የመምህር መጽሐፍ
4ኛ ክፍል
አዘጋጆች
ፀጋዬ በየነ አሸናፊ
ፋሲል መኳንንት ያለው
አርታኢዎች
ቻላቸው ገላው ሰጠኝ
አፀደ ማሩ ደሴ
ዲዛይነር
ገነት አባተ መኮንን
ቡድን መሪ
ማረው ዓለሙ ተሰማ (ፒኤች ዲ)
ምዕራፍ 3 መረዳዳት������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 23
ምዕራፍ 4 ሥርዓተፆታ������������������������������������������������������������������������������������������������������������ 33
ምዕራፍ 5 ጉብኝት���������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 44
ምዕራፍ 6 ስፖርት����������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 54
ምዕራፍ 7 ዉኃ�������������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 65
ምዕራፍ 8 ድርድር���������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 77
ዋቢ መጻሕፍት�������������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 111
iii
የመምህር መጽሐፍና የማስተማር መርሖች
መግቢያ
ይህ የመምህር መጽሐፍ በፍኖተካርታውና በአገርአቀፍ ምዘናዎች ምክረሐሳቦች መሠረት በ2013 ዓ.ም. በተደረገው
የሥርዓተትምህርት ለውጥ መነሻነት የተዘጋጀ ነው። በመሆኑም በመጽሐፉ ዝግጅት የሚከተሉት ጉዳዮች ልዩ ትኩረት
ተሰጥቷቸዋል፤
1. የተማሪዎችን በጥልቀት የማሰብ፣ የመተንተን፣ የመጠየቅ፣ ችግር የመፍታት፣ የመወሰን፣ የመግባባትና የመገምገም ክህሎት
የሚያሳድጉ ዓይነተብዙ ተግባራት ተካትተዋል፤
2. የተማሪዎችን አቀላጥፎ የማንበብ፣ የማዳመጥ፣ የመናገርና የመጻፍ ችሎታ የሚያጎለብቱ ታሪኮችና ተዛማጅ ተግባራት
እንዲኖሩ ተደርጓል፤
3. የትምህርቱ አቀራረብ ከይዘትተኮር ይልቅ ወደተግባርተኮር እንዲያመዝን ሆኗል፤
4. አገርበቀል እውቀቶች እንደአስፈላጊነታቸው በታሪኮች፣ በምንባቦችና በተግባራት ውስጥ ተካትተዋል፤
5. የባሕላዊ ማንነትንና የአርበኝነትን ፋይዳዎች የሚያስገነዝቡ ታሪኮች፣ ምንባቦች፣ ሥነግጥሞችና ሥዕሎች እንደአስፈላጊነታቸው
ተካትተዋል፤
6. ተማሪዎች በአብዛኛው በትብብር የሚማሩባቸው እድሎች ተመቻችተዋል፤
7. ለመማር የመማር ክህሎቶችን ለማጎልበት ሲባል፣ ተማሪዎች በየምዕራፎቹ አራቱን ክሂሎችና ሰዋስዋዊ ይዘቶች የሚማሩባቸው
ዓይነተብዙ ብልሀቶች ተካትተዋል፤
8. የተማሪዎችን የፈጠራ ችሎታ ለማጎልበት ሲባል ቋንቋውን ፈጥረው የሚጠቀሙባቸው በርካታ እድሎች ተመቻችተዋል፤
9. ሥርዐተፆታንና አካቶ ትምህርትን ከግምት ለማስገባት በታሪኮች፣ በምንባቦች፣ በሥዕሎችና በተዛማጅ ተግባራት እንዲሁም
በቋንቋው ትምህርት ይዘት አቀራረቦች ላይ ጥንቃቄ ተደርጓል።
የመምህር መጽሐፉ የሕጻናትን በአማርኛ ቋንቋ በትኩረት የማዳመጥ፣ የመናገር፣ በጥልቀት የማንበብና የመጻፍ ችሎታ ለማበልፀግ
በሚል ታሳቢ የተዘጋጀ ነው። የመጽሐፉ ዝግጅት በተጨማሪም ሕጻናት ማንበብና መጻፍ እንዴት እንደሚማሩ የተካሄዱ ምርምሮችን
ግኝቶችና የአማርኛ ቋንቋን መሠረታዊ ባህርያት መሠረት ያደረገ ነው። የትምህርት ይዘቶቹ በአሥር ምዕራፎች የተደራጁ ናቸው፤
የመጀመሪያዎቹ ዐምስት ምዕራፎች የትምህርት ይዘቶች በመጀመሪያው መንፈቀዓመት፣ ቀሪዎቹ ዐምስት ምዕራፎች ደግሞ
በኹለተኛው መንፈቀዓመት እንዲጠናቀቁ ሆነው የቀረቡ ናቸው። የአንድ ምዕራፍ የትምህርት ይዘቶች ደግሞ በሦስት ሳምንታት
እንዲጠናቀቁ ታስበው ነው የተደራጁት። የየምዕራፎቹ የትምህርት ይዘቶች በአንድ ነጥብ በተለዩ ሦስት ቁጥሮች የተወከሉ ናቸው፤
የመጀመሪያው ቁጥር ምዕራፍን፣ ኹለተኛው ቁጥር ሳምንትንና ሦስተኛው ቁጥር ቀንን የሚወክሉ ናቸው። ለምሳሌ፣ 1.1.1 የሚሉ
ቁጥሮች ምዕራፍ አንድን፣ ሳምንት አንድንና ቀን አንድን በቅደምተከተል ይወክላሉ፤ እንዲሁም 10.2.3 የሚሉ ቁጥሮች ምዕራፍ
አሥርን፣ ሳምንት ኹለትንና ቀን ሦስትን በቅደምተከተል ይወክላሉ።
በአጠቃላይ የመምህርና የተማሪ መጻሕፍቱ የተዘጋጁት ለ150 የትምህርት ቀናት ነው። ይህም በዓመቱ መጀመሪያ የተማሪዎች
ምዝገባንና የፈተና ቀናትን የሚጨምር አይደለም። ይሁንእንጂ በየትምህርትቤቱ የዓመቱ የትምህርት ቀናት በሥርዐተትምህርቱ
ከታሰበው በላይ ሊሆኑ ስለሚችሉ መምህራን የ150 ቀኑን ትምህርት ጨርሻለሁ፤ በማለት ሳይዘናጉ ተማሪዎች ያስቸገሯቸውን
የትምህርት ይዘቶች በዕለታዊ የትምህርት ዕቅድ እየታገዙ ማስተማርና ማለማመድ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም ተማሪዎች
ለየክፍል ደረጃው የተዘጋጁትን አጋዥ የንባብ መጻሕፍት በክፍል ውስጥ በማንበብ እንዲለማመዱም ክፍለጊዜዎችን መጠቀም ተገቢ
ይሆናል።
iv
የመምህር መጽሐፉ በአብዛኛው የሕጻናቱን መማር ለማገዝ የተማሪ መጽሐፉን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ግልፅ መመሪያ
ያቀርባል። በተጨማሪም ተከታታይ ምዘናን እንዴት መተግበር እንደሚቻልና በትምህርቱ ሂደት ውስጥ የሥርዓተፆታንና አካትቶ
ትምህርትን እንዴት ማረጋገጥ አንደሚገባ ድጋፍ ይሰጣል።
የማንበብ/የመጻፍ አላባውያን
ሕጻናት ጠንካራ አንባቢና ጻፊ እንዲሆኑ ሊያዳብሯቸው የሚገቡ ዐምስት የማንበብ/የመጻፍ አላባውያን መኖራቸውን በመስኩ
የተደረጉ ምርምሮች ያመለክታሉ። ሕጻናቱ ራሳቸውን የቻሉ አንባቢዎች/ ፃፊዎች እንዲሆኑ ለመርዳት መምህራን ሥርዓት ባለውና
ግልጽ በሆነ መንገድ እነዚህን አላባውያን ማስተማር ይጠበቅባቸዋል። ሥርዓት ባለው ሁኔታ ሲባልም በትምህርቱ ሂደት አንዱም
ተፈላጊ አላባ ሳይዘለል ክሂሎችን ርስበርስ እንዲደጋገፉ አድርጎ ከቀላል ወደከባድ ማስተማር ማለት ነው። አምስቱ የማንበብ/ የመጻፍ
አላባውያን የሚባሉትም የሚከተሉት ናቸው፤
1. የንግግር ድምጾች ግንዛቤ
2. ትዕምርተድምጻዊ ግንዛቤ
3. አቀላጥፎ ማንበብ
4. የቃላት እውቀት
5. አንብቦ/አዳምጦ መረዳት
ቋንቋን በተመለከተ ሌሎች በጣም ጠቃሚ አላባውያን ቢኖሩም፣ እነዚህ ዐምስት አላባውያን ግን ለሕጻናት ቅድሚያ ሰጥተን
ልናስተምራቸው የሚገቡ ክሂሎች ናቸው። አላባውያኑን በአግባቡ ማስተማር ማለት ሕጻናቱ ራሳቸውን ችለው የሚያነቡና የሚጽፉ
እንዲሆኑ የሚያስችሏቸውን መሠረታዊ ክሂሎች ማስገንዘብ ማለት ነው።
የንግግር ድምጾች ግንዛቤ፡- የንግግር ድምጾችን የመስማት፣ የመለየትና የመገንዘብ ችሎታ ነው። ይህ አላባ በጣም ጠቃሚ ነው፤
ምክንያቱም፣
ድምጾችን ከፊደሎችጋር ለማዛመድ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ነው፤
ማንበብንና ፊደላትን በሥርዓት ሰድሮ ቃላትን ለመጻፍ ስለሚያግዝ ነው።
የንግግር ድምጾች ግንዛቤ ቃላትን፣ ቀለሞችን፣ ዓረፍተነገሮችን በቃል በሚደረግ ልምምድ ብቻ የሚዳብር ነው። በተጨማሪም
በመዝሙር መልክም በሚደረግ ልምምድ ሊጎለብት ይችላል። በዚህ መጽሐፍ የንግግር ድምፆች ግንዛቤ ትምህርት በአብዛኛው
የሚተኮርበት በአንደኛ ክፍል ነው።
ትዕምርተድምጻዊ ግንዛቤ፡- ፊደሎችን ከሚወክሏቸው ድምጾች ጋር አገናኝቶ የመረዳት ችሎታ ነው። ትእምርተድምጻዊ ግንዛቤ
በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም፣
ቃላትን ለይቶ ለመጥራት ያስችላል። ይህም ሕጻናቱ ራሳቸውን የቻሉ አንባቢዎች እንዲሆኑ ያግዛቸዋል፤
የፊደላት አሰዳደር ሥርዓትን ግንዛቤ ያግዛል፤ በዚህም ተማሪዎች የሚያዳምጧቸውን ድምጾች ከትክክለኛዎቹ ፊደሎች ጋር
ማዛመድ ይችላሉ።
ትዕምርተድምጻዊ ግንዛቤ እያንዳንዱን ፊደልና የሚወክለውን ድምጽ በማስተማር ይዳብራል። በተጨማሪም የቃላቱን ፊደሎች፣
ቀለሞች ወይም አካላት (ክፋዮች) የማጣመርና የመነጠል መለማመጃዎችን በመስጠት ይጎለብታል።
አቀላጥፎ ማንበብ፡- አቀላጥፎ ማንበብ ጽሑፍን በትክክልና በተገቢው ፍጥነት ማንበብና የተነበበውን የማስታወስ ችሎታ ነው።
በተጨማሪም በተገቢው አገላለጽ (የድምጽ ቃናንና ጫናን ለይቶ) ማንበብን ያካትታል። አቀላጥፎ ማንበብ አስፈላጊ የሚሆንበት
ምክንያት ተማሪዎች ያለችግር ማንበብ ከቻሉ፣ በመረዳት ላይ ማተኮር ስለሚችሉ ነው።
ተማሪዎች 2ኛ ከፍልን ሲያጠናቅቁ በቃላት ደረጃ ከማንበብ በሐረግ ደረጃ በፍጥነት ወደማንበብ ችሎታ ይሸጋገራሉ።
v
የንግግርና የጽሑፍ አቀላጥፎ በተገቢ ሁኔታ ራስን መግለጽንም ይመለከታል። ይህ ደግሞ ቋንቋውን በትክክል መጠቀምንና ሐሳብን
ለሌላ አካል በንግግርም ሆነ በጽሑፍ በግልጽ ማስተላለፍን ይጨምራል።
አቀላጥፎ ማንበብ ሊዳብር የሚችለው በርካታ ልምምዶችን ከተገቢ ግብረመልሶች ጋር በመስጠት ነው። በመሆኑም የቃልና የጽሑፍ
አቀላጥፎ የሚዳብረው ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲገልጹ በተቻለ መጠን በርካታ ዕድሎችን ከተገቢ ግብረመልሶች ጋር በመስጠት
ነው።
የቃላት እውቀት፡- ቃላትን የመለየት/የማወቅና ፍቻቸውን የመገንዘብ ችሎታ ነው። ምንምእንኳ ቃላትን ማንበብ ቢማሩም የተወሰኑ
ቃላትን ብቻ የሚያውቁ/የሚችሉ ተማሪዎች ትርጉምን ለመፍጠር/ ትርጉም ያለው ነገር ለማፍለቅ ይቸገራሉ። ስለሆነም ይህም አላባ
በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም፣
ለተማሪዎች አቀላጥፎ ማንበብ አሰተዋጽዖ ያላቸውን ቃላት ከጽሑፍ ውስጥ ለይቶ የማውጣት ሂደትን ያቀላጥፋል፤
ተማሪዎች የሚያነቡትን እንዲረዱ ያስችላል፤
ተማሪዎች ሐሳባቸውን ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲያስተላልፉ ያስችላል።
የቃላት ዕውቀት የሚዳብረው አዳዲስ ቃላትን ከነፍቻቸው በማስተማር፣ ተማሪዎች በንግግርም ሆነ በጽሑፍ ቃላትን
እንዲጠቀሙባቸው በማበረታታት፣ ከሚያነቡት ወይም ከሚያዳምጡት ጽሑፍ ውስጥ የቃላትን ፍቺ የሚያገኙበትን ብልሃት
(ስትራተጂ) እንዲማሩ በማድረግ ነው። የ2ኛ ክፍል ተማሪዎች ቃላትን በዓይነት ይመድባሉ፤ ለ2ኛ ክፍል ጠቃሚ የሆኑ የትምህርት
(የትምህርቤት) ቃላትን ይማራሉ፤ የተማሯቸውን አዳዲስ ቃላት ዓረፍተነገሮች ለመፃፍ ይጠቀሙባቸዋል።
አዳምጦ/አንብቦ መረዳት፡- አንድን ጽሑፍ ወይም ንግግር መረዳትና መተርጎም መቻል ነው። በተጨማሪም የማዳመጥና የማንበብ
የመጨረሻ ግብም ነው። ይህ ክሂል ቀጥተኛ መረዳትን ወይም በጽሑፍ ውስጥ ያለን መረጃ ማስታወስን፣ ፈልፍሎ መረዳትን
ወይም በቀጥታ ያልተገለጸን መረጃ መረዳትንና የመረዳት ስልቶችን ወይም ጽሑፉን ለመረዳት ወይም ለመተርጎም አንባቢዎች
የሚጠቀሙባቸውን ብልሃቶች (ስትራተጂዎች) ያጠቃልላል። ይህ ክሂል በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም፣
ተማሪዎች በሁሉም ትምህርቶች በማንበብ እንዲማሩ ብቁ ያደርጋል፤
ተማሪዎች ራሳቸውን ችለው የሚያነቡና የሚያዳምጡ እንዲሆኑ ያስችላል፤ ከዚህም በላይ ተማሪዎች በሕይወት ዘመናቸው
ለመማርና ከተለያዩ ምንጮች መረጃ ለማግኘት ክሂሉን ይጠቀሙበታል።
አዳምጦ/ አንብቦ መረዳት የሚዳብረው በቅድመማዳመጥ/ማንበብ፣ በማዳመጥ/በማንበብ ሂደትና በድኅረማዳመጥ/ማንበብ
ተግባራት ነው። ተማሪዎች ስለጽሑፉ (በቅድመማዳመጥ/ንባብና በማዳመጥ/በማንበብ ሂደት ወቅት) እንዴት መገመት እንደሚችሉ፣
መረዳታቸውን (በራሳቸው) መቆጣጠር አንዲችሉና ያዳመጡትን ወይም ያነበቡትን እንዴት መገምገም እንደሚችሉ መማር
አለባቸው። ለምሳሌ፣ የ2ኛ ክፍል ተማሪዎች ይዘትተኮርና አመራማሪ ጥያቄዎችን ለመመለስ ልምምድ ያደርጋሉ። በሚያነቡበት
ወቅት የራሳቸውን ግንዛቤ ማረጋገጥ (መከታተል) የሚችሉበትን ሁኔታ ይማራሉ። በተጨማሪም ስለጽሑፉ ያላቸውን የግል ሐሳብ
እንዴት እንደሚገልፁ ይማራሉ።
የትምህርቱ ክፍሎች
ሁሉም የቋንቋ ክሂሎች (ማዳመጥ፣ መናገር፣ ማንበብና መጻፍ) ይዘቶች፣ የማንበብና የመጻፍ አላባውያንን በሚያዳብሩበት መልክ
ሆነው ተደራጅተዋል። ይህም ማለት፣
የምንባብ ይዘቶች (ጭብጦች)ና ንኡሳን ርዕሰጉዳዮች በጥቅም ላይ የዋሉት የማንበብንና የመጻፍን አላባውያንን ለማስተማር
ምንጭ በመሆን ነው፤ የቋንቋ ትምህርት ይዘቶችን ለማስተማር በአውድነት ከማገልገል ውጪ በራሳቸው ትምህርት
አይደሉም ማለት ነው፤
በሁሉም ዋና ዋና ምዕራፎች አራቱ የቋንቋ ክሂሎች ተዋህደው ቀርበዋል።
vi
የተማሪ መጽሐፍና የመምህር መጽሐፍ እያዳንዳቸው በሳምንታዊ ትምህርቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው። በተጨማሪም በተማሪ መጽሐፍና
በመምህር መጽሐፍ ውስጥ እያንዳንዱ ትምህርት በሥዕላዊ ምልክቶች የተጠቆሙ የትምህርት ክፍሎች አሉት። በእያንዳንዱ ምዕራፍ
ሥርም በተማሪዎች የሚሠሩ የተለያዩ ተግባራት አሉ። ብዙዎቹ ትምህርቶች ባብዛኛዎቹ ምዕራፎች ውስጥ ቢገኙም አንዳንድ
ትምህርቶች ግን የሚገኙት በተወሰኑ ምዕራፎች ብቻ ነው። ይሁንአንጂ ሁሉም የማንበብና የመጻፍ አላባውያንና ሁሉም የቋንቋ
ክሂሎች በእያንዳንዱ ሳምንት ትምህርት ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል።
የትምህርቱ ክፍሎችም፤
የማዳመጥ ምንባብ
ይህ ክፍል በአዳምጦ መረዳት ላይ ያተኮረ ነው። ተግባራቱም የሚከተሉትን የያዙ ናቸው፤
ተማሪዎች በመምህር የሚነበብ ታሪክ ወይም መረጃሰጪ ጽሑፍ ያዳምጣሉ።
ካዳመጡት ምንባብ ውስጥ የወጡ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ።
ስለታሪኩ ያላቸውን አስተያየት መግለፅ ይጀምራሉ።
ከታሪኩ አላባዎች ውስጥ፤ ባለታሪኮችን፣ የታሪኩን ጊዜና ስፍራ መለየት ይጀምራሉ።
በታሪኩ ውስጥ የሚገኙ አዳዲስ ቃላትን ይማራሉ።
በታሪኩ ላይ ይወያያሉ።
ስለታሪኩ በተወሰኑ ቃላት ይጽፋሉ፤ ወይም ሥዕል ይሥላሉ።
ማጣመር/መነጠል
ይህ ክፍል ልጆቹን ቃላት ለማንበብና በተገቢ የፊደል አሰዳደር ሥርዓት ለመጻፍ እንዲያግዝ ሆኖ ቃላትን በማንበብና ወደተለያዩ
ክፍሎች በመነጠል ወይም በማጣመር ላይ ያተሉራል። ተግባራቱም የሚከተሉትን ያካትታሉ።
ቃላትን “ማጣመር”፡- ቃላቱ የተመሠረቱባቸውን ፊደሎች ወይም የቃላቱን የተነጣጠሉ አሀዶች ለየብቻ ያነባሉ፤ መልሰውም
አንድ ላይ ይሏቸዋል፤
ቃላትን “መነጠል”፡- ቃላቱን ያነባሉ፤ ቀጥለውም ወደፊደላት ወይም ወደአነስተኛ አሀዶች ይነጣጥላሉ፤
ፍቺ ያላቸውን የቃላቱን አሀዶች (ምዕላዶችን) ለይተው ያነባሉ።
vii
ማንበብ
ይህ ክፍል ሕጻናቱ ቃላትን ለመጥራትና ተዘውታሪ ቃላትን ለመገንዘብ እንዲችሉ ዓረፍተነገሮችን፣ አጫጭር ታሪኮችን ወይም
መረጃሰጪ ምንባቦችን እንዲያነቡ በማድረግ ላይ ያተኩራል። በአንብቦ መረዳትም ላይ ያተኩራል። ተግባራቱም የሚከተሉትን
ያጠቃልላሉ፤
አንብቦ መረዳትን/ አቀላጥፎ ማንበብን፤
ከምንባቡ የወጡ ጥያቄዎችን መመለስን፤
ስለምንባቡ ያላቸውን የግል አስተያየት መግለጽን፤
ከታሪክ አላባዎች ባለታሪኮችን፣ የታሪኩን ጊዜና ስፍራ መለየት መጀመርን፤
በምንባቡ ላይ መወያየትን፤
ምንባቡን የሚመለከት ጽሑፍ መጻፍን።
የቃላት ዕውቀት
ይህ ክፍል አዳዲስ ቃላትን በመማርና በመጠቀም ላይ ያተኩራል። ተግባራቱም የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡-
አዳዲስ ተተኳሪ ቃላት መማርን፤
አዳዲስ ቃላትን ከሥዕሎች ወይም ከፍቻቸው ጋር ማዛመድን፤
ቃላትን መመደብን፤
ለቃላት ተመሳሳይና ተቃራኒ መስጠትን፤
ቃላቱን በዓረፍተነገር ውስጥ መጠቀምን፤
ለ2ኛ ክፍል ትምህርታቸው ጠቃሚ የሆኑ አዳዲስ ትምህርታዊ/የት/ቤት ቃላትን መማርን።
መጻፍ
ይህ ክፍል ፊደሎችንና ቃላትን በመመሥረት፣ በተገቢ የፊደላት አሰዳደር ሥርዓት ቃላትን በመጻፍና ሐሳብን በሥዕል ወይም በቃላት
በመግለጽ ላይ ያተኩራል። ተግባራቱም የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፤
ፊደላትንና ቃላትን መጻፍ መለማመድን፤
ቃላትን በተገቢ ፊደላት አሰዳደር መሠረት መጻፍ መለማመድን፤
አጫጭር የቃል ጽሕፈትና የፊደላት አሰዳደር ፈተናዎች መፈተንን፤
ሐሳብን ለሌሎች ለማጋራት ዓረፍተነገሮችን መጻፍን።
ሳምንታዊ ትምህርቶቹ ማዕከል ያደረጉት ከአራቱ የቋንቋ ክሂሎች ማለትም ከማዳመጥ፣ ከመናገር፣ ከማንበብና ከመጻፍ ክሂሎች ጋር
በተቀናጀ ሁኔታ አምስቱን የማንብበ አላባውያንን ለመደገፍ የቀረቡ ጽሑፎችን በማዳመጥና በማንበብ ላይ ነው። የጽሑፎቹ ትኩረት
በየምዕራፎቹ የምንባብ ጭብጦችና ንኡሳን ርዕሰጉዳዮች ላይ ነው። የማዳመጥና የማንበብ ጽሑፎች አዳምጦና አንብቦ መረዳትን
ለማዳበር በጥቅም ላይ ውለዋል። በሌላ መልኩ ደግሞ ለማዳመጥና ለማንበብ የቀረቡ ጽሑፎች ለተማሪዎቹ ማዳመጥንና ማንበብን
