕሮጀክቱ ምክንያት በቀጥታ
ጉዳት የሚደርስባቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፍ አለባቸዉ፡፡ የውይይት ተሳታፊዎች በአበይት ተጽእኖዎች፣
በማቃለያ እርምጃዎችና በአካባቢ አያያዝ እቅዱ ትግበራ ላይ በዝርዝር መወያየትና ስምምነት ላይ መድረስ አለባቸዉ፡፡
ሀሰተኛ የማህበረሰብ ውይይት ማስረጃ የሚያያይዝ አማካሪ ድርጅት (የፕሮጀክት ባለቤት) ሰነዱ ሀሰተኛ መሆኑ
ከተረጋገጠ በማንኛውም ጊዜ አግባብ ባለው ህግ መሰረት ተጠያቂ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የተሰጠው የአካባቢ
ይሁንታ ፍቃድ ወዲያውኑ የሚሰረዝ ይሆናል፡፡ የተካሄደው ውይይት ሪፖርት የሚከተሉትን ነጥቦች ማካተት
ይኖርበታል፤

1) ውይይቱ የተካሄደበት ጊዜ፣ በውይይቱ የተገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ከለር ፎቶግራፎች፣እንዳስፈላጊነቱ የድምጽና
የተንቀሳቃሽ ምስል እንዲያቀርብ ሊደረግ ይችላል፡፡
2) ውይይቱ የተካሄደበት መንገድ ወይም ዘዴ
3) በውይይቱ የተነሱ ስጋቶች/ጥያቄዎች እና የተሰጡ ምላሾች እንዲሁም የማህበረሰቡ የስምምነት ሁኔታ፣
4) የሚመለከታቸው ተሳታፊዎች ስም ዝርዝርና ፊርማ የያዘና ፕሮጀክቱ በሚተገበርበት ወረዳ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም
ኃላፊ የተፈረመና በማህተም የተረጋገጠ የውይይቱ ቃለ ጉባኤ፣

10
5.15 ማጠቃለያና ምክረ-ሃሳብ

ይህ ክፍል ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችሉ ዋና ዋና ጉዳዮችን በአጭሩ ለማስገንዘብ የሚረዳ የተጽዕኖ ዘገባ ክፍል ነው፡፡
በዚህ ክፍል እንዲተገበሩ የተመረጡ አማራጮችና የተመረጡበት ምክንያት በዝርዝር መገለፅ ይኖርበታል፡፡ ሊወገዱ
የማይችሉ አሉታዊ ተፅእኖዎችን ለማካካስ ወይም ተያያዥ የሆኑ ስጋቶችን ለመቀነስ የምንጠቀማቸውን ስልቶች
በዝርዝር ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡ በአጠቃላይ ይህ ክፍል የሚከተሉትን መረጃዎች ማካተት አለበት፡፡
1) የቁልፍ ጉዳዮች ግልጽ ማብራሪያ
2) ጉልህ የሆኑ አሉታዊ ተፅእኖዎችን ለመቀነስ ወይም ለማካካስ የሚወሰዱ እርምጃዎች
3) አዎንታዊና አሉታዊ ተፅእኖዎችን በማመዛዘን የፕሮጀክቱን አዋጭነት
4) ሊተኩ የማይችሉ የአካባቢ ሃብቶችን የሚጠቀም/ የሚያጠፋ መሆኑና አለመሆኑ
5) ለክትትልና ቁጥጥር ስራዎች የሚያስፈልጉ የህግ ማዕቀፎችና ሌሎች ወሳኝ የሆኑ ሃሳቦች ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡
5.16 ዋቢ መፃህፍት/ማጣቀሻዎች

ይህ ክፍል በሪፖርቱ ውስጥ የተጠቀምንባቸውን መጻህፍቶች፣ የጥናት ሪፖርቶች፣ ድረ-ገፆች ወዘተ.. የሚገለጽበት
ክፍል ነው፡፡ ለመረጃነት ጥቅም ላይ የዋሉ የማጣቀሻ ምንጮች ዓለም አቀፍ የአፃፃፍ ስልቶችን በመጠቀም በፅሁፎች
ውስጥና በመጨረሻም ራሱን ችሎ በዚህ ክፍል መቀመጥ ይኖርበታል፡፡

5.17 እዝሎች

በዚህ ክፍል የሚያያዙት መረጃዎች ለገምጋሚው አካል እንደማጣቀሻነት የሚያገለግሉ ስለሆኑ ተለይተው በዋናው
የጥናት ዘገባ ሰነድ መጨረሻ ላይ ይያያዛሉ፡፡ እነዚህ ሰነዶች ገምጋሚው አካል ትክክለኛ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ
የሚያስችሉ ናቸው፡፡ በእዝል ላይ መያያዝ የሚገባቸው መረጃዎች፤
1) የምህፃረ-ቃላት ፍችና የቃላት ትርጉም፣
2) ከሚመለከታቸው የአካባቢ ጥበቃ መ/ቤቶች ወይም ከአካባቢው አስተዳደሮች የተሰጡ የድጋፍ ደብዳቤዎች፣
3) የደህንነት ወይም የምርት ጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣ የጤና እና የምርት ጥራት ማረጋገጫ የምስክር
ወረቀት (ካስፈለገ)፣
4) ጥልቀት ያላቸው ቴክኒካል ሪፖርቶች፣ አመላካች ቻርቶችና የቦታው ካርታ፣
5) የህብረተሰቡን ተሳትፎ የሚገልጹና የፀደቁ ቃለ-ጉባኤዎች፣ በውይይት የተሳተፉ ሰዎች ፎቶግራፎች፣
6) የጥናት ቡድኑ አባላት ዝርዝር መረጃ (ስም፣ ግለ-ታሪክ ወዘተ)፣
7) ጥናቱን ያካሄደው አማካሪ ድርጅት የሙያና ንግድ ፈቃዶች፣
8) የፕሮጀክቱ ባለቤት ስለ ጥናት ሰነዱ ትክክለኛነት የሰጠው ማረጋገጫ፣
9) በቀረበው የመጀመሪያ ረቂቅ የተጽዕኖ ጥናት ዘገባ ላይ በገምጋሚ ባለሙያዎች የተሰጡ አስተያየቶች ቅጅ እና
ሌሎችም ካሉ ሊያያዙ ይገባል፡፡

11
5.18 የነባርና ማስፋፊያ ፕሮጀክት የአካባቢ አያያዝ እቅድ ዝግጅት

በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5.1 እስከ 5.17 የተዘረዘሩት የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርት ዝግጅት ቅደም
ተከተሎች በሙሉ ለአካባቢ አያያዝ እቅድ ዝግጅት የሚያገለግሉ ይሆናሉ፡፡ ይሁን እንጅ የአካባቢ አያያዝ እቅድ
የሚዘጋጀው ወደፊት የሚፈጠሩ ችግሮችን (ተጽዕኖዎችን) በመተንበይ ብቻ ሳይሆን በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ትንተና
ወቅት በተጨባጭ እየተከሰቱ ያሉትን ችግሮችና የችግሮችን የተጽዕኖ ደረጃ በመለየትና የማቃለያ እርምጃ በማዘጋጀት
ይሆናል፡፡ የአካባቢ አያያዝ እቅዱ ሲዘጋጅ ከሌሎች መረጃዎች በተጨማሪ የአካባቢ ምርመራ በማካሄድና የምርመራ
ሪፖርቱን በግብዓትነት በመጠቀም ይሆናል፡፡ ከአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርት ዝግጅት በተመሳሳይ በጥናት ከተለዩ
የተጽዕኖ ማቃለያ እርምጃዎች በመነሳት የአካባቢ አያያዝ እቅዱ የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡

6 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርትን ስለመገምገም


6.1 በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርት ግምገማ ወቅት ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች
1) የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሪፖርት ግምገማ በተዘጋጀው ቢጋር መሰረት መካሄዱን፣ የማህበረሰቡ አስተያየት
መካተቱን፣ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል በቂና የተሟላ መረጃ የያዘ መሆኑን ለማረጋገጥ እና በሰነዱ ውስጥ ያሉ
ክፍተቶችን (ጉድለቶችን) ለመለየት ነው፡፡ በኘሮጀክት ባለቤቶች የተዘጋጀው የአካባቢ ተፅእኖ ግምገማ ሪፖርት
ስልጣን በተሰጠው የአካባቢ ጥበቃ ተቋም፣ በሚመለከታቸው ተቋማት፣ በኘሮጀክቱ ምክንያት ጉዳት
በሚደርስባቸዉና አስተያየት ለመስጠት ፍላጐቱ ባላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቀርቦ መገምገም ይኖርበታል፡፡
2) የሰነድ ግምገማው በሚካሄድበት ወቅት በገምጋሚው ትኩረት ተሰጥቶ መታየት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል
የሚከተሉት ዋነኞቹ ናቸው፡፡
1) ሪፖርቱ በተዘጋጀውና በጸደቀው ቢጋር (ToR) መሰረት ተጠንቶ የቀረበ መሆኑንና ቢጋሩ ተሻሽሎ ከሆነ
የተሻሻለበትን ምክንያት በማጠቃለያና በመግቢያ ጽሁፉ ዉስጥ መጠቀሱን፣ የአካባቢ ወሰን ልየታ ጥናት
ቀርቦ የፀደቀ ስለመሆኑ ከገምጋሚው አካል የተሰጠ ደብዳቤ ከጥናት ሰነዱ ጋር አባሪ ሆኖ መቅረቡን
ማረጋገጥ፣
2) ማንኛዉም ሊያነብ የሚችል ሰዉ ሊረዳዉ የሚችል አጭር ማጠቃለያ ጽሁፍ መኖሩን፣
3) ለዋና ዋና የሪፖርቱ ክፍሎች ጠቃሚ፣ ትክክለኛና ተቀባይነት ያላቸው መረጃዎች መካተታቸውን፣
4) በሪፖርቱ መሰረታዊ የአካባቢ መረጃዎች በአግባቡ መካተታቸውን፣
5) የጥናቱ ግኝቶች የተሟሉና አጥጋቢ መሆናቸውን፣
6) መረጃው ለውሳኔ ሰጭ አካላትና ለሚመለከታቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ግልጽና በቀላሉ የሚረዱት
መሆኑን፣
7) ጉልህ አወንታዊና አሉታዊ ተጽእኖዎች በአግባቡ መለየታቸውንና መተንተናቸውን፣
8) ጉልህ አሉታዊና አወንታዊ ተጽእኖዎች ላይ የተቀመጡ ሙያዊ ውሳኔዎች በአግባቡ መገለጻቸዉን፣
9) ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ባይሆን የሚለዉን ጨምሮ ያሉ የተለያዩ የትግበራ አማራጮች በአግባቡ
መዳሰሳቸውንና አማራጮችን በንጽጽር ለማየት የተጠቀሙባቸው መመዘኛዎች ለሁሉም አማራጮች
በእኩል ክብደት የተሰጣቸው መሆኑን፣

12
10) ከፕሮጀክት አማራጮች መካከል ለአካባቢና ማህበራዊ ሁኔታዎች በአንጻራዊነት ተስማሚ የሆነዉ
አማራጭ መመረጡንና የተመረጠበትም ምክንያት በአግባቡ መገለጹን፣
11) አጋር መ/ቤቶች፣ ጉዳት ሊደርስባቸዉ ይችላል ተብሎ የሚገመቱና በፕሮጀክቱ ላይ አስተያየት
ለመስጠት ፍላጎቱ ያላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች በአግባቡ መሳተፋቸዉን የሚገልጽ ማስረጃ በአካባቢ
ተፅዕኖ ግምገማ ሪፖርት ዉስጥ መኖሩን ፣
12) በጥናቱ ወቅት ለመረጃ ምንጨነት ያገለገሉት ማጣቀሻዎች በአግባቡ መገለጻቸውን፣
13) ሊደርሱ የሚችሉ ተጽእኖዎችን ለመተንበይና ለመለየት ጥቅም ላይ የዋሉ ዘዴዎችና ቀመሮች
እንዲሁም እያንዳንዱን አሉታዊ ተጽእኖ ለማቃለል የተቀመጡ እርምጃዎች በአግባቡ መገለጻቸዉን እና
ያጋጠሙ የመረጃ ክፍተቶች መታየታቸዉን፣
14) የአካባቢ አያያዝና ክትትል እቅዱ ሊለካ የሚችል፣ የሚያስፈልገዉ ወጪ፣ ጊዜና ስራዉን
የሚያከናውን ተቋም/ አካል በዘገባው ዉስጥ መካተቱን፣
15) በአጠቃላይ መረጃው ስለፕሮጀክቱ ትግበራ ውሳኔ ለመስጠት ጠቃሚና በቂ መሆኑን፣
16) የሚቀርበው የጥናት ዘገባ የታደሰ የሙያ ፈቃድና የንግድ ፈቃድ እንዲሁም የአማካሪ ድርጅቱ የሙያ
ፈቃድ፤ የጥናት ቡድኑ የባለሙያዎች ስብጥርና በጥናቱ የተሳተፉበት የጥናት ክፍልና በጥናቱ
ስለመሳተፋቸው የማረጋገጫ ሰነድ፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት፣ በባለሙያዎች ፊርማ
የተረጋገጠ የባለሙያዎች ግለ-ታሪክ፣ በፎቶግራፍ የተደገፈ የማህበረሰብ ተሳትፎ/ውይይት ቃለጉባኤ፣
የአካባቢው የመንግስት አካል ስለፕሮጀክቱ ትግበራ የተስማማበት የድጋፍ ደብዳቤ መያያዙን፣
17) ለግምገማ የቀረበው ሪፖርት የፕሮጀክት ባለቤቱና የአማካሪ ድርጅቱ ማህተም በእያንዳንዱ ገፅ ላይ
ያረፈበት መሆኑን፣ በአሳማኝ ምክንያት ባለሀብቱ ማህተም ማድረግ ካልቻለ የአማካሪ ድርጅቱ ማህተም
በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ የይሁንታ ፈቃድ ይሰጠኝ ከሚለው ማመልከቻ ላይ የፕሮጀክት ባለቤቱ ወይም
የተወካዩ ፊርማና ማህተም ያለበት መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፣
3) የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ባለሙያዉ/ቡድኑ ከላይ በንዑስ አንቀጽ 6.1 ስር በተራ ቁጥር 2 በተዘረዘሩት አስራ
ሰባት የመገምገሚያ ነጥቦች መሰረት በመገምገም የተጽዕኖ ዘገባውን ዝርዝር የግምገማ ሪፖርትና አጠቃላይ
የፕሮጀክቱን ትግበራ የውሳኔ አስተያየት ለኃላፊዎች ይቀርባል፡፡ በቀረበው የውሳኔ አስተያየት ተመስርተው
ኃላፊዎች ውሳኔ ይሰጣሉ፡፡ ኃላፊው የአካባቢ ተጽእኖ ጥናት ዘገባው ዝርዝር ጥናት ጎድሎታል ብሎ ካመነ ወይንም
የቴክኒክ ችግር አለበት ብሎ ከገመገመ መሰረዝ ወይንም እንደገና እንዲጠና ሊያዝዝ ይችላል፡፡
4) በፕሮጀክት ባለቤቶች ተጠንቶ የሚቀርበዉን የፕሮጀክቶች የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሪፖርት ለመገምገም
የሚያገለግሉ መመዘኛዎች በእዝል 15.3 በሰንጠረዥ ተዘርዝረዋል፡፡ ስለዚህ ማንኛውም የአካባቢ ተጽዕኖ
ግምገማ ሪፖርት በዚህ መመዘኛ መሰረት መገምገም አለበት፡፡ በየደረጃዉ ያሉ የአካባቢ ጥበቃ ተቋማት
የቀረበላቸውን የአካባቢ ተፅእኖ ጥናት ዘገባ በ 15 ቀናት ውስጥ መርምረው ምላሽ መስጠት አለባቸው፡፡ ነገር ግን
ፕሮጀክቱ በጣም ጉልህ የሆኑ ችግሮችን የሚያስከትል ከሆነ ምላሽ የሚሰጥበት ቀን ከ 15 ቀናት በላይ ሊዘገይ
ይችላል፡፡ ነገር ግን ምለሽ የሚሰጥበት ጊዜ ከ 30 ቀን መብለጥ የለበትም፡፡ የግምገማ ሥራው እንደተጠናቀቀ
የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ወይም የሚመለከተው በተዋረድ ያለ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም ጥናቱን እንዳለ ሊቀበለው፣
ሊሰርዘው ወይም እንዲስተካከል ሊያዝዝ ይችላል፡፡ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሪፖርቱን ለመገምገም በአካባቢ

13
ጥበቃ ተቋም ባሉ ሙያተኞች ብቻ መገምገሙ በቂ ነው ብሎ ካልታመነበት የተቋሙ የበላይ ሀላፊ ሰነዱ
በዩኒቨርሲቲዎች፣ በምርምር ተቋማትና በሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት እንዲገመገም ሊያዝዝ ይችላል፡፡
6.2 የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሪፖርት ተቀባይነት ላይ ውሳኔ ስለመስጠት

በዕዝል 15.3 የቀረበውን የመገምገሚያ መስፈርት በመጠቀም የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርቱ ተገምግሞ ነጥብ
ይሰጠዋል፤ የነጥቡ ክብደት አጠቃላይ 100 ፐርሰንት ሲሆን በሰነዱ ውስጥ አስፈላጊ መረጃዎች ስለመኖራቸው
ከ 56% እና ሰነዱ ለያዛቸው መረጃዎች በቂነት ከ 44% ነጥብ ይሰጣል፡፡
1) በሰነድ ግምገማው የተገኘው ነጥብ አጠቃላይ ውጤቱ 70 ፐርሰንት ወይም በላይ ከሆነ የአካባቢ ይሁንታ
ሰርተፊኬት ተዘጋጅቶ ይሰጠዋል፡፡ ለባለሃብቱ የሚሰጠው የይሁንታ ፈቃድ በዕዝል 15.9 ላይ የተዘረዘሩትን
የውል ስምምነቶችን ያካተተ ይሆናል፡፡
2) የተሰጠው ነጥብ በ 50 እና በ 70 ፐርሰንት መካከል ከሆነ ሰነዱ እንደገና ተስተካክሎ እንዲቀርብ ነጥብ
የተሰጠበትን መገምገሚያ ቅፅ አባሪ በማድረግ ለፕሮጀክት ባለቤቱ በደብዳቤ ይገለጽለታል፡፡
3) የግምገማ ነጥቡ ከ 50 ፐርሰንት በታች ከሆነ የቀረበው ዘገባ ተቀባይነት የሌለው ወይም ጥራት የጎደለው በመሆኑ
በሌላ አማካሪ ድርጅት ተዘጋጅቶ እንደገና እንዲቀርብ በመግለፅ ነጥብ የተሞላበትን የመገምገሚያ ቅፅ አባሪ
በማድረግ በደብዳቤ ለፕሮጀክት ባለቤቱ ይገለጽለታል፡፡
4) የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሪፖርት የያዘው መረጃ በቂና ትክክለኛ መሆኑን ሳያረጋገጥ የይሁንታ ፈቃድ እንዲሰጠው
የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበ ባለሙያ ወይንም በመስክ መረጋገጥ ያለባቸውን መረጃዎች በአግባቡ ሳያረጋግጥ መተግበር
በሌለበት ቦታ ላይ እንዲተገበር የውሳኔ አስተያየት ያቀረበ ባለሙያ በዲሲፕሊን መመሪያው መጠየቁ እንደተጠበቀ
ሆኖ አግባብ ባላቸው በሀገሪቱ ህጎች ይጠየቃል፡፡
6.3 ስለ አካባቢ ይሁንታ ፈቃድ የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ

የፕሮጀክቶች የይሁንታ ፈቃድ አሰጣጥ ሂደት የባለሙያ የመስክ ስምሪትን የሚጠይቅ በመሆኑ አገልግሎቱ የመንግስትን
ወጭ ይጠይቃል፡፡ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ የአገልግሎት ሙሉ ወጭ በባለሀብቱ እንዲሸፈን በህግ ቢደነገግም
እስካሁን ድረስ በመንግስት በጀት ሲሸፈን መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ ከቀጠለ ደግሞ በመንግስት በጀት ላይ ጫና
መፍጠሩ አይቀርም፡፡ በመሆኑም በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ አዋጆች ቁጥር 181/2003 አንቀጽ 9/4 መሰረት
የፕሮጀክት ባለቤቶች ሙሉ የአካባቢ ተጽዕኖ ወጭዎችን የመሸፈን ግደታ ያለባቸው ቢሆንም ለጊዜው በተወሰነ ደረጃ
የአገልግሎት ወጭ እንዲሸፍኑ በዚህ መመሪያ ተደንግጓል፡፡ ክፍያ የሚከፈልባቸው የአገልግሎት አይነቶችና የክፍያ
መጠን ቀጥሎ በቀረበው ሰንጠረዥ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡ የይሁንታ ፈቃድ ከመሰጠቱ በፊት የአገልግሎት ክፍያ
የተፈጸመበት ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ ከውሳኔ አስተያየት ሪፖርቱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ሰንጠረዥ 1: የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ ለመስጠት፣ ለማደስ ወይም ለመተካት የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ
ተ/ቁ የአገልግሎት አይነት መለኪያ የአገልግሎት ክፍያ በፕሮጀክት ምድብ
የክልል የዞን የወረዳ
1 አዲስ ይሁንታ ፈቃድ መስጠት ብር 1000 500 250
2 በወቅቱ ለቀረበ የእድሳት ጥያቄ ብር 500 250 150
3 በልዩ ልዩ ሁኔታ የጠፋና የተበላሸ የይሁንታ ፈቃድ ለመተካት ብር 600 400 200
(በወቅቱ ለቀረበ)
4 በወቅቱ ላልቀረበ የእድሳት ጥያቄ (የእድሳት ጊዜው ከ 6 ወራት ብር 600 400 200
በላይ ካላለፈ)

14
ተ/ቁ የአገልግሎት አይነት መለኪያ የአገልግሎት ክፍያ በፕሮጀክት ምድብ
የክልል የዞን የወረዳ
5 በወቅቱ ላልቀረበ የእድሳት ጥያቄ (የእድሳት ጊዜው ከ 1 አመት ብር 1000 500 300
በላይ ካላለፈ)
6 በወቅቱ ላልቀረበ የእድሳት ጥያቄ (የእድሳት ጊዜው ከ 2 አመት ብር 1200 700 400
በላይ ካላለፈ)
7 የጠፋና የተበላሸ የፕሮጀክት የይሁንት ፈቃድ መተካት (የእድሳት ብር 1000 500 300
ጊዜው ከ 6 ወራት በላይ ካላለፈ)
8 የጠፋና የተበላሸ የፕሮጀክት የይሁንታ ፈቃድ መተካት (የእድሳት ብር 1200 700 500
ጊዜው ከ 1 ዓመት በላይ ካላለፈ)
9 የጠፋና የተበላሸ የፕሮጀክት የይሁንታ ፈቃድ መተካት (የእድሳት ብር 1400 900 700
ጊዜው ከ 2 ዓመት በላይ ካላለፈ)
10 በወቅቱ ላልቀረበ የይተካልኝና የእድሳት ጥያቄ (የእድሳት ጊዜው ከእንደገና አዲስ የተጠና ሪፖርት እንዲያቀርብ ይገደዳል
2 አመት በላይ ካላፈ) እንጂ አይታደስም

