Вы находитесь на странице: 1из 43

2017-18 የተማሪዎች ግዴታና መብት መግለጫ እንዲሁም የተማሪ

ፍለጋ ማጣራት መረጃ

Shoreline Public Schools


ማውጫ
የተማሪ ዲሲፒሊን�������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 1
ፍቺዎች������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 1
የሚጠበቅ የተማሪ ስነምግባር እና ተገቢ እገዳዎች���������������������������������������������������������������������������������������������� 2
የእርማት እርምጃዎች አካሄዶች��������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 7
የዲስፕሊን እና የአጭር ጊዜ እገዳዎች ቅሬታ አቀራረብ አሰራር������������������������������������������������������������������������15
የረዥም ጊዜ እገዛ፣ ማባረር እና የድንገተኛ ማባረር የሚመለት የክስ መስማት ሂደት������������������������������������ 16
ክስ ሰሚ ሀላፊው የሰጠው የረዥም ጊዜ እገዛ፣ ማባረር እና የድንገተኛ ማባረር የማጽናት ውሳኔ በመቃወም
ይይግባኝ ጥያቄ ማቅረብ።�����������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������17
በእግድ ወይንም የማባረር እርምጃ ወቅት ተመልሶ ትምህርት መጀመር����������������������������������������������������������18
ማረሚያ ቤት መቆየት������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������18
የትምህርት ቤት ውስጥ እግድ�����������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������18
በህጋዊ መልኩ ልጅ ማስጠጋት����������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������19
አድልዎ አለመፈጸም���������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������19
የተማሪ ሰነዶች�����������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������20
ወሲባዊ ትንኮሳ�����������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������21
የትንኮሳ፣ ዛቻ፣ እና ለከፋ (ስድብ)/የኢንተርኔት ለከፋ ክልከላ �����������������������������������������������������������������������22
አድልዎ አለማድረግ፣ የምሬት/አቤቱታ አቀራረብ ሂደት ማሳወቂያ�����������������������������������������������������������������23
ይቅርታ የሚደረግላቸው እና የማይደረግላቸው የመቅረት ሁኔዎች���������������������������������������������������������������� 24
ስነ ምግባር እና ታማኝነት���������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 28
የኢንተርኔት አጠቃቀም������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 29
በአውቶብስ ላይ የተማሪ ጸባይ �������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������30
ራስን የመቆጣጠር እና መለየት አጠቃቀም �������������������������������������������������������������������������������������������������������32
የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ ፕሮቶኮሎች��������������������������������������������������������������������������������������������������� 34
ከጦር መሳሪያ የጸዳ ዞን���������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������37
የካኒን ፍለጋዎች���������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������37
የህጻን ፍለጋ���������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������37
የተማሪዎች ግዴታና መብት መግለጫ
(የተሸሻለው በነሀሴ 2017)
ሾርላይን የመንግስት ትምህርት-ቤቶች (Shoreline Public Schools)
18560 1st Ave. N.E., Shoreline, WA 98155
206.393.6111 ~ www.shorelineschools.org
ይህ የመምሪያ መፅሃፍ የተማሪዎችን አስፈላጊ የሆኑ አይነተኛ እና ስርዓታዊ መብቶችን በሚያብራራው በግዛት
እና በፌደራል ህግጋት እና ደንቦች ላይ መሰረት በማድረግ ነው የታተመው። የዚህ የመመሪያ መፅሃፍ ሁሉም
ደንቦች እንዲህ ባሉት ህግጋት እና ደንቦችን በሚያረጋግጡ መልኩ ነው ሊፈቱ የሚገባው። የዚህ መጽሓፍ ይዘት
የዳሬክተሮች ቦርድ ማናቸውም ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር ካወጣቸው ፖለሲሲዎች እና አሰራሮች ተቀንጭቦ
የታተመ ነው። ፓሊሲዎች እና አካሄዶች በተደጋጋሚ በክለሳ እና ለውጦች ስር መሆናቸው እና በማንኛውም
ሰዓት ሊስተካከሉ እንደሚችሉ ከግምት ውስጥ መግባት አለበት። ሁሉም ፓሊሲዎች እና አካሄዶች ከሁሉም
የትምህርት ቤቱ ህንፃዎች ዋና ቢሮ ሊገኙ ይችላሉ እንዲሁም በአስተዳደሩ የድር ገፅ በ www.shorelineschools.
org ላይ ይገኛሉ።