viii
ለመለማመድ ሰፊ ዕድል የሚፈጥሩ ናቸው። ከጽሑፎቹ የሚገኙት ቃላት ደግሞ ለቃላትና ለትዕምርተድምጻዊ ግንዛቤ ተግባራት
ውለዋል። በጽሑፎቹ የተጠቀሱት ሃሳቦችም በሥዕል ለመወከል፣ ለመወያያነትና ለመጻፍ ተግባራት በጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።
አምስተኛው ቀን ለሳምንቱ የተመደቡት የትምህርት ይዘቶች የሚከለሱበትና የተማሪዎች ችሎታ የሚገመገምበት ነው። በመሆኑም
በዚህ በአምስተኛው ቀን ተማሪዎች በሳምንቱ ውስጥ የተማሯቸውን ይዘቶች በተለያዩ መለማመጃዎች፣ ተግባራትና በትምህርታዊ
ጨዋታዎች ማለማመድ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም በዚሁ በአምስተኛው ቀን የተወሰኑ ተማሪዎችን በመደበኛ ተከታታይ
ምዘና መርጦ መመዘን ያስፈልጋል። ይህም ምዘና ተማሪዎቹ ወደሚፈለገው የብቃት ደረጃ ማደግ ወይም አለማደጋቸውን ለመለካት
በአግባቡ ተመዝግቦ መያዝ አለበት።
የማስተማር መርሖች
ልሥራ፣ እንሥራ፣ ሥሩ
በዚህ ሥርዓተትምህርት ውስጥ ዋነኛው የማስተማሪያ ዘዴ በተለምዶ “ልሥራ፣ እንሥራ፣ ሥሩ” ወይም በትክክለኛ አጠራሩ “የመምህር
ሚናን ቀስበቀስ ለተማሪዎች የማስተላለፍ ሞዴል” (gradual release model) ተብሎ ይታወቃል። ተማሪዎች በመጀመሪያ ጥያቄዎች
ወይም ተግባራት በመምህር ሲሠሩ ያያሉ፤ ቀጥሎም የክፍሉ ተማሪዎች ከመምህራቸው ጋር አብረው በጋራ ይሠራሉ፤ በመጨረሻም
ራሳቸውን ችለው በግላቸው እንዲሠሩ የሚደረግበት የማስተማር ዘዴ ነው። ምንምእንኳ ሁሉም ደረጃዎች በሁሉም ቦታ ተሟልተው
የማይገኙበት ሁኔታ ቢኖርም፣ ሞዴሉ ለአብዛኛዎቹ የትምህርት ክንውኖች ወይም ተግባራት በዚህ የመምህር መጽሐፍ ውስጥ
በግልጽ ተብራርቶ ቀርቧል። ዘዴው ተማሪዎች አዳዲስ ክንውኖችን ወይም ተግባራትን ለመሥራትና በራስ የመተማመን አቅማቸውን
ለመገንባት ይረዳቸዋል።
በትብብር መማር
በትብብር መማር ተማሪዎች በቢጤ ወይም በቡድን ተደራጅተው ከክፍል ጓደኞቻቸው ጋር በመደበኛነት ወይም ለአጭር ጊዜ
ተወስነው የሚሰጧቸውን ተግባራት የመሥራት ዕድልን ይፈጥራል። ይህም ተማሪዎች ከጓደኞቻቸው ጋር አዳዲስ መረጃዎችን
የመለዋወጥ ዕድል ስለሚፈጥር የክፍል ውስጥ መማርን ያጠናክራል። በትብብር መማር ብዙ ተማሪዎች ባሉበት ክፍል ውስጥ
በንቃት እንዲሳተፉ ዕድል ይፈጥራል።
ግብረመልስ መስጠት
አንዱ የማስተማር ዋነኛ አካል ተማሪዎች በተናገሯቸው፣ ባነበቧቸው፣ ባቀረቧቸው ወይም በጻፏቸው ላይ ተመሥርተው የመምህር
ግብረመልስ መስጠት ነው። አንዳንድ ጊዜ ግብረመልስ ሳይሰጡ በሚሠሩ መለማመጃዎች ላይ ብቻ ማተኮር ጠቃሚ ሊመስል
ይችላል። ነገርግን ተማሪዎች የተሰጣቸውን ተግባር እንዴት መሥራት እንዳለባቸውና የሠሩትም ትክክል መሆኑን ወይም አለመሆኑን
ለመረዳት ስለሚጠቅማቸው ግብረመልስ መስጠት አስፈላጊ ነው። ግብረመልስ መስጠት ውጤታማ ይሆን ዘንድ መምህራን
የሚከተሉትን ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፤
ተማሪዎች የሰጡት ምላሽ ትክክል ወይም ስህተት መሆኑን መንገር፤
ተማሪዎቹ የመለሱት መልስ ለምን ትክክል ወይም ስህተት ሊሆን እንደቻለ ማብራራት፤
በትክክል የተሠራውን ለተማሪዎች መንገር፤
የሚጠበቅባቸውን ተግባር በትክክል እንዴት መሥራት እንዳለባቸው ወይም ምን ዓይነት ብልሃት መጠቀም እንደላባቸው
መንገር።
ix
ተማሪዎች የሚነገራቸውን ትክክለኛ መልሶች ወይም አቀራረብ ከመስማት ይልቅ በራሳቸው ወደትክክለኛ መልስ እንዲደርሱ ወቅታዊ
ግብረመልስ በመስጠት ይታገዛሉ። ለምሳሌ፣ አንድ/ዲት ተማሪ አንድ አንቀጽ ሲያነብ/ስታነብ አንድ ቃል ሲጠራ/ስትጠራ ቢሳሳት/
ብትሳሳት በሚከተለው አኳኋን ሊነገረው/ ራት ይገባል፤ አንቀጹን ጥሩ አንበሃል/ሻል፤ ግን የኹለተኛው ዓረፍተነገር ኹለተኛ ቃል
“ቤቶች” ሳይሆን “ቤታችን” ነው፤ ስለ“-ኣችን” መማራችንን ታሳታውሳለህ/ሻለሽ? ወይም አንድ ተማሪ ከምንባቡ ውስጥ ያሉትን
ዋናዋና ነጥቦች እንዲዘረዝር/እንድትዘረዝር ለቀረበለት/ላት ጥያቄ የሰጠውን/ቺውን ምላሽ በማጤን፤ ከምንባቡ ዋናዋና ነጥቦች ውስጥ
ሁለቱን በትክክል መልሰሃል/ሻል፤ ጥሩ ነው፤ ሦስተኛው ነጥብ ምን እንደሆነ ልትነግረኝ/ሪኝ ትችላለህ/ቺያለሽ? ወዘተ።
የማስተማሪያ መርጃዎች
በብዙ አካበቢዎች የሚገኙ የመማሪያ ክፍሎች ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁስ የተሟሉላቸው ናቸው ማለት አዳጋች ነው።
ስለዚህ በቀላሉ ባካባቢው ሊዘጋጁ የሚችሉ የማስተማሪያ መርጃ መሣሪያዎችን ለማዘጋጀት ጥረት ማድረግ ተገቢ ነው። ስለሆነም
ለዚህ ሥርዓተትምህርት ጠቃሚ ከሆኑት ቀላል የማስተማሪያ መርጃ መሣሪያዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፤
ፍላሽ ካርዶች፡- ተማሪዎች የሚማሯቸውን ቃላት የሚያሳዩ ክርታሶች/ ካርዶች ናቸው። እነዚህ ካርዶች ቃላቱን ሰሌዳ ላይ ከመጻፍና
ያን እያጠፉ በመጻፍ ጊዜ ከማጥፋት በፍጥነት ካንዱ ፊደል ወይም ቃል ወደሌላው በቀላሉ እየለዋወጡ ለመጠቀም አመቺ ናቸው።
ከርቀት ለማንበብም ቀላል ስለሆኑ፣ ለሁሉም የክፍል ተማሪዎች፣ ለአነስተኛ ቡድኖች ወይም ለግል በቀላሉ ለመጠቀም ያመቻሉ።
በቀላሉም ቀደምብሎ ለማዘጋጀትና እንዳስፈላጊነቱ ደጋግሞ ለመጠቀም አመቺ ናቸው።
የመውጫ ካርዶች፡- እንደፍላሽ ካርዶች ተቆራርጠው የተዘጋጁ ስለሆኑ፣ ተማሪዎች እየጻፉባቸው ለመምህራቸው የሚያሳዩባቸው
ናቸው። ለምሳሌ፣ የማንበብ ሂደት ተግባራት እነዚህን ክርታሶች በመጠቀም ቢከናወኑ መልካም ነው።
ባለኪስ ሠንጠረዥ (Pocket-Chart)፡- የፖስተር መጠን ያለውና ከሸራ ወይም ከጨርቅ የተዘጋጀ ባለኪስ ሠንጠረዥ ሲሆን፣
ተማሪዎች እንዲያዩዋቸው ፍላሽ ካርዶችን ሊይዝ የሚችል ነው። ይህ ሠንጠረዥ በአንድ ጊዜ በርካታ ፍላሽ ካርዶችን ለማቅረብና
ለማሳየት እንዲሁም ከቦታ ወደቦታ በማዘዋወር ለመጠቀም ያመቻል። ዓረፍተነገሮችንም በአዳዲስ ቃላት ለመመሥረትና ስለቃላቱም
ፍቺ ለመነጋገር ያስችላል።
ትልልቅ መጻሕፍት፡- መምህራን ድምጽ በማሰማት ሲያነቡ፣ ሁሉም የክፍል ተማሪዎች ሊያዩዋቸው የሚችሉ በጣም ትልልቅ
መጻሕፍት ናቸው። ተማሪዎች ከነዚህ መጻሕፍት ቃላትን፣ ሥዕሎችን፣ ምሥሎችን፣ ሠንጠረዦችን ወዘተ. ሲያነቡ ስለርዕሰጉዳዩ
ያላቸውን ግንዛቤ ያዳብራሉ፤ ስለርዕሰጉዳዩም በአዲስና በተለየ መንገድ ለማሰብ ዕድል ይፈጥርላቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ በመጽሐፉ
የቀረቡት መረጃዎች የቀረቡባቸውን መንገዶች ለመተንተን ያስችላቸዋል።
ሥዕላዊ መግለጫ (ፖስተር)፤ ለጭብጥና ለንኡሳን ርዕሰጉዳይ የሚዘጋጁ ሥዕላዊ መግለጫዎች (ለምሳሌ፣ በሥራቸው አርኣያ ስለሆኑ
ሴቶችና በማኅበረሰቡ ውስጥ ስላላቸው ሚና፣ ሰለአካባቢ ጥበቃ ዕቅድ፣ በተውኔት ውስጥ ቀርቦ ስለነበረ ወይም ወደፊት ስለሚቀርብ
ክፍል ወዘተ. የሚዘጋጁ) የተማሪዎችን ፍላጎትና ተሳትፎ ይጨምራሉ። መምህራን እነዚህን ሥዕላዊ መግለጫዎች ርስበርስ ሊለዋወጡ
ይችላሉ፤ ተማሪዎችም አዳዲስ ሥዕላዊ መግለጫዎችን በመፍጠር ረገድ ሊሳተፉ ይችላሉ።
x
በሴማንቲክ ቢጋር መስመሮች ቁልፍ የሆነውን ወይም ማዕከላዊዩን ሐሳብ ከተለያዩ ተዛማጅ ሐሳቦችና ድርጊቶች ጋር
ያገናኛሉ/ያስተሳስራሉ፤
የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሮች አንባቢዎች በፅንሰሐሳቦች ላይና ፅንሰሀሳቦቹ ከሌሎች ፅንሰሐሳቦች ጋር እንዴት እንደተዛመዱ
ትኩረት እንዲያደርጉ ይረዳሉ።
የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሮች አስረጂ ቴክስቶችን፣ እንደሣይንሥና የማህበራዊ ሣይንሥ እንዲሁም የንግድ መማሪያ መጽሐፎችን
ለመማር ማንበብ ያግዛሉ።
በአስረጂ ጽሑፎች ላይ ጥቅም ላይ ሲውሉ፣ የሐሳብ ማደረጃ ቢጋሮች ፅንሰሐሳቦች የሚጋሯቸውን ቴክስታዊ መዋቅር
ለመረዳት ተማሪዎችን ያግዛሉ።
የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሮች በተራኪ ታሪኮች የታሪኮችን መዋቅር ለማመላከት ተግባራዊ ይሆናሉ።
የሐሳብ ማደራጃ ቢጋር በተጨማሪም ለተማሪዎች፣
በሚያነቡበት ጊዜ በታሪክ ወይም በምንባብ መዋቅር ላይ እንዲያተኩሩ ያግዛል፤
በሚያነቡት ቴክስት ዝምድናዎችን ለማየትና ለመመርመር የሚረዱ መሣሪያዎችን ይሰጣል፤
ታሪክ ወይም ምንባብ አንብበው በትክክል የተደራጀና የተዋቀረ ማጠቃለያ ለመጻፍ ይረዳቸዋል፤
xi
ተነሺ ቃላት፡- ተማሪዎች በትናንሽ ሰሌዳዎች ወይም ወረቀቶች ላይ መልሶችን ጽፈው፣ መምህራቸው ጥያቄዎችን
በግላቸው (ለምሳሌ፣ ጥያቄ መጠየቅ፣ መልስ መመለስ፣ በቃላት ዓረፍተነገር መሥራት) እንዴት እንደመለሱ እንዲያዩላቸው
በፊትለፊታቸው በጠረጴዛቸው (በዴስካቸው) ላይ ያስቀምጣሉ።
xii
ሥርዓተፆታና አካቶ ትምህርት
xiii
ለአካለመጠን መድረስ፡- ልጆች፤ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች እያደጉ ሲመጡ በትምህርታቸው ላይ ተጽዕኖ ሊኖራቸው የሚችሉ
አካላዊና ሥነልቦናዊ ለውጦች ማሳየታቸው አይቀሬ ነው። ሴቶች በወር አበባቸው ወቅት በሚሰማቸው የህመም ስሜት
የተነሳ ከክፍል እስከመቅረት ሊደርሱ ይችላሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ መምህራን የተቋረጠባቸውን ትምህርት፣ ጊዜ
ሰጥተውና የማካካሻ መርሐግብር አውጥተው ማስተማር ይኖርባቸዋል። ወንዶች ልጆችም እንዲሁ በሚጎረምሱበት ወቅት
ለትምህርታቸው ትኵረት ላይሰጡና በራሳቸው ላይ ስላለው ለውጥ ብቻ ሊያስቡ ይችላሉ። በመሆኑም መምህራን ይኼን
ለውጥ ተገንዝበው ተገቢውን ድጋፍና ምክር ለሁለቱም ፆታዎች መስጠት ይጠበቅባቸዋል።
ወሲባዊ ትንኮሳ፡- ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ተማሪዎችን በአካል፣ በሥነልቦናና በስሜት እንደሚጎዳ ተገንዝበው፣ መምህራን
በምንም ሁኔታ ወሲብነክ የሆነ አስተያየት ከመስጠት፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ፣ አልፎተርፎም ትንኮሳ ከማድረግ
መቆጠብ አለባቸው። እንዲህ ዓይነቱም ተግባር በራሳቸው በተማሪዎችም ቢሆን እንዳይፈጸም መከላከል አለባቸው።
አካቶ ትምህርት
አንዳንድ ተማሪዎች ለትምህርት ተደራሽ ለመሆንና በእኩልነት የትምህርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የተለየ ተጨማሪ ድጋፍ
የሚሹ ይሆናሉ። ይህ የሚሆነው ልጆች ባለባቸው አካል ጉዳተኝነት ምክንያት (ውሱን የመማር፣ የመስማት፣ የማየት፣ ዕድገት/
ውስንነት፣ የቋንቋ ወይም የመንተባተብ፣ የኦቲዝም፣ የአእምሮ ጉዳት፣ የመስማትና የማየት ወይም የተለያዩ የአካል ጉዳተኛነት
ችግሮች) ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም ከክፍል ደረጃቸው በላይ የአእምሮ ብስለት ወይም የመፍጠር ችሎታም ባላቸው ተማሪዎች
ዘንድም ሊከሰት የሚችል ችግር ነው።
ስለዚህ ችግሮችን ለመቅረፍ በዚህ የመምህር መጽሐፍ ውስጥ የተለያዩ የማስተማሪያ ስልቶች ተካትተዋል። በመሆኑም መጽሐፉ
የተለያዩ የማስተማሪያ ዘዴና የተለያዩ የተግባራት አቀራረቦች፣ የሚታዩ፣ የሚደመጡ፣ የሚዳሰሱ፣ የሚሞከሩ ተግባራትን በማካተት
ተማሪተኮር የሆነ አጠቃላይ መርሕ የተከተለና ተከታታይ ምዘናን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ይህ ክፍል የልዩ
ፍላጎት ተማሪዎችን ለማገዝና ለመደገፍ በክፍል ውስጥ ሊተገበሩ የሚችሉ አጠቃላይ ስልቶችን ያቀርባል። ትኵረት የተሰጠውም
የማስታወስ፣ የተግባቦት፣ የቃላት ዕውቀትና የቋንቋ ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች የበለጠ በማገዝ ላይ ነው። አንዳንዶቹን ችግሮች
ለመቅረፍ የሚከተሉትን መተግበር ይጠቅማል፣
መመሪያን ወይም ትዕዛዝን በራሳቸው ቋንቋ መልሰው እንዲሉት ተማሪዎችን መጠየቅ፤ ይህ የመረዳትና የመመለስ ችግር
ላለባቸውና መመሪያው ላመለጣቸው ተማሪዎች በጣም ጠቃሚ ነው። መመሪያውን ደግሞ የመናገሩን ተግባር ለቢጤያቸው
ወይም ለመምህር ሊያቀርቡ ይችላሉ። መምህራንም በአንድ ጊዜ የሚሰጧቸውን የቃል መመሪያዎች ቊጥር መወሰን
ይኖርባቸዋል።
የፅንሰሐሳብና የስልተትግበራ ግምገማዎች መስጠት፤ እያንዳንዱን ቀን በቀደመው ክፍለጊዜ የተማሯቸውን ክሂሎችና
ሐሳቦች በመከለስ መጀመር ይቻላል። የቀደሙ ትምህርቶች ዕለታዊ ግምገማ ተማሪዎች አዲሱን ትምህርት ከቀደመ
እውቀታቸው ጋር ለማገናኘት ይጠቅማቸዋል።
የተለያዩ የመገናኛ መንገዶችን (የዓይነተብዙ ፍንጮች) መጠቀም፤ በተቻለ መጠን መረጃዎች በተለያየ መንገድ ለምሳሌ፣
በሚደመጡ፣ በሚታዩ፣ በሚዳሰሱ፣ በእንቅስቃሴ በሚታገዙ ዘዴዎች ለማቅረብ መሞከር ጥሩ ነው። ለምሳሌ፣ መዝሙሮችን
ከአካል እንቅስቃሴ ጋር አንድ ላይ መጠቀም ይቻላል።
የዕለት ዝውትሮችን/ክንዋኔዎችን አለመለዋወጥ፤ የመማር ችግር ያለባቸው በርካታ ተማሪዎች እነዚህን የየዕለት ዝውትሮችን
ለማወቅና ምን እንደሚጠበቅባቸው ለመረዳት ይጠቀሙባቸዋል። ስለዚህ እነዚህን ዝውትሮችና የሚጠበቁባቸውን
ትምህርታዊ ግቦች በሰሌዳ፣ በግድግዳ ወይም በጠረጴዛቸው ላይ መጻፍ ወይም መለጠፍ ይጠቅማል።
ለተግባራትና ለተማሪዎች ሥራዎች የበለጠውን ጊዜ መመደብ፤ አንዳንድ ተማሪዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማጤን፣ ከራስ
ጋር አዋህዶ ለማቆየትና አዲሱን ዕውቀትና ክሂል ለመጠቀም ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድባቸው ይችላል። በመሆኑም ተግባሩንና
xiv
የተሰጣቸውን ሥራ እንዲጨርሱ በቂ ጊዜ መስጠት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። የሚሰጣቸውንም የሥራ መጠን መቀነስ
አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፣ ጥቂት ዓረፍተነገሮችን ወይም ቃላትን ሰጥቶ እንዲያነቡ ማድረግ አንዱ መንገድ ነው።
ምንባቡን መከታተል የማይችሉ ከሆነ የሚሰጡ መመሪያዎችን በሰሌዳ መጻፍ፤ በተለይ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ
መስማት የማይችሉ ተማሪዎች ሲኖሩ የሚተላለፉ መመሪያዎችን፣ ቊልፍ ዕሳቤዎችንና ቃላትን ሰሌዳ ላይ መጻፍ አስፈላጊ
ነው። ከዚህ ጋር የተያያዘ በክፍል ውስጥ ተገቢ የሆነ መቼት መፍጠር ለምሳሌ፣ የድምጽ ማስተጋባትና የመቆራረጥ ችግር
እንዳይኖር በማድረግ በመምህርና በተማሪዎች መካከል ለሚኖረው ተግባቦት አመቺ ሁኔታ መፍጠር ይገባል። አስፈላጊ
ሲሆንም የማዳመጡን ምንባብ አባዝቶ መስጠት፣ ሥዕሎችንና የሚታዩ ተጨባጭ ነገሮችን በድጋፍ መልክ መጠቀም
ጠቃሚ ነው።
መመሪያዎችን በቃል ማንበብ፣ ጽሑፎችን ማጕላት፤ የማየት ችግር ላለባቸው ተማሪዎች መምህራን ለሌሎች ተማሪዎች
በሰሌዳ ላይ እየጻፉ እያሉ ለእነዚህ ተማሪዎች መመሪያዎችን ጮክ ብለው ያንብቡላቸው፤ ወደሰሌዳው ጠጋ ብለው
እንዲቀመጡም ይፍቀዱላቸው፤ ከተቻለም መመሪያዎችን በጕልህ ጽፈው በሚታይ ቦታ ሊያደርጉላቸው ይችላሉ።
በመደጋገፍ የመማርና የቢጤ መማማር ዘዴን መጠቀም፤ ተመሳሳይ ወይም የተለያየ ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች በቡድን
አዋቅሮ ርስበርስ እንዲማማሩ ማድረግ ጠቃሚ ነው። በተማሪዎችም መካከል መተዋወቅንና መከባበርንም ይፈጥራል፤
በራስ የመተማመንን ስሜትና ማኅበራዊ ክሂል ያዳብራል። መምህራን ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ለትምህርቱ ሂደት
አስተዋጽዖ እንዳላቸውና የነቃ ሚና እንደሚጫወቱ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።
አንድ ተግባር ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ግልጽ፣ ወቅታዊና አዎንታዊ ግብረመልስ መስጠት፤ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ከሌሎቹ
ተማሪዎች እኩል በተመሳሳይ ፍጥነት ላይማሩ ይችላሉ። ይህም ራሳቸውን ከሌሎቹ ያነሱ አድርገው እንዲቆጥሩ
ሊያደርጋቸው ይችላል፤ ለትምህርት ያላቸውን ተነሳሽነትና የመማር አቅምም ሊጎዳው ይችላል። በመሆኑም ያሳዩት መሻሻል
ጥቂት እንኳ ቢሆን አዎንታዊ የሆነ አበረታች ግብረመልስ መስጠት መዘንጋት የለበትም።
ከላይ የተዘረዘሩትን ስልቶች በሚገባ ለመተግበር መምህራን የተማሪዎቻቸውን ፍላጎትና ችሎታ መረዳት ይኖርባቸዋል።