7 የፕሮጀክት ትግበራ ስለሚከለከልባቸዉና ስለሚሰረዝባቸው አግባቦች

አንድ ፕሮጀክት ቢተገበር/ሲተገበር የሚያስከትለው አሉታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ ከሆነና ተጽዕኖውን በአጥጋቢ ሆኔታ
ማስቀረት የማይቻል ከሆነ ወይም ተጽዕኖውን ለማስቀረት እንደማይቻል ከታመነ ሌላ አማራጭ ቦታ እንዲፈልግ ወይም
ቴክኖሎጂ እንዲጠቀም ይደረጋል፡፡ ስለዚህ ይህ ክፍል የፕሮጀክቱ ትግበራ የሚከለከልባቸውን (የሚቋረጥበትን)
አግባቦች ለመወሰን ያስችላል፡፡ የአንድ ፕሮጀክት ትግበራ የሚከለከለው፡-
1) ሁለት የማይጣጣሙ ፕሮጀክቶች ጎን ለጎን ተግባራዊ እንዲሆኑ የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ዘገባ የቀረበ ከሆነና በኋላ
የቀረበዉ ፕሮጀክት ቀድሞ ከቀረበው ፕሮጀክት ጋር የማይጣጣም ከሆነ የማይጣጣምበትን አሉታዊ ተጽዕኖዎች
በመግለፅ ለፕሮጀክት ባለቤቱ ሌላ አማራጭ ቦታ እንዲፈልግ (የፕሮጀክቱን አይነት እንዲለውጥ) በደብዳቤ
የሚገለፅለት ሲሆን ፕሮጀክቱ በማይጣጣምበት ቦታ እንዳይተገበር ይከለከላል፡፡
2) የፕሮጀክቱ ተዳማሪ ተጽዕኖ በጣም ከፍተኛ ከሆነና አካባቢው ተጽዕኖውን መሸከም የማይችል ከሆነ ለአካባቢው
ቅድሚያ በመስጠት ፕሮጀክቱ እንዳይተገበር ይከለከላል፡፡
3) ፕሮጀክቱ ሊተገበር በታቀደበት ቦታ ወይም አካባቢ ላይ በማህበረሰቡ ዘንድ ፕሮጀክቱ እንዳይተገበር ከፍተኛ
ተቃውሞ ከገጠመ ተቃውሞው እስኪፈታ ለፕሮጀክቱ የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ አይሰጥም፡፡
4) ፕሮጀክቱ ሊተገበር የታሰበበት ቦታ በተለያዩ አካላት የይገባኛል ጥያቄ ውዝግብ ያለበት ከሆነና ውዝግቡ ካልተፈታ
የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ አይሰጥም፡፡
5) ክልላዊና ሀገራዊ ቅርሶችን፣ ጥብቅ ቦታዎችን፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ቦታዎችን፣ ታሪካዊ ሃብቶችን፣ እንዲሁም
ሌሎች በቀላሉ ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን ፕሮጀክቱ በቀጥታ የሚነካ ከሆነና አማራጭ የማይገኝለት ከሆነ
የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ አይሰጥም፡፡
6) ፕሮጀክቱ የሚጠቀምባቸው ቴክኖሎጂዎች በአካባቢ ጥበቃ ህጎች የተቀመጡትን የልቀት ደረጃዎች ሊያሟሉ
የማይችሉ ከሆኑና ፕሮጀክቱ ከፍተኛ ልቀት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ እንዲሁም የተከለከሉ ግብዓቶችን የሚጠቀም
ከሆነ የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ አይሰጥም፡፡
7) ማንኛውም በአለም ባንክ በጀት ድጋፍ የሚደገፍ ፕሮጀክት ከዓለም ባንክ ፖሊሲ ወይም የህግ ማዕቀፎች ጋር
የሚቃረን ወይም በባንኩ እንዲተገበር የማይፈቀድ ከሆነ የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ አይሰጥም፡፡

15
8) ከላይ በአንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 1 እስከ 7 የተጠቀሱትን የፕሮጀክት ትግበራ ክልከላዎች በመተላለፍ ወደ ተግባር
የገባ ማንኛውም ፕሮጀክት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሽህ ብር) ተቀጥቶ ፕሮጀክቱ እንዲዘጋ ወይም
በራሱ ወጭ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወር ይደረጋል፡፡
9) በምድብ አንድና ሁለት ውስጥ ለተካተቱ ፕሮጀክቶች የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖ ማቃለያ እቅድ ሳያዘጋጁና
የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ ሳይሰጣቸው፤ የአዘጋጁትም ቢሆኑ የተጽዕኖ ማቃለያ እቅዳቸው በፕሮጀክቱ ግንባታና
ትግበራ ዲዛይን ውስጥ ሳይካተት ለፕሮጀክቶች የግንባታ ፈቃድ የሚሰጥ በየደረጃው ያለ የከተማ ልማትና
ኮንስትራክሽን ወይም ኢንዱስትሪና ኢንቨስትምንት ቢሮ ኃላፊ ወይም ባለሙያ በብር 50,000.00 (በሀምሳ
ሺህ ብር) ወይንም በአምስት አመት ጽኑ እስራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል፡፡
10) በምድብ አንድና ሁለት ውስጥ ለተካተቱ ፕሮጀክቶች የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖ ማቃለያ እቅድ ሳያዘጋጁና
የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ ሳይሰጣቸው፤ የአዘጋጁትም ቢሆኑ የተጽዕኖ ማቃለያ እቅዳቸው በፕሮጀክቱ ግንባታና
ትግበራ ዲዛይን ውስጥ ሳይካተት ለፕሮጀክቶች የስራ ፈቃድ የሚሰጥ የማንኛውም መስሪያ ቤት/ ድርጅት
ኃላፊ/ባለሙያ በብር 50,000.00 (በሀምሳ ሽህ ብር) ወይንም በአምስት አመት ጽኑ እስራት ወይም
በሁለቱም ይቀጣል፡፡
11) በየደረጃዉ ካሉ የአካባቢ ጥበቃ ተቋማት የይሁንታ ፈቃድ ሳይሰጠዉ ወደ ተግባር የገባ ማንኛውም ፕሮጀክት
አሉታዊ አካባቢያዊና ማህበራዊ ተጽዕኖ ካለው ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሽህ ብር) ተቀጥቶ ፕሮጀክቱ በሶስት
ወራት ጊዜ ውስጥ የአያያዝ እቅድ አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ ይገለጽለታል፤ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ
ዘገባውን ማቅረብ ካልቻለ ስራውን እንዲያቆም ይደረጋል፣
12) በአካባቢና በሰዉ ጤና ላይ ተጽዕኖ እያስከተለ ያለ ፕሮጀክት ከሆነና ይህንኑ ለመከላከል አለመቻሉ
በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ወይም በተዋረድ ባለ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም በምርመራ የተረጋገጠ ከሆነ የፕሮጀክቱ
ይሁንታ እንዲሰረዝ (ስራውን እንዲያቆም) ይደረጋል፣
13) የፕሮጀክቱ ባለቤት የተጽእኖ ማቃለያ እርምጃዎችን ካልተገበረ እና በተሰጠው ግብረ መልስ መሰረት
ተግባራዊ የማያደርግ ከሆነ ባለስልጣኑ ወይም በሚመለከተው በተዋረድ ያለ የአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤት ብር
50,000.00 (ሀምሳ ሽህ ብር) ተቀጥቶ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡ በተሰጠው ማስጠንቀቂያ መሠረት
የኘሮጀክቱ ባለቤት ችግሩን የማያስተካክል ከሆነ ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከታቸው በተዋረድ ያለ የአካባቢ
ጥበቃ መስሪያ ቤት የሰጠውን የይሁንታ ፈቃድ ያግዳል ወይም ይሰርዛል፡፡ ሌሎችም ፈቃድ ሰጭ መስሪያ ቤቶች
ለኘሮጀክቱ ትግበራ የሰጡትን የስራ ፈቃድ ይህን ውሣኔ ተከትለው ማገድ ወይም መሠረዝ አለባቸው፡፡
14) በአዋጅ ቁጥር 181/2003 ዓ.ም አንቀፅ 15 (5) መሰረት የፕሮጀክት ባለቤቱ የአካባቢ ተቆጣጣሪዎችን
ክትትል፣ ምርመራና ቁጥጥር እንዳያካሄዱ ወይም ወደ ፕሮጀክቱ ግቢ እንዳይገቡ የከለከለ እንደሆነ ብር
30‚000.00 (ሰላሳ ሽህ ብር) ተቀጥቶ የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፤ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ
ባለማክበር ለሁለተኛ ጊዜ ክትትል፣ ምርመራና ቁጥጥር እንዳይካሄድ ወይም የአካባቢ ተቆጣጣሪዎችን ወደ
ፕሮጀክቱ ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ ከከለከለ ባለሥልጣኑ ወይም በተዋረድ ያሉ የአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤቶች
የሰጡትን የይሁንታ ፈቃድ ያግዳሉ ወይም ይሰርዛሉ፡፡ ሌሎችም ፈቃድ ሰጭ መስሪያ ቤቶችም ለኘሮጀክቱ ትግበራ
የሰጡትን የስራ ፈቃድ ይህን ውሣኔ ተከትሎ ማገድ ወይም መሠረዝ አለባቸው፡፡
15) የፕሮጀክት ባለቤቱ ባቀረበው ጥናት መሰረት የአካባቢ አያያዝ ዕቅዱን ስለመተግበሩ በዓመት ሁለት ጊዜ
ለሚመለከተው የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ወይንም በተዋረድ ላለ የአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤት ሪፖርት ማቅረብ

16
አለበት (የሪፖርት ማድረጊያ ቅፁ በዕዝል 15.4 ተያይዟል)፡፡ የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ ትግበራውን በወቅቱ
ሪፖርት የማያደርግ ከሆነ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፤ በተከታታይ ሶስት ጊዜ ለሚመለከተው የአካባቢ ጥበቃ
መስሪያቤት የአፈጻጸም ሪፖርት ካላቀረበ የባለስልጣን መስሪያቤቱ ወይም በተዋረድ ያለ የአካባቢ ጥበቃ
መስሪያቤት የሰጠውን የይሁንታ ሰርተፊኬት ያግዳል ወይም ይሰርዛል፡፡
16) ለፕሮጀክቱ ተደጋጋሚ የአካባቢ ክትትልና ምርመራ በማድረግ ችግሮችን እንዲያስተካክል ቢገለጽለትም ችግሩን
አላስተካክልም በማለቱ የመጨረሻ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጽፎ በተሰጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ችግሩን
ማስተካከል ያልቻለ ፕሮጀክት የማስተካከያ እርምጃዎች ተግባራዊ እስከሚደረጉ ድረስ ፕሮጀክቱ ስራዉን
እንዲያቆም ይደረጋል፡፡

8 የአካባቢ ህግ ማስከበር ግብረ-ሀይል ስለማቋቋም፣ተግባርና ኃላፊነት

አብዛኞች የልማት ፕሮጀክቶች አደገኛ ቆሻሻቸውን በቀጥታ ወደ አካባቢ በመልቀቃቸው የተነሳ በምግብ ስራዓተ
ሰንሰለት፣ በስርዓተ-ምህዳርና በሰዎች ላይ የማይቀለበስ ውስብስብ ችግር እያስከተለ ስለሆነ በአንቀጽ 7 ላይ
በተገለጸው አግባብ ተጽዕኖውን ማስወገድ ካልተቻለ በአካባቢ ህግ ማስከበር ግብረ ሀይል አማካይነት የአካባቢ ህግ
የማስከበር ስራ ይሰራል፡፡ በዚሁ አግባብ፡-
1) ፋብሪካዎችና የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻቸውን አክመውና የሀገሪቱን የቆሻሻ የልቀት ደረጃዎች
ጠብቀው ማስወገድ አለባቸው፡፡ ፕሮጀክቶች አካባቢን ከመበከል እንዲታቀቡ ተደጋጋሚ ድጋፍ ተደርጎላቸው
የአካባቢ ህግን ለማክበር ፈቃደኞች ካልሆኑ የአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤት የፕሮጀክቱን የይሁንታ ፈቃድ ይሰርዛል፤
ይህን ተከትሎ የስራ ፈቃድ ስጭ ተቋማት የሰጡትን ፈቃድ ይሰርዛሉ፡፡ የአካባቢ ጥበቃ ግብረ ሀይልም የአካባቢ
ህጉን ለማስከበር ፕሮጀክቱን ይዘጋል (እንዲቋረጥ) ያደርጋል፡፡
2) ከአካባቢ ጥበቃ መ/ቤት የሚቀርብለትን የምስልና የጽሁፍ ማስረጃ መሰረት በማድረግ የአካባቢ ህግ ማስከበር
ግብረ ሀይል በአዋጅ ቁጥር 181/2003 አንቀጽ 15 መሰረት የመዝጋት (የማገድ) እርምጃ መወሰድ አለበት፡፡
3) ይህን አስተዳደራዊ እርምጃ (ውሳኔ) ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ተቋማት የተዋቀረ የአካባቢ ህግ
አስከባሪ ግብረ ሀይል በዚህ መመሪያ ተቋቁሟል፡፡
4) ግብረ-ሀይሉ በክልል ደረጃ የሚከተሉትን ተቋማት በአባልነት አቅፏል፡-

የግብረ-ሀይሉ አባል የሚሆኑ መስሪያ ቤቶች አባልነት


ከክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መስሪያ ቤት የሚመደብ ሰብሳቢ
ከክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚመደብ አባል
ከክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የሚመደብ አባል
ከክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የሚመደብ አባል
ከክልል የማዕድን ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የሚመደብ አባል
ከክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሚመደብ አባል
ከክልል ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ የሚመደብ አባል
ከክልሉ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥ/ልማት ባለስልጣን የሚመደብ ጸሀፊና አባል ይሆናሉ
5) ከዚህ በላይ የተቋቋመው ግብረ ሀይል የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን የሚያቀርብለትን
የአካባቢ ብክለትና ብክነት የምርመራና ክትትል ሪፖርት ማስረጃዎች እየመረመረና አስፈላጊም ሲሆን የመስክ
ምልከታ እያደረገ በመረጃ ላይ የተመሰረተ እርምጃ ይወስዳል፡፡ እርምጃው ፕሮጀክቶችን ለተወሰነ ጊዜ መዝጋት
ወይንም መሰረዝ ሊሆን ይችላል፡፡

17
6) የአካባቢ ጥበቃ ግብረ ሀይል በዚህ መመሪያ መሰረት በየደረጃው ባሉ የዞንና የወረዳ አደረጃጀቶች የተቋቋመ ሲሆን
ተግባርና ኃላፊነቱንም በዚህ አንቀጽ በተገለጸው አግባብ ይወጣል፡፡

9 ለአካባቢ አማካሪ ድርጅቶችና ባለሙያዎች የአማካሪነት የሙያ ፈቃድ ስለመስጠት

ይህ ክፍል ባለስልጣኑ የአካባቢ አማካሪ ድርጅቶችንና አማካሪ ባለሙያዎችን የሙያ ፈቃድ ለመስጠት፣ አመልካቾች
ማሟላት የሚገባቸዉን መስፈርቶችና ሰነዶች፣ የአማካሪዎችን ተግባርና ኃላፊነት የሚወስን ይሆናል፡፡

9.1 የአካባቢ ተጽዕኖ ዘገባ የማዘጋጀት ስልጣን

1) ለማንኛውም ፕሮጀክት የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ዘገባ የሚዘጋጀዉ በዚህ መመሪያ ዉስጥ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን
በሚያሟሉ የባለሙያዎች ስብጥርና ህጋዊ ፈቃድ ባላቸው አማካሪ ድርጅቶች ብቻ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የዓለም
ባንክ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ሀገራችን ባፀደቀችው ህግ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
2) የአካባቢ አማካሪነት የሙያ ፈቃድ ለማዉጣት የሚፈልግ ባለሙያ በዕዝል 15.5-15.7 ከተጠቀሱት የትምህርት
ዝግጅቶች አንዱ ሊኖረዉ ይገባል፡፡ ለመጀመሪያ ዲግሪ አምስት ዓመትና በላይ የሥራ ልምድ፣ ለሁለተኛ ዲግሪ
ሶስት ዓመትና በላይ የሥራ ልምድ እና ለሶስተኛ ዲግሪ ሁለት ዓመትና በላይ የሥራ ልምድ ያለው/ያላት መሆን
አለበት፡፡

9.2 በአካባቢ አማካሪነት ስራ ለመሰማራት መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች

1) የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ፣


2) በአማካሪ ድርጅት የተደራጁ መሆን አለባቸው፤
3) አንድ አማካሪ ድርጅት ፈቃድ ለማውጣት 6 የተለያዩ የሙያ ዘርፎችን ያካተቱ አማካሪ ባለሙያዎች መያዝ ያለበት
ሲሆን ስድስቱም ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው መሆን አለባቸው፣
4) በአንድ የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናትና ዘገባ ዝግጅት ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ቁጥር ቢያንስ አራት ባለሙያዎች ሆኖ
እንደ ፕሮጀክቱ ባህሪ የተለያየ የሙያ ስብጥር ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፣
5) የባለሙያዎች ቁጥር እንደ ፕሮጀክቱ ባህሪ የሚለያይ ሆኖ በዝቅተኛው ቁጥር ላይ ያሉት አራቱም ባለሙያዎች
የተለያየ የአማካሪነት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሊኖራቸው ይገባል፣
6) የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣
7) የታደሰ የአማካሪነት የድርጅት ፈቃድ፣
8) የራሱ የሆነ የተሟላ ቋሚ ጽ/ቤት ያለው፣ ስራስኪያጅና ጸሀፊ ባለሙያ ያለው
9) መሰረታዊ የአካባቢ መረጃ መሰብሰቢያና መለኪያ መሳሪያዎችን (ጅፒኤስ፣ቪዲዮ ካሜራ፣ድጅታል
ካሜራ፣ኮምፒውተር ወዘተ) ያሟላ መሆን ይኖርበታል
10) ለአማካሪ ባለሙያ የሙያ ብቃት እንዲሁም ለአማካሪ ድርጅት (firm) ፈቃድ የሚሰጠው በክልሉ አካባቢ
ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ብቻ ነው፡፡
11) አንድ ባለሙያ ከሁለት አማካሪ ድርጅቶች በላይ አማካሪ ሆኖ እንዲሰራ ወይም እንዲደራጅ አይፈቀድም፡፡

18
9.3 የሙያ ብቃት ማስረጃ በአዲስ ለማውጣትና ለዕድሣት አገልግሎት ክፍያ

1) የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ስርቲፊኬት ወይም የአማካሪ ድርጅት ፈቃድ የሚታደሰው በዚህ መመሪያና በአካባቢ
ህጎች የተካተቱ ህጎችና የሙያ ስነ ምግባሮች አፈጻጸም በምርመራ ከተረጋገጠ በኋላ ይሆናል፡፡
2) ባለሙያዎች አዲስ የሙያ ፈቃድ ለማዉጣት፣ ደረጃቸውን ለማሳደግና የጠፋባቸው በድጋሚ ለማዉጣት ብር
300.00 (ሶስት መቶ ብር) የአገልግሎት ክፍያ መክፈል አለባቸዉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አዲስ የሙያ ፈቃድ
ለማውጣት ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ የጠፋባቸውን ለመተካትና ደረጃቸውን ለማሳደግ አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ /
3x4 መጠን/ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3) አዲስ የአማካሪ ድርጅት ፈቃድ ለማውጣት፣ የአማካሪ ድርጅት ደረጃ ለማሳደግና የጠፋን የድርጅት ፈቃድ
በድጋሜ ለማውጣት ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) የአገልግሎት ክፍያ መከፈል አለበት፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ /3x4 መጠን/ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4) የአማካሪ ድርጅት ፈቃድ በየሁለት ዓመቱ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) የአገልግሎት ክፍያ በመክፈል፤
የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ደግሞ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር)በመክፈል ይታደሳል፡፡
5) የአማካሪ ድርጅት ፈቃድ ወይም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ
ካልታደሰ በቀጣይ ሶስት ወራት ውስጥ ከአገልግሎት ክፍያ በተጨማሪ የቅጣት ብር 500.00 (አምስት መቶ
ብር) እንዲከፍል በማድረግ እንዲታደስ ይደረጋል፡፡ በዚህ የጊዜ ገደብ ውሰጥ ሳይታደስ ከቀረ ለሚቀጥሉት
ተጨማሪ ሶስት ወራት 800.00 (ስምንት መቶ ብር) ቅጣት እንዲከፍል በማድረግ እንዲታደስ ይደረጋል፡፡
በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ካልታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱ ወይም የአማካሪ ድርጅቱ ፈቃድ
ለአንድ አመት ይታገዳል፡፡
6) ነባር የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው ባለሙያዎች ይህ መመሪያ በወጣ በ 6 ወራት ጊዜ ውስጥ አዲስ
የማመልከቻ ፎርም በመሙላትና ያላቸውን ማስረጃ በማቅረብ አዲስ የሙያ ብቃትና የአማካሪ ደርጅት ፈቃድ
ማውጣት አለባቸው፡፡ ይህ መመሪያ በወጣ በ 6 ወራት ጊዜ ውስጥ ፈቃዳቸውን ለሚያሳድሱ አማካሪ ባለሙያዎች
ምንም አይነት የአገልግሎት ክፍያ አይጠየቅም፡፡
7) ከ 6 ወራት በኋላ ነባሩ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ካልታደሰ የማያገለግል ሲሆን ከዚህ በኋላ ለሚቀርብ
የፈቃድ ይታደስልኝ ጥያቄ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፍል እየተደረገ
ይታደሳል፡፡ ይህም ሆኖ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱ ካልታደሰ የብቃት
ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱ እንደተሰረዘ ይቆጠራል፡፡

9.4 የአካባቢ አማካሪ ድርጅቶችና ባለሙያዎች ተግባርና ኃላፊነት

1) የአማካሪ ድርጅት ፈቃድ ወይም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ሁለት ዓመት
ከመሙላቱ ከሁለት ወራት በፊት ጀምሮ ሁለት ዓመት እሰኪሞላው ድረስ ለባለስልጣኑ ቀርቦ መታደስ አለበት፡፡
ሆኖም አንድ ባለሙያ መስሪያ ቤት ሲቀይር አዲሱ ስራው ከአማካሪነት ስራው ጋር የጥቅም ግጭት የሌለው
መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
2) አንድ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ የተሰጠው ባለሙያ በሁለት ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥሮ መስራት ይችላል፡፡
3) አንድ የአካባቢ አማካሪ ድርጅት የቀጠራቸውን ባለሙያዎች ሙሉ ማስረጃ በየደረጃው ላለ የአካባቢ ጥበቃ
መስሪያ ቤት የማስወቅ ግዴታ አለበት፡፡ የባለሙያ ለውጥ ሲኖር አማካሪ ድርጅቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ
ለሚመለከተው የአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤት ለውጡን ማሳወቅ አለበት፡፡

19
4) አማካሪ ድርጅቱ ለአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤት የሚያቀርበው ማስረጃ የባለሙያዎችን ሙሉ መረጃ፣ በድርጅቱ
ውስጥ ያላቸውን ኃላፊነት፣ ስምና ፊርማ ያካተተ መሆን አለበት
5) አንድ አማካሪ ድርጅት የሚያዘጋጃቸውን ከአስር አመት ያነሰ የቆይታ ጊዜ ያላቸውን የተጽዕኖ ጥናት ዘገባዎች
በሙሉ በመረጃ ቋት የማስቀመጥና በበጀት ዓመቱ ውስጥ ያዘጋጃቸውን የጥናት ሪፖርቶች አካባቢ ጥበቃ
ባለስልጣን በሚያዘጋጀው የሪፖርት ቅጽ መሰረት ለባለስልጣኑ ሪፖርት የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
6) የአማካሪ ድርጅት ፈቃድ ወይም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የያዘ ማንኛዉም ሰዉ የምስክር
ወረቀቱን ያለአግባብ ከተጠቀመበት ወይም የሌላን ሰው የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለአግባብ ተጠቅሞ
ከተገኘ ወይም የሚጠቀምበትን የአማካሪነት ፈቃድ ማህተም ለሌላ አስተላልፎ/የራሱን ሰጥቶ/፣ ሀሰተኛ መረጃ
አያይዞ ከተገኘ ባለስልጣኑ ወይም የሚመለከተዉ የአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤት ፈቃዱ እንዲሰረዝና በህግ
እንዲጠየቅ ያደርጋል፡፡

7) ከላይ የተገለጹት ተግባርና ኃላፊነቶች እንደተጠበቁ ሆኖ የሚከተሉት ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የምስክር ወረቀቱ
ይሰረዛል፡-
1) ምስክር ወረቀት የተሰጠው ባለሙያ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ፣ ወይም በራሱ ጥያቄ
ወይም በሌላ ምክንያት ስራውን ሲተው፣
2) አመልካቹ የምስክር ወረቀቱን ያገኘው በማጭበርበር መሆኑ ከተረጋገጠ፣
3) የምስክር ወረቀት የተሰጠው ድርጅት መክሰሩ ወይም መፍረሱ አግባብነት ባለው ፍ/ቤት
ሲረጋገጥ ወይም በራሱ ምክንያት ስራውን አቁሞ የምስክር ወረቀቱን ሲመልስ፣
4) አመልካቹ ከብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ ዓላማዎች ጋር የሚቃረኑ ተግባራትን
ሲያከናውን ከተገኘ፣
5) የአማካሪ ድርጅቱ ለሰራው የአካባቢ ተፅዕኖ ዘገባ መልሶ የአካባቢ ኦዲት ሰርቶ ከተገኘ፣
6) ፈቃድ ባላገኘበት የማማከር ደረጃና ዘርፍ ተሰማርቶ ከተገኘ፣
8) የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ወይም የአማካሪ ድርጅት ፍቃድ የተሰጠው አካል በሰው ወይም በድርጅት ላይ ሆነ ብሎ
ወይም በቸለልተኝነት ሙያው የሚጠይቀውን ሥነ-ምግባር በመጣስ ስራውን ተገቢ ባልሆነ አሰራር ያከናወነ
ስለመሆኑ ከተጠቃሚዎች በህግ የተረጋገጠ ማስረጃ ሲቀርብ፤ የሌላ ሰውን ስራ የራሱ አስመስሎ የቀዳ ወይም
የገለበጠ፤ እንደ ጥፋቱ ደረጃ ከአንድ አመት እገዳ እስከ ምስክር ወረቀት ስረዛ የሚደርስ እርምጃ ይወሰዳል፡፡
9) አንድ የአካባቢ አማካሪ ድርጅት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አግኝቶ
የአማካሪነት ስራ ሲሰራ የሚያቀርባቸው የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ዘገባዎች ላይ በተደጋጋሚ የጥራት ችግር
የሚያጋጥም ከሆነ በመጀመሪያ የቃል ማስጠንቀቂያ፣ ቀጥሎም የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው በኋላ የሰነዱን
ጥራት የማያስተካክል ሆኖ ሲገኝ ባለስልጣኑ የሰጠውን የአካባቢ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት በመሰረዝ
የአካባቢ አማካሪነት ስራውን እንዲያቋርጥ ያደርጋል፡፡
10) አንድ ሰው የተለያዩ የአካባቢ አማካሪነት የሙያ ፈቃዶች ካሉት በአንድ ጥናት ውስጥ መሳተፍ የሚችለው
በአንዱ የሙያ ፈቃድ ብቻ ይሆናል፡፡ የትምህርት ዝግጅቱ ፈቅዶለት ከአንድ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር
ወረቀት ያገኘ ባለሙያ አንድ ሰነድ ዝግጅት ላይ ከአንድ መስክ በላይ ከተሠማራ ለአንድ አመት እገዳ
ይጣልበታል፡፡
11) አንድ አማካሪ ድርጅት የራሱን የልማት ፕሮጀክት በአማካሪነት ሊሰራ አይፈቀድለትም፡፡ በመሆኑም ገለልተኛ
በሆነ የአካባቢ አማካሪ ድርጅት አሰርቶ ማቅረብ አለበት፡፡ አንድ አማካሪ ድርጅት የራሱን የልማት ፕሮጀክት
ሲሰራ ከተገኘ ለአንድ አመት እገዳ ይጣልበታል፡፡

20
9.5 ለምዝገባ መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች

1) ማንኛዉም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለማዉጣት የሚቀርብ አመልካች በቅድሚያ ባለስልጣኑ
ያዘጋጀዉን የምዝገባ ፎርም ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡
2) የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለሚያወጡ ባለሙያዎች ሁለት የቅርብ ጊዜ 3x4 መጠን ያለዉ ጉርድ
ፎቶ ግራፍ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3) አዲስ የአካባቢ አማካሪነት ድርጅት ፈቃድ የምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ጥያቄ ያቀረበ ድርጅት በባለስልጣኑ
መስሪያቤት የተሰጠና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንዲሁም የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4) የምስክር ወረቀት እንዲሰጣቸው ጥያቄ ያቀረቡ የድርጅት ባለቤቶች ከአንድ ግለሰብ በላይ ከሆኑ ስልጣን ባለው
አካል የፀደቀ የድርጅት መመስረቻ ሰነድ፣ መተዳደሪያ ደንብ እና ማመልከቻውን ይዞ የቀረበው ሰው የውክልና
ማስረጃ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
5) የአንድ አማካሪ ድርጅት የአማካሪነት ደረጃ በዚህ መመሪያ በዕዝል 15.7 በተዘረዘሩት የመመዘኛ መስፈርቶች
መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
6) ደረጃው እንዲሻሻል የጠየቀ አማካሪ ድርጅት በዚህ መመሪያ መሠረት ማሟላት ያለበት የባለሙያ ዓይነትና ብዛት
በዕዝል 15.7 የተገለጸ ሲሆን፤ የታደሰ የባለሙያዎች የቀበሌ መታወቂያ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር፣ የታደሰ የብቃት
ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር እንዲሁም ከተቀጣሪ ባለሙያዎች ጋር የተደረገ የስራ ውል
ስምምነት ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
7) አዲስ የአካባቢ አማካሪ ድርጅት ፈቃድ የምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ጥያቄ ያቀረበ ድርጅት የመስሪያ ቢሮ ያለው
መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ ወይም ሕጋዊ የቤት ኪራይ ውል ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር እና የድርጅቱ ባለቤት ወይም
የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ 3x4 የሆነ ሁለት ፎቶ ግራፍ ማቅረብ አለበት፡፡
8) አዲስ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚቀርብ ማመልከቻ የአመልካቹን ዋና የትምህርት
ማስረጃና የሥራ ልምድ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
9) በመንግስት ወይም በግል መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት በቋሚነት ተቀጥረው የሚሰሩ ባለሙያዎች በተቋማቸው
የሚሰሩት ስራ የሙያ ፈቃድ ከሚጠይቁበት የአማካሪነት ስራ ዘርፍ ጋር የጥቅም ግጭት የማይፈጥር መሆኑን
ወይም የማማከር ስራ እንዲሰሩ ስለመፍቀዱ ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት/ድርጅት የጽሁፍ ማረጋገጫ ወይም የድጋፍ
ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

9.6 የአማካሪ ድርጅት ወይም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አሰጣጥ ሂደት

1) የአማካሪ ድርጅት ወይም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ይሰጠኝ ማመልከቻ ለባለስልጣኑ ቀርቦ
ለባለሙያዎች በተመራ በ 4 ቀናት ውስጥ የማስረጃ ሰነዱ ተግምግሞ ለውሳኔ ይቀርባል፡፡ የሚቀርበው ማመልከቻ
በእዝል 15.8 ላይ በተያያዘው ቅጽ መሰረት የሚቀርብ ይሆናል፡፡
2) የቀረበው የማመለክቻ ሰነድ ከተመረመረ በኋላ ውጤቱ ላይ ኃላፊው ወይም ዳይሬክተሩ የፈረበት ውሳኔ
ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ለ 5 ቀናት ተለጥፎ እንዲቆይ ይደረጋል፡፡
3) አንድ ባለሙያ ከሁለት የሙያ ዘርፎች በላይ ፈቃድ ሊወስድ አይችልም እንዲሁም ከሁለት አማካሪ ድርጅቶች
በላይም በመስራች አባልነት ሊመዘገብ አይችልም፡፡

21
4) የአማካሪ ድርጅቱ ወይም አመልካቹ ባለሙያ ያላሟላቸው ሰነዶች ካሉ እንዲሟሉ በስልክ/ በማስታወቂያ
ይነገረዋል፤ የማለፊያ ውጤቱን ላገኘ አመልካች ደግሞ ውሳኔ በተሰጠ በ 10 ቀናት ውስጥ የሙያ ፈቃድ/ የብቃት
ማረጋገጫ ሰርተፊኬቱ ይሰጠዋል፡፡
5) አንድ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ይሰጠኝ ብሎ የሚጠይቅ ጀማሪ ባለሙያ የአማካሪነት የምስክር
ወረቀት የሚሰጠው ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ የሆነውን 50% ውጤት ሲያገኝ ሲሆን የከፍተኛ አማካሪነት
የምስክር ወረቀት የሚሰጠው በመመዘኛዎች መሰረት ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ የሆነውን 70% ውጤት ሲያገኙ
ነው (መስፈርቱን በዕዝል 15.5 ይመልከቱ)
6) አንድ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ይሰጠኝ ብሎ የሚጠይቅ ባለሙያ በአቀረበው ማስረጃ ማለፍ ካልቻለ
በድጋሜ ማመልከት የሚችልው ከአንድ ዓመት የቆይታ ጊዜ በኋላ ይሆናል፡፡ የተጭበረበረ ማስረጃ አያይዞ
የሚያቀርብ ባለሙያ ካለ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዳይሰጠው እገዳ ይደረግበታል፡፡
7) በደረጃ I እና በደረጃ II የአካባቢ አማካሪ ድርጅት ፈቃድ ለማውጣት የሚያመለክቱ አካላት የአማካሪነት ፈቃድ
ለማግኘት በዚህ መመሪያ ዕዝል 15.7 ላይ የተገለጸውን ዝቅተኛ መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
8) አንድ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የተሰጠው ባለሙያ ወይም ፍቃድ የተሰጠው አማካሪ ድርጅት የደረጃ
ይሻሻልልኝ ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው ከአንድ ዓመት የቆይታ ጊዜ በኋላ ይሆናል፡፡

9.7 ስለምስክር ወረቀት አሰጣጥና ይዘት

1) በዚህ መመሪያ ውስጥ የተዘረዘሩ መስፈርቶች ላሟላ ባለሙያ ወይም አማካሪ ድርጅት የአማካሪነት የምስክር
ወረቀቱ ይሰጠዋል፡፡

2) በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እንደ አግባቡ የሚከተሉትን
መረጃዎች መያዝ አለበት፡፡
1) የባለሙያውን /የድርጅቱን ሙሉ ስም፣
2) የስራ አድራሻ፣
3) የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠበት የማማከር አገልግሎት ዘርፍ
4) የምስክር ወረቀቱ ደረጃ፣
5) የምስክር ወረቀቱ የተሰጠበት ቀን፣
6) የምስክር ወረቀቱ ፀንቶ የሚቆይበት የጊዜ ገደብ፣
7) የባለሙያውን ፎቶ ግራፍ (የድርጅቱን ባለቤት) የስራ አስኪያጅ ፎቶ ግራፍ፣
8) መለያ ቁጥር፣
9) የፈቃድ ሰጪውን ኃላፊ ስም፣ ፊርማና የባለስልጣኑ መሰሪያ ቤት ማኅተም፣

9.8 ስለቅሬታ አቀራረብ


1) በውሳኔ አሰጣጡ ቅር የተሰኘ ማንኛውም አመልካች ውሳኔው በተገለፀ በ 5 ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በጽሁፍ
ለባለስልጣኑ ማቅረብ ይችላል፡፡ አመልካቹ በ 5 ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ካላቀረበ ውሳኔውን እንደተቀበለ
ይቆጠራል፡፡
2) ቅሬታ የቀረበለት ባለሙያ ወይም ኃላፊ በ 10 ቀናት ውስጥ ቅሬታውን መርምሮ ምላሽ መስጠት አለበት፡፡
3) ባለሙያው ወይም ኃላፊው ቅሬታውን መርምሮ በሰጠው ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ አመልካች ቅሬታውን
ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይችላል፡፡

22
10 የይሁንታ ፈቃድ ሳይዙ ወደ ተግባር የገቡና የሚገቡ ፕሮጀክቶችን አሰራር ስለመወሰን

የአካባቢ ይሁንታ ሳይሰጣቸው ወደ ትግበራ የገቡ (የሚገቡ) ፕሮጀክቶች አካባቢን እየበከሉና ማህበረሰብን እየጎዱ
መቀጠል ስሌለባቸው አዋጅ ቁጥር 181/2003 ዓ.ም አንቀጽ 6 (1 ሐ) ህጉን ተፈፃሚ በማድረግ የሚደርሰውን
ጉዳት መከላከል (ማስቀረት) የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ በመሆኑም፡-
1) አዋጅ ቁጥር 181/2003 ዓ.ም አንቀጽ 6 (1 ሐ) መሰረት የተሰጠውን የዕፎይታ ጊዜ በመጠቀም የአካባቢ
አያያዝ ዕቅድ ሳያዘጋጅና ይሁንታ ሳያገኝ ወደተግባር ገብቶ የተገኘ ፕሮጀክት ከሃምሳ ሺህ ብር እስከ አንድ መቶ
ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል፡፡ ቅጣቱን ከፈጸመ በኋላም በ 3 ወራት ጊዜ ውስጥ የፕሮጀክቱን የአካባቢ
ምርመራ በራሱ ወጭ በማካሄድ ችግሩን (ተጽዕኖውን) የሚያቃልል የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ አዘጋጅቶ በማቅረብ
ይሁንታ ሰርተፊኬት ማግኘት አለበት፡፡
2) በዚህ መመሪያ በተራ ቁጥር 10.1 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ የፕሮጀክት ባለቤቱ በተሰጠው የጊዜ ገደብ
ውስጥ የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ በማቅረብ ይሁንታ ሰርተፊኬት ሳያገኝ የቀረ እንደሆነ ከመቶ ሃምሳ ሺህ ብር
በማያንስና ከሁለት መቶ ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡
3) ፕሮጀክቱ በአካባቢና በማህረሰቡ ላይ ጉዳት ወይም ብከለት ያደረሰ እንደሆነ በሌሎች ህጎች የሚጠየቅ መሆኑ
እንደተጠበቀ ሆኖ የንግድ ፈቃዱ ለተወሰነ ጊዜ እንዲታገድ ወይንም ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ ለፈቃድ ሰጪ
መስሪያ ቤቱ በደብዳቤ ይገለፃል፡፡ ደብዳቤው የደረሰውም የንግድ ፈቃድ ሰጪ መስሪያቤት የሰጠውን የንግድ
ፈቃድ ማገድ ወይንም መሰረዝ ይኖርበታል፡፡ የአካባቢ ግብረ-ሀይልም ይህ የማገድ (የመዘረዝ) ውሳኔ ተግባራዊ
እንድሆን የማድረግ ኃላፊነት አለበት
4) የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አዋጅ ቁጥር 181/2003 አንቀጽ 25/2 መሰረት አዋጁ ከወጣ በኋላ የአካባቢ
ተፅዕኖ ግምገማ የጥናት ዘገባ ሳያቀርብና የይሁንታ ፈቃድ ሳያገኝ ወደ ተግባር የገቡ ፕሮጀክት ከሃምሳ ሺህ ብር
በማያንስና ከመቶ ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ተቀጥቶ በ 3 ወራት ጊዜ ውስጥ የፕሮጀክቱን የአካባቢ
ምርመራ በማካሄድ ተጽዕኖውን የሚያቃልል የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ አዘጋጅቶ በማቅረብ የይሁንታ ሰርተፊኬት
ማግኘት አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ የፕሮጀክቱ ስራ ለጊዜው እንዲቋረጥ ተደርጎ የአካባቢ አያያዝ እቅድ በተሟላ
መንገድ ተዘጋጅቶ በሚመለከተዉ አካል ተቀባይነት ሲያገኝ ፕሮጀክቱ እንደገና ስራ እንዲጀምር ይደረጋል፡፡
በአካባቢ ክትትልና ቁጥጥር በሰውና አካባቢ ላይ ጉዳት ማድረሱ ከተረጋገጠ በወንጀልና በፍታብሔር ህጎች
እንዲጠየቅ ይደረጋል፡፡
5) በዚህ መመሪያ በተራ ቁጥር 10.3 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ የፕሮጀክት ባለቤቱ የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ
በማቅረብ የይሁንታ ሰርተፊኬት ሳያገኝ የቀረ እንደሆነ አግባብ ባላቸው ህጎች መጠየቁ እንደተጠበቀ ሆኖ የንግድ
ፈቃዱ እንዲሰረዝ ለፈቃድ ሰጪ መስሪያ ቤቱ በደብዳቤ ይገለፃል፡፡ ደብዳቤው የደረሰውም የንግድ ፈቃድ ሰጪ
መስሪያ ቤት የሰጠውን የንግድ ፈቃድ መሰረዝ ይኖርበታል፡፡ የአካባቢ ጥበቃ ግብረ ሀይልም የማገድ/ የመዘረዝ
ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
6) ፕሮጀክቱ በአካባቢና በማህረሰቡ ላይ ጉዳት ወይም ብከለት ያደረሰ እንደሆነ አግባብ ባላቸው ህጎች መጠየቁ
እንደተጠበቀ ሆኖ የስራ/የንግድ ፈቃዱ እንዲሰረዝ ለፈቃድ ሰጪ መስሪያ ቤቱ በደብዳቤ ይገለፃል፡፡ ደብዳቤው
የደረሰውም የስራ/የንግድ ፈቃድ ሰጪ መስሪያቤት የሰጠውን የስራ/የንግድ ፈቃድ መሰረዝ ይኖርበታል፡፡ የአካባቢ
ጥበቃ ግብረ ሀይልም የማገድ/ የመዘረዝ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡

23
7) በዚህ መመሪያ የተደነገገዉ እንደተጠበቀ ሆኖ በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት ጥፋት ሲፈፅም ድርጅቱ
እንዲከፍለው ከተፈረደበት መቀጮ በተጨማሪ የአካባቢ ህጉን ማስከበር የነበረበት ኃላፊ/መሪ መፈፀም
የሚገባውን ተግባር በትጋት ያልተወጣ በመሆኑ ከአምስት ሺህ ብር በማያንስና ከአስር ሺህ ብር በማይበልጥ
የገንዘብ መቀጮ ወይንም ከአንድ አመት በማያንስ ከ 3 ዓመት በማይበልጥ እስራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል፡፡
8) አዋጅ ቁጥር 181/2003 ዓ.ም ወይም በሥሩ የወጣዉን ይህን መመሪያ በመጣስ ጥፋተኛነቱ የተረጋገጠበትን
ሰው/ድርጅት ከሚወሰንበት ከማንኛውም ቅጣት በተጨማሪ የደረሰውን ጉዳት በሙሉ በራሱ ወጪ
እንዲያስተካክል ወይም እንዲተካ እና ካሳ እንዲከፍል ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት ማዘዝ ይችላል፡፡
9) በዚህ መመሪያ በተራ ቁጥር 10.6፣ 10.7 እና 10.8 የተደነገገዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ፕሮጀክቱ በአካባቢ ላይ
ያደረሰዉ ጉዳት ከፍተኛ ከሆነ ፕሮጀክቱ እንዲቋረጥ፣ እንዲዘረዝ ወይም የቦታ ለዉጥ እንዲያደርግ ባለስልጣኑ
ወይንም በዞንና በወረዳ ያሉ የአካባቢ ጥበቃ መ/ቤቶች ሊወስኑ ይችላሉ፡፡ የአካባቢ ጥበቃ ግብረ ሀይልም ይህ
ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
10) በዚህ መመሪያ በተራ ቁጥር 10.6፣ 10.7 እና 10.8 የተደነገገዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ፕሮጀክቱ ያደረሰው
ጉዳት ከፍተኛ ካልሆነ እና በተፅዕኖ ማቅለያ መቀነስ የሚቻል ከሆነ በ 3 ወራት ጊዜ ውስጥ የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ
በማዘጋጀት ይሁንታ ሰርተፊኬት እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ አቅርቦ ይሁንታ ሰርተፊኬት
የማያገኝ ከሆነ ግን ፕሮጅከቱ እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡
11) በተራ ቁጥር 10.1፣ 10.3፣ 10.4 እና 10.10 የተጠቀሱት እንደተጠበቁ ሆኖ ፕሮጀክቶች የአካባቢ
አያያዝ ዕቅድ ካዘጋጁ በኋላ የተዘጋጀዉን የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስቸግር አዲስ ሁኔታ
ወይም አሰራር የሚከሰት ከሆነ የአካባቢ አያያዝ ዕቅዱ መከለስና በሚመለከተዉ አካል በኩል እንደገና መጽደቅ
አለበት፡፡
12) አንድ የአካባቢ አያያዝ እቅድ የሚያገለግልበት የጊዜ ርዝማኔ ጣሪያ 10 ዓመት ሲሆን የ 3 ዓመት የዝርዝር
ተግባራት የድርጊት መርሀ ግብር ይኖረዋል፡፡ የዝርዝር ተግባራት እቅድ በየ 3 ዓመቱ የሚዘጋጅ ሲሆን ከአስር
አመት በኋላ ሰነዱ ሙሉ በሙሉ በአዲስ መልክ የሚከለስ ይሆናል፡፡
11 ስለአካባቢ ወሰን ልየታ ሪፖርት ዝግጅት

የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ጥናት ከመጀመሩ በፊት የአካባቢ ወሰን ልየታ ማካሄድ እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚታይ
ሂደት ነው፡፡ የአካባቢ ወሰን ልየታ (scoping) ተካሂዶ ለአካባቢ ጥበቃ ተቋም ከቀረበ በኋላና ይሁንታ ሲገኝ ወደ
ዋናው ጥናት ይገባል፡፡ የወሰን ልየታ ጥናት አላማ ዋና ዋና የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖዎችንና ትኩረት የሚሹ
ጉዳዮችን ለመለየትና የተጽዕኖ ጥናት ስራውን በእቅድ ለመምራት ነው፡፡ የወሰን ልየታ ጥናት ሪፖርት
ለሚመለከተው የአካባቢ ጥበቃ መስሪያቤት ከመቅረቡ በፊት ፕሮጀክቱ ስለሚያስከትላቸው አካባቢያዊና
ማህበራዊ ተጽዕኖዎች ከሚመለከታቸው አካላትና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ግልጽ ውይይት ሊካሄድ ይገባዋል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚከተሉት ነጥቦች የወሰን ልየታን አካሄድና አሰራር የሚመለከቱ ናቸው፡፡