በትምህርትቤት ውስጥ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ሥልጠና ያላቸው መምህራን ካሉ ከነሱ ጋር በመሆን በጋራ በመሥራት የተማሪዎቹን
ፍላጎቶች መለየትና በትምህርቱም ሂደት ለማካተት መሞከር ያስፈልጋል።
xv
ሀ. እንደትምህርትቤት፣ ዳቦቤት፣ መሥሪያቤት ወዘተ. ያሉት ጥምር ቃላት በመሆናቸው በወጥነት አንድ ላይ ተጠጋግተው
እንዲጻፉ ተደርገዋል፤ መምህራን ትኵረት ሰጥተው ራሳቸውም በጥንቃቄ እየተጠቀሙ ለተማሪዎቻቸው እንዲያለማምዷቸው
ያስፈልጋል።
ለ. እንደቅድመንባብ፣ ድኅረንባብ፣ ኅብረተሰብ፣ ቅድመማዳመጥ ወዘተ. ያሉ ባለአጣማሪ (-ኧ-) ቃላትም በተዘበራረቀ መንገድ
መጻፋቸውና በትምህርት አሰጣጣችንም ሆነ በአጻጻፍ ሥርዓታችን ላይ ችግር መሆናቸው የቆየ ጉዳይ ነው፤ ስለዚህ በአሁኖቹ
መጻሕፍት ውስጥ አንድ ላይ ተጠጋግተው እንዲጻፉና መምህራን ራሳቸው በጥንቃቄ እየተጠቀሙ ለተማሪዎቻቸው
እንዲያስተምሩ ይጠበቃል።
ሐ. ሌላው እዚህ ላይ የሚጠቀስ ማሻሻያ በመስተዋድዳዊ ሐረግ ውስጥ መስተዋድዱንና አብረዋቸው የተዋቀሩትን ስማዊ ሐረጎች
በተዘበራረቀ መንገድ ከመጻፍ በወጥነት ለመጠቀም የተደረገው ሙከራ ነው። እንደሚታወቀው መስተዋድዳዶችን ስ-፣ ስለ-
እንደ-፣ እንድ-፣ ወደ-፣ እስከ- ወዘተ. በሙሉ ማለት በሚቻልበት ሁኔታ (ዘንድ የሚለው መኖሩን ሳንዘነጋ) ራሳቸውን ችለው
ለብቻቸው መቆም የሚችሉ አለመሆናቸውን በሰዋስው እያስተማርን፣ አብዛኞቻችን ስንጽፍ ግን ልክ ራሳቸውን እንደቻሉት
ቃላት በኹለት ነጥብ እየለየን ነው። ይሁንና በነዚህ አዳዲስ መጻሕፍት ውስጥ በወጥነት፣ ለምሳሌ፣ እንዲበላ፣ እንደመጣ፣
እንደአባቱ፣ ወደትምህርትቤት፣ ስለመጣ፣ ስለአበበ፣ ስበላ፣ ሲበላ፣ ከቤቱ በላይ፣ ወዘተ. የሚሉት አንድ ላይ እንዲጻፉና
ትምህርቱም በዚሁ ዓይነት እንዲሰጥ ተዘጋጅቷል።
መ. ሌላው ትኵረት የሚሻ ጉዳይ የብዙ ቊጥር ቃላትን የምንጽፍበት ሥርዓት ነው። እንደሚታወቀው ቃላትን ወደብዙ ቊጥር
የምንለውጥባቸው መንገዶች እንደቃላቱ ክፍል የተለያዩ ቢሆኑም፣ በተለይ በስሞች ላይ የሚታየው ወጥነት የጎደለው ይመስላል።
ለምሳሌ፣ ቃል ብሎ ቃላት ወይም ቃላት ማለት ሥርዓት የተከተለ ሲሆን፣ ቃላቶች ማለት ግን ብዙ ቊጥርን የሚያመለክተውን
ቃል እንደገና የብዙ ቊጥር ምዕላድ ጨምሮ (ቃል + -ኣት= ቃላት + -ኦች= ቃላቶች) ማብዛትን የሚያሳይ የተዘወተረ ግድፈት
ነው። በመሆኑም በወጥነት በአንዱ መንገድ ማለትም በአማርኛው የብዙ ቊጥር ምዕላድ -ኦችን (ከነዘሮቹ) መጠቀምና ቃላት፣
መምህሮች፣ ሕፃኖች፣ ዕፆች ወዘተ. እያሉ፣ አለበለዚያም ከግእዝ ቋንቋ ወስደን በምንጠቀምበት የብዙ ቊጥር ሥርዓት፣ ቃላት፣
መምህራን፣ ሕፃናት፣ ዕፅዋት ወዘተ. በማለት መጻፍና ይህንኑም ለተማሪዎች በወጥነት ማስተማር በጣም አስፈላጊ ሆኗል።
ከዚህ በተለየ ግን መምህራኖች፣ ቃላቶች፣ ዕፅዋቶች እያሉ መጠቀም (በቋንቋው ውስጥ መነሻ ምክንያት ያለው ቢመስልም)
ሥርዓታዊም ተገቢም አይመስልም፤ እንደትልቅ ሕፀፅ የሚወስዱ ሰዎች ቢያጋጥሙም አይደንቅም። ስለሆነም መምህራን
ከላይ በተመለከተው መሠረት በተግባር እንዲጠቀሙና እንዲያስተምሩ አደራ ተጥሎባቸዋል።
በኹለተኛ ደረጃ ትኵረት የሚሠጠው ጉዳይ በአማርኛ የፊደል ገበታ ላይ ሞክሼ ፊደላት የመኖራቸው ጉዳይ ነው። እዚህ ላይ የቆየውን
አተካሮ ትተን (ወደፊት መሠረታዊ እልባት እስኪያገኝ) በተቻለ መጠን በወጥነት ፊደላቱን መጠቀም ግን ለሌላ ጊዜ የሚተው
ባለመሆኑ በአሁኖቹ መጻሕፍት ውስጥ ትኵረት ለመስጠት ጥረት ተደርጓል። እንደመነሻ የተወሰደውም በአብዛኛው በጥቅም ላይ
እየዋሉ ያሉበት መንገድ ነው። በዚህም፣ ለምሳሌ ከመጻፍ ጋር የተገናኙትን ከነዝርዝራቸው ጽሕፈት፣ ጸሐፊ፣ መጻፍ፣ አጻጻፍ ወዘተ.፣
ከሥን ጋር የሚዋቀሩትን ሥነጽሑፍ፣ ሥነሕዝብ፣ ሥነሥርዓት ወዘተ.፣ ከሕግ ጋር የሚዋቀሩትን ሕገመንግሥት፣ ሕገተፈጥሮ፣
ሕገወጥ፣ ወዘተ፣ ዝርዝሩ ብዙ በመሆኑ ጉዳዩን በጥሞና በማጤንና መጻሕፍቱን በጥንቃቄ እያነበቡ፣ በመጻሕፍቱ ውስጥ በተጻፉበት
መንገድ መረዳትና በዚሁ ዓይነትም ለተማሪዎች ማስተማር ስለሚገባ መምህራን ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።
በመጨረሻም መጠቀስ ያለበት ሌላው ከአጻጻፍ ጋር የሚያያዝ ጉዳይ የቋንቋ ክሂሎችን ለመሠየም የምንጠቀምበትና የምንጽፍበት
መንገድ ነው። ስለሆነም አራቱ የቋንቋ ክሂሎች በወጥነት ማዳመጥ (ማድመጥ አይደለም)፣ መናገር (ንግግር አይደለም)፣ ማንበብ
(ንባብ አይደለም) እና መጻፍ (ጽሕፈት ወይም ጽሑፍ አይደለም) በመሆናቸው በዚሁ ዓይነት መንገድ እንዲጻፉና በተግባር ላይ
እንዲውሉ ይጠበቃል።
xvi
ምዕራፍ አካባቢ ጥበቃ
1
የምዕራፉ ዓላማዎች
አካባቢያችን
አካባቢ ሊበከል የሚችልባቸው መንገዶች ብዙ ናቸው። በየጊዜው የሚለቀቁ መርዛማና በካይ ጋዞች ለአካባቢ ብክለት ይዳርጋሉ።
ከፋብሪካዎች፣ ከመኪናዎች፣ ከወፍጮ ቤቶች ወዘተ የሚወጣው የተቃጠለ ጋዝ አካባቢን ይመርዛል። ቆሻሻን በአግባቡ
አለማስወገድ የአካባቢን ውበትና ጤናማነት ይቀንሳል። የደኖች መመንጠርም የአካባቢን ሚዛን በእጅጉ ያዛባል።
የአካባቢ መበከል ደግሞ ለበርካታ ችግሮች ይዳርጋል። አካባቢ ሲበከል የአየር ንብረት መዛባት፣ ጎርፍ፣ ድርቅና ረሃብ ይከሰታሉ።
ልዩ ልዩ አየርወለድና ውኃወለድ በሽታዎችም ይስፋፋሉ። የተፈጥሮ ሃብትም ይመናመናል። አፈር በጎርፍ ስለሚታጠብ መሬት
ለምነቷን ታጣለች፤ ምርታማነቷም ይቀንሳል። በአጠቃላይ የተበከለ አካባቢ ለኑሮ ምቹ አይሆንም። በዚህ የተነሳ ሰዎች ቀያቸውን
ለቀው ስለሚሰደዱ ለከፋ ስቃይ ይዳረጋሉ።
ëëë አካባቢን ከብክለት መጠበቅ የሚቻለው እንዴት ነው? ëëë
ይሁን እንጅ አካባቢን ከብክለት በመጠበቅ ለኑሮ ምቹ ማድረግ ይቻላል። ለዚህ ደግሞ በርካታ ርምጃዎችን መውሰድ ይጠይቃል።
ከመኖሪያ ቤቶችና ከድርጅቶች የሚወጣውን ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ በመለየት ሰብስቦ መቅበር ወይም እንደገና ወደምርት መቀየር
ተገቢ ነው። የተራቆተን መሬት በደን በመሸፈን የአፈር መሸርሸርን መከላከልና የአካባቢን ስነምህዳር መጠበቅ ያስፈልጋል። ወደህዋ
የሚለቀቀውን የተቃጠለ ጋዝ ለመቀነስ ታዳሽ የኃይል ምንጮችን በአማራጭነት መጠቀም ይገባል። እንዲህ ሲሆን አካባቢ ውብ፣
ለኑሮም ተስማሚ ይሆናል።
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. ተማሪዎች ለቀረቡት ቃላት በታሪኩ መሠረት አውዳዊ ፍቺ እንዲጽፉ ይጠይቋቸው።ምሳሌ ሠርተው ያሳዩ።)
[ተ. ለተሰጡት ቃላት በትክክል አውዳዊ ፍቺ ይጽፋሉ።]
[የአካባቢ ሚዛን-ተፈጥሮ፣ መበከል- መመረዝ/ መቆሸሽ፣ ውኃወለድ- ውኃ አመጣሽ/ በውኃ የሚተላለፍ፣ ቀዬ- መንደር]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. “ቁጭት” የሚለውን ታሪክ ከማንበባቸው በፊት በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ እንዲወያዩ ያድርጉ። ዐይነስውራን ተማሪዎች
ከጎናቸው ከሚገኙ ተማሪዎች ጋር እየተወያዩ እንዲሰሩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመ ንባብ ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ።]
ቃላት (7 ደቂቃ)
(መ. ከታሪኩ ለወጡት ቃላት አውዳዊ ፍቺ እንዲሰጡ ይጠይቋቸው፤ በአዛምድ የቀረቡትንም ቃላት ከተመሳሳያቸው ጋር
እንዲያዛምዱ ያድርጉ፤ተማሪዎቹ ተግባራቱን ሠርተው ሲጨርሱ መልሳቸውን እጅ እያወጡ ለክፍሉ እንዲናገሩ ያድርጉ።)
[ተ. ለተሰጡት ቃላት አውዳዊ ፍቺ ይሰጣሉ፤ ቃላትን ከተመሳሳይ ፍቻቸው ጋር ያዛምዳሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. ለተሰመረባቸው ቃላት አውዳዊ ፍቺ እንዲሰጡ ያድርጉ፤የማስተካከያ መልስ ይስጧቸው።)
[ተ. ለተሰመረባቸው ቃላት አውዳዊ ፍቺ ይሰጣሉ።]
አስቴርና ሶፊያ
አስቴርና ሶፊያ ጓደኛሞች ናቸው። ሁለቱም የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ በጣም ይዋደዳሉ። ሁለቱም ተመሳሳይ ባህርይ
አላቸው፤ ውይይት ይወዳሉ። ዘወትር በልዩልዩ ርዕሰጉዳዮች ላይ ይወያያሉ። ዛሬም በአንድ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ
ይዘዋል።
አስቴርና ሶፊያ በአካባቢያቸው በሚከሰቱ ችግሮች ላይ ተጨንቀዋል። የድርቅ ተደጋግሞ መከሰትም አሳስቧቸዋል። የትውልድ
ቀያቸው ሙቀት መጨመርም ረፍት ነስቷቸዋል። አካባቢያቸው በደራሽ ጎርፍ መሸርሸሩ ቆጭቷቸዋል። የምድር በረከት መቀነስም
አስደንግጧቸዋል። የዛሬው ውይይታቸው በዚህ ላይ ነው። የቀጠሮው ሰዓት ሲደርስ ተገናኙ።
ëëë
ለችግሮቹ ምን አይነት መፍትሔዎችን የሚጠቀሙ ይመስላችኋል? ëëë
በአካባቢያቸው የተከሰቱ ችግሮች በጣም እንዳሳሰቧቸው ተነጋገሩ። ለሙቀት መጨመርና ለድርቅ መከሰት ምክንያቶት በሆኑት
ጉዳዮች ላይ መወያየት ቀጠሉ። የችግሩ ዋነኛ ምንጭ የደኖች መመንጠር ስለመሆኑ ተስማሙ። ሰዎች ለማገዶ፣ ለቤት መስሪያና
ለአጥር ማጠሪያ ዛፎችን መቁረጣቸው ትክክል እንዳልሆነ ተግባቡ። ችግሩን ለማስወገድ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማሰብ ጀመሩ።
ችግኞችን በብዛት መትከልና መንከባከብ ከተቻለ ችግሩ እንደሚቀረፍ ተማመኑ። ስለሆነም ራሳቸው አርዓያ ሆነው መታየት
እንዳለባቸው ተረዱ። በአካባቢያቸው ባለው ክፍት ቦታ ላይ አሥር አሥር ችግኞችን ሊተክሉ ተስማሙ። ጓደኞቻቸውንም
አስተባብረው በርካታ ችግኞችን ለመትከልና ለመንከባከብ ቃል ገቡ። ውይይታቸውን ሲጨርሱ የችግኝ መትከያ ጉዳጓድ ለመቆፈር
ተቀጣጥረው ተለያዩ።
ውሏችን ለአካባቢያችን
(መ. “ውሏችን ለአካባቢያችን” የሚለውን ምንባብ ከጓደኞቻቸው ጋር በመጋራት በትክክል፣ በፍጥነትና በተገቢ አገላለጽ ማንበብን
ያለማምዱ። በዚህ ደረጃ ትኩረት የሚደረገው ምንባቡን አቀላጥፈው ማንበብ እንዲችሉ ማድረግ ላይ ነው። ስለሆነም
ምንባቡን ሲያነቡ በደንብ ተከታትለው ግብረ መልስ ይስጧቸው።)
[ተ. “ውሏችን ለአካባቢያችን” የሚለውን ታሪክ ከጓደኞቻቸው ጋር በመጋራት በትክክል፣ በፍጥነትና በተገቢ አገላለጽ ማንበብን
ይለማመዳሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄ ላይ እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄ ላይ ከመምህር ጋር ይወያያሉ።]
ቃላት (7 ደቂቃ)
(መ. በሳጥን ውስጥ ያሉትን ቃላት በተሰመረባቸው ቃላት ተክተው ዓረፍተነገሩን እንደገና እንዲጽፉ ያድርጉ። ቃላቱን በትክክል
መተካታቸውን ለማረጋገጥ መልሱን እንዲገልጹ ያድርጉ። እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ይስጧቸው።)
[ተ. ቃላቱን በተመሳሳይ ቃላት ይተካሉ።]
ጣናን እንታደግ
ጣና ሀይቅ ልዩ በሆነ መልክዓምድራዊ ሂደት የተፈጠረ ነው። ተመራማሪዎች ከብዙ ዓመታት በፊት በተከሰተ የእሳተገሞራ ፍንዳታ
እንደተፈጠረ ያስረዳሉ።
ጣና ሀይቅ ከሰሜን እስከ ደቡብ 75 ኪ.ሜ. ይረዝማል። በተመሳሳይ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለው ርዝመት 60 ኪ.ሜ. ነው።
ጣና ሀይቅ 3600 ስኩየር ኪ.ሜ. ስፋት ይሸፍናል። ከባህር ወለል በላይ 1830 ሜትር ከፍታ አለው። ጣና በስፋቱ በኢትዮጵያ
አንደኛ ነው። በአፍሪካ ደግሞ ከቪክቶሪያና ከታንጋኒካ ሀይቆች ቀጥሎ የሶስተኛ ደረጃ ባለማዕረግ ነው። ከፍተኛው ጥልቀቱ 14
ሜትር ሲሆን አማካይ ጥልቀቱ ደግሞ 9 ሜትር ነው።
በሀይቁ ላይ የሚገኙት ጥንታዊ ገዳማትና ደሴቶች አለምአቀፍ የቱሪስት መስህብ በመሆን ያገለግላሉ። በትራንስፖርትና በዓሳ
ምርት አገልግሎት ስለሚሰጥ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው የጎላ ነው። ለአባይ ወንዝም ከፍተኛ የዉኃ መጠን ስለሚለግስ ለህዳሴው
ግድብ የወደፊት ተስፋ ነው።
ëëë የጣና ሐይቅ የዉኃ መጠን ቢቀንስ ወይም ቢበከል ምን ምን ጉዳቶች ሊከሰቱ ይችላሉ? ëëë
ይህ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለአለም ህዝብም ብርቅና ድንቅ፣ ሳቢና ማራኪ የሆነ ተፈጥሯዊ ሀብታችን በጠና ታሞ
በጣረሞት ላይ ይገኛል። ሀይቁ በዙሪያው በሚገኙ ነዋሪዎች በሚጣል ደረቅ ቆሻሻና በሚለቀቅ ፈሳሽ ቆሻሻ እየተመረዘ ነው።
“እምቦጭ” በሚባል አደገኛ መጤ አረም ሰፊው የሀይቁ አካል እየተወረረ ነው። ከከፍተኛ ቦታዎችና ባካባቢው ከሚገኙ የእርሻ
መሬቶች በጎርፍ እየተሸረሸረ በሚገባው ደለል የውኃ መጠኑ በእጅጉ እየቀነሰ ነው። በሀይቁ ላይ የተጋረጠውን ከፍተኛ አደጋ
ድንበር ሳንለይ በአገርአቀፍ ደረጃ ስልት ዘይደንና በጀት መድበን መታደግ ይኖርብናል። በመሆኑም “ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ
መጠንቀቅ” ነውና ሁላችንም በመረባረብ ጣናን እንታደግ።
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ እንዲወያዩ ያድርጉ። ለቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ግብረመልስ መስጠት አያስፈልግም።
ራሳቸው ታሪኩን አዳምጠው ግምታቸው ትክክል ወይም ስህተት መሆኑን ያረጋግጣሉ።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ከመምህር ጋር ይወያያሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. ተማሪዎች ምንባቡን ከማንበባቸው በፊት በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጓቸው።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር ይወያያሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. የቀረቡትን ቃላት በምንባቡ መሠረት ከተመሳሳይ ፍቻቸው ጋር እንዲያዛምዱ ያድርጉ። ግብረመልስ ይስጡ።)
[ተ. ቃላቱን ከተመሳሳይ ፍቻቸው ጋር ያዛምዳሉ። የሠሩትን ለመምህር ያቀርባሉ።]
የምዕራፉ ዓላማዎች
የትምህርትቤታችን እንግዳ
ዛሬ በትምህርትቤታችን ውስጥ አንድ እንግዳ ተገኝተዋል። የኢትዮጵያን ብሄራዊ መዝሙር ዘምረን ሰንደቅዓላማችንን ሰቅለናል።
ርዕሰመምህሯ ከእንግዳው ጋር ሊያስተዋውቁን ንግግራቸውን ጀመሩ። “እንደምን አደራችሁ ተማሪዎች? በመካከላችን የተገኙት
እንግዳ ከመንገድ ትራንስፖርት መስሪያቤት የመጡ ናቸው። አጭር ትምህርት ስለሚሰጧችሁ በጽሞና ተከታተሉ” አሉን።
እንግዳውም ርዕሰመምህራችንን አመስግነው ንግግራቸውን ቀጠሉ። “እንደምን አደራችሁ ተማሪዎች?” አሉና ምላሻችንን
ሳይጠብቁ ወደትምህርቱ አመሩ። “ስለመንገድ ላይ ደህንነት ለማስተማር ነው የመጣሁት። በአገራችን ብሎም በክልላችን
በየጊዜው በርካታ ሰዎች በመኪና አደጋ ጉዳት ይደርስባቸዋል። ስለሆነም ራሳችሁን ከአደጋ ልትጠብቁ ይገባል። በመኪና መንገድ
ላይ መጫወት ራስን ለጉዳት ያጋልጣል። ምንጊዜም የእግረኛ መንገድ ብቻ ተጠቀሙ። ግራ አቅጣጫችሁን ይዛችሁ መጓዝንም
አትርሱ። ምክንያቱም መኪና ሲመጣ ፊትለፊት የማየት እድል ይፈጥርላችኋል” አሉና ወደያዙት ማስታወሻቸው አቀረቀሩ።
ëëë
እስካሁን ካዳመጣችሁት ታሪክ ምን ተረዳችሁ?ëëë
አሁንም ንግግራቸውን ቀጠሉ። “መንገድ ማቋረጥ ስትፈልጉ ደግሞ የእግረኛ ማቋረጫዎችን ተጠቀሙ። በዚህ ጊዜም ቢሆን
መኪና ወይም ሌሎች ተሸከርካሪዎች አለመምጣታቸውን ማረጋገጥ ይኖርባችኋል። ተምራችሁ ለአገራችሁ፣ ለማኅበረሰባችሁና
ለወላጆቻችሁ ልትጠቅሙ የምትችሉት ራሳችሁን ከአደጋ ስትጠብቁ ብቻ ነው” ካሉ በኋላ ሰዓታቸውን ተመለከቱ። በመጨረሻም
ወደርዕሰመምህሯ ዞረው ምስጋና በማቅረብ ትምህርታቸውን አጠናቀቁ።
ቃላት (7 ደቂቃ)
(መ.ዓረፍተነገር በመስራት የቃላቱን አውዳዊ ፍቺ እንዲያሳዩ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ ምሳሌ ይስጡ።)
[ተ. የቃላቱን አውዳዊ ፍቺ በዓረፍተነገር ያሳያሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ውይይት እንዲያካሂዱ ይጠይቁ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ያደርጋሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. ተማሪዎች ቃላቱን ከተቃራኒያቸው ጋር እንዲያዛምዱ ያድርጉ። በትክክል ማዛመዳቸውን ያረጋግጡ፤ እንዳስፈላጊነቱ
ማስተካከያ ይስጡ።)
[ተ. የተሰጡትን ቃላት ከተቃራኒያቸው ጋር ያዛምዳሉ። መልስ 1. ሐ 2. ሠ 3. ረ 4. ሰ 5. ለ]
ቃላት (7 ደቂቃ)
(መ. በዓረፍተነገሮቹ ውስጥ የተሰመረባቸውን ቃላት በሳጥን ውስጥ ካሉት መርጠው እንዲተኩ ያድርጉ። መልሳቸው ትክክል
መሆኑን በማረም ያረጋግጡ።)
[ተ. በዓረፍተነገሮቹ ውስጥ የተሰመረባቸውን ቃላት በተመሳሳይ ቃላት ይተካሉ።]
የትራፊክ ፖሊስ
የትራፊክ ፖሊስ የመንገድ ላይ ደንቦችን የሚያስከብር ባለሙያ ነው። በመኪና አደጋ ምክንያት የሰው ህይወትና ንብረት ጉዳት
እንዳይደርስበት የሚቆጣጠርና ህግን የሚያስከብር ሰው ነው። ሹፌሮች ጠጥተው እንዳያሽከረክሩ፣ በፍጥነት እንዳይነዱና ዕቃና ሰው
ከልክ በላይ እንዳይጭኑ ይቆጣጠራል።
በተለይ በትልልቅ ከተሞች ተሽከርካሪዎች መስቀለኛ መንገድ ላይ ተራቸውን ጠብቀው እንዲተላለፉ የሚያደርጉት አረንጓዴ፣ ቢጫና
ቀይ መብራቶች በትክክል መስራታቸውን ይከታተላል። ሰዎች ለማቋረጫ ተብሎ በተዘጋጀ የዜብራ መስመር ብቻ ተጠንቅቀውና
ተራቸውን ጠብቀው እንዲተላለፉ ያስተምራል።
ማንኛውም አሽከርካሪ ቀይ መብራት ሲበራ መቆም ይኖርበታል። ቢጫ ሲበራ መዘጋጀትና አረንጓዴ ሲበራ ማለፍ እንዳለበት ሊያውቅ
ይገባዋል። የመብራት ደንብ አክብሮ፣ ተራውን ጠብቆ የማያሽከረክር ሹፌር ለአደጋ ተጋላጭ ይሆናል። በተለይ በመስቀለኛ መንገዶች
አሽከርካሪዎች ያለተራቸው ለማለፍ ሲሽቀዳደሙ ለአደጋ ይዳረጋሉ። በዚህ መልኩ በሀገራችን በሰውና በንብረት ላይ የሚደርሰው
አደጋ የትየለሌ ሆኗል።
ስለሆነም የትራፊክ ፖሊስ የመኪና አደጋዎችን ለመቀነስና ለመከላከል ተግቶ የሚሰራ ነው። ከቅርብ አመታት ወዲህ አደጋዎችን
ለመቀነስ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችንም እያሳተፈ ይገኛል። በትምህርትቤትና በቀበሌ ፈቃደኛ ወጣቶችን በመመልመል የመንገድ
ላይ ደህንነት ስልጠና እየሰጠ ነው። ወጣቶች ከስልጠና በኋላ በተመረጡ የመኪና መንገዶች የትራፊክ ደንቦችን እንዲያስከብሩ
አሰማርቷል። የትራፊክ ፖሊስ በእግረኞች ስህተት፣ በሹፌሮች ችኩልነትና በመኪና ብልሽት ምክንያት አደጋ እንዳይከሰት ጥረት
ያደርጋል። በዚህም የሰው ልጆችን ህይወት ከሞት፣ ንብረታቸውንም ከጥፋት ለመታደግ የሚሰራ ትጉህ ባለሙያ ነው ሊባል ይችላል።
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ከተማሪዎች ጋር ይወያዩ። ዐይነስውራን ተማሪዎች ካሉ በኹለተኛው ጥያቄ ላይ ሐሳባቸውን
እንዲናገሩ ይጠይቋቸው።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር ይወያያሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን እንዲያሟሉ ያድርጉ። ምሳሌ ሠርተው ያሳዩአቸው።)
[ተ. የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን በተፈላጊ ሐሳቦች አሟልተው ይጽፋሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. “እኔ ማነኝ?” የሚለውን ታሪክ ከማንበባቸው በፊት በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ።]
ድኅረንባብ (7 ደቂቃ)
(መ. የድኅረንባብ ጥያቄዎችን በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ። መልሳቸውን ለክፍሉ እንዲያቀርቡ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ
ማስተካከያ ይስጧቸው።)
[ተ. የድኅረንባብ ጥያቄዎቹን በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
ቃላት (7 ደቂቃ)
(መ. ቃላት በታሪኩ ውስጥ ባላቸው አውዳዊ ፍቺ ዓረፍተነገር እንዲመሠርቱ ያድርጉ። የሠሩትን ያርሙላቸው።)
[ተ. ቃላቱ በታሪኩ ውስጥ ባላቸው አውዳዊ ፍቺ ዓረፍተነገር ይሠራሉ።]
ድኅረማዳመጥ
(መ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎችን እውነት ወይም ሀሰት በማለት እንዲመልሱ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ ይስጧቸው።)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን እውነት ወይም ሐሳብ በማለት ይመልሳሉ።]
ፍጥነትና መዘዙ
ይደርሳል ተስፋ ይባላል። ከአባቱ ከአቶ ተስፋ አለኸኝና ከእናቱ ከወ/ሮ ስመኝ ቀራለም ሰኔ 19 ቀን 1972 ዓ.ም. በባህርዳር ከተማ
ተወለደ። እናትና አባቱ ፈጣሪ ሀብት የሰጣቸው ስለሆኑ ተቀማጥሎ ያደገ መልከመልካም፣ ቁመቱ ሎጋ፣ ሲያዩት የሚያማልል ልጅ
ነበር።
እድሜው ለትምህርት ሲደርስ በሰርፀድንግል አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤት ትምህርቱን መከታተል ጀመረ። ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ
ጎበዝ ተማሪ ሰለነበር በ1990 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍልን በከፍተኛ ውጤት አጠናቀቀ። በ1991 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
የህክምና ትምህርቱን ለሰባት ዓመታት ተከታትሎ በ1997 ዓ.ም በማዕረግ ተመረቀ።
እናትና አባቱ፣ እህትና ወንድሙ እንደማለዳ ፀሐይ ፈክተውና ባላቸው ልብስና ጌጥ አሸብርቀው ሊያስመርቁት ወደ አዲስ አበባ
ሄዱ። እዚያው አዲስ አበባ የሚኖሩ ዘመዶቻቸውን ጨምሮ በአንድ ሆቴል ውስጥ ሲበሉና ሲጠጡ ፣ ሲዘፍኑና ሲጨፍሩ አመሹ።
እኩለ ሌሊት ሲሆን ድካም ተሰማቸውና ወደየአልጋ ክፍላቸው ሄደው ከነልብሳቸው ተጋደሙ፤ ወዲያው እንቅልፍ ጣላቸው።
ወደባህርዳር ለመመለስ ማልደው ተነሱ። በመጠጥ ብዛት የተነሳ ድካም እያናወዛቸው ሁሉም አንድ ላይ በግል መኪናቸው
ተሳፈሩ። የመኪናዋን መሪ የጨበጡት የቤተሰቡ አባወራ ናቸው። አባወራው ከፍ ባለ ድምጽ ባህላዊ ዘፈን ከፍተዋል። የቤተሰቡ
አባላት ድካም ቢሰማቸውም ከሙዚቃው ጋር ማዜም ጀምረዋል። አባወራው አንዳች በሆነ የደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው መኪናዋን
እንደአውሎ ነፋስ ያከንፏት ጀመር።
ተመራቂውና አስመራቂው ቤተሰብ በሙሉ በአንድነት “አባዬ! ቀስ በል! አባዬ! ቀስ በል!” እያሉ ይጮሀሉ። የሰማቸው ግን
አልነበረም። ከአዲስ አበባ ከንጋቱ በአስራአንድ ሰዓት የተነሳችው መኪና ጠመዝማዛውን መንገድ ተያይዘዋለች። ደስታ ያሰከራቸው
አባት ፍጥነታቸውን ጨምረዋል። ቤተሰቦቻቸው ቢማፀኗቸውም ሊሰሟቸው ፈቃደኛ አልሆኑም።
“ሞት የጠራውን ገላጋይ አያስቀረውም” እንደተባለው ወደድልድዩ መታጠፊያ ሲደርሱ መኪናዋ መንገዱን ስታ ቁልቁል
ወደሸለቆው በአየር ላይ ተንሳፈፈች።
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. “ፍጥነትና መዘዙ” የሚለውን ታሪክ ከማዳመጣቸው በፊት በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹ ላይ ይወያያሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
መ. (የሰፈሬ ልጆች የሚለውን ታሪክ ከማንበባቸው በፊት በጥያቄዎቹ ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ ያድርጉ። መልስ መስጠት
አያስፈልግም።)
[ተ. በቅድመ ማንበብ ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ።]
ቃላት (7 ደቂቃ)
(መ. በቀረቡት ቃላት በታሪኩ መሠረት አውዳዊ ፍቺ እንዲሰጡ በማድረግ ዓረፍተነገር እንዲሰሩ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ
ለመልሳቸው ማስተካካያ ይስጧቸው።)
[ተ. ቃላቱ በታሪኩ መሠረት አውዳዊ ፍቺ እንዲኖራቸው አድርገው ዓረፍተነገር ይሠራሉ። መልስ፡- ጎብኚዎቹ ወደጎንደር ለመሄድ
በየመኪናቸው ተሳፈሩ። (ገቡ ለማለት)]
የምዕራፉ ዓላማዎች
ከዚህ ምዕራፍ ትምህርት በኋላ ተማሪዎች፡-
የቀረበውን ምንባብ አዳምጠው ስሜታቸውን ያንፀባርቃሉ፤
ለክፍል ደረጃው በሚጠበቅ የፍጥነት መጠን ምንባቦችን ያነባሉ፤
ቅጥያዎችን የያዙ ቃላትን በመጠቀም አረፍተነገር ይመሠርታሉ፤
ድርብና ድብልቅ ዓረፍተነገሮችን ይፅፋሉ።
ድር ቢያብር
እኛ ኢትዮጵያዊያን ውብ ባህል አለን። ከውብ ባህላችን መገለጫዎች መካከል አንዱ መረዳዳት ነው። መረዳዳት በልዩልዩ መንገዶች
ይከናወናል። ይኸውም በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በሐሳብ ወዘተ ሊሆን ይችላል።
ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች በብዙ መልኩ ሊቸገሩ ይችላሉ። መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት ሊሳናቸው ይችላሉ። ስለሆነም የእለት
ጉርስ የዓመት ልብስ በመስጠት ልንረዳቸው ይገባል። አምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ነው፤ ለአምሳ ሰው ግን ጌጡ ነውና ከተባበርን
ችግሩን እናቀልላቸዋለን። በመኖሪያ ቤት እጦት ወይም በእርጅና ምክንያት የሚቸገሩ በርካታ ወገኖች አሉንና ልንደርስላቸው ይገባል።
አቅመ ደካማ የሆኑ ሰዎችን በጉልበታችን የምናግዝባቸው ብዙ አማራጮች አሉን። አንደኛው አማራጭ የመኖሪያ ቤታቸውን
በመስራት ወይም በማደስ መርዳት ነው። ሰዎች አቅም በማጣት የደረሰ አዝመራቸውን በወቅቱ መሰብሰቡ ሊያቅታቸው ይችላል።
አዝመራቸው በወቅቱ ባለመሰብሰቡ የተነሳ ምርታቸው ሊቀንስባቸው ይችላል። ስለሆነም አዝመራቸውን በወቅቱ በማጨድ፣
በመሰብሰብና ምርቱን በማስገባት ማገዝ ኹለተኛው አማራጭ ሊሆን ይችላል።
በእድሜ አንጋፋ የሆኑ ሰዎች አቅም ሊያንሳቸው፤ አይናቸውንም ሊከልላቸው ይችላል። መንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ የሌሎችን ድጋፍ
ይፈልጉም ይሆናል። በዚህ ወቅት መንገድ በማሻገርና በማመላከት መርዳት ይጠበቅብናል።
ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ከሌሎች ምክር ይሻሉ። አንድን ጉዳይ ለምን፣ እንዴትና መቼ ማከናወን እንዳለባቸው ለመወሰን የሌሎችን
ሐሳብ ይፈልጋሉ። በዚህ ጊዜ ጠቃሚ ሐሳብ በመስጠት ልንረዳቸው ይገባናል። እንዲህ ሲሆን ነባሩን የመረዳዳት ባህል ማስቀጠል
እንችላለን።
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. ታሪኩን ከማንበባቸው በፊት በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ይወያያሉ።]
አርሶአደሮቹ
የአገራችን አርሶአደሮች ብልሆች ናቸው። ሥራዎቻቸውን መቼና እንዴት ማከናወን እንዳለባቸው ያውቃሉ። የእርሻ መሬታቸውን
በወቅቱ ያርሳሉ፤ ያለሰልሳሉ። በየዓመቱ ለመሬቱ ተስማሚ የሆነ የእህል ዓይነት እያፈራረቁ ይዘራሉ። አረም እንዳይውጠው
ተከታትለው ያርማሉ። አዝመራው ሲደርስ ያጭዳሉ፤ ምርታቸውን ወደጎተራ ያስገባሉ።
የአገራችን አርሶአደሮች ቤት ለመስራት ሲፈልጉም ርስበርስ ይረዳዳሉ። በተናጠል ለማከናወን የሚያስቸግራቸውን ወይም
የማይቻላቸውን ተግባር በቀላሉ ለመፈፀም መረዳዳት እንደሚያስፈልጋቸው ያውቃሉ። በሌላም በኩል የአንዱን ጉድለት ሌላኛው
እየሞላ መኖርንም ተለማምደውታል። ስለሆነም አንድ በሬ ብቻ ያለው ገበሬ የጎረቤቱን በሬ ወስዶ ሲያርስ ይውላል። በሌላ ቀን
ደግሞ የራሱን በሬ ለጎረቤቱ ይሰጠዋል፤ ጎረቤቱ ሲያርስ ይውላል። የዘር እህል ሲቸግራቸውም ርስበርስ ይረዳዳሉ። ያለው ለሌለው
ይሰጠዋል፤ ያበድረዋል። ተበዳሪውም ምርቱን ሲሰበስብ አመስግኖ ይመልሳል።
በአጠቃላይ ልባሞቹ ገበሬዎች በመረዳዳት እንጅ በተናጠል ኑሮን መግፋት እንደማይቻል ጠንቅቀው ያውቃሉ። ስለሆነም ርስበርስ
መረዳዳትን ባህል አድርገውታል።
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹ ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ። ታሪኩን ማንበብ ከመጀመርዎ በፊት የሐሳብ
ማደራጃ ቢጋሩን በደብተራቸው ላይ አዘጋጅተው የታሪኩን ርዕስ ተመልክተው ማወቅ የሚፈልጓቸውን ጉዳዮች እንዲጽፉ
ያድርጉ። ከዚያም ታሪኩን ሲያነቡላቸው እያዳመጡ ይቆዩና ከታሪኩ የተማሩትን እንዲጽፉ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ርስበርሳቸው ይወያያሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. ታሪኩን ከማንበባቸው በፊት በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር ይወያዩ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ።]
ድኅረንባብ (8 ደቂቃ)
(መ. የታሪኩን ዋና ሐሳብ የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩ ላይ በቅደምተከተል እንዲጽፉ ያድርጉ። የጻፉት ትክክል ስለመሆኑ ይከታተሉ፤
እንዳስፈላጊነቱ ማስተካከያ ይስጧቸው።)
[ተ. የታሪኩን ፍሰት በሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩ ውስጥ ይጽፋሉ።]
ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ዝናብ ወደቤታቸው ይገባል። በላስቲክ ለመከለል ቢሞክሩም ነፋሱ እያነሳ ይወስድባቸዋል። የቤቱ ወለል
እንደውጩ ሁሉ ጭቃ ሆኗል። የቤቱ ቅዝቃዜ ከውጩ የተለየ አይደለም። እማማ በዚች ደሳሳ ቤት ውስጥ ብቻቸውን ለረጅም
ዓመታት ኖረውባታል። ሆኖም እንደአሁኑ የተሰቃዩበት ጊዜ አልነበረም። ቤቷ እንደእማማ ከዓመት ዓመት እያረጀት ሄዳለች። ከላይ
ዝናብ፣ ከጎን ወጨፎ፣ ከመሬት ጎርፍ ይገባል። እማማ ጉልበትም ሆነ ገንዘብ ስለሌላቸው ቤታቸው ሲፈርስ ከማየት ውጪ ምንም
አማራጭ አልነበራቸውም።
ëëë
የእማማ ዕጣ ፈንታ ምን የሚሆን ይመስላችኋል?ëëë
እማማ እንደዛሬ ሲደሰቱ አይቻቸው አላውቅም። በጤና፣ በፍቅርና በሰላም እንድንኖር መረቁን። እኛም በእማማ ደስታ እርካታ
ተሰማን። ርስበርስ ስንረዳዳ ብዙ መስራት እንደምንችልም ተገነዘብን።
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. ታሪኩን ከማዳመጣቸው በፊት በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ ያድርጉ)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ ይወያያሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ። ተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ጥያቄውን በአግባቡ
መመለስ እንዲችሉ በቅድሚያ ሠንጠረዡን በደብተራቸው እንዲያዘጋጁና ከርዕሱ በመነሳት የሚያውቁትንና ማወቅ
የሚፈልጉትን ጉዳይ በሰንጠረዡ ውስጥ እንዲፅፉ ያድርጉ። በማስከተልም የተማርኩት የሚለውን አምድ ታሪኩን ካነበቡ
በኋላ እንዲሞሉ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር ይወያያሉ። ሠንጠረዡን በደብተራቸው በማዘጋጀት የሚያውቁትንና ማወቅ
የሚፈልጉትን ጉዳይ ይመዘግባሉ።]
ማንበብ (7 ደቂቃ)
(መ. “ያገርልጅ የማርእጅ” የሚለውን ታሪክ ለመረዳት ድምጽ ሳያሰሙ እንዲያነቡ ያድርጉ።)
[ተ. ታሪኩን ለመረዳት ድምጽ ሳያሰሙ በየግላቸው ያነባሉ።]
ቃላት (8 ደቂቃ)
(መ. ለተሰመረባቸው ቃላትና ሐረጋት አውዳዊ ፍቺ እንዲሰጡ ያድርጉ፤ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ይስጧቸው።)
[ተ. ለቃላቱና ለሐረጋቱ አውዳዊ ፍቺ ይሰጣሉ።]
የምዕራፉ ዓላማዎች
አንዳንድ ሰዎች የሴትና የወንድ ስራ የተለያየ መስሎ ይታያቸዋል። በዚህም ሴትን ደካማ ወንድን ጠንካራ አድርገው ያስባሉ።
ከጥንት ጀምሮ ወንድ በአደን፣ ሴት በምግብ ማብሰል ሲሳተፉ ነበር። ወንዶች በእርሻና በንግድ ሲሰማሩ ሴቶች በጉልጓሎና
በአረም በወፍጮና በፈትል እንደሚሰማሩ ይታወቃል። ይህ የሆነው ከልማድና ከባህል የተነሳ እንጂ በተፈጥሮ የስራ ክፍፍል ስላለ
አይደለም። በእርግጥ ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ ሴት አርግዛ፣ አምጣና ወልዳ እንዲሁም አጥብታ ልጅ ታሳድጋለች። በዚህ የተነሳ
ጉልበቷ ሊቀንስ ስለሚችል ከባድ ስራ ለመስራት ትቸገር ይሆናል።
ጊዜው እየዘመነ ስልጣኔ እየተስፋፋ በመጣ ቁጥር ግን የሴቶች እኩልነት ህግና ደንብ ወጥቶለት ተግባራዊ ሊደረግ ይችላል።