24
11.1 የወሰን ልየታ አሰራር ቅደም ተከተል
1) የፕሮጀክቱ ባለቤት የወሰን ልየታ ሪፖርት ከማቅረቡ በፊት አጠቃላይ ዝርዝር የፕሮጀክቱን መግለጫ (project
description) ከተጽዕኖ ልየታ (screening) ሪፖርት ጋር ለባለስልጣኑ ወይንም በተዋረድ ላለ የአካባቢ
ጥበቃ መስሪያቤት ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
2) በአንቀጽ 11.1. የተጠቀሰው ግደታ እንደተጠበቀ ሆኖ የፕሮጀክት የወሰን ልየታ ሪፖርት እንዲያቀርብ
የሚፈቀድለት አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ዝርዝር መግለጫ (project description) ተገምግሞ ከአካባቢና
ማህበራዊ ደህንነት አኳያ ተቀባይነት ሲያገኝ ብቻ ይሆናል፡፡
3) የአካባቢ ወሰን ልየታ ዘገባ የውጭ ሽፋን የሚይዛቸው መረጃዎች
1) የፕሮጀክቱ ስም
2) የፕሮጀክቱ ባለቤት ስምና ሙሉ አድራሻ
3) የአማካሪ ድርጅቱ ሙሉ ስምና አድራሻ
4) ሰነዱ የተዘጋጀበት ጊዜ ወርና አመት እንዲሁም ሰነዱ የተዘጋጀበት ቦታ ስም
11.2 የወሰን ልየታ ዘገባ ስለሚይዛቸው ዝርዝር ሃሳቦች
1) ስለፕሮጀክቱ የተለያዩ መግለጫዎች
1) አጠቃላይ የፕሮጀክቱ መግለጫ (የፕሮጀክቱን ስም፣ ዓላማ፣ ባለቤት፣ የሚካሄድበት ቦታ፣
እና የፕሮጅክቱ የቆይታ ጊዜ)
2) ፕሮጀክቱ የሚጠቀመው የግብዓት አይነትና መጠን፣ የምርት አይነትና መጠን ፣ የቆሻሻ
አይነትና መጠን፣ የአመራረቱ ዘዴ፣ በእያንዳንዱ የፕሮጀክቱ ደረጃዎች (ግንባታ፣ ትግበራ እና
መዝጊያ ጊዜ) የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
3) ፕሮጀክቱ የሚጠቀመው ቴክኖሎጂ፣ የሚጠቀመው ግብዓትና የፕሮጀክቱ የትግበራ ጊዜን
መሰረት በማድረግ ለእያንዳንዳቸው ቢያንስ ሁለት ሁለት አማራጮችን በማወዳደር
ከአካባቢያዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት አኳያ የተሻለውን አማራጭ ለመምረጥ
የሚያስችል የጥናት ስራ እንደሚሰራ እንዲሁም ፕሮጀክቱ ቢተገበርና ባይተገበር ያለውን
ጠቀሜታና ጉዳት ለማመዛዘን የሚያስችል ትንተናዎችን የሚያካተት መሆን ይኖርበታል፤
2) ፕሮክቱ የሚተገበርበትን ልዩ ቦታና ተጽዕኖ የሚያደርስበትን አካባቢ አጭርና ግልፅ የሆነ
ባዮፊዚካልና ማህበረ ኢኮኖሚ መረጃ መያዝ አለበት፡፡ መረጃውም የውሃ አካላትን፣ የአፈርን፣
የእንስሳትንና እፅዋትን፣ የጥበቅ ቦታዎችንና ተያያዥነት ያላቸውን የስርዓተ-ምህዳሮች
ጠቀሜታን፣ የማህበራዊና ባህላዊ እሴቶችን፣ ታሪካዊ ቅርሶችን፣ የህብረተሰብ ጤናና የመሰረተ
ልማት ሁኔታዎችን መረጃ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
3) በፕሮጀክቱ ትግበራ ምክንያት ይከሰታሉ ተብለው የሚገመቱ ጉልህ አዎንታዊና አሉታዊ
ተፅዕኖዎችን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
4) የህብረተሰብ ተሳትፎ መረጃ (በፕሮጀክቱ ትግበራ ተጠቃሚ፣ ተጎጂ፣ ፍላጎቱ ያላቸውና
የሚመለከታቸውን አካላት ተለይተው ከፕሮጀክት ባለቤትና ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር
የተወያዩበትና የተፈራረሙበት ቃለ ጉባኤና ምስል) ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡ የማህበረሰብ
ውይይት ቃለጉባኤ የሚከተሉትን ነጥቦች ያካተተ መሆን አለበት፡-

25
1) ለህብረተሰቡ የቀረቡ የፕሮጀክቱ ዋና ዋና አካባቢያዊና ማህበራዊ አሉታዊና
አዎንታዊ ተጽዕኖዎች፣
2) ህብረተሰቡ ስለፕሮጀክቱ ተጽኖዎች ያለው አመለካከት፣
3) በፕሮጀክቱ አካባቢ ያለ የቀበሌና ወረዳ የመንግስት አስተዳደር አካላት ስለፕሮጀክቱ
አካባቢያዊና ማህበራዊ አሉታዊ ተፅዕኖዎች የሰጡት አስተያየት፣
4) በህብረተሰቡ የተነሱ ስጋቶች፣
5) በተነሱ አሉታዊ ተፅዕኖዎችና ስጋቶች ላይ የተቀመጡ የመፍትሄ ሃሳቦች ናቸው፡፡
5) የአካባቢ ወሰን ልየታ ሪፖርቱ የመጨረሻ ውጤቱ የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ቢጋር ማዘጋጀት
ስለሆነ ቢጋሩ የሚከተሉትን ነጥቦች ያካተተ መሆን አለበት፡-
1) የፕሮጀክቱ የመነሻ ሃሳብና የፕሮጀክቱና የጥናቱ ዓላማዎች፣
2) በካርታ የተደገፈ የፕሮጀክት ቦታው መገኛና አዋሳኞች፣
3) የአካባቢ ተጽዕኖ የጥናት ዘዴ (ስልት) ከመረጃ ስብሰባ እስከ ማጠቃለያ ጥቅም ላይ
የሚውሉ ዝርዝር የጥናት ዘዴዎች፣
4) ሊከሰቱ የሚችሉ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ተጽእኖዎች፣ የተጽእኖዎችን
ዝርዝርና አሳሳቢነት
5) የጥናት ቡድኑ የሙያ ስብጥር፣ ኃላፊነትና ግዴታዎች፣
6) በቀጣይ በስፋት መተንተን ያለባቸው አማራጮች፣
7) የህብረተሰብና የተቋማት የተሳትፎ ሁኔታ በተጽዕኖ ጥናት ዘገባ ዝግጅትና በረቂቅ
የተጽዕኖ ጥናት ዘገባ ግምገማ፣
8) ጥናቱ የሚያካትታቸው ዋና ዋና አካባቢዊና ማህበራዊ ተፅዕኖዎች እና ሌሎች ቁልፍ
ጉዳዮች፣
9) በአካባቢ ተጽዕኖ የአሰራር መመሪያ ክፍል 2 ላይ የተገለጸው የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት
ሰነድ ይዘት (table of contents) እና
10) የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ጥናት ስራ የሚካሄድበት የጊዜ ሰሌዳ ናቸው፡፡
11) አሳማኝ ምክንያት ካልተፈጠረ በስተቀር የአንድ ፕሮጀክት የተጽዕኖ ግምገማ
የጥናት የጊዜ ሰሌዳ የወሰን ልየታው ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት
ውስጥ መጠናቀቅ አለበት፡፡
12) የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ስራው በጸደቀው የጊዜ ሰሌዳ ለማጠናቀቅ የማያስችል
አሳማኝ ምክንያት ለአካባቢ ጥበቃ ተቋም የበላይ ኃላፊ ቀርቦ ልዩ የጥናት የጊዜ
ሰሌዳ ማስተካከያ ካልተሰጠ በስተቀር በቢጋሩ ውስጥ በጸደቀው የጊዜ ሰሌዳ
መሰረት ተጠናቅቆ የማይቀርብ የተጽኖ ጥናት ሪፖርት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
በመሆኑም የተጽዕኖ ጥናት ስራው ውድቅ ሆኖ እንደገና ከወሰን ልየታ ሪፖርት
ዝግጅት ጀምሮ እንዲጠና ይደረጋል፡፡

26
6) ዕዝሎች
የሚከተሉት መረጃዎች በዕዝል ውስጥ መያያዝ አለባቸው፤
1) የጥናት ቡድኑ አባላት የትምርት ዝግጅትና የሥራ ልምድ መረጃ ወይም ግለ-ታሪክ፣
2) የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የታደሰ የአካባቢ አማካሪ ድርጅት እና የሙያ ፈቃድ፣
3) የህብረተሰብ ተሳትፎ ቃለ ጉባኤ፣
4) የፕሮጀክቱ ቦታ ካርታና ኮኦርዲኔትስ፣አካባቢውን የሚያሳዩ ፎቶግራዎች፣
5) የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፊዎችን የሚያሳዮ ከለርድ ፎቶግራፎች፣
6) በፕሮጀክት ባለቤቱና በአማካሪ ድርጅቱ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት ለማካሄድ
የተስማሙበት በሁለቱም ፊርማና ማህተም የተረጋገጠ የጥናት ውል ስምምነት
ማስረጃ፣
7) ከሚመለከታቸው አካላት የድጋፍ ደብዳቤ እና ሌሎችም መረጃዎች ካሉ እና
8) ከመጨረሻው የወሰን ልየታ ዘገባ ቀድሞ በቀረበው ሰነድ ላይ ከባለሙያዎች
እንዲካተትና እንዲስተካከል የተሠጠ አስተያየት ቅጅ
11.3 የወሰን ልየታ ሪፖርትን በተመለከተ የባለሙያዎች ተግባርና ኃላፊነት
1) የተለየ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች የፕሮጀክት የመስክ ምልከታ የሚያካሂዱት አንድ
ጊዜ ብቻ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን የፕሮጀክቱ ባህሪ ውስብስብ ከሆነ በአካባቢ ጥበቃ ተቋማት የበላይ ኃላፊዎች
ውሳኔ ሁለተኛ መስክ ምልከታ እንዲደረግ ሊታዘዝ ይችላል፡፡
2) የወሰን ልየታ ዘገባ ለባለስልጣኑና በተዋረድ ለሚገኙ የአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤቶች ለግምገማ ሲቀርብ የጥናት
የውል ስምምነት ሆኖ ስለሚያገለግል በባለሀብቱና በአማካሪ ድርጅቱ ተረጋግጦና ማህተም አርፎበት ሊቀርብ
ይገባል፡፡
3) አንድ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ባለሙያ ለግምገማ ከቀረበለት የወሰን ልየታ ሪፖርት በመነሳት ፕሮጀክቱ ምን ምን
ተጽዕኖዎች ሊያደርስ እንደሚችል ቀድሞ ማወቅ ይጠበቅበታል፤ ፕሮጀክቱ የሚያስከትለውን የአካባቢ ተጽዕኖ
ቀድሞ የማያውቀው ከሆነ (የዕውቀት ክፍተት ካለበት) ለሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ማሳወቅ አለበት፡፡
4) የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ከዚህ በላይ በአንቀጽ 11.2 የተዘረዘሩት መረጃዎች በቀረበው የወሰን ልየታ ዘገባ
ውስጥ መካተታቸውን በመገምገም የፕሮጀክቱ ጉልህ ተጽዕኖዎችንና ጉዳዮችን በአግባቡ መለየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
5) የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ከዚህ በላይ በአንቀጽ 11.2 የተዘረዘሩት ተግባራት በትክክል በመስክ
መከናወናቸውን ለማረጋገጥና ፕሮጀክቱ ከተገለጸው የፕሮጀክት ቦታ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ለማረጋገጥ
የሚያስችል ቸክሊስት በማዘጋጀት የመስክ ምልከታ ያደርጋሉ፡፡
6) የመስክ ምልከታ ቸክሊስቱ ከፕሮጀክቱ ዝርዝር መግለጫ፣ በሪፖርቱ እዝል ላይ ከተያያዙ መረጃዎችና በክልሉ
የተጽኖ አሰራር መመሪያ ላይ ከተዘረዘሩት የፕሮጀክት ተጽዕኖ መጠይቆች መካከል የፕሮጀክቱን አይነት መሰረት
በማድረግ ይዘጋጃል፡፡
7) የመስክ ምልከታ ያደረገ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ በአዘጋጀው ቸክሊስት መሰረት የሰበሰበውን መረጃ በመተንተን፣
በምስል በማስደገፍና የውሳኔ ሀሳብ በማካተት የመስክና የዴስክ ግምገማውን ያካተተ የወሰን ልየታ ዘገባ
ግብረመልስ በማዘጋጀት ዘገባውን ላቀረበ አማካሪ ድርጅት በ 3 ቀናት እንዲደርስ ያደርጋል፡፡ የግብረ ምልሱ

27
ግልባጭ ለክትትል ይረዳ ዘንድ ለክፍል ሀላፊው (ለዳሬክቶሬት ዳሬክተሩ ወይም ቡድን መሪው) እንዲደርስ
መደረግ አለበት፡፡
12 ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ህጎች
1) ከዚህ መመሪያ ጋር ተቃራኒ የሆነ ህግ ወይም አሰራር በዚህ መመሪያ ዉስጥ በተመለከቱት ጉዳዮች ላይ
ተፈፃሚነት አይኖረዉም፡፡
2) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአካባቢ ጥበቃ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ለአካባቢ አማካሪዎች
ፈቃድ ለመስጠት የወጣ መመሪያ ቁጥር 01/2006 ዓ.ም በዚህ መመሪያ ተሽሯል፡፡
13 መመሪያ ስለማሻሻል

ይህን መመሪያ ባለስልጣኑ አስፈላጊ ሆኖ ባገኘዉ ጊዜ ሊያሻሽለዉ ይችላል፡፡

14 መመሪያዉ የሚጸናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት


የአካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን
ባህርዳር ሀምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም

28
15 ዕዝሎች
15.1 የአካባቢ አያያዝ እቅድ ፎርማት
የፕሮጀክቱ አሉታዊ የማቅለያ የታቀዱ የተጽእኖ ፈጻሚ የማቃለያ ተግባራት የሚተገበሩበት ጊዜ የሚያስ
የፕሮጀክቱ ምዕራፍ

ዝርዝር ተፅኖዎች ተግባራት/ ማቅለያ ተግባራት አካል 2010 2011 2012 ፈልግ
ተግባራት tasks በጀት
or 1 2 3 4 1 2 3 4 1 2 3 4
activiti
es መለኪያ መጠን
ግንባታ
ቅድመ
ግንባታ
አገልግሎትወቅት
በማምረት/
ፕሮጀክቱ ሲዘጋ/
ሲጠናቀቅ

29
15.2 የአካባቢ ክትትል እቅድ ፎርማት

የፕሮጀክቱ የተፅዕኖ የተግባራት ክትትሉ የተፅዕኖ የክትትል ፈጻሚ ወጪዎች


ተጽዕኖ ማቅለያ አመላካቾ የሚደረግበት ማቅለያ ድግግሞሽ ተቋም/አካ
ተግባራት ች ቦታ ተግባራት ል
መፈፀ
ማቸውን
ማረጋገጫ
ዘዴዎች

ይህ የአካባቢ ክትትል ዕቅድ በአማርኛ ተዘጋጅቶ ለፕሮጀክት ባለቤቱ መሰጠት ያለበት ሲሆን ዕዝል ላይም
አብሮ መያያዝ ይኖርበታል፡፡ የሚዘጋጀው የአካባቢ ምርመራና ክትትል ሪፖርት በተቋሙ በጸደቀው
የመስክ ቢጋር መሰረት የሚቀርብ ሆኖ በዋናነት መግቢያ፣ የተከናወኑ ዋናዋና ተግባራት፣ እቅድ ክንውን
በሰንጠረዥ፣ የምርመራ፣ ክትትልና ቁጥጥር ግኝቶች፣ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች፣ ያጋጠሙ ችግሮች፣
የተወሰደ የመፍትሄ እርምጃና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ያካተተ ይሆናል፡፡

15.3 የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሪፖርት ግምገማ ማጠቃለያ ቅፅ

የአካ/ተ/ግ/ሰነድ ርዕስ፣ ……………ቀንና ቁጥር ……………የኘሮጀክቱ ስም ………………......

30
የገምጋሚው/ዎቹ/ ስም …………………………………
ተ የመገምገሚያ መስፈርቶች ክብደት ሌላ ተጨማሪ
/ቁ የዘገባው ክፍል የዘገባው ክፍል የሚያስፈልግ
አስፈላጊነት በቂነት መረጃ
/ትክክለኛነት
1 ስለ ፕሮጀክቱ የቀረበው ገለጻ 9 6
1.1 የፕሮጀክቱ አላማና አካላዊ (ፊዚካላዊ) ባህርይ በበቂ ሁኔታ 3.5 1
ተገልጸዋል?
1.2 የፕሮጀክቱ ስፋትና መጠን በደንብ ተለክቶ ተገልጧል ወይ? 0.9 0.8
1.3 የምርት ሂደቱ እና የሚጠቀማቸው ግብዓቶች በደንብ 1.6 1.5
ተዘርዝሯል ወይ?
1.4 ዝቃጭ/ቅሪትና ወደ አካባቢ የሚለቀቁ ቆሻሻዎች (ፕሮጀክቱን 1.3 0.8
የሚመለከተው ከሆነ) በአግባቡ ተገልጧል?
1.5 የአደጋና አደገኛ ነገሮች ስጋቶች በትክክል ተገልጸዋል? 1.4 1.2
1.6 በፕሮጀክቱ አገላለፅ ላይ ሌሎች አስፈላጊ ጥያቄዎች ካሉ? 0.3 0.7
2 የፕሮጀክቱ አማራጮች ገለፃ 5 5.6
3 የፕሮጀክቱ አካባቢ መሰረታዊ መረጃ ገለፃ 12.6 8
3.1 የፕሮጀክቱ አካባቢ ሁኔታ/ጉዳዮች ገለፃ 5.6 3.4
3.2 የመረጃ አሰባሰብ ስልትና የአሰባሰብ ዘዴ ትክክለኛነት 4.8 2.6
3.3 በአካባቢ ሁኔታዎች አገላለፅ ላይ ሌሎች አስፈላጊ ጥያቄዎች 2.2 2
ካሉ
4 የፕሮጀክቱ ጉልህ አካባቢዊና ማህበራዊ ተፅዕኖዎች ገለፃ 13.3 10
4.1 የተፅዕኖ ወሰን ልየታ ሁኔታ 3.6 1.2
4.2 ቀጥተኛ የአካባቢ ተፅዕኖዎች ትንበያ 1.4 1.3
4.3 ቀጥተኛ ያልሆነ፣ ጊዜያዊ፣ የአጭር ጊዜ፣ ቋሚ፣ የረዥም ጊዜ፣ 1.8 1.3
ድንገተኛ፣ ተዳማሪና አንዱ በሌላው ላይ የሚያደርሰው
መስተጋብራዊ ተፅዕኖዎች ትንበያ
4.4 በሰዎች ጤናና ዘላቂ ልማት ጉዳዮች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ 2.4 1.7
ተጽዕኖዎች/ለውጦች ትንበያ
4.5 የተፅዕኖዎችን ክብደት ደረጃ መገምገም ሂደት 1.8 1.8
4.6 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ዘዴ 1.4 0.9
4.7 በተፅዕኖ ገለፃ ላይ ሌሎች አስፈላጊ ጥያቄዎች ካሉ 0.5 0.5
4.8 በማህበረሰብ ዉይይቱ ወቅት ማህበረሰቡ ያነሳቸዉ 1.3 1.3
አስተያየቶች፣ አመለካከቶችና ስጋቶች በአካባቢ ተጽእኖ
ግምገማ ዘገባው ዉስጥ መካተቱንና ቃለጉባኤ መያያዙን
5 የተፅዕኖ ማስተሰረያ/ማቅለያ ትንታኔ 10.2 9
6 የማጠቃለያ ፅሁፍ አገላለፅ 2.8 3.2
7 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት አቀራረብ/አገላለፅ/አፃፃፍ 2.2 2.2
ጥራት
ጠቅላላ የተሰጠ ክብደት 56 44

15.3.1 የአካባቢ ተጽእኖ ጥናት ዘገባ መገምገሚያ ዝርዝር መመዘኛ ቅፅ


1. የአካ/ተ/ግ/ሰነድ ርዕስ፣ ቀንና ቁጥር ……………………….
2. የኘሮጀክቱ ስም ………………………………………......
3. የገምጋሚው/ዎቹ/ ስም …………………………………
…………………………………
………………………………...
ተ. ቁ የመገምገሚያ ነጥቦች ሌላ ተጨማሪ የሚያስፈልግ መረጃ
የመረጃው
አስፈላነት
የመረጃ

በቂነት

አለ

ክፍል 1. ፕሮጀክቱ ስለሚያከናውናቸው


ተግባራት ሙሉ መግለጫ
የፕሮጀክቱ አላማና አካላዊ (ፊዚካላዊ) ባህርይ
1.1 የፕሮጀክቱ አስፈላጊነትና አላማዉ በበቂ ሁኔታ ተገልጸዋል?

31
ተ. ቁ የመገምገሚያ ነጥቦች ሌላ ተጨማሪ የሚያስፈልግ መረጃ

የመረጃው
አስፈላነት
የመረጃ

በቂነት
አለ

1.2 ፕሮጀክቱ የሚተገበርበት ፕሮግራም በበቂ ሁኔታ ተገልጧል?


ፕሮጀክቱ ግንባታ በሚጀምርበትና በሚጨርስበት ጊዜ፣
አገልግሎት በሚሰጥበት ወይም ምርት በሚያመርትበት ጊዜ እና
ስራ በሚያቆምበት ጊዜ የሚከናወኑ ተግባራት በዝርዝር
ተገልጸዋልን?

1.3 ሁሉም የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ክፍሎች ተጠቅሰዋል?


1.4 እያንዳንዱ የፕሮጀክቱ ክፍሎች የሚገኙበት ቦታ በካርታ፣
በፕላን እንዲሁም በስዕላዊ መግለጫ በአግባቡ ተመልክቷል?
1.5 በፕሮጀክቱ የግንባታ ቦታዎች የአቀማመጥ እቅድ በአግባቡ
ተመልክቷል? (የቦታዉን አቀማመጥ የማደላደል ስራ፣
ህንጻዎችን፣ ከመሬት በታች የሚሰሩ ስራዎችን፣ መጋዝኖችን፣
የዉሃ መስመሮችን፣ የእጽዋት ቦታዎችን፣ የመተላለፊያ
መንገዶችን፣ የፕሮጀክቱን ወሰን እና ሌሎች ፊዚካላዊ
ግንባታዎች ይጨምራል)
1.6 የመስመር ዝርጋታ ፕሮጀክቶች ማለትም የሀይል
ማስተላለፊያ መስመሮች፣ የቧንቧ መስመሮች፣ መንገዶች፣
የውስጥ ለውስጥ መተላላፊያ መንገዶች፣ የአግዳሚና ቋሚ
መተላላፊያዎች አቀማመጥ፣ ከመሬት በታች ያሉ መተላለፊያ
መስመሮች ስራ በአግባቡ ተገለጸዋል?
1.7 ሁሉም የፕሮጀክቱ ግንባታ ስራዎች ተጠቅሰዋል?
1.8 ፕሮጀክቱ አገልግሎት በሚሰጥበት ጊዜ ወይም ምርት
በሚያመርትብት ጊዜ የሚከናወኑ ተግባራት በሙሉ
በአግባቡ ተገልጸዋል?
1.9 ፕሮጀክቱ ስራ በሚያቆምበት ወቅት የሚሰሩ ስራዎች በሙሉ
ተገልጸዋል? (ማሽን ነቀላ፣ ህንጻ ማፍረስ፣ ማጽዳት፣
ቦታዉን ወደ ነበረበት መመለስ ወዘተ)
1.10 ሌሎች ለፕሮክቱ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ አገልግሎቶች
በሙሉ ተገልጸዋል? (የማጓጓዣ መንገዶች፣ ዉሃ፣ የፍሳሽ
ማስወገጃ መስመሮች፣ የቆሻሻ ማስወገጃ፣ የሚያስፈልገዉ
ሀይል ወይም ተጨማሪ የሚሰሩ የመንገድ፣ የሀይል መስመር
እንዲሁም የዉሃ ቧንቧ መስመሮች ወዘተ)
1.11 በፕሮጀክቱ ልማት የተነሳ ሊተገበሩ የሚችሉ ሌሎች
ልማቶች ተልይተዋል? (አዲስ የቤቶችና መንገዶች ግንባታ፣
የዉሃ ወይም የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃዎች፣ የግንባታ
ማቴሪያሎች መቆፈሪያ ቦታዎች ወዘተ)
1.12 በፕሮጀክቱ ምክንያት የሚቀየር ወይም የሚያቆሙ ነባር
ስራዎች ተለይተዋል?
1.13 ከዚህ ፕሮጀክት ጋር ተደማሪ ተጽእኖ ሊያደርሱ የሚችሉ
ነባር ወይም የታቀዱ ልማቶች ተለይተዉ በአግባቡ
ተገልጸዋል?
የፕሮጀክቱ ስፋት /መጠን
1.14 በፕሮጀክቱ ቋሚ የግንባታ ክፍሎች እንዲዉል የታቀደዉ
የቦታ ስፋት መጠኑ ተገልፆ በካርታ ላይ ተመልክቷል?
1.15 በፕሮጀክቱ ግንባታ ወቅት በጊዚአዊነት የሚያገለግል ቦታ
(መጋዝን፣ ካምፕ ወዘተ) መጠን ታዉቆ በካርታ ላይ
ተመልክቷል?
1.16 በፕሮጅከቱ ትግበራ ወቅት በጊዜአዊነት ሲያገለግሉ የነበሩትን
ቦታዎች መልሶ የማልማት እቅድ ተካቷል? (የካባ ቦታዎች፣
የመወጣጫ ግንባታዎች፣ የአፈርና አሸዋ ማውጫ ቦታዎች
1.17 ወዘተ )
የፕሮጀክቱ አካል የሆኑት የህንጻ ግንባታዎች ወይም ሌሎች
የግንባታ ስራዎች መጠንና ቦታ ተለይተዋል? (የወለል