ባህሉ ካልተጫናቸው በስተቀር ሴቶች በሬ ጠምደው ያርሳሉ፤ ሸማ ይሠራሉ፤ አናጺና ግንበኛ በመሆን ቤታቸውን ይሠራሉ።
ለዚህም በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በፎገራ ወረዳ የሚገኘውን የአውራአምባ ማኅበረሰብ ለአብነት መጥቀስ ይቻላል። በዚህ
ማኅበረሰብ ወንዶች ልጅ ያዝላሉ፤ እህል ይፈጫሉ፤ እንጀራ ይጋግራሉ፤ ጥጥ ይፈትላሉ፤ ውኃ ይቀዳሉ። ይህ ያንች ስራ ነው፤
ይህ ደግም ያንተ ስራ ነው በማለት አይገፋፉም። ማንኛውንም ስራ በእኩል ተሳትፎ ያከናውናሉ፤ ከሚገኘው ውጤትም በእኩል
ድርሻ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
ቃላት (7 ደቂቃ)
(መ. በሳጥን ውስጥ ያሉትን ቃላት የሴት ተግባራት፣ የወንድ ተግባራት ወይም የጋራ ብለው እንዲመድቡ ያድርጉ። በምድቦቹ ላይ
እንዲወያዩ ያድርጉ)
[ተ. በሳጥን ውስጥ ያሉትን ቃላት የሴት ተግባራት፣ የወንድ ተግባራት ወይም የጋራ ብለው ይመድባሉ፤ በምድቦቹ ላይ ርስበርስ
ይወያያሉ።]
(ማስታወሻ፡- የወንድ ብቻ የሚባል ተግባር የለም። የሴት ተግባራት ተፈጥሯዊ የሆኑት ማርገዝና ማጥባት ብቻ ናቸው።
ሌሎቹ ተግባራት የጋራ በሚለው ሥር ይሰፍራሉ።)
አቀላጥፎ ማንበብ (13 ደቂቃ)
(መ. “ክብር ለእናቶቻችን” የሚለውን ታሪክ በትወና መልክ በጥንድ እየተቀባበሉ በትክክል፣ በፍጥነትና በተገቢ አገላለጽ አቀላጥፈው
እንዲያነቡ ያድርጉ።)
[ተ. ታሪኩን በትወና መልክ ጥንድ ሆነው እየተቀባበሉ በትክክል፣ በፍጥነትና በተገቢ አገላለጽ ያነባሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. ታሪኩን ከማንበባቸው በፊት በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ።]
ቃላት (7 ደቂቃ)
(መ. የተሰመረባቸውን ቃላት በሳጥኑ ውስጥ ባሉ ቃላት በመተካት ዓረፍተነገሮቹን እንደገና እንዲጽፉ ያድርጉ።)
[ተ. የተሰመረባቸውን ቃላት በተመሳሳይ ቃላት ተክተው ይጽፋሉ።]
እኩልነት
ብዙዎቻችን የሴቶችን አቅም ዝቅ አድርጎ የሚያይ የተዛባ አመለካከት ይዘን ቆይተናል። ከፍያለ ችሎታ የሚጠይቁ ወይም የተሻለ
ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን የወንድ ስራ አድርጎ መቁጠር የተለመደ ነበር። በትምህርት ዓለም እንደሳይንስና ሒሳብ የመሳሰሉትን
ትምህርቶች ለሴቶች ከባድ ለወንዶች ግን ቀላል አድርገው የሚያስቡም አንዳንድ ግለሰቦች ነበሩ። ነገር ግን ሴቶችም በሳይንስና
በሂሳብ ከወንዶች እኩል አቅም እንዳላቸው ጥናቶች ያሳያሉ። በተጨማሪም ዶክተር ሲባል ከወንድ ጾታ ጋር ነርስ ሲባል ደግሞ ከሴት
ጾታ ጋር እናዛምድ ነበር። አርሶአደርን ስናስብም ወንድ እንጂ ሴት በአዕምሯችን አትመጣም።
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. ታሪኩን ከማዳመጣቸው በፊት በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር ውይይት ያደርጋሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. ታሪኩን ከማንበባችን በፊት በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ይወያያሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. በተሰመረባቸው ቃላት ከታሪኩ ውጭ ባላቸው ፍቺ ዓረፍተነገር እንዲመሠርቱ መመሪያ ይስጡ። እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ
ይስጡ።)
[ተ. ላሚቱ ተጠምዳ ስለዋለች በጣም ደክሟታል።]
ድኅረማዳመጥ(10 ደቂቃ)
(መ. በታሪኩ መሠረት የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን “እውነት” ወይም “ሀሰት” ብለው እንዲመልሱ ያድርጉ፤ ለመልሳቸው ምክንያት
እንዲሰጡ ይጠይቋቸው።)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን እውነት ወይም ሀሰት በማለት ይመልሳሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. በ “ሀ” ክፍል ካሉት ቃላት ጋር አብረው የሚሄዱ ቃላትን ከ “ለ” ክፍል በመምረጥ እንዲጽፉ ያድርጉ።)
[ተ. ቃላቱን ከተስማሚ ፍቻቸው ጋር ያዛምዳሉ።]
ችግሩን ቀመስነው
ተ. የእናቴን የስራ ጫና አባታችንም ሆነ እኛ ተረድተነው አናውቅም። ለአፍታ እንኳ ሳታርፍ ጀምበሯ ትጠልቃለች። እንጨት ራሷ
ፈልጣ እንጀራ ትጋግራለች። ብዙ ሸክም አዝላ ወደገበያ ሄዳ ትመጣለች። ዛሬ ድንገት አመማትና ሆስፒተታል ሄደች። ዶክተሩ
ከሥራ ብዛት የተነሳ የልብ ድካም ህመም ስላመማት ለሳምንት ያህል ተኝታ እንድትታከም አዘዙ። እኛም እያዘንን ወደቤታችን
ሄድን። ቤቱ በጣም ቀዝቅዞ አገኘነው። ከሰል ማን ያያይዝ!፤ ምግብ ማን ይስራ! በጣም ራበን። መተያየት ብቻ ሆነ። ህጻኑ ልጅ
ማልቀስ ጀመረ። እናታችን የተሸከመችው ከባድ ኃላፊነት አሁን ገባን። ስራ ብናግዛት ኖሮ እንደማትታመም ተረዳን። ከዚህ
በኋላ ግን የየድርሻችንን መስራት እንዳለብን ተገንዝበናል።]
በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለውን ማህበራዊ ልዩነት ለማስቀረት ብዙ ጥረት ተደርጓል። ህግ እየተደነገገ፣ ደንብና መመሪያ
እየወጣ በሴቶች ላይ የሚደርሰው የስራ ጫና መቀነስ እንዳለበት በይፋ ታውጇል። የተገኘው ተግባራዊ ለውጥ ግን አጥጋቢ
አይደለም። በተለይ የገጠሩ አካባቢ ከከተማው ጋር ሲነጻጸር ልዩነቱ ሰፊ ነው።
እስካሁን ድረስ በገጠር በሚኖሩ እናቶቻችን ላይ ያለው የስራ ጫና የከፋ ነው። ሴቶች በረሃ ወርደው እንጨት ይለቅማሉ።
ሁሉንም ባያካትትም በእጃቸው ይፈጫሉ። የቀንድ ከብት በረት፣ የጋማ እንስሳት ጋጥ ፣ የፍየልና የበግ ጉረኖ ያጸዳሉ። ሌሊቱን
በቂ እንቅልፍ ሳያገኙ ለቀጣዩ ቀን የሚሆን ምግብ ሲያዘጋጁ ያድራሉ። በጧት ሁሉንም እንደየባህሪው ቤት ባፈራው እህልውኃ
አስተናግደው ይሸኛሉ። በቤት ውስጥ ከሚሰሩት ስራ በተጨማሪ በውጪ ከአባወራው ጋር እኩል ሲደክሙ ውለው የሚመለሱት
በምሽት ነው። በተለይ ዘር በሚዘራበት፣ አዝመራ በሚታረምበትና በሚሰበሰብበት ወቅት ያለባቸውን የሥራ መደራረብ በቃላት
መግለጽ ያስቸግራል። በገጠር ሴት ልጆችን ወደትምህርት ቤት የመላክ ባህል ቢሻሻልም ከከተማው ጋር ሲታይ ገና ብዙ ይቀረዋል።
ያለዕድሜና ያለአቻ ጋብቻም እስካሁን አልተገታም።
ወደከተማ ሴቶች ህይወት ስንመለስ በግብርናው ዘርፍ ከሚኖሩ የስራ ጫናዎች ነጻ ናቸው። ስልጣኔ በመምጣቱ የምግብ ማብሰል
ተግባራት በኤሌክትሪክ ኃይል ስለሚከናወን ድካማቸውን ቀንሶላቸዋል። ወንድ ሴት ሳይሉ ሁሉንም ልጆቻቸውን እኩል
ያስተምራሉ። ሴቶች በአለባበስና በንጽህና ከወንዶች አይተናነሱም። ህጻናትንና ጠቅላላ ቤተሰቡን የመንከባከብ ሁኔታም እኩል
ነው ለማለት ባያስደፍርም ወንዶችም እየተጋሩት ነው።
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. “የከተማችን ከንቲባ” የሚለውን ታሪክ ከማንበባቸው በፊት በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ
ያድርጉ።
[ተ. ታሪኩን ከማንበባቸው በፊት በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ይወያያሉ።]
ቃላት (8 ደቂቃ)
(መ. በዓረፍተነገሮቹ ለተሰመረባቸው ቃላት አውዳዊ ፍቺ እንዲሰጡ ያድርጉ።)
[ተ. ለተሰመረባቸው ቃላት አውዳዊ ፍቺ ይሰጣሉ]
ድኅረማዳመጥ
(መ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎች ባዳመጡት ታሪክ መሠረት በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ፤ እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ ይስጡ።)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
የምዕራፉ ዓላማዎች
የአቡነ አሮን ገዳም በመቄት ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከወልድያ ወደጎንደር አቅጣጫ 150 ኪሎሜትር ርቃ ከምትገኘው
የአግሪት መንደር የኹለት ሰዓት የእግር ጉዞ ያስኬዳል። ደብሩ የሚገኝበት ስፍራ ደብረዳሪት ይባላል። ደብሩ የታነፀው በ1330ዎቹ
አቡነ አሮን በተባሉ የሐይማኖት አባት ነው። ገዳሙ በዋሻ ውስጥ ተፈልፍሎ የተሰራ ነው። ደብሩ ዐምስት የተለያዩ ክፍሎች
አሉት። በየክፍሎች አራት አራት አምዶች ይገኛሉ። ገዳሙ ኹለት በሮችና ሰባት መስኮቶች አሉት። የበሩ መግቢያ ባለኹለት
ተከፋች ነው። ከሰባቱ መስኮቶቹ አንደኛው በጣራው ላይ ይገኛል። የጣራው መስኮት መዝጊያ የሌለው በመሆኑ በፀሐይ ጊዜ
ብርሃን ያስገባል። በዝናብ ጊዜ ግን ምንም ውኃ አያስገባም። ይህንን ተዓምረኛ መስኮት ስቁረት በማለት ይጠሩታል።
አቡነ አሮን ዋሻውን ለመፈልፈል የተጠቀሙበት መጥረቢያ በማህደር ሆኖ ተቀምጧል። ለገዳሙ አገልግሎት የሚሰጡ ኹለት
ሙቀጫዎች አሉ። የደብሩ ካህናት እንደሚሉት ከሙቀጫዎቹ አንደኛው ከእንቧጮ የተሰራ ነው። በርካታ ጥንታዊ ስዕሎችና
የብራና መጻሕፍት ይገኛሉ። የአቡነ አሮን መቃብርም በገዳሙ ውስጥ ይገኛል።
(ምንጭ፤ የአማራ ክልልና መስህቦቿ። ቀን የሌለው መጠነኛ ማሻሻያ ተደርጎ የተወሰደ)
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ ይወያያሉ።]
ማስታወሻ
ቅጽሎች የስም ገላጮች ናቸው። የሚገልጹትም የስሙን አይነት፣ መጠንና ባህሪ ነው። በዚህም የስሙን ቀለም፣ መልክ፣ ቅርጽ፣
ባህሪ፣ ወዘተ ለማመልከት የሚያገለግሉ ናቸው።
የጎዜ መስጊድ
የጎዜ መስጊድ ከደብረብርሃን ከተማ 93 ኪሎሜትር ርቃ ከምትገኘው የሸዋሮቢት ከተማ በስተምዕራብ በ15 ኪሎ ሜትር ርቀት
ላይ ይገኛል። የተሰራው በ15ኛ መቶ ክፍለዘመን ነው። ከ500 ዓመታት በላይ ዕድሜ እንዳለው ይነገርለታል። አሠራሩ አራት
ማዕዘን ነው። ግድግዳውና ጣራው ባልተጠረቡ ድንጋዮች ተገንብቷል። የድንጋዩን ክዳን የተሸከሙት አራት አግዳሚ የጣውላ
ወራጆች ናቸው። አራት ምሰሶዎችም አሉት። መስጊዱ የአርጎባን መንደሮች በስተግርጌው አድርጎ ከኮረብታ ላይ ይገኛል።
በዙሪያው ጥንታዊ የመቃብር ስፍራና የድሮ ኗሪዎች የዉኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓዶች አሉት። በውስጡ ደግሞ የሃይማኖቱ መሪዎች
አራት ጦሮች ይገኛሉ።
የአርጎባ ማኅበረሰብ አባላት በመስጊዱ ዙሪያ ይኖሩ ነበር። አሁን ግን ኮረብታውን ለቀው ከግርጌ መንደራቸውን መሥርተው
ይኖራሉ። ይሁን እንጅ መስጊዱ አሁንም ዋነኛ የእምነት ቦታቸው ነው። ይህ መስጊድ የአርጎባን ማኅበረሰብና በአካባቢው ያለውን
ውብ የተፈጥሮ መስህብ በስተግርጌው አድርጎ ሲታይ ዓይንን ይማርካል።
(ምንጭ፤ የአማራ ክልልና መስህቦቿ። ቀን የሌለው፤ መጠነኛ ማሻሻያ ተደርጎ የተወሰደ)
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. ታሪኩን ከማዳመጣቸው በፊት በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ከተማሪዎች ጋር ይወያዩ።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹ ላይ ከመምህር ጋር ይወያያሉ።]
ቃላት (8 ደቂቃ)
መ. (ቃላቱን ከተቃራኒያቸው ጋር እንዲያዛምዱ ያድርጉ።)
[ተ. ማዕዘን- ቀጥ ያለ፣ ውብ- የማያምር፣ …በማለት ያዛምዳሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. በዓረፍተነገሮቹ ለተሰመረባቸው ቃላት አውዳዊ ፍቺ እንዲሰጡ ያድርጉ።”)
[ተ. ሀ. አቋርጦ ለ. ፎቅ/ ከፍ ያለ ማማ ሐ. ውበት ... በስፋት ተኝቶ/ተንሰራፍቶ]
የማዳመጥሂደት (7 ደቂቃ)
(መ. የጎዜ መስጊድ የሚለውን ታሪክ ደግመው ያንብቡላቸው”)
[ተ. ታሪኩ ሲነበብ በጥንቃቄ ያዳምጣሉ።]
ይስማ ንጉሥ
በ1881 ዓ.ም. አጼምንሊክና የኢጣሊያ ተወካይ ኮን አንቶኔሊ የውጫሌን ውል የተፈራረሙበት ቦታ ይስማ ንጉሥ ይባላል። ይህ
ታሪካዊ ቦታ ከደሴ ወልድያ መንገድ 60 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ውጫሌ ከተማ ለመድረስ ሰባት ኪሎሜትር ሲቀር
ወደግራ ገባ ብሎ ከአንባሰል ተራራ ግርጌ ይገኛል። ቦታው ኢጣሊያ በውጫሌ ውል ስምምነት አማካይነት ኢትዮጵያን በቅኝ
ግዛት ለመያዝ ሴራ የሸረበችበት ነው። ይህ ሴራ በመጋለጡ በሀገራቱ መካከል ውዝግብ እንደተፈጠረና ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ፈር
ቀዳጅ የሆነው ታላቁ የአድዋ ጦርነት እንደተጀመረ ታሪክ ያስረዳል።
የቦታው ስያሜ የተሰጠው የአፄ ምንሊክ ባለቤት በሆኑት በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ነው። ስያሜው የውሉን 17ኛ አንቀጽ ለማፍረስ
በጊዜው የተገደዱበትን ታሪካው ገጽታ የሚያንጸባርቅ ነው። ከተናገሩትም “ይስሙ ንጉሥ! ጦርነት አልወድም ከዚህ መሳይ ውል
ግን ጦርነት እመርጣለሁ” የሚለው ይጠቀሳል። ከዚህ በመነሳትም ለቦታው ይስማ ንጉሥ የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል።
ከይስማ ንጉስ በቅርብ ርቀት ከሰሜን ወደደቡብ ተዘርግቶ ከሰማይ ጋር የገጠመ የሚመስለው ስመገናናው የአምባሰል ተራራም
ከነግርማ ሞገሱ ይታያል።
(ምንጭ፤ የአማራ ክልልና መስህቦቿ። (ቀን የሌለው)። መጠነኛ ማሻሻያ ተደርጎ የተወሰደ)
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹ ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ ያድርጉ)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹ ላይ ርስበርስ ይወያያሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. በ “ሀ” ክፍል ያሉትን ቃላት አብረዋቸው የሚሄዱ ቃላትን ከ‹‹ለ›› ክፍል መርጠው እንዲያዛምዱ ያድርጉ።)
[ተ. ቃላትን አብሯቸው ከሚሄድ ቃል ጋር ያዛምዳሉ።]
ቅድመንባብ (5 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ በቀረቡት ቃላት ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ያደርጋሉ።]
የምዕራፉ ዓላማዎች
ከዚህ ምዕራፍ ትምህርት በኋላ ተማሪዎች፡-
ተመሳሳይ መረጃዎችን አዳምጠው መልዕክቶቹን በቃል ይለዋወጣሉ፤
በእያንዳንዱ አንቀፅ ውስጥ የሚገኘውን ጽሑፍ ሐሳብ አንብበው ያብራራሉ፤
የቃላት እውቀታቸውን በልምምድ ያሳድጋሉ፤
የባለቤትና ማሰሪያ አንቀፅ ስምምነት ያላቸውን ዓረፍተነገሮች ይመሠርታሉ።
ዘመናዊ ስፖርት ዘመናዊ የውድድር ቦታ ተዘጋጅቶለት በብዙ ተመልካቾች ታጅቦ ይከናወናል። ዘመናዊ ስፖርት በዓይነት እየበዛና
በክንውኑም በጣም አስደሳች እየሆነ መጥቷል። ይህን የስፖርት አይነት በሦስት ከፍሎ ማየት ይቻላል።
አንደኛው የኳስ ጨዋታ ሲሆን የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣ የቅርጫት ኳስ፣ የጠረጴዛ ኳስና የእጅ ኳስ ተብሎ ይከፈላል። እነዚህ የኳስ
ጨዋታ ዓይነቶች በቡድን አንዳንዴም በጥንድ የሚከናወኑ ናቸው። ለምሳሌ የእግር ኳስና የመረብ ኳስ በቡድን፣ የጠረጴዛ ኳስ ደግሞ
በጥንድ የሚከናወኑ ናቸው።
ኹለተኛው ዘመናዊ ስፖርት “ሩውዝ” ወይም አትሌቲክስ ነው። ከስያሜው እንደምንረዳው ይህ ዘርፍ ሩጫን፣ ውርወራንና ዝላይን
ያካትታል። ሩጫ በተለያዩ ርቀቶች ከትምህርትቤት ጀምሮ እስከዓለምአቀፍ የሚከናወን ነው። አገራችን ኢትዮጵያ በሩጫ ውድድር
ዓለምአቀፍ እውቅና አላት።
ሶስተኛው የአካል ብቃት እንቅስቃሴን፣ ክብደት ማንሳትንና ሌሎችን ያካትታል። ከጨዋታዎች ባህሪ አንጻር ከከተማ እስከገጠር
ታዋቂነት ባይኖራቸውም የቦክስ፣ የሜዳ ቴኒስና የጎልፍ ስፖርቶችም ዘመናዊ ናቸው። ከእነዚህ ሁሉ በተጨማሪ ዘመናዊ ስፖርት
በመኪና በሞተር ሳይክልና በተራ ባይስክል የሚደረጉ ውድድሮችንም ያካትታል።
ዘመናዊ ስፖርት ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ነው። ተጫዋቾቹ ብዙ ገንዘብ እየተከፈላቸው ለአንድ ቡድን ሲሰለፉ ማየት የተለመደ
ሆኗል። ተመልካቾች ገንዘብ ከፍለው ስታዲየም በመግባት ጨዋታውን መመልከት ያስደስታቸዋል። አንዳንድ ሰዎች ጨዋታውን
ከሚታደሙት ሰዎች በሚሰበሰበው ገንዘብ የዓለም ቱጃር ለመሆን በቅተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ጨዋታውን በቴሌቪዝን
ለሚመለከቱ ግለሰቦች የውርርድ ትኬቶችንም በመሸጥ ገቢ የሚሰበስቡ ድርጅቶችም እየበዙ መጥተዋል። በዚህ የተነሳ የኳስ ጨዋታ
በተለይ የእግር ኳስ ጨዋታ የቁማርተኞች መፈልፈያ እየሆነ ነው።
(ምንጭ፡- አራተኛ ክፍል አማርኛ እንደአፍመፍቻ ቋንቋ የመምህር መምሪያ (2006) ተሻሽሎ የተወሰደ።)
ቅድመንባብ (2 ደቂቃ)
(መ. ታሪኩን ከማንበባቸው በፊት በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ መመሪያ ይስጡ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ያደርጋሉ።]
ድኅረንባብ (8 ደቂቃ)
(መ. በታሪኩ መሠረት የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን እንዲያሟሉ ያድርጉ፤ ቀድመው ለሚጨርሱ ጎበዝ ተማሪዎች ተጨማሪ ጥያቄ
እንዲሰሩ ይጠይቋቸው።)
[ተ. በታሪኩ መሠረት የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን አሟልተው ይጽፋሉ።]
ስፖርት ለጤንነት
ሰው በአካሉ ገዝፎ እንዳያጣ ጤና፣
ጥንካሬን አጥቶ ሰርቶ እንዳይዝናና፣
በሽተኛ እንዳይሆን ታስሮ በስንፍና፣
ስፖርት ጠቃሚ ነው ለሰው ህልውና።
ያለልክ መጠጣት እንዳገኙ መብላት፣
ስራን ቸል ብሎ እንደልብ መተኛት፣
ጤናን ያጎድላሉ ያመጣሉ ጉዳት፣
ለእኒህ ሁሉ ጠንቆች መድሃኒት ነው ስፖርት።
ስፖርት ለጤንነት በእጅጉ ይጠቅማል፣
ለአካል ጥንካሬም በጣም ያስፈልጋል፣
ጠንካራ ድልድይ ነው ሁሉን ያገናኛል፣
በፍቅር አስተሳስሮ አንድነት ይፈጥራል።
ደስተኛ እንዲሆን አካሉ በርትቶ፣
ጤናው ተጠብቆ ህሊናው ረክቶ፣
ስራውን ከውኖ ሂወቱ እንዲሰምር፣
ልጅ አዋቂ ሳይል ስፖርትን ያዘውትር።
ቅድመማዳመጥ (2 ደቂቃ)
(መ. በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ከመምህር ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ።]
ድኅረማዳመጥ (8 ደቂቃ)
(መ. ባዳመጡት ግጥም መሠረት ጥያቄዎቹን በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ።)
[ተ. የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ይወያያሉ።]
(መ. “ስፖርት ለጤንነት” የሚለውን ግጥም በድጋሚ ያንብቡላቸው ፤ በመቀጠል በግጥሙ መሠረት የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎችን
እንዲመልሱ ያድርጉ።)
[ተ. የግጥሙን ታሪክ መምህር በድጋሚ ሲያነቡ በጥሞና አዳምጠው የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ።]
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ከአካል ብቃት መጎልበት ባለፈ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ሩጫ፣ የእግር ጉዞ፣ ዋና፣ ክብደት ማንሳትን ጨምሮ ልዩልዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የሚከተሉትን የጤና
ጠቀሜታዎች ያስገኛል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰውነት የጭንቀትና የድብርት ስሜትን ለማስወገድ የሚያግዘውን ሆርሞን እንዲያመነጭ ይረዳዋል።
የዚህ ሆርሞን መኖር ደግሞ የደስተኝነት ስሜትና ቀና አስተሳሰብ እንዲኖር ያደርጋል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጡንቻዎችን
ለማፈርጠም፣ አጥንትን ለማጠንከርና አቅምን ለማሳደግ ያስችላል። ባለሙያዎች እንደሚሉት ለስድስት ተከታታይ ሳምንት
የሚሰራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰዎች በከፍተኛ ድካም እንዳይጠቁ ያደርጋል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ በበሽታ የመያዝ እድልን እንደሚጨምር ባለሙያዎች ይገልጻሉ። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
በደም ውስጥ ያለውን የስብ ክምችት እንዲሟሟ በማድረግ ለደም ግፊት የመጋለጥ እድልን እንደሚቀንስ ያስረዳሉ። አዘውትሮ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ወደ አንጎል የሚሄደውን የደም ፍሰት በማስተካከል ለአዕምሮ ጤና ደህንነት ይረዳል። ከዚህ
ባለፈም ለአዕምሮ እድገት የሚረዱ ሆርሞኖችን በማመንጨት ለጤናማ የአዕምሮ እድገትና የማስታወስ ችሎታን ለማዳበር
ይጠቅማል።
በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በራስ የመተማመን ስሜት ለማዳበር እንደሚረዳ ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ። ይህም
ሰውነት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት አዎንታዊ አስተሳሰብ እንዲዳብር የሚረዱ አዳዲስ ህዋሶችን ከማመንጨቱ ጋር የተያያዘ
መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ምንጭ፦ healthline.com
ድኅረማዳመጥ (8 ደቂቃ)
(መ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን በቃላቸው እንዲመልሱ ያድርጉ። ግብረመልስ ይስጧቸው)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን በቃላቸው ይመልሳሉ።]
የምዕራፉ ዓላማዎች
ከዚህ ምዕራፍ ትምህርት በኋላ ተማሪዎች፡-
መደበኛ ባልሆነ መቼት ውስጥ በሚቀርብ ሚና ጨዋታ ድርሻ ወስደው ይጫወታሉ፤
የጽሁፉን ሐሳብ በዝርዝር አንብበው ያብራራሉ፤
የተሟላ አረፍተነገር በራስ ይፅፋሉ፤
ተውሳከ ግሶችን ተጠቅመው ዐረፍተነገሮችን ይመሠርታሉ፤
ስለውኃ የሚያትቱ መዝሙሮችን ይዘምራሉ፤
በተሰጣቸው ርዕሰጉዳይ ላይ ይከራከራሉ፤
የተሰጧቸውን ግሶች ተጠቅመው የተሟላ አረፍተነገር ይፅፋሉ።
የዉኃ ህክምና
ዉኃ በፈሳሽ፣ በበረዶና በጋዝ መልኩ የተለያዩ ጠቀሜታዎችን ይሰጣል። ቀዝቃዛ፣ ሙቅና ፍል ዉኃም አገልግሎቱ ለየቅል ነው። ዉኃን
መጠጣት የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል። ለምሳሌ ዉኃ በመጠጣት የኩላሊት፣ የጨጓራ፣ የፊኛ፣ የአንጀትና
የጣፊያ በሽታዎችን ወዘተ ማስወገድ ይቻላል።
ሁልጊዜ ጠዋት ቁርስ ከመመገባችን በፊት ከዐምስት ብርጭቆ ያላነሰ ዉኃ ብንጠጣ ለተለያዩ ውስጣዊ የጤና ችግሮቻችን መፍትሄ
እናገኛለን። ዉኃ በተፈጥሮው የአሲድነት ፀባይ የሌለው በመሆኑ ለሰውነታችን ውስጣዊ ኡደት መቀላጠፍ የሚሰጠው ጠቀሜታ
ከፍተኛ ነው። በአግባቡ ሳይታኘኩ ወደ አንጀታችን የሚገቡ ምግቦች በቀላሉ እንዲብላሉና በጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ ረገድ
ዉኃ የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው።
በጣም የቀዘቀዘ ዉኃ ማይግሪን ለተባለው ራስ ምታት ፍቱን መድኀኒት ነው። ህመሙ በሚነሳበት ወቅት በጣም የቀዘቀዘ ዉኃን
ለዐምስት ደቂቃዎች ያህል አናት ላይ በመያዝ ህመሙን ማስታገስ ይቻላል። ቀዝቃዛ ዉኃ ለሌሎችም በሽታዎች ፍቱን መድኀኒት
ነው።
ዉኃ በሞቃትና በፍል መልኩ ጥቅም ላይ ሲውል ደግሞ ለመገጣጠሚያ ችግሮች፣ ለጉንፋን፣ ለብርድ፣ ለኢንፍሉዌንዛ ፈዋሽ መድኀኒት
ነው። ሞቅ ያለ ዉኃ ህመም በሚሰማን ቦታ ላይ ማፍሰስ (መነከር) ከህመም እፎይታን ሊያስገኝ ይችላል። በአደጋ (መውደቅ፣
መጋጨት) በሚደርስ ጉዳት ሳቢያ በሰውነታችን ላይ ለሚከሰት እብጠት፣ የጡንቻ መሸማቀቅ ወይም ውልቃት በረዶ ፈጣን ፈውስን
ያስገኛል።
በዉኃ ህክምና በመታገዝ ፈውስ ለማግኘት በምንሞክርበት ወቅት ያሉብንን የጤና ችግሮች በሚያባብስ መልኩ እንዳይሆንብን
ልንጠነቀቅ ይገባል። ቁስለት ባለባቸው የሰውነት አካላት ላይ ሙቅም ሆነ ቀዝቃዛ ዉኃ መጠቀም የለብንም። ስለሆነም በዉኃ ህክምና
ፈውስ ለማግኘት ስናስብ የጤና ባለሙያዎችን ማማከር ጠቃሚ ነው።
ቅድመማዳመጥ (5 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹ ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. ታሪኩን ከማዳመጣቸው በፊት በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹ ላይ ርስበርሳቸው ይወያያሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ርስበርስ እንዲወያዩና ዳራዊ እውቀታቸውን እንዲናገሩ ያድርጉ።)
[ተ. የቅድመንባብ ጥያቄዎቹን ተወያይተው ይመልሳሉ።]
ድኅረማዳመጥ (8 ደቂቃ)
(መ. ጥያቄዎቹን ባዳመጡት ምንባብ “እውነት” ወይም “ሀሰት” ብለው በቃላቸው እንዲመልሱ ያድርጉ፤ ለምን እውነት ለምን ሀሰት
እንዳሉ ለመልሳቸው ማብራሪያ እንዲያቀርቡ ይጠይቋቸው።)
[ተ. የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎቹን በቃላቸው እውነት ወይም ሀሰት ብለው በምክንያት ይመልሳሉ።]
መፍትሔ
መንስኤ ችግር
ሊመታው ብሎ ራርቶ ተወው፣
የልጁ ዉሃ መርጨት የአባትዬው መናደድ፤ መበሳጨት
ልጅም ይቅርታ ጠየቀ።
ዉኃና ጥቅሙ
ህይወት ያለው ፍጡር ሁሉ ለመኖሩ ከሚያስፈልጉት ነገሮች መካከል አየርና ዉኃ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። እፅዋትና እንሰሳት
ያለ ዉኃ መቆየት አይችሉም። ለዚህም ነው “ዉኃ ህይወት ነው” የሚባለው።
ዉኃ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት። ከሰውነታችን ክብደት ውስጥ 60 በመቶ የሚሆነው ዉኃ ነው። ደማችንም 90 በመቶ
ዉኃ ነው። ህዋሶቻችን፣ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችንና ጡንቻዎቻችን ተግባራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ በቂ ዉኃ
ያስፈልጋቸዋል። የሰውነታችን የሙቀት መጠን እንዲመጣጠን ዉኃ ትልቅ ጠቀሜታ አለው። ምክንያቱም ሰውነታችን በትንፋሽ፣
በሽንትና በላብ በርካታ ዉኃ ያስወጣል። ይህን ዉኃ የምንተካው ፈሳሽነት ያላቸውን ምግቦች በመውሰድና ዉኃ በመጠጣት ነው።
ዉኃ የምግብ አፈጫጨት ሥርዓትን ለመጠበቅ የሚያስችል ንጥረ ነገር ነው። የተመገብናቸው ምግቦች እንዲሰባበሩና ማዕድናትና
ንጥረነገሮች እንዲሟሙ የሚያደርገው ዉኃ ነው። ቆሻሻና አላስፈላጊ ነገሮች ከሰውነታችን ውስጥ እንዲወገዱም ያደርጋል።
ሰውነታችን በላብና በሽንት አማካይነት የቆሻሻ ቅንጣቶች እንዲወገዱ የሚያደርገው በዉኃ አማካይነት ነው።
የሰውነታችንን ንጽህና ልንጠብቅ የምንችለው በዉኃ ብቻ ነው። ልብሳችንና ገላችን ሲቆሽሽ በማጽዳት ከተለያዩ በሽታዎችና
መጥፎ ጠረን የምንላቀቀው በዉኃ ነው። ምግብ ለማዘጋጀትም ዉኃ በጣም አስፈላጊ ነው። አብዛኛዎቹ ምግቦቻችን ያለዉኃ
የማይዘጋጁ መሆናቸው የዉኃን ጠቀሜታ ከፍ ያደርገዋል።
አምርተን ልንበላ፣ አጭደን ልንቅም የምንችለው አዝርዕቶቹ በቂ ዉኃ ሲያገኙ ብቻ ነው። አዝርዕቶች ለምልመው፣ አብበው፣
አሽተውና ጎምርተው ፍሬ እንዲሰጡ ዉኃ ይፈልጋሉ። የሚያድጉትና የሚለመልሙት በዉኃ ነው። ያለ ዉኃ ከእጽዋትና ከእንስሳት
ምርት ማግኘት ከቶውንም አይቻልም።
ከእነዚህ ጠቀሜዎች በተጨማሪ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ለአሳ ምርትና ለመዝናኛነት ትልቅ ጠቀሜታ አለው።
ስለሆነው ዉኃን በአግባቡ ማስተዳደርና መጠቀም አስፈላጊ ነው። በቤታችን ያለውን የቧንቧ ዉኃ፣ በአካባቢያችን የሚገኙ
ምንጮችን፣ ሀይቆችን፣ ወንዞችንና ባህሮችን በአግባቡ በመንከባከብ ልጠቀምባቸው ይገባል።
(ምንጭ፤ ሄልዝ ላይን ዶት ኮም፣ (መጋቢት 19፣1019) ማሻሻያ ሆኖ የተወሰደ።)
ቅድመማዳመጥ (5 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. የቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹን ተወያይተው ይመልሳሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. ታሪኩን ከማንበባቸው በፊት በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ውይይት ያደርጋሉ።]
ድኅረማዳመጥ (8 ደቂቃ)
(መ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎችን ባዳመጡት ምንባብ መሠረት በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ
ሊሰጧቸው ይችላሉ።)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
ድኅረንባብ (8 ደቂቃ)
(መ. ያነበቡትን ታሪክ መሠረት አድርገው ጥያቄዎቹን በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ።)
[ተ. የድኅረንባብ ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
የቤት ሥራ
የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ። ባለፈው ሳምንት የአካባቢ ሳይንስ መምህራችን የቤት ስራ ሰጥተውናል። “የዉኃ መገኛዎች ምን ምን
ናቸው?” ይላል የቤት ስራው። እኔ የተወሰነ ሞክሬዋለሁ። ግን ታላላቆቻችሁን ጠይቃችሁ እንድትመጡ ስለተባልን እማዬን ለመጠየቅ
ፈለግሁ።
እማዬ በወረዳችን የዉኃ ጽህፈትቤት ውስጥ ባለሙያ ናት። ስለዉኃ በቂ ግንዛቤ እንዳላት አምናለሁ። ስለሆነም “እማዬ!” አልኳት።
“አቤት” አለችኝ። “አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ” አልኳት። “ምን ዓይነት ጥያቄ ነው?” አለችኝ። “የቤት ስራ የተሰጠሁት ነው” አልኳት።
እርሷም በራስ መተማመን ስሜት “ጠይቀኝ” አለችኝ። ጥያቄውን አነበብኩላት። ቀላል ጥያቄ እንደጠየኳት ገብቶኛል። “ይህንማ ራስህ
አትሰራውም እንዴ?” አለችኝ። እኔም “ሞክሬዋለሁ ግን ሰፋ ያለ ማብራሪያ ለማግኘት ስለፈለግሁ ነው” አልኳት።
“ዉኃ ከምን ከምን ይገኛል አይደል ያልከኝ?” በማለት ጠየቀችኝ። “አዎ!” አልኳት። “ዉኃ በተለያዩ መንገዶች ልናገኝ እንችላለን።
ከምንጭ፣ ከጉድጓድ፣ ከዝናብ፣ ከወንዝ፣ ከባህር፣ ከሃይቅና ከውቅያኖስ እናገኛለን” አለችኝ። እኔም “እሽ እማዬ አመሰግናለሁ! ከዝናብ
ዉኃ እንዴት ልናገኝ እንደምንችል ልታብራሪልኝ ትችያለሽ?” አልኳት። እማዬ ጊዜ ሳታባክን ማብራሪያዋን ቀጠለች። “ዉኃ ከእፅዋትና
ከሌሎች ዉኃማ አካላት በፀሐይ ሙቀት አማካይነት ይተናል። በትነት መልክ የወጣው ዉኃ ሞቃትና ቀላል ስለሆነ ወደከፍተኛ ቦታ
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹ ላይ ከተማሪዎችጋር ይወያዩ። ጥያቄዎቹ የተማሪዎቹን የቀደመዕውቀት ለመቀስቀስ የቀረቡ
ስለሆኑ እርስዎ መልስ አይስጡ።)
[ተ. ታሪኩን ከማንበባቸው በፊት በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹ ላይ ከመምህር ጋር ይወያያሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸውጋር እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር ውይይት ያደርጋሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. በተሰጡት ቃላት ላይ -ኦች ወይም -ዎች ቅጥያዎችን በመጨመር ወደ ብዙ ቁጥር እንዲቀይሩ ያድርጉ፤ በሳድስ በሚጨርሱት
ቃላት ላይ /-ኦች/፣ በአናባቢ በሚጨርሱ ቃላት ላይ ደግሞ /-ዎች/ እንደሚጨመር ልብ ይበሉ።)
[ተ. በቃላት ላይ -ኦች ወይም -ዎች በመጨመር ወደብዙ ቁጥር ይቀይራሉ።]
ድኅረማዳመጥ (7 ደቂቃ)
(መ. የዝናብ ውኃ አፈጣጠር ዑደትን የሚያሳይ የቢጋር ሠንጠረዥ በደብተራቸው ሠርተው እንዲያሟሉ ያድርጉ።)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
ድኅረንባብ (8 ደቂቃ)
(መ. የድኅረንባብ ጥያቄዎቹን “ጥቁር እንግዳ” በሚለው ታሪክ መሠረት በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ፤ እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ
ይስጡ።)
[ተ. የድኅረንባብ ጥያቄዎቹን በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
መጻፍ (5 ደቂቃ)
(መ. ሥርዓተነጥቦች ተጠቅመው ዓረፍተነገር እንዲመሠርቱ ያድርጉ። ምሳሌዎችን በመስጠት የቀረበውን የሥርዓተነጥብ ማስታወሻ