32
ተ. ቁ የመገምገሚያ ነጥቦች ሌላ ተጨማሪ የሚያስፈልግ መረጃ

የመረጃው
አስፈላነት
የመረጃ

በቂነት
አለ

ስፋትና የህንጻዉ ርዝመት፣ የአፈር ማዉጫ ጉድጓዶች


ስፋት፣ የአፈርና የዉሃ መከላከያ የባዮ ፊዚካል ስራዎች፣
ድልድዮች፣ የዉሃ ፍሰት ወይም ጥልቀት ወዘተ)
1.18 የህንጻ መዋቅሮችና ገፅታዎች ወይም ሌሎች ስራዎች
አይነትና ይዘት ተጠቅሰዋል? (ጥቅም ላይ የሚዉሉት
ግባቶችና አይነታቸዉ፣ የህንጻዉ ቅርጽ፣ የእጽዋት ዝርያዎች
አይነት ወዘተ)
1.19 በከተማ ልማትና በተመሳሳይ የልማት ፕሮጀክቶች
በሚከናወኑበት ጊዜ ልማቱን ተከትለው ሊሰፍሩ የሚችሉ
ማህበረሰቦች ወይንም ሊፈጠር የሚችል የንግድ ማህበረሰብ
በአግባቡ ተገልጿል?
1.20 ፕሮጀክቱ ማህበረሰብንና የስራ እንቅስቃሲዎችን
የሚያፈናቅል ከሆነ በፕሮጀክቱ ምክንያት የሚፈናቀል
ህብረተሰብ ብዛትና ሌሎች ጉዳዮች ተገልጸዋል?
1.21 አዲስ የመንገድ መሰረተ ልማት ወይም ጉልህ የሆነ የትራፊክ
ፍሰት ለዉጥ ሊያስከትል የሚችሉ ፕሮጀክቶች ከሆነ
የአዲሱ ትራፊክ አይነት፣ መጠኑ፣ ጊዜአዊ መተላላፊያ
መስመሮች እና የቦታ ስርጭቱ ተገልጿል?
የአመራረት ሂደቶችና ግብአቶች
1.22 ፕሮጀክቱ በሚተገበርበት ጊዜ የሚከናወኑ አጠቃላይ ሂደቶች
ተጠቅሰዋል? (የማመምረት ወይም የምህንድስና ሂደቶች፣
ለግብአት የሚሆኑ ጥሬ እቃዎችን የማምረት፣ የግብርና
ወይም የደን ዉጤቶችን የማምረት ዘዴዎች፣የማዉጣት
ሂደቶች ወይም ተፈላጊውን ምርት ከጥሬ ዕቃው
የመለየትወዘተ)
1.23 በፕሮጀክቱ የሚመረቱ የምርት አይነቶችና መጠን
ተገልጸዋል?
1.24 በግንባታ ወቅትና ፕሮጀክቱ ስራውን በሚጀምረበት ወቅት
የሚያስፈልጉ ግብአቶችና የሀይል ፍላጎት መጠንና አይነት
ተገልጧል?
1.25 ግብአቶችን መጠቀም ከአካባቢ አንጻር ያለዉ አድምታ
1.26 ተብራርቷል ?
የሀይልና የግብአት አጠቃቀም ዉጤታማነት ተገጸዋል?
1.27 ፕሮጀክቱ በግንባታ፣ በማምረት/አገልግሎት በመስጠት ሂደት
እና ፕሮጀክቱ ስራ በሚያቆምበት/ማጠናቀቂያ ወቅት
የሚጠቀምባቸዉ፣ የሚከዝናቸዉ፣ ወይም የሚያመርታቸዉ
ዋና ዋና አደገኛ ቁሶች አይነትና በመጠን ተለይተዋል?
1.28 የግብአት እቃዎችን ወደ ፕሮጀክቱ ስለማጓጓዙና ስለ ትራፊክ
ፍሰቱ ቁጥር ተጠቅሷል?
በግንባታ፣
በትግበራ እንዲሁም
ስራ በሚያቆምበት/ የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ወቅት
1.29 በፕሮጀክቱ ምክንያት የስራ አድል መፈጠሩን ወይም ከስራ
መፈናቀል ካለ ተጠቅሷል?
በግንባታ፣
በትግበራ እንዲሁም
ስራ በሚያቆምበት/ የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ወቅት
1.30 ፕሮጀክቱ በግንባታ፣ በማምረት/አገልግሎት በመስጠት ሂደት
እና ፕሮጀክቱ ስራ በሚያቆምበት/ማጠናቀቂያ ወቅት
ለሰራተኞችና ደንበኞች አገልግሎት ስለሚሰማሩ
የትራንስፖርት ተደራሽነትና የትራፊክ እንቅስቃሴ ቁጥር
ተጠቅሷል
1.32 ለቋሚና ጊዜአዊ ሰራተኞች የቤትና ሌሎች አገልግሎቶች
አቅርቦት በተመለከተ ተገልጧል?

33
ተ. ቁ የመገምገሚያ ነጥቦች ሌላ ተጨማሪ የሚያስፈልግ መረጃ

የመረጃው
አስፈላነት
የመረጃ

በቂነት
አለ

ዝቃጭ/ቅሪትና ወደ አካባቢ የሚለቀቁ ቆሻሻዎች (ከፕሮጀክቱ የሚመነጩ ካሉ)


1.33 ፕሮጀክቱ በግንባታ፣ በማምረት/አገልግሎት በመስጠት ሂደት
እና ፕሮጀክቱ ስራ በሚያቆምበት/ማጠናቀቂያ ወቅት
በፕሮጀክቱ የሚመነጭ የደረቅ ቆሻሻ መጠንና አይነት
ተለይተዋል? (የግንባታና የህንጻ ፍርስራሽ ቆሻሻ፣ የተበላሸ
ግብዓት/ምርት፣ የምርት ሂደት ቆሻሻ፣ ተረፈ ምርት፣ አደገኛ
ቆሻሻ፣ ከቤት ወይም ከንግድ ድርጅቶች የሚመነጭ ቆሻሻ፣
የግብርና ወይም የደን ውጤቶች ቆሻሻ፣ ከፕሮጀክት ቦታ
ማፅዳትየሚሰበሰብ ቆሻሻ፣ የማእድን ማዉጣት ቆሻሻ፣
ፕሮጀክቱ ሲዘጋ/ሲጠናቀቅ የሚመነጭ ቆሻሻ ወዘተ)
1.34 በፕሮጀክቱ ምክንያት የሚመነጨዉ ሁሉም የደረቅ ቆሻሻ
ዉህዶችና የመርዛማነት ደረጃ ወይም አደገኝነት ተገልጧል?
1.35 ደረቅ ቆሻሻን የመሰብሰብ፣ የማከማቸት፣ የማከም፣
የማጓጓዝና በመጨረሻም የመስወገዱ ስራ ተገለጧል?
1.36 የደረቅ ቆሻሻ መጨረሻ ላይ የሚወገድበት ቦታዉ ተለይቷል?
1.37 ፕሮጀክቱ በግንባታ፣ በማምረት/አገልግሎት በመስጠት ሂደት
እና ፕሮጀክቱ ስራ በሚያቆምበት/ ማጠናቀቂያ ወቅት
ከፕሮጀክቱ የሚመነጨዉ ፍሳሽ ቆሻሻ በአይነትና በመጠን
ተለይቷል? (ከፕሮጀክት ግቢ የሚመነጭ ጎርፍ፣ በምርት
ሂደት የሚፈጠሩ ፍሳሽ ቆሻሻዎች፣ የማቀዝቀዣ ውሃ/ቆሻሻ፣
ከግቢ የሚወጣ ፍሳሽ ቆሻሻ፣ ከማጣሪያ የሚወጣ የተጣራ
ፍሳሽ ቆሻሻ ወዘተ)
1.38 በፕሮጀክቱ ምክንያት የሚመነጨዉ ሁሉም የፍሳሽ ቆሻሻ
ዉህዶችና የመርዛማነት ደረጃ ወይም አደገኝነት ተገልጧል?
1.39 የፍሳሽ ቆሻሻ አሰባበሰብ፣ አቀማመጥ፣ ማከም፣ መጓጓዝና
በመጨረሻም ማስወገደጃ ዘዴዎች ተገልጧል?
1.40 የሁሉም ፍሳሽ ቆሻሻ የመጨረሻ ማስወገጃ ቦታዉ ተለይቶ
ታዉቋል?
1.41 ፕሮጀክቱ በግንባታ፣ በማምረት/አገልግሎት በመስጠት ሂደት
እና ፕሮጀክቱ ስራ በሚያቆምበት/ ማጠናቀቂያ ወቅት
በፕሮጀክቱ የሚመነጩ የጋዝና የብናኝ ልቀቶች አይነትና
መጠን ተለይተዋል? (የምርት ሂደት ልቀት፣ የጭስ ልቀት፣
ነዳጅን ከሚጠቀሙ ከቋሚና ተንቀሳቃሽ የሀይል
ማመንጫዎች የሚወጣ ልቀት፣ ከተሽከርካሪ የሚወጣ
ልቀት፣ ከእቃዎች አያያዝ የሚወጣ አቧሯ፣ ሽታ ወዘተ)
1.42 በፕሮጀክቱ ምክንያት ወደ አየር የሚለቀቁትሁሉም ልቀቶች
ዉህዶችና የመርዛማነት ደረጃ ወይም አደገኝነት ተገልጧል?
1.43 ወደአየር የሚለቀቁ ልቀቶች አሰባሰብ፣ ማጣራትና
በመጨረሻም ወደ አየር የሚለቀቁበት ዘዴዎች ተገልጧል?
1.44 ሁሉም የጋዝ ልቀቶች ወደ አየር የሚለቀቁበት ቦታ
እንዲሁም የሚለቀቁት ጋዞች ባህርይ ተለይተዋል?
(የጋዝ/የጭስ መልቀቂያ ቧንቧ ቁመት፣ የጋዙ/የጭሱ የልቀት
ፍጥነትና የሙቀት ደረጃ ወዘተ)
1.45 ፕሮጀክቱ ቆሻሻ የሚያመነጭ ከሆነ ከነዚህ ቆሻሻዎችና
ዝቃጮች መልሶ የመጠቀም እድሉ ካለ ተብራርቷል?
(መልሶ መጠቀም፣ ለዳግም ዑደት ማዋል ወይም ከፍሳሽና
ደረቅ ቆሻሻ ሀይል ማመንጨት)
1.46 ፕሮጀክቱ ድምጽን፣ ሙቀትን፣ ብርሀን ወይም የኤሌክትሮ
ማግኔቲክ ራዴሽን መጠን የሚጨምር ከሆነምንጫቸዉና
መጠናቸዉ ተለይቶ ታዉቃል?
1.47 ፕሮጀክቱ ዝጋጭና የጋዝ/ጭስ ልቀት የሚያመነጭ ከሆነ
የዉህዶችን አይነትና መጠናቸዉን መለኪያ ዘደዎች
ተቀምጠዋል የጋጠሙ ችግሮችስካሉ ተገልፀዋል?
1.48 ፕሮጀክቱ ዝቃጭና ጋዝ/ጭስ ልቀቶችን የሚያነጭ ከሆነ

34
ተ. ቁ የመገምገሚያ ነጥቦች ሌላ ተጨማሪ የሚያስፈልግ መረጃ

የመረጃው
አስፈላነት
የመረጃ

በቂነት
አለ

የዝቃጩንና የልቀቱን መጠን ለማወቅ ስለተጠቀመው ዘዴ


እርግጠኛነት አብሮ ተብራርቷል?
የአደጋና አደገኛ ነገሮች ስጋቶች
1.49 በፕሮጀክቱ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶች/አደጋዎች
ተገልጸዋል?
ከአደገኛ ነገሮች አያያዝ ችግር ሊደርስ የሚችል ስጋት
ከሚፈሱ ነገሮች እሳትና ፍንዳታዎች የሚከሰት አደጋ
የተሸከርካሪ አዳጋ/ስጋት
ከማምረቻ መሳሪዎች መሰበር ወይም አለመስራት ጋር
የሚመጡ አደጋዎች/ስጋቶች
ፕሮጀክቱ በተፈጥሮ አደጋዎች መጋለጥ ምክንያት ሊመጡ
የሚችሉ ስጋቶች (የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ጎርፍ፣ የመሬት
መንሸራተት ወዘተ)
1.50 አደጋና ያልተለመዱ ሁኔታዎችን ለመከላከል ስለሚወሰዱ
እርምጃዎች ተብራርቷል? (የመከለከያ ዘዴዎች፣
ስልጠናዎች፣ የመጠባበቂያ እቅዶች፣ የአደጋጊዜ እቅድ
ወዘተ)
ስለፕሮጀክቱ ማብራሪያ ሌሎች ተጨማሪ ጥያቄዎች
የፕሮጀክት አማራጮችን በተመለከተ
2.1 ፕሪጀክቱንየበለጠ ውጤታማ የተደረገበት ሂደት
ተብራርቷል?
2.2 ፕሮጅከቱን የበለጠ ውጤታማ በማድረግ ሂደት የተሻሉ
አመራጮች ካሉ ግምት ዉስጥ ገብተዋል?
2.3 ፕሮጅቱ ከመተግበሩ በፊት ያለዉ የአካባቢዉ/ቦታዉ
አጠቃላይወይም ነባራዊሁኔታ ተብራርቷል?
2.4 የተጠቀሱት አማራጮች ተዓማኝነትና ለፕሮጀክቱ ትክክለኛ
አማራጮች ናቸዉ?
2.5 አካባቢያዊ ምክንያቶችን ጨምሮ ፕሮጀክቱ የተመረጠበት
ዋና ምክንያቶች ተብራርተዋል?
2.6 በፕሮጅክት አማራጮች የሚደርሰዉ አካባቢያዊ ተጽእኖ
ከፕሮጀክቱ ተጽእኖ ጋር በተነፃፃሪነት ተገለጧል?
የዋና ዋና አካባቢያዊ ተፅዕኖዎች ማቅለያ አማራጮች ሊተገበር
ከታሰበው ፕሮጀክት ጋር ጠቀሜታው በተነፃፃሪነት ተቀምጧል
ውይ?
የፕሮጀክቱን አማራጮች በተመለከተ ሌሎች ጥያቄዎች
2.7 በጥናት ሰነዱ የተዘረዘሩ አማራጮች ከቦታ፣ ከጊዜ፣ ከቴክኖሎጂ፣ ከጥሬ
ዕቃ፣ ከዲዛይ፣ ከሂደት፣ የማቅለያ ዘዴዎች እና ፕሮጀክቱ ቢተገብርና
ባይተገበር አማራጮችን የዳሰሰ ነው ወይ?
2.8 በእያንዳንዱ አማራጭ ቢንያስ ሁለት ማወዳደሪያ አማራጮች ቀርበው
የከአካባቢና ማህበራዊ ጉዳዮች ግምት ውስጥ ገብተው የተሻለውን
አማራጭ በመምረጥ የተከናወነ ነው ወይ?
ክፍል 3 በፕሮጀክቱ ምክንያት ተጽእኖ ሊደርስባቸዉ ስለሚችሉ አካባቢዎች ገለጻ
የአካባቢዉነባራዊ ሁኔታ
3.1 ለፕሮጀክቱ አገልግሎት ሚውለው ቦታና አካባቢው የመሬት
አጠቃቀሙ ሁኔታ፣ በፕሮጀክቱ የሚወሰደው ቦታ፣
በፕሮጀክቱ ቦታ የሚኖሩ ወይም ቦታውን እየተጠቀሙ ያሉ
ሁሉም ሰዎች ተለይተዋል ወይ? (የመኖሪያ፣ የንግድ፣
የኢንዱስትሪ፣ የግብርና፣ የመዝናኛ ወዘተ)
3.2 የፕሮጀክቱ ቦታና አካባቢዉ መልከዓ-ምድር፣ ስነ-ምድር
እንዲሁም አፈር ሁኔታተብራርቷል?
3.3 የአካባቢዉ መልከአምድር ወይም የአካባቢዉ ስነምድር
ጉልህ መለያ ባህርያት ወይም ገፅታዎች እንዲሁም የአፈሩ

35
ተ. ቁ የመገምገሚያ ነጥቦች ሌላ ተጨማሪ የሚያስፈልግ መረጃ

የመረጃው
አስፈላነት
የመረጃ

በቂነት
አለ

ሁኔታናእየሰጠ ያለዉ ጥቅም ተብራርቷል? (የአፈሩ ለምነት፣


አፈሩ ለክለት ያለዉ ጥንካሬ፣ ለግብርና ያለዉ ጠቀሜታና
ለግብርና የሚዉለዉ የመሬት ጥራትን ጨምሮ)
3.4 ፕሮጀክቱ የሚተገበርበት ቦታና አካባቢዉ ስላሉ እጽዋትና
እነስሳት እንዲሁም የተፈጥሮ መኖሪያ ቦታዎች (ሚችጌ)
በተመለከተ የተብራራና በካርታ ላይ የተመላከተ ነዉ?
3.5 በፕሮጀክቱ ጉዳት ሊደርስባቸዉ የሚችሉ የስነህይዎት መኖሪ
ቦታዎች ባህርያትና በዉስጣቸዉ የያዟቸዉ የዝርያ ብዛት
የሚገልጽ ማብራሪያ አለ እንደዚሁም ተለይተው የታወቁልዩ
ጥበቃ የሚደረግላቸዉ ዝርያዎች ወይም ቦታዎች ተለይተዉ
ተቀምጠዋል(በፕሮጀክቱ አካባባቢ ካለ)?
3.6 ፕሮጀክቱ በዉሃ አካላት ላይ ተጽእኖ የሚያደርስ ከሆነ
የዉሃዉ ሁኔታና አካባቢዉ በአግባቡተገልጧል? (ወራጅና
የቆመ የዉሃ አካላትን ጨምሮ የከርሰምድር ዉሃ፣ ሀይቆች፣
ዉሃ አዘል መሬት፣ ጎርፍና ማንጣፈፊያን ይጨምራል)
3.7 በፕሮጀክቱ ተጽእኖ ሊደርስበትየሚችልየውሃ ሃብት፣ የውሃ
ባህሪና ስርጭት፣ ፍሰት፣ የዉሃ ጥራት እንዲሁም የዉሀ
አጠቃም ተገልጸዋል? (ለመጠጥ ዉሃ አቅርቦት፣ አሳ
ማስገርና እርባታ፣ ለገላ መጣጠቢያና መዋኛ፣ ለመጓጓዣ፣
ለተጣራፍሳሽ ማስወገጃ ያለዉ ጠቀሜታ፣ ስነውበት፣ ወዘተ
ጭምር)
3.8 የአካባቢዉ ከባቢ አየር በፕሮጀክቱ ተጽእኖ የሚደርስበት
ከሆነ የአየር ንብረትና የእለታዊ የአየር ሁኔታ እንዲሁም
በወቅቱ ያለዉ የአየር ጥራት ሁኔታ ተገልጧል?
3.9 ፕሮጀክቱ በአካባቢዉ ድምጽ ላይ ተጽእኖ የሚያስከትል
ከሆነ የወቅቱ የድምጽ ደረጃ ተመልክቷል?

3.10 የአካባቢዉ ብርሀን፣ ሙቀትና ኤሊክትሮማግኔቲክ ጨረራ


ሁኔታ በፕሮጀክቱ ተጽእኖ የሚደርስባቸዉ ከሆነ የወቅቱ
ነባራዊ ሁኔታ ተገልጸዋል?

3.11 በፕሮጀክቱ ጉዳት ሊደርስባቸዉ የሚችሉ ቁሳዊ ሀብቶች


ተብራርተዋል? (ህናጻዎችና ሌሎች አዉታሮች፣ የማእድን
ሀብቶች፣ የዉሃ ሀብቶችን ወዘተ ይጨምራል)
3.12 የፕሮጀክቱ የስራ እንቅስቃሴ የሚነካቸዉ/የሚያቋርጣቸው
የከርሰምድር ቅሬተ አካልና ቦታዎች፣ የታሪካዊ፣ ስነ-ህንፃዎች
ወይም ሌሎች የማህበራዊና ባህላዊ ጠቀሜታ ያለቸዉ
ቦታዎች እንዲሁም ተከልለው የሚጠበቁ/ጥብቅ ቦታዎችን
ጨምሮ ተብራርተዋል?
3.13 በፕሮጀክቱ ሊጎዳምክክንያት ጉዳት ሊደርስበት የሚችል
መልክዓ-መድር፣ተከልሎ የሚጠበቅ/ጥብቅ መልክዓ-ምድር
ቦታን ጨምሮ ተገልጧ?
3.14 የአካባቢዉ የህብረተሰቡ አሰፋፈር፣ አኗኗ፣ ስርጭት፣ የህዝብ
ብዛት፣ የህዝብ እድገት፣ ትፍፍግ፣ ስነተዋልዶ፣ ጋብቻ፣የጤና
ሁኔታ እና ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች
(ለምሳሌ የስራ እድል ሁኔታ) ተገልጧል?
3.15 ከላይ ከተዘረዘሩት ዉስጥ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ባይሆንም
ወደፊት ሊለወጡ የሚችሉ የአካባቢ ሁኔታዎች ካሉ
ተብራርተዋል ወይ?
የመረጃ አሰባሰብና የመረጃ አወሳሰድ ዘዴ
3.16 የጥናቱ ወሰን ስፋት በፕሮጀክቱ ጉልህ ተጽእኖ
ሊድርስባቸዉ ይችላል ተበሎ የሚታሰቡትን ሁሉንም
ቦታዎች የሚያካትት ነዉ?