ያብራሩላቸው።)
[ተ. ሥርዓተነጥቦችን በዓረፍተነገሮቹ ውስጥ በተገቢ ቦታ በማስገባት ዓረፍተነገር ይመሠርታሉ።]
የምዕራፉ ዓላማዎች
በብዙዎች ዘንድ ፊት ተነስቶት የነበረና በሂደት ግን ፍቱን አዋጭነቱ እየታመነበት የመጣ ነው- ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት።
እንዲጐለብቱ ከሚፈለጉት ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶቻችን አንዱ የአባጋር የእርቅ ሥርዓት ነው። “እምባ የሚደርቀዉ በፍርድ
ሳይሆን በፍቅር ነው” ይላሉ የአባጋር ሥርዓት ተከታይ አባቶች። አባጋር በአንባሰል ወረዳ የሚዘወተር ቢሆንም በሌሎች የደቡብና
የሰሜን ወሎ አካባቢዎችም ተግባራዊ የሚደረግ የግጭት አፈታት ሥርዓት ነው።
አባጋር ማለት በአካባቢው አጠራር የተጣላ የሚታረቅበትና አጥፊው በሀገር ሽማግሌዎች ፊት “ተው” የሚባልበት ሥርዓት ነው።
ዱአ አድርገው ከተጣሉት ሰዎች መካከል ጥልን የሚያባርሩበት ሰርዓት ነው። አባጋር የሚለው ቃል በቃል ሲተረጐም ደግሞ የሀገር
ራስ፣ መሪ፣ አስታራቂ የሚል ፍቺ አለው።
የአባጋር የእርቅ ሥርዓት ከሃይማኖትና በባህል ጋር የተሳሰረ ነው። በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች በተለያዩ አለመግባባቶች ቅራኔ ውስጥ
ይገባሉ። ወይም ነብስ ሊያጠፉ ይችላሉ። በዚህ ወቅት የአካባቢው ሽማግሌዎችና ኗሪዎች እርቅ እንዲመጣ ከሳምንት እስከ አንድ ወር
ድረስ ፈጣሪያቸውን እየተለማመኑ የሚያካሂዱት ሥርዓት ነዉ። የአባጋር ሥርዓት ሲከናወን አንድ ገዳይ ሰው ገድሎ ከጠፋ የገዳይ
ቤተሰቦች ከሟች ቤተሰቦች ጋር አስታርቁን ብለው በአባጋር ቦታ ይቀመጣሉ። እርቁ ካልተፈፀመ በስተቀር የገዳዩ ቤተሰቦች ከዚያ
ቦታ አይነሱም።
በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ይስማ ንጉሥ አካባቢ የሚገኙ አባጋሮች የእርቅ ሥርዓት በእስልምና እምነት ተከታዮች የሚካሄድ
ነው። በደሴ ዙሪያ አንዳንድ አካባቢዎችም በክርስትና እምነት ተከታዮች የሚከናወን የአባጋር ሥርዓት ይገኛል።
የአባጋር ሥርአት ሲከናወን ገዳይ ወይም የተገደለበት ቤተሰብ የተለያዩ እምነት ተከታይ ቢሆኑም ሁሉም በአባጋር ሥርአት ይገዛሉ።
ምክንያቱም ሁሉም የሀገር ወግና ደንብ ባህል ስለሆነ በአባጋር አማካኝነት እርቁ ይካሄዳል። የክርስትና እምነት ተከታይ ቢሆንም
መስቀል ይዘዉ አብረውት ካህናት በተገኙበት እርቁ እንዲካሄድ ይደረጋል። ይህም ሁለቱም እምነቶች በመከባበርና በመቻቻል
አብረው መኖራቸውን ያሳያል።
(ቱር ኢን ኢትዮጵያ። ሚያዘያ 1 2019። ከሚል ድረገጽ ከፊል ማሻሻያ ተደርጎበት የተወሰደ)
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመ ማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ከተማሪዎች ጋር ይወያዩ።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ያደርጋሉ።]
ቅድመንባብ (5 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ። )
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ።]
ቃላት (7 ደቂቃ)
(መ. የተሰጡትን ሐረጋት በታሪኩ መሠረት አውዳዊ ፍቺ እንዲኖራቸው አድርገው ዓረፍተነገር እንዲሰሩ ያድርጉ።
[ተ. በአባጋር ሽምግልና የተጎጂ ቤተሰቦችን እንባ ማድረቅ ይቻላል። “ማጽናናት፣ መካስ” የሚል ፍቺ ያለው ሲሆን ይህን ፍቺ
ያስገኘው የተጎጂ ቤተሰቦች የሚለው ነው።]
ድኅረማዳመጥ (7 ደቂቃ)
(መ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹ በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ።)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
ድኅረንባብ (8 ደቂቃ)
(መ. የድኅረንባብ ጥያቄዎችን ትክክለኛ መልስ በመምረጥ እንዲመልሱ ያድርጉ። ለመልሳቸው ማብራሪያ ይጠይቁ።)
[ተ. የድኅረንባብ ጥያቄዎቹን በመምረጥ ይመልሳሉ።]
ማስታወሻ
ተማሪዎችን በቡድን አደራጅተው ለሚቀጥለው ቀን እንደሽማግሌና እንደታራቂዎች ሆነው አጭር ድራማ አዘጋጅተው እንዲመጡ
የቤት ሥራ ይስጧቸው።
(መ. ዓረፍተነገሮቹን በቅንፍ ውስጥ ካሉት ቃላት ትክክለኛውን እየመረጡ እንዲያሟሉ ያድርጉ።
[መልስ ሀ. [ተ. ጠርቶ] ለ. [ተ. አሳውቆ] ሐ. [ተ. ወድቀው] መ. [ተ. እያስታወሱ]
ሽምግልና ኹለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች አማካይነት የሚከናወን ጥላቻን አርቆ ፍቅርንና ይቅርታን በልብ ውስጥ ለመዝራት
የሚፈጸም ባህላዊ የእርቅ ሥርዓት ነው። ኢትዮጵያውያን ለሽምግልና ትልቅ ክብር ይሰጣሉ። በሽምግልና ያምናሉ፤ ችግሮቻቸውን
በሽምግልና ይፈታሉ። ቂምና ቁርሾ ሁሉ የሚሽረው በሽምግልና ስለመሆኑ ጽኑ እምነት አላቸው።
በአገራችን ሽምግልና ካለው ክብርና ተቀባይነት አንጻር “ሰማይ ቢቀደድ ሽማግሌ ይሰፋዋል” ይባላል። በባህላችን ከሽምግልና
የሚያመልጥ ነገር እንደሌለ ይታመናል። እንዲያውም ሽምግልና አመጣጡ ከሰው ልጅ አብሮነት ጋር እንደሆነም ይገለጻል። ሰው
ከሰው ጋር አብሮ ሲኖር ግጭት ይፈጠራል። እናም ያ ግጭት እየከረረ ሄዶ ቂምና ቁርሾ እንዳይያዝበትና አደጋ እንዳያስከትል
የሽምግልና ሚና ላቅ ያለ ነው። ሽምግልና የሰው ነፍስ እንዳይጠፋ፣ ሰላም እንዲሰፍንና አንድነት እንዲጠናከር ያደርጋል። በሽምግልና
ሥርዓት የተፈጸሙ ወንጀሎች ይጣራሉ፣ አጥፊውና የበደሉ መጠን ይለያል። በዳይና ተበዳይ ከተለዩ በኋላ ለበደሉ ካሳ ይጣላል።
በመጨረሻም “አንተም ተው፣ አንተም ተው” በሚል የተጣሉ እንዲታረቁ ይደረጋል። በዚህ መልኩ ደም የተቃቡ ሰዎችም ሳይቀሩ
እርቅ እንዲያወርዱ ሽምግልና ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
ሽምግልና በግጭት ምክንያት የተጣላን ሁሉ የማስማማት ጉዳይ ነው። ስለሆነም እንዲያሸማግሉ የሚመረጡ ሰዎች በእድሜ ከፍ ያሉ
ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች መስፈርቶችንም የሚያሟሉ ሊሆኑ ይገባል። በማህበረሰቡ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው፣ የሚፈሩ፣ የሚደመጡና
የሚታፈሩ ሊሆኑ ይገባል። ተናግረው የሚያሳምኑ፣ አንደበተርቱዕና ነገር አዋቂ መሆንም ይጠበቅባቸዋል። የመምከርና የመመረቅ ፀጋ
የተሰጣቸው እንዲሆኑም ይፈለጋል። ሽማግሌዎቹ እነዚህ ችሎታዎች ያሏቸው ከሆኑ ተሸማጋዮቹ ጊዜ ሳይወስዱ እርቁን ይቀበሉታል፤
ይቅርታቸውም ከልብ ይሆናል።
(ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሰኔ 14/2012 ማሻሻያ ተደርጎ የተወሰደ)
ቅድመማዳመጥ (4 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ ያድርጉ። አይነስውራን ተማሪዎች ካሉ ስለስዕሉ ጓደኞቻቸው
እንዲገልፁላቸው ያድርጉ ወይም ርስዎ ይግለፁላቸው። ከዚያም ግምታቸውን ሊጠይቋቸው ይችላሉ።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹ ላይ ርስበርሳቸው ይወያያሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር ይወያያሉ።]
ቃላት (7 ደቂቃ)
(መ. በምሳሌው መሠረት የቃላቱን ዋናቃልና ቅጥያዎች ነጣጥለው እንዲያወጡ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ ይስጧቸው።)
[ተ. ቅጥያዎቹን ከዋናው ቃል ላይ ለያይተው ይጽፋሉ።]
ድኅረማዳመጥ (8 ደቂቃ)
(መ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎችን ባዳመጡት ምንባብ መሠረት በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ)።
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
ድኅረንባብ (8 ደቂቃ)
(መ. የድኅረንባብ ጥያቄዎችን ባነበቡት ታሪክ መሠረት በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ መመሪያ ይስጡ።)
መልስ፡- ሀ. [ተ. ቆላ አካባቢ ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ታሪኩ ፍየል ብቻ ያለበትና በግ የሌለበት ስለሚል።]
ለ. [ተ. ቀደም ባሉት ዘመናት ነው፤ ምናልባትም በ1990ዎቹ ሳይሆን አይቀርም)
ገንዘብ ለህፃናት
ቡሬ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ። ለረጅም ዓመታት በፍቅርና በመተሳሰብ ይኖሩ ነበር። አራት ልጆችን አፍርተዋል።
ሁለቱ ወንዶች ናቸው። የመጀመሪያ ልጃቸው ገና ስምንት ዓመቱ ነው። በልጆች አስተዳደግ ላይ የተለያዩ አቋሞች በመያዛቸው
ሳቢያ በባልና በሚስት መካከል አልፎ አልፎ አለመግባባቶች ይፈጠሩ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን ለልጆች ብር መስጠት ችግር አለው ችግር የለውም በሚል ክርክር ይጀምራሉ። ሚስት ለልጆች የሚያፈልጋቸውን
ነገር በቤት ውስጥ አዘጋጅተው ወይም ራሳቸው ወላጆች ገዝተው መስጠት እንዳለባቸው እንጅ ብር ሊሰጧቸው እንደማይገባ
ትገልፃለች። ባል ደግሞ ልጆቻቸው ቤት ውስጥ የማያገኙትን ነገር ገዝተው እንዲበሉ ብር ቢሰጣቸው ችግር እንደማይኖርና
ልጆቻቸውም እንደሚደሰቱ ይገልፅላታል። በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋም በመወያየት መፍታት እንዳለባቸው ተገነዘቡ።
ታዲያ ሁለቱም ሌላ ጊዜ እንደሚያደርጉት ሁሉ አሳማኝ የሚሏቸውን ሐሳቦች እያቀረቡ መወያየት ጀመሩ። “ልጆቻችን ለጋ
ናቸው። ስለሆነም ለከረሚላ፣ ለዳቦ፣ ለብስኩት፣ ለሙዝ፣ ለብርቱካን ወዘተ እያልን ብር ልንሰጣቸው አይገባም” ስትል ሚስት
ሀሳቧን ገለፀች። ባልም የሚስቱ ሐሳብ የተዋጠለት አይመስልም። ጉሮሮውን እህህም ብሎ ካፀዳ በኋላ “ምን ችግር አለው? ገዝተው
እንዲበሉ ማድረግ ጉዳቱ ምኑ ላይ ነው? ልጆቻችንን እያስደሰትን ማሳደግ አይጠበቅብንም ትያለሽ?” ሲል መልሶ ጠየቃት።
እናትም ማብራሪያ ለመስጠት የሚያስችላትን እድል ስላገኘች ንግግሯን በደስታ ቀጠለች። “የልጆችን ፍላጎት ማሟላትና እንዲደሰቱ
ማድረግ እንደሚገባ አምናለሁ። ልጆቻችን ክፉና ደጉን አልለዩም። ስለሆነም ከፍ እስኪሉ ድረስ የሚያስፈልጋቸውን ራሳችን
እየገዛን ልንሰጣቸው ይገባል። ብር ከለመዱ የተቀመጠ ገንዘብ ማንሳት ይጀምራሉ። ልጆችን ሥርዓት ማስያዝ የምንችለው
ደግሞ እኛው ራሳችን ነን። ለመግዛት ወደሱቅ ሲሄዱስ ቢሆን በመኪና ቢገጩብን ወይም በሌቦች ታፍነው ቢሰረቁብን ማነው
የሚጎዳው?” ስትል ንግግሯን በጥያቄ ቋጨችው። አባት በዚህ መንገድ አስቦት ስለማያውቅ በሚስቱ ብልህነትና አስተዋይነት
በጣም እየተገረመ በሀሳቧ ተስማማ። ለልጆቹ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ራሱ እየገዛ ያመጣላቸው ጀመር።
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. ታሪኩን ከማዳመጣቸው በፊት በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ።]
ቅድመንባብ (2 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከጓኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ያደርጋሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. በምሳሌው መሠረት ዋና ቃሉንና ቅጥያውን በማጣመር አዲስ ቃል እንዲመሠርቱ ያድርጉ።)
[ተ. ዋና ቃሉንና ቅጥያውን በማጣመር አዲስ ቃል ይመሠርታሉ።]
የምዕራፉ ዓላማዎች
ከዚህ ምዕራፍ ትምህርት በኋላ ተማሪዎች፡-
የተቀረፁ ንግግሮችን አዳምጠው ዋናውን ሐሳብ ይናገራሉ፤
አንድ ጽሑፍ አንብበው የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን ይሠራሉ፤
ነጠላ ዓረፍተነገሮችን በመጠቀም አንቀፅ ይፅፋሉ፤
ቃላትን በገቡበት አውድ ይበይናሉ፤
መስተዋድዶችን ተጠቅመው ዓረፍተነገሮችን ይመሠርታሉ።
የመጀመሪያው ጋዜጣ
አዕምሮ በአማርኛ ቋንቋ ይታተም የነበረ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጋዜጣ ነው። አዕምሮ የተመሰረተው በግሪካዊው አንድርያ ካቫዲያ
እ.አ.አ በ1902 ዓ.ም. ነበር። እ.አ.አ. ከ1906-07 ዓ.ም. ይታተም የነበረው ጋዜጣ ባለሦስት ገጽ ዜናንና ባለአንድ ገጽ ማስታወቂያን
ያካተተ ነበር። ዜናው በአውሮፓ ስላለ ጦርነት፣ ስለመሪዎች ጉብኝት እንዲሁም በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ስለተደረጉ
ስምምነቶች የሚያትት ነበር። በሀገር ውስጥ የንጉሱ የስራ እንቅስቃሴ፣ ንግግሮች፣ አዋጆች፣ በከተማው ውስጥ የተከሰቱ አዳዲስ
ጉዳዮች እንዲሁም ለአሳታሚው የሚላኩ ደብዳቤዎች ይዳሰሱ ነበር።
እ.አ.አ.1924 እስከ 1935 ዓ.ም. በነበረው እትም ጋዜጣው በዋነኛነት በወቅቱ የዓለም ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር። የወቅቱ የአውሮፓ
ሀገራት ግንኙነት፣ የውጭ ዜናና ፖለቲካ፣ በተለይ የኃይል አሰላለፍና የኃይል ሚዛንን የተመለከቱ ጉዳዮች በሰፊው በአዕምሮ ጋዜጣ
ይተነተኑ ነበር።
ëëë እስካሁን ካደመጣችሁት ምንባብ ምን ተረዳችሁ? ëëë
የአዕምሮ ጋዜጣ አብዛኞቹ ጽሁፎች የኢትዮጵያን አንድነት የሚሰብኩና የዘር ልዩነትንም የሚያወግዙ ነበሩ። በተለይ የኢትዮጵያ
አንድነት የተሻለ ትምህርት ለማግኘት፣ ለስልጣኔና ለዘመናዊ የኑሮ ዘይቤ ያለውን ሚና አጉልተው የሚያሣዩ ነበሩ። እ.አ.አ ከ1935
ዓ.ም. ጀምሮ በአዕምሮ ጋዜጣ ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር የነበራትን ምኞት የሚያጋልጡ ጽሁፎች መታተም ጀመሩ።
አዕምሮ ጋዜጣ በመጀመሪያ በእጅ ይፃፍ ስለነበር የሥርጭት መጠኑ 24 ቅጅዎች ብቻ ነበር። እ.አ.አ. በ1929 ዓ.ም የማባዣ ማሽን
ከተገኘ በኋላ ወደ 200 ኮፒ ደርሶ እንደነበር የታሪክ ተመራማሪዎች ይገልፃሉ።
(ምንጭ፤@Team Sewasew 2021)
ድኅረማዳመጥ (6 ደቂቃ)
(መ. የተከናወኑትን ተግባራት ከዓመተምህረቶቹ ጋር እንዲያዛምዱ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ ታሪኩን ይድገሙላቸው።)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን እያዛመዱ ይሠራሉ።]
ቅድመንባብ (2 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ያደርጋሉ።]
ድኅረማዳመጥ (8 ደቂቃ)
(መ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን ባዳመጡት ታሪክ መሠረት በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ።)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
ጠያቂዋ ተማሪ የአራተኛ ክፍል ተማሪ ናት። በትምህርቷ ጎበዝ ስትሆን በስነምግባሯም የተመሰገነች ናት። ብዙ ጊዜ መጠየቅ
ትወዳለች። ዛሬ ደግሞ አባቷ ስለብዙሃን መገናኛ ምንነት እንዲነግሯት ፈልጋለች። አባቷ ስራ ውለው ሲመጡ ማስታወሻዋን ይዛ
ወደአባቷ ተጠጋች። ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ጥያቄ ልትጠይቃቸው እንደፈለገች ገለፀችላቸው። አባቷም ፈቃደኛነታቸውን
በፈገግታ አጅበው ገለፁላት።
አባቷም “አዎ! ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ጋዜጣ፣ መፅሔት ወዘተ ሁሉ የብዙሃን መገናኛ መንገዶች ናቸው” አሏት።
ጠያቂዋ ተማሪ “በዓለማችን ምን ያህል የሬዲዮና የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያዎች አሉ? በኢትዮጵያስ?” ስትል ጠየቀቻቸው።
አባቷም ትንሽ አሰቡና “አይ ልጄ! በጣም ብዙ ናቸው። ለቁጥር የሚያታክቱ ናቸው። አገራችን ኢትዮጵያ አጥጋቢ ባይሆኑም ጥቂት
የሬዲዮና የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያዎች አሏት። በእነዚህም የተለያዩ መርሃግብሮች ይተላለፉባቸዋል።” በማለት ገለፁላት።
ጠያቂዋ ተማሪ አንገቷን ቀለስ አድርጋ “እሽ አባዬ በዓለማችን ስለሚኖሩ የመጽሔትና የጋዜጣ ብዛትስ የምታውቀው ይኖር ይሆን?”
በማለት ጠየቀቻቸው።
አባቷም “ይህን ያህል ብዬ ቁጥር አልነግርሽም። ግን አያሌ የመጽሔትና የጋዜጣ ህትመቶች በየቀኑ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወዘተ
እንደሚታተሙ በእርግጠኝነት አውቃለሁ። የውጩን ተይውና የአገር ውስጡን ብንመለከት እንኳ ጥቂት የማይባሉ ህትመቶችን
እናገኛለን። ጥራታቸውንና የመረጃዎቻቸውን ትክክለኛነት ርግጠኛ ባልሆንም በቁጥር ግን አናሳ አይደሉም። ይህን ስልሽ ግን በቁጥር
አስታውሶ ለመናገር እንጅ በአገር አቀፍ ደረጃ በቂ ናቸው ማለቴ አይደለም” አሏት።
ጠያቂዋ ተማሪም “ለአንድ አገር ምን ዓይነት መገናኛ ብዙሃን፣ በምን ያህል መጠን ያስፈልጋል?” ስትል ጠየቀቻቸው።
አባቷም “አንድ አገር የጠቀስኩልሽን ሁሉንም ዓይነት የብዙሃን መገናኛ መንገዶች ሊጠቀም ይገባዋል። ከተቻለ ብዙ የቴሌቪዥንና
የሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያዎች በርካታ የህትመት ውጤቶች ያስፈልጋሉ”
ጠያቂዋ ተማሪ የተሰጣትን ማብራሪያ በማስታወሻዋ ላይ መዝግባ ስትጨርስ “አባዬ በጣም አመሰግንሃለሁ” አለቻቸው።
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹ ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር ይወያያሉ።]
የማዳመጥሂደት (7 ደቂቃ)
(መ. ታሪኩን ረጋ ብለው ያንብቡላቸው፤ እንዳስፈላጊነቱ ይድገሙላቸው። ከማዳመጥሂደት ጥያቄው ላይ ሲደርሱ ማንበብን
ለአፍታ ያህል ገታ አድርገው ጥያቄውን ይጠይቋቸው፤ ወዲያው ንባብዎን ይቀጥሉ።)
[ተ. መምህር ታሪኩን ሲያነቡ በአስተውሎት ያዳምጣሉ። ማስታወሻ ይይዛሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከተማሪዎች ጋር ይወያዩ፤ እርስዎ የተማሪዎቹን ሐሳብ መቀበል እንጂ መልስ መስጠት
አይጠበቅብዎትም።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ከመምህራቸው ጋር ይወያያሉ።]
ድኅረማዳመጥ (8 ደቂቃ)
(መ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን በቃል እንዲመልሱ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ ይስጧቸው።)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን በቃል ይመልሳሉ።]
ድኅረንባብ (8 ደቂቃ)
(መ. የድኅረንባብ ጥያቄዎቹን በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ ይስጡ።)
[ተ. የድኅረንባብ ጥያቄዎቹን በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
ሀያትና ፀዳለ
ሀያትና ፀዳለ በአንዲት የገጠር ከተማ የሚኖሩ ጓደኛሞች ናቸው። የሚማሩት በአንድ ትምህርትቤት ውስጥ ነው። በእድሜም ሆነ
በክፍል ደረጃ አቻ ናቸው። ሁለቱም የመማር ፍላጎትና የማወቅ ጉጉት አላቸው። የቅርብ ጎረቤት ስለሆኑ በጋራ ሲያጠኑ ይውላሉ።
ርስበርስ ይጠያየቃሉ፤ በተለያዩ ጽንሰሐሳቦች ላይ ይከራከራሉ። በየትኛውም ርዕሰጉዳይ ላይ በቂ ግንዛቤ ሊኖራቸው እንደሚገባ
ያምናሉ። ስለሆነም በክፍል ደረጃቸው የቀረቡላቸውን ይዘቶች አንድ በአንድ ለማወቅ ጥረት ያደርጋሉ።
ወሩ ግንቦት ነው። በአራተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ዘጠነኛው ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል። የምዕራፉ ርዕስ “ብዙሃን መገናኛ”
ስለሚል በዚህ ላይ በቂ ግንዛቤ ለመያዝ ብዙ አንብበዋል፤ ሰዎችንም ጠይቀዋል። አሁን ደግሞ በነሀያት ቤት ውስጥ ሆነው እየተወያዩ
ነው። ድንገት ውይይታቸው ወደክርክር ተቀየረ። የመከራከሪያ ርዕሳቸውም “ከሬዲዮና ከቴሌቪዥን ለማህበረሰቡ የበለጠ ጠቃሚ
የትኛው ነው?” የሚል ነው።
ሀያት ቴሌቪዥን ከሬዲዮ የበለጠ ጠቃሚ ነው የሚል አቋም ይዛለች፤ ፀዳለ ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ ቆማለች። ሁለቱም ሲከራከሩ
የክርክር መመሪያ ይጠብቃሉ። አንዷ ስትናገር ሌላኛዋ ታዳምጣለች፤ እንጅ አይደራረቡም።
ሀያት ወደ ፀዳለ እያየች “ቴሌቪዥን ከሬዲዮ ይበልጥ የሚጠቅመው ድምፅን ከምስል ጋር አቀናጅቶ ስለሚያቀርብ ነው። በዚህም
ለአድማጭም ሆነ ለተመልካች ሊተላለፍ የተፈለገው መልዕክት ግልፅ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ሳቢነቱም ቢሆን ከፍተኛ ነው” አለች።
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ መመሪያ ይስጡ።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ያደርጋሉ።]
ቅድመንባብ (2 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. ዋናውን ቃልና ቅጥያዎቹን በማጣመር አዲስ ቃል እንዲመሠርቱ መመሪያ ይስጡ፤ እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ ይስጡ።)
[ተ. ዋናውን ቃልና ቅጥያዎቹን በማጣመር ቃል ይመሠርታሉ።]
ድኅረማዳመጥ (8 ደቂቃ)
(መ. ባዳመጡት ታሪክ መሠረት የሐሳብ ማደራጃ ቢጋር እንዲያሟሉ ያድርጉ።)
[ተ. የማዳመጥ ታሪኩን መሠረት አድርገው የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን ያሟላሉ።]
ድኅረንባብ (8 ደቂቃ)
(መ. የድህረንባብ ጥያቄዎች በቃላቸው እንዲመልሱ ያድርጉ፤ እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ ይስጡ)
[ተ. የድህረንባብ ጥያቄዎችን በቃላቸው ይመልሳሉ።]
የምዕራፉ ዓላማዎች
ሲራራ ነጋዴ
አያቴን በአካል አላውቃቸውም። ከመወለዴ በፊት ነው በዘጠና ዓመታቸው ያረፉት። በሀብት የተምነሸነሹ ሲራራ ነጋዴ እንደነበሩ
ሰምቻለሁ። የገንዘባቸውን ልክ፣ የሀብታቸውን መጠን አያውቁትም ነበር ይባላል። የሚኖሩት አንዳቤት ውስጥ ነበር። የንግድ
ሥራቸውን የሚያከናውኑት መኪና ስለማይገኝ በበቅሎ እየጫኑ ነበር። ታዲያ ወደአዲስአበባ የሚሄዱት ከአስራ ዐምስት ያላነሱ
በቅሎዎችን ይዘው ነበር። በተመሳሳይ ጓደኞቻቸውም እንዲሁ በቅሎዎችን ይዘው በአንድነት ይጓዙ ነበር። ከአሥር ቀናት አድካሚ
የእግር ጉዞ በኋላ አዲስ አበባ ይደርሱና የሚፈልጉትን መሸመት ይጀምራሉ።
ከአዲስ አበባ የሚመለሱት አንድ ወር ያህል ቆይተው ነው። በርካታዎቹ ቀናት ለጉዞ ይውላሉ፤ ጥቂቶቹን ደግሞ ተዘዋውሮ ለመሸመት
ያውሉታል። አያቴ አብዛኛውን ጊዜ አሞሌ ጨው፣ ዝሃና ሌሎች ሸቀጣ ሸቀጦችን ያመጣሉ። አያቴ የተመለሱ ቀን ቤተዘመዱ ሁሉ
“እንኳን በደህና ገባችሁ!” ለማለት ይሰበሰባል። በእድሜ የሚያንሱት የአያቴን ጉልበት በመሳም አክብሮታቸውን ይገልፁ ነበር።
ትልልቆቹን ደግሞ አያቴ ዝቅ ብለው ሰላምታ ይሰጧቸው ነበር። ታዲያ ይህን ስሰማ ያን ሁሉ ፍቅርና አክብሮት ወዴት ሰደድነው
እላለሁ።
አያቴ የእያንዳንዱን ሸቀጥ ዋጋ ዝርዝር ካሳወቁ በኋላ አባቴ እንዲሸጥ ያደርጉ ነበር። አባቴ ለአያቶቼ የመጀመሪያ ልጅ ስለሆነ ትልቅ
ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር። ሸቀጡን ይሸጣል፤ ገንዘቡን ለአባቱ ገቢ ያደርጋል። በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ ያለንብረት ይቆጣጠራል።
የራሱን ጎጆ እስኪቀልስ ድረስ በዚህ መልኩ ወላጆቹን ያገለግል ነበር። ይኸው እስከዛሬ ድረስ አባቴ የአደገበትን የንግድ ሥራ
ተከትሏል። በርካታ ሀብትና ንብረትም አፍርቷል። አንዳቤት ወረዳ ውስጥ ከሚኖሩ ስመጥር ሀብታሞች መካከል አንዱ ለመሆን
በቅቷል።
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. በድኅረማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎችን ተወያይተው ይመልሳሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ ያድርጉ፤ ሐሳባቸውንም ይቀበሉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. አብረው የሚሄዱ ቃላትን መርጠው እንዲያዛምዱ ያድርጉ። ምሳሌ ሠርተው ያሳዩአቸው።)
[ተ. አብረው የሚሄዱ ቃላትን ያዛምዳሉ።]
ድኅረማዳመጥ (5 ደቂቃ)
(መ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎችን በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ ይስጡ።)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎችን በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
ድኅረንባብ (5 ደቂቃ)
(መ. ጥያቄዎቹን ባነበቡት ታሪክ መሠረት “እውነት” ወይም “ሀሰት” በማለት እንዲመልሱ ያድርጉ፤ ለመልሳቸው ምክንያት
እንዲሰጡ ያድርጉ።)
[ተ. የድኅረንባብ ጥያቄዎችን እውነት ወይም ሀሰት በማለት በማስረጃ ይመልሳሉ።]
ህግና ንግድ
የንግድ ሥራ ለመሥራት የንግድ ፈቃድ ማውጣት የአስፈላጊ ነው። የንግድ ፈቃድ በአንድ የንግድ ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችልና
ሕጋዊ ከለላ የሚያጎናጽፍ ነው። ሰዎች በሚፈልጉት የሥራ መስክ ያለሥጋት መሥራት የሚችሉት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ሲኖራቸው
ብቻ ነው።
ይሁን እንጅ አንዳንድ ሰዎች የንግድ ፈቃድ ሳያወጡ የንግድ ሥራ መስራት ይፈልጋሉ። እነዚህ ሰዎች ፈቃድ የላቸውምና ህጋዊ
አይደሉም። የንግድ ፈቃድ ሳያወጡ መስራትም ወንጀል ነው። የመንግስትን የገቢ መጠን ያሳጣል፤ የአገርንም እድገት ያዳክማል።
ቁጥጥርና ክትትል ለማድረግም ምቹ አይሆንም። ግለሰቦች ፈቃድ ከሌላቸው የስራቸው ቀጣይነት አስተማማኝ አይሆንም። ህጋዊ
አለመሆናቸው ከተደረሰበት ድርጅታቸው እንደሚዘጋ ያውቃሉና ሁልጊዜ በስጋት ውስጥ ይኖራሉ። በስጋት ውስጥ ሆኖ መስራት
ደግሞ በሥራ ውጤታማ አያደርግም።
የንግድ ፈቃድ የያዙ ሰዎች ግን ያለምንም ሥጋት መሥራት ይችላሉ። ህጋዊ ስለሆኑ መብቶቻቸውን የመጠየቅና የማስከበር እድል
አላቸው። ማንኛውንም የንግድ ሥራ ሕጋዊ ፈቃድ ይዞ መሥራት ለንግድ አሠራር ሥርዓት የራሱ ድርሻ አለው። ፈቃድ ይዞ
መሥራት ለሕግ ተገዢ መሆንንም ያሳያል። ተገቢውን ግብር በወቅቱ በመክፈል ለአገር እድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ
ይሆናል። ምክንያቱም በግብር የሚሰበሰበው ገንዘብ እንደመንገድ፣ መብራት፣ ውሃ የመሳሰሉትን መሠረተልማቶች ለማሟላት
ያስችላል። የትምህርት ተቋማትን በማስፋፋት ዜጎችን ለማስተማር ይረዳል። የጤና ተቋማትንም በማስፋፋት ተገቢ የጤና
አገልግሎት ለመፍጠርም ያስችላል።
ስለሆነም በንግድ ዘርፍ የሚሰማሩ ሰዎች ህጋዊ ፈቃድ ማውጣት ይኖርባቸዋል። ያለፈቃድ የሚሰሩ ሰዎችን መምከርና መገሰፅ
አስፈላጊ ነው። ግብር እየከፈሉ መስራት ጠቃሚ መሆኑን ማስተማር ያስፈልጋል። ህጋዊ ሆነው ተገቢ ግብር ለመክፈልም
ገቢያቸውንና ወጪያቸውን ለገቢዎች ጽህፈትቤት ማሳወቅ ይኖርባቸዋል። እንዲህ ያለው መረጃ ግብርን በገቢያቸው መጠን ብቻ
አስልቶ ለመጣል ያስችላል። በዚህም ነጋዴዎች ያልተጋነነና ትክክለኛ የግብር መጠን እንዲከፍሉ ያግዛቸዋል።
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ከመምህር ጋር እንዲወያዩ ያድርጉ፤ መልሳቸውን ይቀበሉ።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ያደርጋሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ርስበርሳቸው እንዲወያዩ ያድርጉ።)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ ይወያያሉ።]
ቃላት (7 ደቂቃ)
(መ. በተሰጡት ቃላት አውዳዊ ፍቺ እንዲኖራቸው አድርገው ዓረፍተነገር እንዲሰሩ ያድርጉ። ምሳሌ ሠርተው ያሳዩአቸው።)
[ተ. በቃላቱ ዓውዳዊ ፍቺ እንዲያሳዩ አድርገው ዓረፍተነገር ይመሠርታሉ።
ምሳሌ፡- በበዓል ሰሞን ወደገበያ የሚወጣው ሸማች በርካታ ነው።
ድኅረማዳመጥ (5 ደቂቃ)
(መ. ባዳመጡት ታሪክ መሠረት የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎቹን በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ ይስጡ።)
[ተ. ሀ. ፈቃድ የሌለው ንግድ በመንግስት ያልተመዘገበ ስለሆነ መንግስት ማግኘት ያለበትን ግብር እንዳይሰበስብ ያደርገዋል።]
ለ. ግብር ባለመክፈላቸው ከዛሬ ነገ መንግስት ያዘን ፤ ወይም ንብረታችን ተወረሰ፤ ወይም ታሰርን እያሉ ስለሚጨነቁ ነው።]
አቶ መስፍን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ነጋዴዎች መካከል አንዱ ናቸው። ከገበያው በስተምስራቅ አቅጣጫ የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ አላቸው።
በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ትልቅ ከተማ እየሄዱ ሸቀጦችን በመኪና ጭነው ያመጣሉ። ባልተጋነነ ትርፍ ለማኅበረሰቡ ይሸጣሉ።
የአካባቢው ሰው በአዘቦት ቀን ሳይቀር በሰልፍ የሚፈልገውን ነገር ሲገዛ ይውላል። ተጎራብተዋቸው ያሉ ነጋዴዎች ግን በየሸቀጦቹ
የሚጨምሩት ዋጋ ከፍ ያለ ነበር። ስለሆነም ብዙ ሰው ከነሱ ይልቅ ከአቶ መስፍን መግዛትን ይመርጣል። ከነሱ ይጠይቃል፣ ከአቶ
መስፍን ይገዛል።
ጎረቤቶቻቸው ያላግባብ በሸቀጦች ላይ ዋጋ እንዲጨምሩ አቶ መስፍንን ወተወቷቸው፤ ቆይተውም ተቀየሟቸው። እርሳቸው ግን ተገቢ
ያልሆነ ትርፍ ማግበስበስ እንደማይሹ ተናገሩ። ያላግባብ የተሰበሰበ ገንዘብም እንደማይባረክላቸው ገለጹ። ይልቁንም ጎረቤቶቻቸው
ዋጋ እንዲያስተካክሉ አሳሰቧቸው። የንግድ ሥራ ቀስበቀስ የሚታደግበት እንጅ በአቋራጭ የሚከበርበት አለመሆኑን አስረዷቸው።
ጎረቤቶቻቸው ግን የአቶ መስፍንን ምክር እንደንቀት ቆጠሩት። ሰደቧቸው፤ ዛቱባቸው። ሊበቀሏቸውም ቀን ይቆጥሩላቸው
ጀመር። አቶ መስፍን ግን ዛቻውን ከእቁብ ሳይቆጥሩ ሥራቸውን መሥራት ቀጠሉ። በርካታ ደንበኞቻቸው ይህንን ስለሰሙ መከታ
እንደሚሆኑላቸው ቃል ገቡላቸው።
ቅድመማዳመጥ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ላይ ርስበርስ እንዲወያዩ መመሪያ ይስጡ።)
[ተ. በቅድመማዳመጥ ጥያቄዎች ይወያያሉ።]
ቅድመንባብ (3 ደቂቃ)
(መ. በቅድመንባብ ጥያቄዎች ላይ ከተማሪዎች ጋር ተወያዩ። ሐሳባቸውን ይቀበሉ)
[ተ. በቅድመንባብ ጥያቄዎቹ ላይ ከመምህራቸው ጋር ይወያያሉ።]
ቃላት (5 ደቂቃ)
(መ. ባዳመጡት ታሪክ መሠረት ለቀረቡት ቃላትና ሐረጋት ፍቺ እንዲሰጡ ያድርጉ፤)
[ተ . ከነመረጃው፣ መቦርቦር/መፈልፈል፣ በጥቅል/በደርዘን፣]
ድኅረማዳመጥ (5 ደቂቃ)
(መ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎችን በጽሑፍ እንዲመልሱ ያድርጉ። እንዳስፈላጊነቱ ግብረመልስ ይስጡ።)
[ተ. የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎችን በጽሑፍ ይመልሳሉ።]
ማረው አለሙ። (2005)። በሳል ድርሰት ማስተማሪያ። አዲስ አበባ፤ አልፋ አታሚዎች።
ባየ ይማም። (1987)። የአማርኛ ሰዋስው። ት.መ.ማ.ማ.ድ
ብርሃነ መስቀል ደጀኔ። (1987)።ዉኃ ዉኃ የሚያሰኝ ጉዞ።
ቱር ኢን ኢትዮጵያ። (ሚያዘያ 1 2019)።
አብክመ ባህልና ቱሪዝም። (ቀን የሌለው)። አማራ ክልልና መስህቦቿ።
አዲስ ዘመን ጋዜጣ። (ሰኔ 14/ 2012)።
ኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና አብክመ ትምህርት ቢሮ። (2007)። ስድስተኛ ክፍል አማርኛ እንደአፍመፍቻ ቋንቋ የተማሪ
መጽሐፍ።
ኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና አብክመ ትምህርት ቢሮ። (2006)። አራተኛ ክፍል አማርኛ እንደአፍመፍቻ ቋንቋ የመምህር
መምሪያ።
ከበደ ሚካኤል። (1999)። ታሪክና ምሣሌ። አዲስ አበባ፤ ሜጋ አሳታሚና ማከፋፈያ፡፡
ዘሪሁን አስፋው። (1992)። የሥነጽሑፍ መሠረታውያን። አዲስ አበባ፤ ንግድ ማተሚያ ድርጅት።
ደረጀ ገብሬ። (1996)። ተግባራዊ የጽሕፈት መመሪያ። አዲስ አበባ፤ ንግድ ማተሚያ ድርጅት።
ጌታሁን አማረ። (1989)። የአማርኛ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ። አዲስ አበባ፤ አልፋ አታሚዎች።
healthline.com. (March 19, 2019). Why Is Water Important? 16 Reasons to Drink Up.
https://am.Sewasew.com/p/። (2021)። አዕምሮ የመጀመሪያው በአማርኛ ይታተም የነበረ ጋዜጣ።
111