36
ተ. ቁ የመገምገሚያ ነጥቦች ሌላ ተጨማሪ የሚያስፈልግ መረጃ

የመረጃው
አስፈላነት
የመረጃ

በቂነት
አለ

3.17 መሰረታዊ መረጃጃዎችን በማሰብሰቡ ሂደት ሁሉምንም


የሚመለከታቸዉ ሀገር አቀፍና ክልላዊ ድርጅቶችና ተቋማት
ጋር ግንኙነት ተደርጓል?
3.18 የመሰረታዊ መረጃ ምንጮችናየተሰበሰበው መረጃ በበቂ
3.19 የአካባቢዉን ነባራዊ ሁኔታ መሰረታዊ መረጃ ለመሰብሰብ
በሚካሄደዉ የአካባቢ ዳሰሳዊ ጥናት ወቅት ተግባር ላይ
የዋሉት ዘዴዎች፣ ያጋጠሙ ማንኛዉም ተግዳሮቶች
እንዲሁም ያልተጠበቁ ሁኔዎች መረጃ ተጠቅሷል?
3.20 የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማን ለማጥናት ጥቅም ላይ የዋሉ
ዘዴዎች አግባብነት ያላቸዉ ነበሩ?
3.21 በአካባቢ መሰረታዊ መረጃው ላይ ያሉ ጠቃሚ የመረጃ
ክፍተቶች ተለይተዋል? ይህንን ክፍተት ለማስወገድ
የተወሰዱ ዘዴዎችስ ?
3.22 የአካባቢዉን ነባራዊተገልጸዋል
መሰረታዊ መረጃ በበቂ ሁኔታ
ለመግለጽ የዳሰሳ ጥናት ቢያስፈልግ ነገር ግን በተለያዩ
ምክንያቶች ይህን ማድረግ ሳይችል ቢቀር ምክንያቶች
ተዘርዝረዋል ወደፊትስ እንዴት መጠናት እንዳለበት
ተመላክቷል?
የአካባቢዉን መሰረታዊ መረጃበተመለከተ ሌሎች ጥያቄዎች ካሉ

ክፍል 4 በፕሮጀክቱ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ጉልህ የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖዎችን ገለፃ
የተጽእኖዎች ወሰን ልየታ
4.1 ለአካባቢ ተጽዕኖጥናትየወሰን ልየታ የአሰራርሂደቱ ተለይቶ
4.2 የታወቀ ነበር
ለአካባቢ ወይ?
ተጽዕኖጥናት ወሰን ልየታ የተጠቀሙበት ስልታዊ
ዘዴ ግልጽ ነበር?
4.3 ለአካባቢ ተጽዕኖጥናት የወሰን ልየታ ወቅት በቂ የሆነ
ማህበረሰቡ ዉይይት መካሄዱን የሚገልጹ መረጃዎች
ቀርበዋል?
4.4 በማህበረሰብዉይይቱ ወቅት ማህበረሰቡ ያነሳቸዉ
አስተያየቶች፣ አመለካካቶችና ስጋቶች በአካባቢ ተጽእኖ
ግምገማ ዘገባው ዉስጥ ተካቷል?
ቀጥተኛና ዋና (የመጀመሪያ ደረጃ )የሆኑየአካባቢ ተጽእኖዎች ትንበያ
4.5 ፕሮጀክቱ በመሬት አጠቃቀም ላይ፣ በህብረተሰቡ ላይ እና
በሀብት ላይ የሚያደርሰዉ ቀጥተኛ እና ዋና (የመጀመሪያ
ደረጃ) ተጽእኖዎች ተገልጸዋል (ከተቻለ በመጠን ጭምር)?
4.6 ፕሮጀክቱ በመሬት ገጽታና በአፈር ባህርይ ላይ የሚያደርሰዉ
ቀጥተኛ እና ዋና (የመጀመሪያ ደረጃ) ተጽእኖዎች ተገልጸዋል
(በመጠን ጭምር)?
4.7 ፕሮጀክቱ በእጽዋት፣ በእንስሳትና በተፈጥሮ መኖሪያዎች
(ሙቹጌ)ላይ የሚያደርሳቸዉ ቀጥተኛ እና ዋና (የመጀመሪያ
ደረጃ) ተጽእኖዎች ተገልጸዋል (ከተቻለ በመጠን ጭምር)?
4.8 ፕሮጀክቱ በዉሃ ሃብት ስርጭት፣ ፍሰት፣ ባህሪ እና በዉሃ
ጥራት ላይ የሚያደርሳቸዉ ቀጥተኛ እና ዋና (የመጀመሪያ
ደረጃ)ተጽእኖዎች ተገልጸዋል (ከተቻለ በመጠን ጭምር)?
4.9 ፕሮጀክቱ በዉሃ አጠቃቀም ላይ የሚያደርሰዉ ቀጥተኛ እና
ዋና (የመጀመሪያ ደረጃ)ተጽእኖ ተገልጸዋል (ከተቻለ
በመጠን ጭምር)?
4.10 ፕሮጀክቱ በአየር ጥራትና በአየር ንብረት ሁኔታ ላይ
የሚያደርሰዉ ቀጥተኛ እና ዋና (የመጀመሪያ ደረጃ)ተጽእኖ
ተገልጧል (ከተቻለ በመጠን ጭምር)?
4.11 ፕሮጀክቱ በአካባቢው ላይየሚያደርሰዉ ቀጥተኛና ዋና
(የመጀመሪያ ደረጃ)የሆነ የድምጽ (ጫጫታና ንዝረት)
ተጽእኖ ተገልጧል (ከተቻለ በመጠን ጭምር)?

37
ተ. ቁ የመገምገሚያ ነጥቦች ሌላ ተጨማሪ የሚያስፈልግ መረጃ

የመረጃው
አስፈላነት
የመረጃ

በቂነት
አለ

4.12 ፕሮጀክቱ በሙቀት፣ ብርሃን ወይም ኤሌክትሮመግኒጢሳዊ


ጨረራ ላይ የሚያደርሰዉ ቀጥተኛ እና ዋና (የመጀመሪያ
ደረጃ) ተጽዕኖ ተገልጧል (ከተቻለ በመጠን ጭምር)?
4.13 ፕሮጀክቱ በቁሳዊ እሴቶችና ታዳሽ ባልሆኑ የተፈጥሮ
ሀብቶች ላይ የሚያደርሰዉ ቀጥተኛ እና ዋና (የመጀመሪያ
ደረጃ)ተጽእኖ ተገልጧል?
4.14 ፕሮጀክቱ ባህላዊ ጠቀሜታ ባላቸዉ ቦታዎች ላይ
የሚያደርሰዉ ቀጥተኛ እና ዋና (የመጀመሪያ ደረጃ)ተጽእኖ
ተገልጧል?
4.15 ፕሮጀክቱ በመልከዓምድር ገጽታና ዉበት ላይ የሚያደርሰዉ
ቀጥተኛ እና ዋና (የመጀመሪያ ደረጃ) ተጽእኖ በአግባቡ
ተገልጧል?
4.16 በፕሮጀክቱበህብረተሰቡ አሰፋፈር፣ አኗኗ፣ ስርጭት፣ የህዝብ
ብዛት፣ የህዝብ እድገት፣ ትፍፍግ፣ ስነተዋልዶ፣ ጋብቻ፣የጤና
ሁኔታ እና ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ላይ
የሚያደርሰዉ ቀጥተኛ እና ዋና (የመጀመሪያ ደረጃ) ተጽእኖ
ተገልጧል? (ከተቻለ በመጠን ጭምር)

ሁለተኛ ደረጃ ተጽእኖ፣ ቀጥተኛ ያልሆነ፣ ጊዜአዊ፣ ለአጭር ጊዜ፣ ቋሚ፣ የረጅም ጊዜ፣ በድንገተኛ፣ ተደማሪና አንዱ ተጽእኖ በሌላዉ ላይ
የሚያደርሰዉ (መስተጋብራዊ) ተጽእኖዎች ትንበያ
4.17 ከላይ በተዘረዘሩት አካባቢያዊ ጉዳዮች ተመስርቶ በዋና
(የመጀመሪያ ደረጃ) ተጽዕኖዎች ምክንያት የሚከሰቱ ሌሎች
ሁለተኛ ደረጃ ተጽዕኖዎች ተገልፀዋል ከተቻለ በቁጥር
(በአሃዝ)? (በአፈር አየርና ዉሃ ብክለቶች ምክንያት
በእጽዋት፣ እንስሳት ወይም የተፈጥሮ መኖሪያዎች (ምቹጌ)
ላይ የሚደርስ ተጽእኖ፣ በዉሃ ሃብት ለዉጥና በዉሃ ጥራት
ለዉጥ ምክንያቶች በዉሃ አጠቃቀም ላይ የሚደርስ ተጽእኖ፣
በአፈር መድረቅና መሰነጣጠቅ ምክንያት በመሬት ዉስጥ
ባለቅሬተ-አካል ላይ የሚደርሱ ተጽእኖዎች)
4.18 ፕሮጀክቱ በሚዘጋበት ወይም የተወሰነ ጊዜ ዋናውን ስራ
በሚሰራበት ወይም በግንባታ ወቅት የሚደርሱ
ጊዜያዊ/ለአጭር ጊዜ የሚቆዩ ተጽእኖዎች ተገልጸዋል?
4.19 ፕሮጀክቱ በግንባታ፣ ዋናውን ስራ በሚሰራበት (በማምረት
ሂደት) ወይም በሚዘጋበት ወቅት የሚደርሱ ቋሚ፣ ዘላቂ
ወይም የረዥም ጊዜ ተጽእኖዎች ተገልጸዋል?
4.20 ፕሮጀክቱ በእድሜ ዘመኑ በየጊዜዉ ወደ አካባቢ በሚለቀዉ
የበካይ ነገሮች ጥርቅም ምክንያት ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ
ተጽእኖዎች ተጠቅሰዋል?
4.21 ከአደጋዎች፣ ከአልተለመዱ ሁኔታዎች ወይም ፕሮጀክቱ
በተፈጥሮ ወይም በሰዉ ሰራሽ አደጋዎች በመጋለጡ
ምክንያት የሚፈጠሩ ተጽእኖዎች ተብራርተዋል?ከተቻለ
በአሃዝ
4.22 በፕሮጀክቱ ተዛማጅ/ተጓዳኝ ስራዎች ምክንያት በአካባቢ
ላይ የሚደርሱ ተጽእኖዎች ተጠቅሰዋል? (ተዛማጅ ወይም
ተጓዳኝ ስራዎች ለፕሮጀክቱ መጋቢ መንገድ ስራና መሰረተ
ልማቶች፣ ለግንባታ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ምሳሌ የድንጋይ፣
የጠጠር፣ የአሸዋናየአፈር ማዉጫ ቦታዎች፣ የሀይል
አቅርቦትና ማምረት፣ ቆሻሻ ማስወገድ ወዘተ)
4.23 በፕሮጀክቱ ተጓዳኝ ስራዎች ምክንያት በአካባቢ ላይ
የሚደርሱ ቀጥተኛ ያልሆኑ ተጽእኖዎች ተገልጸዋል? (ተጓዳኝ
ስራዎች ማለት የፕሮጅከቱ አካል ሳይሆኑ ነገር ግን
ፕሮጀክቱን የሚያጠናክሩ ናቸዉ፡፡ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ
አዳዲስ እቃዎችንና አገልግሎቶችን ማቅረብ፣ ፕሮጀክቱን
ለመደገፍ የቤት አገልግሎቶችንና ሌሎች ንግዶችን ማቅረብ
ወዘተ)

38
ተ. ቁ የመገምገሚያ ነጥቦች ሌላ ተጨማሪ የሚያስፈልግ መረጃ

የመረጃው
አስፈላነት
የመረጃ

በቂነት
አለ

4.24 የፕሮጀክቱ ተደማሪ ተጽእኖዎችና መስተጋብራዊ ወይም


አንዱ በሌላዉ ላይ የሚያደሱት ተጽእኖዎችን ጨምሮ
ከሌሎች ነባርና አዳዲስ ፕሮጀክቶች ጋር በመሆን በአካባቢ
ላይ የሚያደርሱት ተጽእኖዎች ተገልጸዋል
4.25 የእያንዳንዱ ተጽእኖ ከመልከአ-ምድራዊ ስፋት፣ ከቆይታ
ጊዜ፣ ከመከሰትድግግሞሽ፣ ወደ ነበረበት ከመመለስ እና
ተጽእኖዉ ከመከሰት እድል አንጻር ተለይተዋል?
በሰዉ ጤናና ዘላቂ ልማት ጉዳዮች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ተጽእኖዎችን መተንበይ
4.26 በፕሮጀክቱ በሰዉ ጤናና ደህንነት ላይ ሊደርሱ የሚችሉ
የመጀመሪያና (ዋና) ሁለተኛ ደረጃ ተጽእኖዎች ተገልጸዋል?
(ወደ አካባቢ መርዛማ ነገሮችን በመልቀቅ፣ ከፕሮጀክቱ ጋር
በተያያዙ አደጋዎች ምክንያት የሚደርሱ የጤናስጋቶች፣
ከፕሮጀክቱ ጋር በተያያዙ በበሽታ አምጭ ነፍሳቶች መለወጥ
ምክንያት የሚመጡተጽእኖዎች፣ ለጉዳት ተጋላጭ በሆኑ
ክፍሎች ላይ የሚደርሱ፣ የአኗኗር ዘየ ለዉጦች ወዘተ
የሚደርሱ ተጽእኖዎች)
4.27 በብዝሀ ህይዎት፣ በአለም የአየር ጸባይ ለዉጥና በዘላቂ
ልማት ላይ የሚደርሱ ተጽእኖዎች ተብራርተዋል?
የተጽእኖዎችን ክብደት /ደረጃ መገምገም
4.28 የተተነበዩትን ተጽእኖዎች ደረጃ/ክብደት ማሟላት
ከሚገባቸዉ የህግ ግዴታዎች አንጻር ተቃኝተዋል?
4.29 በአካባቢ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ተጽእኖዎችን ለመገምገም
አግባብነት ያላቸዉ የክልል፣ የፌደራል ወይም የአለም አቀፍ
የአካባቢ ደረጃዎችና የአሰራር መመሪያዎች በጥቅም ላይ
ዉለዋል?
4.30 ከአሉታዊ ተጽኖዎች በተጨማሪ አወንታዊ ተጽዕኖዎችም
ተገልጸዋል?
4.31 የእያንዳንዱ ተጽእኖ ክብደት/ደረጃ ተብራርቷል?
የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ዘዴ
4.32 ተጽእኖዎችን ለመተንበይ ጥቅም ላይ የዋሉ ዘዴዎችና ለምን
እነዚህ ዘዴዎች እንደተመረጡ እንዲሁም ያጋጠሙ
4.33 የፕሮጀጅቱን ትክክለኛ ዝርዝር ሁኔታና በአካባቢ ላይ
የሚያደርሰዉን ተጽእኖ እርግጠኛ አለመሆን ለትንበያ
አስቸጋሪ ጉዳዮች መሆናቸዉ ተገልጸዋል?
4.34 የካባቢ ተጽእኖዎችን ለመተንበይ የሚያገልግሉ መረጃዎች
በሚሰበሰቡበት/በሚደራጁበት ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች
ተለይተው ታወቀዋል ወይ፣ በጥናቱ ውጤት ላይ
የሚያስከትሉት እንድምታስ ተገልጧል?
4.35 የተጽእኖዎች ደረጃ/ክብደት መገምገሚያ መነሻዎች
ወይምመስፈርቶቹተብራርተዋል?
4.36 የአካባቢ ተጽእኖዎች የተገለጹት ሊተገበሩ የሚችሉ
የማስተሰርያ ዘዴዎችን መሰረት አድርገዉ ነዉ?ቀሪታዊ
ተጽእኖዎችስ ተገልጸዋል?
4.37 የእያንዳንዱ ተጽእኖ ግምገማ ደረጃ ለፕሮጀክቱ የይሁንታ
ዉሳኔ ለማሰጠት በሚያስችል ሁኔታ ነዉ የተካሄደው? በዋና
ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ እና ጠቃሚ ያልሆኑ ወይም
የማያስፈልጉ ጉዳዮችን ያስወገደ ነዉ?
4.38 ግምገማዉ ለጉልህ ተጽእኖዎች የበለጠ ትኩረት የሰጠና
ለዝቅተኛ ተጽእኖዎች ደግሞ ዝቅተኛ ትኩረት የሰጠ ነዉ?
ሌሎች ሊከሰቱ የሚችሉ ተጽዕኖዎች ጥያቄዎች ካሉ

ክፍል 5 የተጽእኖ ማስተሰረያ /ማቅለያ መግለጫ

39
ተ. ቁ የመገምገሚያ ነጥቦች ሌላ ተጨማሪ የሚያስፈልግ መረጃ

የመረጃው
አስፈላነት
የመረጃ

በቂነት
አለ

5.1 በየትኛዉም አካባቢ ላይ ጉልህ አሉታዊ ተጽእኖዎች


በሚኖሩበት ጊዜ ለማስተሰረያ/ለማቅለያ የሚሆኑ አማራጮች
ተብራርተዋል?
5.2 ተጽእኖዎችን ለማስተሰረይ/ለማቅለል የፕሮጀክት ባለቤቱ
ሊተገብራቸዉ ስላቀዳቸዉ ዘዴዎች በግልጽ ተብራርተዋል?
የተፅዕኖውን ጉልህነትና ክብደት ለመቀነስ የሚያመጣዉ
ለዉጥስ ተገልጧል?
5.3 ለከባድና ጉልህ ተጽዕኖችየተቀመጡየማስተሰርያ ዘዴዎች
የተዋጣላቸዉ/ዉጤታማ የመሆኑ ጉዳይ አጠራጣሪ ከሆነ
ጉዳዩ ተብራርቷል?
5.4 የፕሮጀክት ባለቤቱ የማስተሰርያ/ማቅለያ ዘዴዎችን ተግባራዊ
ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ግልጽ ነው ወይስ የተቀመጡ
የማቅለያ ዘዴዎች የማይፈፀሙ ለይስሙላ የተቀመጡ
ናቸው?
5.5 የፕሮጀክት ባለቤቱ ያቀረባቸዉን የማስተሰርያ/ማቅለያ
ዘዴዎች ለምን እንደመረጣቸዉ ምክንያቱ ተገልጧል?
5.6 የማስተሰርያ/ማቅለያ ዘዴዎችን ለመተግበር የሚመለከታቸዉ
አካላት ወጪዉን ጨምሮ በግልጽ ተቀምጧል?
5.7 አሉታዊ ተጽእኖዎችን የማስተሰረያ/የማቅለል ስራ ተግባራዊ
ማድረግ የማይቻል ከሆነ ውይም የፕሮጀክት ባለቤቱ ምንም
አይነት የማስተሰረያ/ማቅለያ ዘዴዎችን ተግባራዊ ላለማድረግ
ከመረጠ ምክንያቱ በግልጽ ተብራርቷል?
5.8 የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ አጥኝ ቡድኑ እና የፕሮጀክቱ
ባለቤት በአማራጭ ስልት ማለትም የቦታ ለዉጥ፣ የዲዛይንና
አቀማመጥ ለዉጥ፣ የአሰራር ዘዴዎችንና ሂደቶች ለዉጥ፣
የትግበራ እቅድና የአመራር ትግራ ለዉጥ እንዲሁም
ተጽእኖዎችን የማስተሰረያ ምፍትሄና በማካካስ እርምጃዎችን
በመዉሰድ አማራጮችን በሰፊዉ መዳሰሳቸዉ ወይም ግምት
ወስጥ ማስገባታቸው ግልጽ ነዉ?
5.9 ቅሪት ተጽእኖዎችን ለመከታተልና ለመቆጣጠር ቅድመ
ዝግጅቶች ተደርገዋል?
5.10 የተጽኖ ማስተሰርያ ዘዴዉ የሚያደርሰዉ ሌላ አሉታዊ
ተጽእኖ ተጠቅሷል?
ሌሎች የተጽዕኖ ማስተሰረያ /ማቅለያ ጥያቄች
ክፍል 6 አጭር ማጠቃለያ ጽሁፍ
6.1 የአካባቢ ዘገባ ሪፖርቱ አጭር የማጠቃለያ ጽሁፍ አካቷል?
6.2 አጭር የማጠቃለያ ጽሁፉ ስለፕሮጀክቱ አጭርና ግልጽ የሆነ
መግለጫ፣ የፕሮጀክቱን አካባቢ፣ ፕሮጀክቱ በአካባቢ ላይ
ያለዉን ተጽእኖ እና ለተጽእኖዎች የማቅለያ ዘዴዎችን
6.3 ያካተተ ነዉ?አጭር ጽሁፉ ጉልህ አጠራጣሪ የሆኑ ጉዳዮች
የማጠቃለያ
ስለ ፕሮጀክቱና ስለሚያስከትላቸው አካባቢዉ ተጽእኖዎች
ያብራራል?
6.4 የማጠቃለያ አጭር ጽሁፉ የፕሮጀክቱን የመጽደቅ ሂደትና
የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ጥናት ያለዉን ሚናያብራራል?
6.5 የማጠቃለያ አጭር ጽሁፉ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ጥናት
ስልቱን በተመለከተ አጭር ማብራራያ አለዉ?
6.6 የማጠቃለያ አጭር ጽሁፉ የተጻፈዉ በርካታ ጊዜ
ወይምበድግግሞሽ ሙያዊ ቃላትን፣ ዝርዝር መረጃዎችን እና
ሳይንሳዊ ትንታኔዎችንመጠቀምን ባስወገደ መልኩ ነዉ?
6.7 የማጠቃለያ ጽሁፉ በፕሮጀክቱ ለሚጎዱና ፍላጎቱ ላላቸዉ
አባላት በቀላሉ ሊረዱት በሚችሉት ሁኔታ ተፃፈ ወይም
ተደራሽ ነዉ ወይ?

40
ተ. ቁ የመገምገሚያ ነጥቦች ሌላ ተጨማሪ የሚያስፈልግ መረጃ

የመረጃው
አስፈላነት
የመረጃ

በቂነት
አለ

በማጠቃለያ አጭር ጽሁፍ ሌሎች ጥያቄዎች

7 ክፍል 7 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናቱ


አቀራርብ/አጻጻፍ ጥራት
7.1 በጥናቱ ዉስጥ የተጠቀሱት አካባቢያዊ መረጃዎች በአንድ
ወይም ከዚያ በላይ በሚሆኑ የመረጃ ምንጮች በግልጽ
የሚገኙ ናቸዉ?
7.2 የሰነዱ ይዘት ማዉጫ በሰነዱ መጀመሪያ ገጾች ላይ ነዉ?
7.3 የጥናቱ ሂደት/ቅደም ተከተል በግልጽ ተጽፏል?
7.4 የጥናቱ አቀራረብ አጭርና ግልጽ ሆኖ አላስፈላጊ የሆኑ
መረጃዎችን ያስወገደ ነዉ?
7.5 የጥናቱ ጽሁፍ ጠቃሚ የሆኑ ሰንጠረዥ፣ ምስል፣ ካርታ፣
ፎቶዎች እና ሌሎች ስዕላዊ መግለጫዎችን ተጠቅሟል?
7.6 ሁሉም ትንታኔዎችና ማደማደሚያዎች በመረጃና
በማስረጃበበቂ ሁኔታ የተደገፉ ናቸዉ?
7.7 ሪፖርቱ በዋናዉን የጥናት ጽሁፍ ውስጥ ያሉ ዋና ይዘቶችን
አንብቦ መረዳት ሳያስፈልግ በርካታ መረጃዎችን ለማግኘት
እንዲቻል እዝሎችን አካቷል ወይ?
7.8 አንባቢዉ መረጃዎችን በሰነዱ ዉስጥ በቀላሉ ሊያገኝ
እንዲችል ሰነዱ በአግባቡ የተደራጀና በግልጽ የተዋቀረ ነዉ?
7.9 ለሁሉም የመረጃ ምንጮች ማጣቀሻዎች በአግባቡ
ተገልጸዋል ?
7.10 በአጠቃላይ በሰነዱ ዉስጥ ሙያዊ ቃላቶች አጠቃቀም
ወጥነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ ዉለዋል?
7.11 ሰነዱ ሲነበብ በውስጡ የተገለጹት ርዕሰ
ጉዳዮችንየማይጣረሱና እርስ በርስ የመደጋገፍና እንደ አንድ
ሙሉ ሰነድ ማየት በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ነው?
7.12 የሰነዱ ጽሁፍ አገላለጹ ሚዛናዊ እንዲሁም አድሎ የሌለበት፣
ያልተዛባናዓላማውን ያልሳተ ነዉ?
የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናቱ አቀራርብ/አጻጻፍ ጥራት ላይ ሌሎች ጥያቄዎች

41
15.3.2 የተፅዕኖ ግምገማ ሪፖርቱን ለመገምገም የሚጠቅሙ ማብራሪያዎች
1) በሰነዱ ዉስጥ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች መሟላታቸውን ለማረጋገጥ ሪፖርቱን በፍጥነትና በግርድፉ ማንበብ ይገባል፣
2) እያንዳንዱ የመገምገሚያ ጥያቄ ለፕሮጀክቱ አግባብነት ያለው መሆኑን ማረጋገጥና አግባብነት ካለዉ በመገምገሚያ
ሰንጠረዡ ረድፍ ሁለት ላይ አዎ በማለት መጻፍ ይገባል፤
3) ፕሮጀክቱን በተመለከተ በጣም አስፈላጊ የሆኑና በመጠይቁ ያልተካተቱ ጉዳዮች ካሉ በመገምገሚያ ቅጹ መጨረሻ ረድፍ ላይ
ማካተት ይቻላል፣
4) የመገምገሚያ ጥያቄዉ ከፕሮጀክቱ ጋር አግባብነት መኖሩ ከተረጋገጠ ሰነዱን በጥልቀት በመገምገም ከጥያቄዉ ጋር
ተያያዥነት ያለዉ ጉዳይ በአግባቡና በበቂ ሁኔታ የተገለፀ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ሰነዱ ይህን ጥያቄ አሟልቶ ከተገኘ
“አዎ” ወይም አሟልቶ ካልተገኘ ደግሞ “አይደለም” በማለት በመገምገሚያ ሰንጠረዡ 3 ኛ ረድፍ ላይ መሞላት አለበት፣
5) የመረጃውን በቂነት በማረጋገጡ ሂደት ዉስጥ ያልተካተቱ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችና ለውሳኔ አሰጣጥ አስፈላጊ የሆኑ
ነጥቦች ካሉ እንዲካተቱ መደረግ አለበት፣
6) የቀረበው የጥናት ዘገባ በቂ ከሆነ ገምጋሚ ባለሙያው የፕሮጀክት ባለቤቱን ተጨማሪ መረጃ እንዲያቀርብ አይጠይቅም፣
7) የመገምገሚያ ቅፁ በሚዘጋጅበት ጊዜ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነጥቦች
1) ዉሳኔ ሰጭዉ አካል ፕሮጅክቱን ለማጽደቅ የሚጠቀምባቸው የህግ ማዕቀፎችና ውሳኔ ለመስጠት የሚፈልጋቸው
ነጥቦች መካተታቸውን፣
2) የፕሮጀክቱ ይሁንታ ፈቃድ አሰጣጥ ሂደት የተጽዕኖ ዘገባ ግምገማ መርህን መሰረት ያደረገ ወይም ዝርዝር
የፕሮጀክቱን ዲዛይን መሰረት ያደረገ መሆኑን፣
3) የፕሮጀክቱን ትልቅነትና ዉስብስብነት እንዲሁም የፕሮጀክቱ አካባቢ የተጋላጭነት ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ
መሆኑን፣
4) በአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ዘገባ ውስጥ የተጠቀሱት አካባቢያዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸዉ ከሆነ
በአግባቡ መተንተናቸውና ትኩረት የተሰጣቸው መሆኑን
5) በፕሮጀክቱ ምክንያት ጉዳት የሚደርስባቸዉና የሚያገባቸዉ የማህበረሰብ ክፍሎች አስተያየትና የተነሱ አወዛጋቢ
ጉዳዮች መካተታቸውን፣
6) የመጠይቁ ምላሽ “አይደለም” ከሆነ ወደፊት መታየት የሚገባቸዉን ጉዳዮች ማሰብና በቅጹ ረድፍ አራት ላይ
ማስታዎሻ መጻፉን ማረጋገጥ፤
8) ፕሮጀክቱን የማፅደቅ የውሳኔ አስተያየት የሚሰጠው በመጨረሻ ደረጃ ላይ የተሰጡት ነጥቦች ተደምረው በሚገኘዉ ዉጤት
መሰረት ይሆናል፡፡

15.4 የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ ያገኘ ፕሮጀክት የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ማድረጊያ
ቅጽ
የሪፓርት ቁጥር -------------- ሪፓርቱ የተጠናቀረበት ቀን --------------
ክፍል-1፣ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ መግለጫ
1. የፕሮጀክቱ ሥም፣ 6. የአካባቢ ይሁንታ የተሰጠበት ቀን፣
2. የፕሮጀክቱ ባለቤት ሥም፣ 7. 1የአካባቢ ይሁንታ የተሰጠበት ቦታ፤
3. ፕሮጀክቱ ሥራ የጀመረበት ቀን፣ 8. የአካባቢ ይሁንታ ምዝገባ ቁጥር፣

1የአካባቢ ይሁንታ ሰርተፈኬት የተሰጠበት ቦታ የሚለው በክልል ደረጃ ከሆነ ክልል፣ በዞን ወይም በወረዳ ደረጃ የተሰጠ ከሆነ
የዞኑ ወይም የወረዳው ስም ይጻፍ

42
4. የፕሮጀክቱ ቦታ ስፋት፣ 9. የፕሮጀክቱ የአካባቢ ተጽእኖ ሰነድ ቁጥር፣
5.ፕሮጀክቱ የሚገኝበት 10. የፕሮጀክቱ ሰራተኞች ብዛት፡-
ዞን፡….. ወረዳ፡…. ቀበሌ/ልዩቦታ፡….. ቋሚ፡…….ጊዜያዊ (አማካይ በወር)፡….. ድምር…..
ክፍል-2፣ በአካባቢ አያያዝ ዕቅድ መሠረት የታቀዱ የማቃለያ እርምጃዎች አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ
ተ.ቁ የፕሮጀክቱ የታቀዱ የተጽዕኖ ማቃላያ የዉጤት ክትትል የተገኘ የሚጠበቅ/መ ለልዩነት
ምዕራፍ እርምጃዎች/mitigation አመላካቾች/parameter የተደረገበት ውጤት ሆን የነበረት ምክንያት
/project measures/ s to be ቀን /Rresul ዉጤት
stage/ monitored/ t/

ክፍል-3፣ አጠቃላይ አስተያየት


1. በተዘጋጀው የአካባቢ ተጽእኖ ጥናት ዘገባ ውስጥ ያልተለዩ/አዲስ ተጽእኖዎች ተከስተው ከሆነ፡-
1. የተጽእኖው አይነትና የተከሰተበት
ምክንያት--------------------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------
2. ለተከሰተው ተጽእኖ የማቃለያ እርምጃ ተወስዶ ከሆነ ይገለጽ
-----------------------------------------------------------------------------------------------
---------------------------------
3. ለተከሰተው ተጽእኖ የማቃለያ እርምጃ ካልተወሰደ ምክንያቱ ይገለጽ
-----------------------------------------------------------------------------------------------
-------------------------
4. ለተከሰተው ተጽእኖ የታቀደዉ የማቃለያ እርምጃ
አይነት----------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------
5. የተጽእኖ ማቃለያ እርምጃው የሚከናወንበት ጊዜ፣ ማን እንደሚያከናውነውና መከናወኑን
እንዴት ክትትል እንደሚደረግ ይገለጽ
-----------------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------
2. ከላይ በክፍል 2 የተገለጸውን መሰረት በማድረግ በቀጣይ መሻሻል ባለባቸው ወይም መካሄድ ባለባቸው
ጉዳዮች ላይ ምክረ-ሀሳብ (Recommendation) ቀጥሎ ይቅረብ።
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------
--------------------------------
3. ሪፖርቱን በሚመለከተዉ የፕሮጀክት ሃላፊ/ባለቤት በማህተምና በፊርማ ተረጋግጦ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ሪፖርቱን ያጠናቀረዉ ስም-----------------ኃላፊነት---------------ፊርማ------------ ቀን------------
ያረጋገጠዉ ኃላፊ ስም ------------------------ፊርማ--------------------- ቀን------------

ማሳሰቢያ፡- የቀረበዉን ሪፖርት ትክክለኛነት በባለስልጣኑ የአካባቢ ተቆጣጣሪ ባለሙዎች የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡

15.5 የአካባቢ አማካሪ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ምልመላ፣ መመዘኛና ማወዳደሪያ መስፈርት


የአካባቢ አማካሪ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ምልመላና መረጣ መገምገሚያና የነጥብ አሰጣጥ ሂደቱ የሚከተሉትን
መስፈርቶች የያዘ ይሆናል፡-
የመመዘኛ መስፈርቶች
አንድ አመልካች አጠቃላይ ክብደቱ ከ 100 በሆኑ 5 ዋና ዋና መመዘኛ መስፈርቶች ይገመገማል፡-
1. የትምህርት ዝግጅት …………………………………………………… 25
2. የስራ ልምድ …………………………………………………………… 25
3. የማማከር፣ የስልጠናና የአካባቢ ግምገማ/ምርመራ የስራ ልምድ………25
4. የጥናትና ምርምር የስራ ልምድ………………………………………………20

43
5. የህትመቶች ……………………………………………………………… 5

1. የትምህርት ዝግጅት …………………………………………………………………..25


አመልካቹ በዕዝል 15.6 ከተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች ቢያንስ በአንዱ የመጀመሪያ ዲግሪ ሊኖረው ይገባል፡፡
የትምህርት ዝግጅቱ በሚከተለው ሁኔታ ነጥብ ይሰጠዋል፡-
የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት …………………………………….. 19 ነጥብ
ሁለተኛ ዲግሪ ያለው/ያላት …………………………………………… 21 ነጥብ
ሶስተኛ ዲግሪ ያለው/ያላት ………………………………………………. 25 ነጥብ
2. የስራ ልምድ ………………………………………………………………………….. 25
አመልካቹ/ቿ በአካባቢ አማካሪነት ሙያ ለመወዳደር ወይም ለመሳተፍ በመረጠው/ችው የአማካረነት የሙያ
ዘርፍ ለድግሪ ቢያንስ 5 ዓመት፣ ለማስተር ቢያንስ 3 ዓመት እና ለዶክትሬት ድግሪ ቢያንስ 2 ዓመት አግባብነት
ያለው የሥራ ልምድ ሊኖረው/ራት ይገባል፡፡ ለእያንዳንዱ ዓመት ቀጥተኛ የስራ ልምድ 2.5 ነጥብ ይሰጣል፡፡
በመሆኑም 10 ዓመትና ከዚያ በላይ ቀጥተኛ የስራ ልምድ ካለው/ካላት 25 ነጥብ ይሰጣል፡፡ ቀጥተኛ የስራ
ልምድ ላልሆኑት ተጨማሪ ዓመታት የስራ ልምድ ደግሞ ለእያንዳንዱ ዓመት 0.5 ነጥብ ይሰጣል፡፡ ከ 10 ዓመት
በላይ ላለ የሥራ ልምድ ምንም አይነት ነጥብ አይሰጠውም፡፡
“ቀጥተኛ የስራ ልምድ የሚያዘው የአካባቢ አማካሪነት ፈቃድ ከሚያወጣበት የአማካሪነት የሙያ ዘርፍ ጋር ቀጥተኛ
የተግባር ግንኙነት ያለው ሆኖ በድፕሎማና ከዚያ በላይ ባለ የትህምርት ዝግጅት የተገኘ የሰራ ልምድ ብቻ
ይሆናል፡፡ በከፍተኛ አመራር፣ በመካከለኛ አመራርና በባለሙያነት ደረጃ ዘርፉን ከሚመለከቱ ድርጅቶችና
ተቋማት የተገኘ የስራ ልምድና በድፕሎማና በድግሪ ደረጃ በመምህርነት የተገኘ የስራ ልምድ ቀጥተኛ የሥራ
ልምድ ተብሎ ይያዛል፡፡
3. የማማከር፣ የስልጠናና የአካባቢ ግምገማ/ምርመራ የስራ ልምድ………………….25
1. በማማከር አገልግሎት የተሳተፈባቸው ልምዶች-----------------------------7.5
2. ስልጠና በመሳተፍ/ በመስጠት የተሳተፈባቸው ልምዶች ………………7.5
3. በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማና ምርመራ የተሳተፈባቸው ………………………10
3.1 በማማከር አገልግሎት የተሳተፈባቸው ልምዶች
1. የሙያ ፈቃድ ለማውጣት በጠየቀበት የሙያ ዘርፍ በአካባቢ የማማከር አግልግሎት አንድ የፀደቀ የአካባቢ
ተፅዕኖ ግምገማ ሰነድ ካለው/ካላት 1.5 ነጥብ ይሰጣል፤
2. የሙያ ፈቃድ ለማውጣት በጠየቀበት የሙያ ዘርፍ በአካባቢ የማማከር አግልግሎት ሁለት የፀደቀ
የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሰነድ ካለው/ካላት 3 ነጥብ ይሰጣል፤
3. የሙያ ፈቃድ ለማውጣት በጠየቀበት የሙያ ዘርፍ በአካባቢ የማማከር አግልግሎት ሶስት የፀደቀ የአካባቢ
ተፅዕኖ ግምገማ ሰነድ ካለው/ካላት 4.5 ነጥብ ይሰጣል፤
4. ተጨማሪ 2 የፀደቁ የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ሰነዶች ያሉት/ያላት ከሆነ ለእያዳንዱ ሰነድ 1.5 ነጥብ
ይሰጣል፡፡ ከ 5 በላይ ላሉ የፀደቁ የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ሰነዶች ነጥብ አይሰጥም፡፡
5. በመሆኑም አመልካቹ/ቿ ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉም ማስረጃዎች ካሉት/ላት አጠቃላይ የሚሰጡት ነጥቦች
ድምር ውጤት ከ 7.5 መብለጥ የለበትም፡፡
3.2. ስልጠና በመሳተፍ/በመስጠት የተሳተፈባቸው ልምዶች

44
1. የአማካሪነት የብቃት ማረጋገጫ እንዲሰጠው ከጠየቀበት ዘርፍ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ የአንድ ቀን
ስልጠና ከአሰለጠነ/ች ወይንም ከሰለጠነ/ች 2.5 ነጥብ ይሠጣል
2. የአማካሪነት የብቃት ማረጋገጫ እንዲሰጠው ከጠየቀበት/ችበት ዘርፍ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ በድግግሞሽ
የሁለት ቀናት ስልጠና ከአሰለጠነ/ች ወይንም ከተሳተፈ/ች 5 ነጥብ ይሠጣል
3. የአማካሪነት የብቃት ማረጋገጫ እንዲሰጠው ከጠየቀበት/ችበት ዘርፍ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ በድግግሞሽ
የሶስት ቀናት ስልጠና ከሰጠ/ች ወይንም ከተሳተፈ/ች 7.5 ነጥብ ይሠጣል፡፡ ሆኖ ግን ከ 3 ጊዜ በላይ
በድግግሞሽ የተሰጡ ማስረጃዎች ቢኖሩም ተጨማሪ ዋጋ አይሰጣቸውም፤ በመሆኑም አጠቃላይ
የሚሰጠው ነጥብ ከ 7.5 መብለጥ የለበትም፡፡
4. የአማካሪነት ፈቃድ ከተጠየቀበት ዘርፍ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያለውን ኮርስ ለማስተማሩ መረጃ
የሚያቀርብ የከፍተኛ ተቋማት መምህር ሙሉ ነጥብ ይሰጠዋል፡፡
3.3. የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ/ ምርመራ
1. የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ሰነድ ግምገማ ወይም የአካባቢ ምርመራ ልምድ ለእያዳንዳቸው ለአንድ ሰነድ
/ለአንድ ፕሮጀክት 2 ነጥብ ይሰጣል፡፡
2. አምስትና ከዚያ በላይ የሆኑ የአካባቢ ጥናት ዘገባዎችን ግምገማ ያካሄደ/ የፕሮጀክቶችን ምርመራ
ያካሄደ 10 ነጥብ ብቻ ይሰጣል፡፡
3. ከአምስት በላይ የሚሆኑ የፕሮጀክትን ዘገባዎች መገምገም/ ፕሮጀክቶችን መመርመር ተጨማሪ
ነጥብ አያስገኝም፡፡ በመሆኑም ጠቅላላ የሚገኝ ከፍተኛ ነጥብ ከ 10 አይበልጥም፡፡
4. የጥናትና ምርምር የስራ ልምድ……………………………………………………..20 ነጥብ
ባለሙያው ካመለከተበት የአማካሪነት የሙያ ፈቃድ ጋር የሚገናኝ አንድ የጥናት/የምርምር ሰነድ
ያዘጋጀ/ች ለመሆኑ/ኗ ህጋዊ ማስረጃ የሚያቀርብ/የምታቀርብ ከሆነ 2.5 የሚሰጥ ሲሆን 8 እና ከዚያ
በላይ ለሆኑ የጥናት/ምርምር ሰነዶች ማስረጃ ከቀረበ 20 ነጥብ ብቻ ይሰጣል፡፡ ይህም ማለት ጠቅላላ
የሚገኝ ከፍተኛ ነጥብ 20 ይሆናል፡፡
5. ህትመቶች …………………………………………………………………………. 5 ነጥብ
የአማካሪነት ፈቃድ በተጠየቀበት የሙያ ዘርፍ የታተሙ የጥናት ፅሁፎች ለግምግማ ይያዛሉ፡፡
እያንዳንዱ በጋዜጣ ወይም በመጋዚንስ/መፅሄት ላይ የወጡ እያንዳንዳቸው ፅሁፎች አንዳንድ ነጥብ ይሰጣቸዋል፡፡
በአካባቢ ጥበቃ ዙሪ ስልጠና ለመስጠት የተዘጋጁ የስልጠና ማንዋሎች ወይም የታተሙ የምርምር ፅሁፎች
እያንዳንዳቸው አንዳንድ ነጥብ ይሰጣቸዋል፡፡ ለማንኛውም ሲንፖዚየም፣ ኮንፈረንስና ጥናቶች የቀረቡ የጥናት
ፅሁፍ ለእያንዳንዱ ሁለት ሁለት ነጥብ ይሰጣል፡፡ ለማኝኛውም ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር አግባብነት ላለው የታተመ
መፅሃፍ 5 ነጥብ ይሰጠዋል፡፡ ይሁንና የሚሰጠው አጠቃላይ ነጥብ ድምር ከ 5 መብለጥ የለበትም፡፡ ከአካባቢ ጥበቃ
ጉዳይ ውጭ ህትመቶች ላሉት ለእያንዳንዱ ህትመት 0.5 ነጥብ ይሰጣል፡፡ ለዚህም የሚሰጠው አጠቃላይ ነጥብ
ድምር ከ 5 መብለጥ የለበትም፡፡

45
15.6 በአካባቢ ዘርፍ የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናትና ኦዲት አገልግሎት የሚሰጡ አማካሪ ባለሙያዎች
መስፈርት
ተ. የብቃት ማረጋገጫ የሚሰጠው የትምህርት ደረጃ አግባብነት ያለው
ቁ የሚሰጥባቸው የብቃት የሥራ ልምድ
የአካባቢ ዘርፍ ጉዳዮች ደረጃ (በአመት)
በአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ጀማሪ በኢኮኖሚክስ፣ ኢንቫሮንመንታል ኢኮኖሚክስ፣ አግሪካልቸርራል ለመጀመሪያ ድግሪ፡
1 ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ አማካሪ ኢኮኖሚክስ ወይም ተመሳሳይ መስክ ቢያንስ የመጀመሪያ 5 ና በላይ
ጉዳዮች ተንታኝ ድግሪ ያለው ለሁለተኛ ድግሪ፡ 3 ና
በላይ
ባለሙያ ከፍተኛ በኢኮኖሚክስ፣ ኢንቫሮንመንታል ኢኮኖሚክስ፣ አግሪካልቸርራል ለዶክተሬት ድግሪ፡
አማካሪ ኢኮኖሚክስ ወይም ተመሳሳይ መስክ ቢያንስ የመጀመሪያ 2 ና በላይ
ድግሪ ያለው
2 በአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ጀማሪ በሶሾሎጂ፣ በሶሻል ስተዲስ፣ ሶሻል ዎርክስ፣ ሶሻል ለመጀመሪያ ድግሪ፡
ዘርፍ የማህበራዊ አማካሪ አንትሮፖሊጂ ወይም ተመሳሳይ መስክ ቢያንስ የመጀመሪያ 5 ና በላይ
ጉዳዮች ተንታኝ ድግሪ ያለው ለሁለተኛ ድግሪ፡ 3 ና
ከፍተኛ በሶሾሎጂ፣ በሶሻል ስተዲስ፣ ሶሻል ዎርክስ፣ ሶሻል በላይ
ባለሙያ
ለዶክተሬት ድግሪ፡
አማካሪ አንትሮፖሊጂ ወይም ተመሳሳይ መስክ ቢያንስ የመጀመሪያ
2 ና በላይ
ድግሪ ያለው
3 በአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ጀማሪ በአካባቢ ጤና፣ በአካባቢ ሳይንስ፣ የሥራ አካባቢ ጤንነትና ለመጀመሪያ ድግሪ፡
ዘርፍ የአካባቢ ጤና አማካሪ ደህንነት ወይም ተመሳሳይ መስክ ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪ 5 ና በላይ
ባለሙያ ያለው ለሁለተኛ ድግሪ፡ 3 ና
ከፍተኛ በአካባቢ ጤና፣ በአካባቢ ሳይንስ፣ የሥራ አካባቢ ጤንነትና በላይ
ለዶክተሬት ድግሪ፡
አማካሪ ደህንነት ወይም ተመሳሳይ መስክ ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪ
2 ና በላይ
ያለው
4 በአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ጀማሪ በብዝሃ ሕይወት፣ በደን/ዱር እንስሳት/ እንስሳት እርባታ፣ ለመጀመሪያ ድግሪ፡
የብዝሐ ሕይወት እና አማካሪ በሥነ-ሕይወት በእጽዋት /በአግሮኖሚ ወይም ተመሳሳይ 5 ና በላይ
የስርዓተ-ምህዳር መስክ ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪ ያለው ለሁለተኛ ድግሪ፡ 3 ና
ከፍተኛ በብዝሃ ሕይወት፣ ስነ-ምህዳር በደን/ዱር እንስሳት/ እንስሳት በላይ
ተንታኝ ባለሙያ
ለዶክተሬት ድግሪ፡
አማካሪ እርባታ፣ በሥነሕይወት በእጽዋት ሳይንስ /በአግሮኖሚ ወይም
2 ና በላይ
ተመሳሳይ መስክ ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪ ያለው
5 በአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ጀማሪ በውሃ ሀብት አጠቃቀም፣ ተፈጥሮ ሃብት አያያዝ፣ የውሃ ለመጀመሪያ ድግሪ፡
የውሃ ሀብት አማካሪ ምህንድስና፣ የከርሰ ምድር ጥናት ወይም ተመሳሳይ መስክ 5 ና በላይ
አጠቃቀም አጥኚ ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪ ያለው ለሁለተኛ ድግሪ፡ 3 ና
ከፍተኛ በውሃ ሀብት አጠቃቀም፣ ተፈጥሮ ሃብት አያያዝ፣ የውሃ በላይ
ባለሙያ
ለዶክተሬት ድግሪ፡
አማካሪ ምህንድስና፣ የከርሰ ምድር ጥናት ወይም ተመሳሳይ መስክ
2 ና በላይ
ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪ ያለው
6 በአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ጀማሪ በአካባቢ መሀንዲስ፣ ኬሚካል መሃንዲስ፣ በአካባቢ አያያዝ፣ ለመጀመሪያ ድግሪ፡
ዘርፍ የአካባቢ ብክለት አማካሪ በአካባቢ ሳይንስ፣ ኬሚስትሪ ወይም ተመሳሳይ መስክ 5 ና በላይ
ተንታኝ ባለሙያ ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪ ያለው ለሁለተኛ ድግሪ፡ 3 ና
ከፍተኛ በአካባቢ መሀንዲስ፣ ኬሚካል መሃንዲስ፣ በአካባቢ አያያዝ፣ በላይ
ለዶክተሬት ድግሪ፡
አማካሪ በአካባቢ ሳይንስ፣ ኬሚስትሪ ወይም ተመሳሳይ መስክ
2 ና በላይ
ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪ ያለው
7 በአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ጀማሪ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በኬሚስትሪ፣ በአካባቢ ሳይንስ ለመጀመሪያ ድግሪ፡
ዘርፍ የሙቀት አማቂ አማካሪ በአካባቢ ጤና ወይም ተመሳሳይ መስክ ቢያንስ የመጀመሪያ 5 ና በላይ
ጋዝ ልቀት ተንታኝ ድግሪ ያለው ለሁለተኛ ድግሪ፡ 3 ና
ከፍተኛ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በኬሚስትሪ፣ በአካባቢ ሳይንስ በላይ
ባለሙያ
ለዶክተሬት ድግሪ፡
አማካሪ በአካባቢ ጤና ወይም ተመሳሳይ መስክ ቢያንስ የመጀመሪያ
2 ና በላይ
ድግሪ ያለው

46
15.7 በአካባቢ ዘርፍ የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናትና ኦዲት አገልግሎት የሚሰጡ አማካሪ ድርጅቶች
መስፈርት
ለአማካሪው አማካሪው ድርጅት የሚያስፈልጉት የሚሰማራባቸው ሌሎች መስፈርቶች
ድርጅት ባለሙያዎች የአካባቢና
ተ.ቁ
የሚሰጠው የሙያ ማህበረሰብ ተፅዕኖ
ዝርዝር ብዛት
ደረጃ ደረጃ ጥናት መስኮች
1 I የኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ከፍተኛ  በፕሮጀክቶች  ስራ አስኪያጁን ጨምሮ
1
ተንታኝ ባለሙያ አማካሪ ምድብ በክልል ቢያንስ ሁለት ቋሚ
የማህበራዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ምድብ ሰራተኞች
1
ተንታኝ ባለሙያ አማካሪ የተዘረዘሩትን  መነሻ ካፒታል ቢያንስ
የአካባቢ ጤና ተንታኝ ከፍተኛ ጨምሮ ሌሎች 200 ሺ ብር
1
ባለሙያ አማካሪ ሙሉ የአካባቢ  የመስሪያ ቦታ/ቢሮ
የብዝሐ ሕይወት እና ተፅዕኖ ግምገማ ቢያንሰ 30 ካሬ ሜትር
ከፍተኛ የሚያስፈልጋቸ
የስርዓተ-ምህዳር 1  የቢሮ የጽህፈት
አማካሪ ውን
ተንታኝ መሳሪያዎች/ኮምፒዩተ
የውሃ ሀብት አጠቃቀም ጀማሪ ፕሮጅክቶች
1 ሮች
ተንታኝ ባለሙያ አማካሪ ዝርዝር የጥናት
የአካባቢ ብክለት ከፍተኛ 1 ዘገባ ያዘጋጃል፤
ተንታኝ ባለሙያ አማካሪ  በምድብ
ያልተካተቱ
ትልልቅ
ፕሮጅክቶችን
ዝርዝር የጥናት
ዘገባ ያዘጋጃል፤
2 II የኢኮኖሚያ ጉዳዮች ጀማሪ  በዞን ምድብና  ስራ አስኪያጁን ጨምሮ
1
ተንታኝ ባለሙያ አማካሪ ከዚያ በታች ቢያንስ ሁለት ቋሚ
የማህበራዊ ጉዳዮች ከፍተኛ የተመደቡ ሙሉ ሰራተኞች
1
ተንታኝ ባለሙያ አማካሪ የአካባቢ ተፅዕኖ  መነሻ ካፒታል ቢያንስ
የአካባቢ ጤና ተንታኝ ጀማሪ ግምገማ 150 ሺ ብር
1
ባለሙያ አማካሪ የሚያስፈልጋቸ  የመስሪያ ቦታ/ቢሮ
የብዝሐ ሕይወት እና ጀማሪ ውን ቢያንሰ 20 ካሬ ሜትር
የስርዓተ-ምህዳር አማካሪ 1 ፕሮጅክቶች  የቢሮ የጽህፈት
ተንታኝ ዝርዝር የጥናት መሳሪያዎች/ኮምፒዩተ
የውሃ ሀብት አጠቃቀም ጀማሪ ዘገባ ያዘጋጃል፤
1 ሮች
ባለሙያ አማካሪ  በምድብ
የአካባቢ ብክለት ከፍተኛ 1 ያልተካተቱ
ተንታኝ ባለሙያ አማካሪ መካከለኛና
በታች ያሉ
ፕሮጅክቶችን
ዝርዝር የጥናት
ዘገባ ያዘጋጃል፤
በደረጃ I ፈቃድ ያገኘ አማካሪ ድርጅት ከፍተኛ ድርጅት ሲሆን የማንኛውንም ፕሮጀክት የአካባቢ
ተጽዕኖ ጥናት ዘገባ ማዘጋጀት ይችላል፡፡ በደረጃ II የአማካሪነት ፈቃድ ያገኘ ድርጅት በደረጃ II የተዘረዘሩ
ፕሮጀክቶችን ብቻ የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ዘገባ ማዘጋጀት ይኖርበታል፡፡

47
15.8 ማመልከቻ ቅጾች

15.8.1 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ባለሙያ የሚሞላ
የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ አዲስ ለሚጠየቁ

ሙሉ ስም …………………………………………………………………
አድራሻ
ክልል…………………………ዞን…………………………………
ወረዳ…………………………ከተማ……………………………
ክፍለከተማ……………...…..ቀበሌ………………………..የቤ.ቁ……………………….
ስልክ የቢሮ………………………ሞባይል………………………ፋክስ……………………
ኢ-ሜይል ………………………………………………………
አሁን የሚሰሩበት መስሪያ ቤት……………………………………………
ስም፡ ……………………………………………
አድራሻ፡……………………………………………
1. የትምህርት ደረጃ
ተ.ቁ የተማሩበት ኮሌጅ/ ዩኒቨርስቲ የትምህርት መስክ የዲግሪ ደረጃ
ስም (የመጀመሪያ፣ሁለተኛ፣ ዶክትሬት)

2. የስራ ልምድ
ተ.ቁ የስራ ሃላፊነት የሰሩበት ጊዜ የስሩበት መስሪያቤት ስምና አድራሻ
ከ እስከ

3. የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች (መሰማራት ከሚፈልጉት ዘርፍ ጋር ግንኙነት ያለው)


…………………………………………………………………………………………………
………………………………………………………………………………
4. የብቃት ማረጋገጫ ማግኘት የሚጠይቁበት የአካባቢ ዘርፍ ጉዳዮች
5. የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት
6. የአካባቢ ኦዲት
7. የብቃት ማረጋገጫ ማግኘት የሚጠይቁበት ዝርዝር የአካባቢ ዘርፍ
ጉዳይ………………………………………….

8. የጠየቁት የብቃት ደረጃ


1) አማካሪ
2) ከፍተኛ አማካሪ

48
[

9. የሚከተሉትን መረጃዎች ከቅፁ ጋር አብረው ያያይዙ


1) የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
2) የትምህርት ማስረጃ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር
3) የዘረዘሩትን የሥልጠና ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ጋር
4) የተዘጋጁ ዘገባዎችና ዘገባዎቹን ማዘጋጀትዎን የሚስረዳ መረጃ (ጀማሪ አማካሪ-ደረጃ 1
አመልካቾችን አይመለከትም)
5) የሥራ ልምድ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር
6) አንድ ፎቶ ግራፍ

የአመልካች ስም………………………………ፊርማ ……………….ቀን …………………...

15.8.2 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ባለሙያ የሚሞላ
የአገልግሎትመጠየቂያ ቅጽ ደረጃ ለማሳደግ
ሙሉ ስም …………………………………………………………………
አድራሻ

49
ክልል…………………………ዞን…………………………………
ወረዳ……………………………ከተማ……………………………
ክፍለከተማ……………...………ቀበሌ………………….የቤ.ቁ………………………
ስልክየቢሮ………………………ሞባይል………………………ፋክስ……………………
ኢ-ሜይል………………………………………………………
አሁን የሚሰሩበት መስሪያቤት
ስም፡
አድራሻ፡

1. የትምህርት ደረጃ
ተ.ቁ የተማሩበት ኮሌጅ/ ዩኒቨርስቲ ስም የትምህርት መስክ የዲግሪ ደረጃ

2. የስራ ልምድ
ተ.ቁ የስራ ሃላፊነት የሰሩበት ጊዜ የስሩበት መስሪያቤት ስምና አድራሻ
ከ እስከ

3. የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች(መሰማራት ከሚፈልጉት ዘርፍ ጋር ግንኙነት ያለው)


…………………………………………………………………………………………………
…………………………………………………………………………………………………
…………………………………………………………………………………………
…………………………………………………………………………………………
………………………………………………
4. ቀደም ሲል የብቃት ማረጋገጫ ያገኙበት የአካባቢ ዘርፍ ጉዳዮች
5. የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት
6. የአካባቢ ኦዲት

7. እንዲሠጠዎት የጠየቁት የብቃት ደረጃ


1) አማካሪ
2) ከፍተኛ አማካሪ

8. የሚከተሉትን መረጃዎች ከቅፁ ጋር አብረው ያያይዙ


9. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ከአንድ ፎቶኮፒ ጋር
1) የትምህርት ማስረጃ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር

50
2) የዘረዘሩትን የሥልጠና ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ
3) የተዘጋጁ ዘገባዎችና ማዘጋጀተዎን የሚያስረዳ መረጃ
4) የሥራ ልምድ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ
5) አንድ ፎቶ ግራፍ
የአመልካች ስም………………………….ፊርማ ……………….ቀን …………………...

15.8.3 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ባለሙያ የሚሞላ
የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ እድሳት ለሚጠይቁ
ሙሉ ስም …………………………………………………………………
አድራሻ
ክልል…………………………ዞን…………………………………
ወረዳ…………………………ከተማ……………………………
ክፍለከተማ……………...…..ቀበሌ………………………..የቤ.ቁ……………………….
ስልክየቢሮ………………………ሞባይል………………………ፋክስ……………………
ኢ-ሜይል………………………………………………………

51
አሁን የሚሰሩበት መስሪያቤት
ስም፡
አድራሻ፡
1. የትምህርት ደረጃ
ተ.ቁ የተማሩበት ኮሌጅ/ ዩኒቨርስቲ ስም የትምህርት መስክ የዲግሪ ደረጃ

2. የስራ ልምድ
ተ.ቁ የስራ ሃላፊነት የሰሩበት ጊዜ የስሩበት መስሪያቤት ስምና አድራሻ
ከ እስከ

3. የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች(መሰማራት ከሚፈልጉት ዘርፍ ጋር ግንኙነት ያለው)


…………………………………………………………………………………………………
………………………………………………………………………………………
4. የብቃት ማረጋገጫ ማግኘት የሚጠይቁበት የአካባቢ ዘርፍ ጉዳዮች
1) የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት
2) የአካባቢ ኦዲት

5. የጠየቁት የብቃት ደረጃ


1) አማካሪ
2) ከፍተኛ አማካሪ

6. የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የተሰጠበት ቀን ……………………………………………..


[

7. የሚከተሉትን መረጃዎች ከቅፁ ጋር አብረው ያያይዙ


8. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ከአንድ ፎቶኮፒ ጋር
1) የትምህርት ማስረጃ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር
2) የተዘረዘሩትን የሥልጠና ሰርተፊኬት ከፎቶ ኮፒ ጋር
3) የተዘጋጁ ዘገባዎችና ዘገባዎቹን ማዘጋጀተዎን የሚያስረዳ መረጃ (ጀማሪ አማካሪ-1
አመልካቾችን አይመለከትም)
4) የሥራ ልምድ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር
5) የቀድሞውን የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር
6) አንድ ፎቶ ግራፍ

52
የአመልካች ስም………………………………….ፊርማ ……………….ቀን …………………...

15.8.4 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ባለሙያ የሚሞላ
የአገልግሎትመጠየቂያቅጽ ለጠፈ ምስክር ወረቀት ምትክ ለሚጠይቁ
ስም …………………………………………………………………
አድራሻ
ክልል …………………………ዞን …………………………………
ወረዳ……………………………ከተማ ……………………………
ክፍለ ከተማ……………...………ቀበሌ………………….የቤ.ቁ ……………………ስልክ……….
የቢሮ………………………ሞባይል………………………ፋክስ……………………
ኢ-ማይል ………………………………………………………
1) ቀደም ሲል ያገኙት የአካባቢ ዘርፍ ጉዳዮች

1) የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት


2) የአካባቢ ኦዲት
2) አግንተውት የነበረው ደረጃ
1. አማካሪ (ደረጃ 2)
2. ከፍተኛ አማካሪ
3) የሚከተሉትን መረጃዎች ከቅፁ ጋር አብረው ያያይዙ
1) የአመልካች የቀበሌ መታወቂያ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር

53
2) ሰርተፊኬቱ ስለመጥፋቱ የሚያረጋግጥ የፖሊስ ማስረጃ
3) አንድ ፎቶ ግራፍ
የአመልካች ስም………………………………………….ፊርማ ……………….ቀን ………

15.8.5 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ድርጅት የሚሞላ
የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ የምስክር ወረቀት ለሚጠይቅ
የድርጅቱ ስም …………………………………………………………………
አድራሻ
ክልል…………………………ዞን…………………………………
ወረዳ……………………………ከተማ……………………………
ክፍለከተማ……………...………ቀበሌ………………….የቤ.ቁ………………………
ስልክ………… የቢሮ………………………ሞባይል………………………ፋክስ……………………
ኢ-ሜይል………………………………………………………
1. ለመሰማራት የሚጠይቁት የአካባቢ ዘርፍ ጉዳዮች
1) የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት
2) የአካባቢ ኦዲት
2. የስራ አስኪያጅ
መሉ ስም …………………………………………………………………
አድራሻ
ክልል…………………………ዞን…………………………………
ወረዳ……………………………ከተማ……………………………
ክፍለከተማ……………...………ቀበሌ………………….የቤ.ቁ………………………
ስልክየቢሮ………………………ሞባይል………………………ፋክስ……………………
ኢ-ሜይል………………………………………………………

54
የትምህር ደረጃ………………………………………………………

3. የሰው ሃይል
ተ.ቁ. የባለሙያው ስም የምዝገባ ቁጥርና ቀን ሰርተፊኬት ያገኘበት የቅጥር ሁኔታ
መስክ
በኮንትራት በቋሚነት

4. የመስክ የላቡራቶሪ መሣሪያዎች


ተ.ቁ የመሣሪያዎቹ ዝርዝረ ብዛት

5. የጠየቁት ደረጃ
1) ደረጃ አንድ
2) ደረጃ ሁለት
6. የሚከተሉትን መረጃዎች ከቅፁ ጋር አብረው ያያይዙ
1) የአመልካች የቀበሌ መታወቂያ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር
2) የድርጅቱን ባለቤትነት /ቶችን የሚመለክት ማስረጃ
3) የተጠቀሱትን የባለሙያዎች ሰርተፊኬት ኮፒ
4) ከባለሙያዎች የተደረገው የቅጥር ስምምነት ኮፒ
5) የመስሪያ ቦታ የሚያሳይ መረጃ
6) የመስክ የላቦራቶሪ መሳሪያዎችን የሚያሳይ ዝርዝር
7) የመነሻ ካፕታል የሚያሳይ የባንክ ማስረጃ
8) አንድ ፎቶ ግራፍ
የአመልካች ስም……………………….ፊርማ ……………….ቀን …………………...

55
15.8.6 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ድርጅት የሚሞላ
የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ ደረጃ ለማሰደግ
የድርጅቱ ስም …………………………………………………………………
አድራሻ
ክልል…………………………ዞን…………………………………
ወረዳ……………………………ከተማ……………………………
ክፍለከተማ……………...………ቀበሌ………………….የቤ.ቁ………………………
ስልክየቢሮ………………………ሞባይል………………………ፋክስ……………………
ኢ-ሜይል………………………………………………………
1. ለመሰማራት የሚጠይቁት የአካባቢ ዘርፍ ጉዳዮች

1) የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት


2) የአካባቢ ኦዲት
2. የስራ አስካሄጅ
መሉ ስም …………………………………………………………………
አድራሻ
ክልል…………………………ዞን…………………………………
ወረዳ……………………………ከተማ……………………………
ክፍለከተማ……………...………ቀበሌ………………….የቤ.ቁ………………………
ስልክ………………………… የቢሮ………………………ሞባይል………………………
ፋክስ……………………
ኢ-ሜይል………………………………………………………
የትምህር ደረጃ………………………………………………………

3. የሰው ሃይል

56
ተ.ቁ. የባለሙያው ስም የምዝገባ ቁጥርና ቀን ሰርተፊኬት ያገኘበት መስክ የቅጥር ሁኔታ
በኮንትራት በቋሚነት

4. የመስክ የላቡራቶሪ መሣሪያዎች


ተ.ቁ የመሣሪያዎቹ ዝርዝረ ብዛት

5. የጠየቁት ደረጃ
1) ደረጃ አንድ
2) ደረጃ ሁለት
6. የሚከተሉትን መረጃዎች ከቅፁ ጋር አብረው ያያይዙ
1) የአመልካች የቀበሌ መታወቂያ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር
2) የድርጅቱን ባለቤትነት /ቶችን የሚመለክት ማስረጃ
3) የተጠቀሱትን የባለሙያዎች ሰርተፊኬት ኮፒ
4) ከባለሙያዎች የተደረገው የቅጥር ስምምነት ኮፒ
5) የመስሪያ ቦታ የሚያሳይ መረጃ
6) የመስክ የላቦራቶሪ መሳሪያዎችን የሚያሳይ ዝርዝር
7) የመነሻ ካፕታል የሚያሳይ የባንክ ማስረጃ
8) አንድ ፎቶ ግራፍ
የአመልካች ስም………………………….ፊርማ ……………….ቀን …………………...

57
15.8.7 በአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአማካሪ ድርጅት የሚሞላ የአገልግሎት
መጠየቂያ ቅጽ የብቃት ማረጋገጫን ለማሳደስ
የድርጅቱ ስም ………………………………………………………………… አድራሻ
………………………………………
ክልል…………………………ዞን…………………………………ወረዳ……………………………
ከተማ……………………………
ክፍለከተማ……………...………ቀበሌ………………….የቤ.ቁ………………………

ስልክየቢሮ………………………ሞባይል………………………ፋክስ…………………… ኢ-

ሜይል………………………………………………………
1. የተሰማሩበት የአካባቢ ዘርፍ ጉዳዮች
1) የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት
2) የአካባቢ ኦዲት
2. ብቃት ማረጋገጫ የተሰጠበት ቀን………………………………..
3. የስራ አስካሄጅ
መሉ ስም …………………………………………………………………
አድራሻ
ክልል…………………………ዞን…………………………………
ወረዳ……………………………ከተማ……………………………
ክፍለከተማ……………...………ቀበሌ………………….የቤ.ቁ………………………
ስልክየቢሮ………………………ሞባይል………………………ፋክስ……………………
ኢ-ሜይል………………………………………………………የትምህር
ደረጃ………………………………………………………

4. የሰው ሃይል
ተ.ቁ. የባለሙያው ስም የምዝገባ ቁጥርና ቀን ሰርተፊኬት ያገኘበት መስክ የቅጥር ሁኔታ
በኮንትራት በቋሚነት

5. የመስክ የላቡራቶሪ መሣሪያዎች


ተ.ቁ የመሣሪያዎቹ ዝርዝረ ብዛት

58
6. የጠየቁት ደረጃ
1) ደረጃ አንድ
2) ደረጃ ሁለት
7. የሚከተሉትን መረጃዎች ከቅፁ ጋር አብረው ያያይዙ
1) የአመልካች የቀበሌ መታወቂያ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር
2) የድርጅቱን ባለቤትነት /ቶችን የሚመለክት ማስረጃ
3) የታደሰ የባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ኮፒ
4) ከባለሙያዎች የተደረገው የቅጥር ስምምነት ኮፒ
5) የመስሪያ ቦታ የሚያሳይ መረጃ
6) የመስክ የላቦራቶሪ መሳሪያዎችን የሚያሳይ ዝርዝር
7) የመነሻ ካፕታል የሚያሳይ የባንክ ማስረጃ
8) አንድ ፎቶ ግራፍ

የአመልካች ስም………………………………………….ፊርማ……………….ቀን-------------------

59
15.8.8 በአማካሪ ድርጅት የሚሞላ የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ ለጠፋ የምስክር ወረቀት ምትክ ለሚጠይቁ
የድርጅቱ ስም …………………………………………………………………
አድራሻ
ክልል …………………………ዞን ………………………………ወረዳ……………………………ከተማ
……………………………
ክፍለከተማ……………...………ቀበሌ………………….የቤ.ቁ………………………ስልክ………………….

የቢሮ………………………ሞባይል………………………ፋክስ……………………ኢ-ሜይል
………………………………………………………
1. ቀደም ሲል ያገኙት የአካባቢ ዘርፍ ጉዳዮች
1) የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት
2) የአካባቢ ኦዲት
2. አግንተውት የነበረው ደረጃ
3) ደረጃ አንድ
4) ደረጃ ሁለት
3. የስራ አስካሄጅ
መሉ ስም …………………………………………………………………
አድራሻ
ክልል …………………………ዞን …………………………………ወረዳ……………………………ከተማ
……………………………
ክፍለከተማ……………...………ቀበሌ………………….የቤ.ቁ………………………ስልክ……………

የቢሮ………………………ሞባይል………………………ፋክስ……………………ኢ-ማይል
………………………………………………………
4. የሚከተሉትን መረጃዎች ከቅፁ ጋር አብረው ያያይዙ
1) የአመልካች የቀበሌ መታወቂያ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር
2) የድርጅቱን ባለቤትነት /ቶችን የሚመለክት ማስረጃ
3) ሰርተፊኬት ስለመጥፋቱ የሚያረጋግጥ የፖሊስ ማስረጃ
4) አንድ ፎቶ ግራፍ
የአመልካች ስም………………………………………….ፊርማ ……………….ቀን ………

15.9 የፕሮጀክት ባለቤቱ የውል ስምምነት

እኔ የ
---------------------------------------------------------------------------------- ------------------------------------------------------------------------

ፕሮጀክት ባለቤት በፕሮጀክቴ ግብዓት፣ ተግባራትና ውጤት የተነሳ የሚከሰቱ ተጽዕኖዎችን ለመከላከልና
ለመቀነስ የሚከናወኑ ተግባራት ለመፈጸም የተስማማሁ መሆኔን እየገለጽሁ ተጽዕኖውን መከላከልና

60
መቀነስ ካልተቻልሁ ለተጽዕኖው የካሳ ክፍያ ለመፈጸም በአዋጅ ቁጥር 181/2003 አንቀጽ 9/4
መሰረት ቃል ገብቻለሁ፡፡ የአካባቢ አያያዝ እቅድ ተግባራትን/ግደታዎችን በተቀመጠላቸው መጠን፣
የአፈጻጸም ጥራትና የጊዜ መርሀግብር በማከናወን በየስድስት ወሩ የአፈጻጸም ሪፖርት ለሚመለከተው
የአካባቢ መስሪያቤት ለማቅረብ ቃል ገብቻለሁ፡፡

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ግደታዎች አለመወጣቴ በአካባቢ ምርመራ፣ ክትትልና ቁጥጥር ከተረጋገጠ
በአዋጅ ቁጥር 181/2003 አንቀጽ 25/4 መሰረት ብር 20,000/ሀያ ሽህ ብር/ ቅጣት ለመንግስት
ገቢ አደርጋለሁ፡፡ ፕሮጀክቴ በአካባቢው ስርዓተ ምህዳርና በማህበረሰቡ ላይ ጉዳት ካደረሰ አግባብ ባለው
ህግ መጠየቄ እንደተጠበቀ ሆኖ በአዋጅ ቁጥር 181/2003 አንቀጽ 25/6 መሰረት ለጉዳቱ የካሳ ወጭ
ወይንም የስርዓተ ምህዳሩን ማገገሚያ ወጭ ሙሉ በሙሉ የምሸፍን መሆኑን ተገንዝቢያለሁ፡፡
እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 181/2003 አንቀጽ 25/3 መሰረት ፕሮጀክቴ ያደረሰው አካባቢያዊና
ማህበራዊ ጉዳት ከፍተኛ መሆኑ በምርመራ፣ ክትትልና ቁጥጥር ከተረጋገጠ የፕሮጀክቴ የስራ
እንቅስቃሴ የሚቋረጥ መሆኑን ተገንዘቢያለሁ፡፡ ከዚህ በላይ የተዘተዘሩትን የህግ ማዕቀፎች የማውቃቸው
መሆኔንና ግደታየንም ለመፈጸም የተስማማሁ መሆኔን በተለመደው ፊርማየ አረጋግጣለሁ፡፡
የፕሮጀክቱ ባለቤት ስም ---------------------------------------------------------------- ፊርማ----------------------------------------------
ቀን--------------------------------------ክብ ማህተም

61

Вам также может понравиться