የተማሪ ስነምግባር
{ከፖሊሲ #3310 የተቀነጨበ፣ ተማሪ ለሚያሳያቸው የስነምግባር ጉድለቶች ለማረም ተግባራዊ የሚደረጉ
የዲሲፕሊን እና የእርምት እርምጃዎች}
የትምህርት ቤቱን ደንቦች ለማስፈጸም በስራ ላይ የዋሉት ዘዴዎች ሞያዊ ውሳኔዎችን ያካተቱ ናቸው።
የሚከተሉት ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው፦

1. በእለትከእለት፣ ከተማሪተማሪ፣ እና ከአስተማሪ አስተማሪ ያልተዛቡ አንድአይነት ሁኔታዎችን በስራ


ላይ ማዋል፤
2. ያልተገባ ስነምግባር ክብደት፤
3. የተማሪው ተፈጥሮ እና የቀድሞ ባህሪይ፤
4. ለተማሪ፣ ለወላጅ እና ለሌሎች ያለው ሚዛናዊነት፤
5. ብቃት፤ እና
6. ያልተገባ ስነምግባሩ በትምህርታዊ ሁኔታ ላይ ያለው ጫና።
ፍቺ፦
ዲሲፕሊን — የትምህርት አይነቱ ተሰጥቶ ከሚያልቅበት አጠቃላይ የትምህርት ጊዜ ጋር የማይስተካከል ከትምህርት
የማግለል እርምጃ፣ ከማገድ ውጪ፣ ከትምህርት ክፍል፣ ከትምህርት አይነት፣ ወይንም እንቅስቃሴ ማግለል
ወይንም ለጊዜው የማስወገድ እርምጃን ጨምሮ ሁሉም አይነት የእርምት እርምጃዎች። ዲስፕሊን ማለት
ካማናቸውም በዲስትሪክቱ የሚካሄዱ አይነት እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ ከአትሌቲክስ ፕሮግራሞች እና የማጓጓዣ
አገልግሎቶችን መገለልንም ያካትታል።
“መታገድ” ተሳትፎ ከማድረግ መከልከልማለትነው (ይህም ለፈጣን የትምህርት ክፍለጊዜለ “ዲሲፒሊን” ዓላማዎች
ካልሆነ በቀር) ለተጀመረ ክፍለጊዜ በማንኛውም ነጠላርዕስ ወይም የትምህርትጊዜ፣ ወይም በማንኛውም ሙሉ
የትምህርት አይነት ወይም ክፍል የጊዜ ሰሌዳ ሲሆን።
«የአጭር-ጊዜ እግድ» ማንኛውም አይነት ለተወሰነ ጊዜ የሚደረግ እግድ ሲሆን ከተወሰኑ የቀን መቁጠሪያ ቀናት እስከ
አስር ተከታታይ የትምህርት ቀናት ያልበለጠ ነው።
የረዥም ጊዜ እግድ — ከአስር (10) ተከታታይ የትምህርት ቀናቶች የሚበልጥ እንዲሁም ከአንድ የትምህርት ተርም
(90 የትምህርት ቀናት) የማይበልጥ እግድ።
ማባረር — ተማሪው በከፍተኛ ሀላፊው ወይንም በሚመለከተው አካል ከዲስትሪክቱ ትምህርት-ቤት ከተወገደበት
ቀን አንስቶ ታሳቢ የሚሆን ከአንድ የትምህርት ተርም (90 የትምርት ቀናት) በላይ የማይዘልቅ ከትምህርት
ተሳትፎ የማባረር እርምጃ።
ድንገተኛ የማስወገድ እርምጃ — የተማሪው በትምህርት-ቤት መኖር በተጨባጭ በተማሪው፣ በሌሎች ተማሪዎች፣
ወይንም በትምህርት-ቤቱ ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ እና ቀጣይነት ያለው አደጋ ሊያስከትል ይችላል ተብሎ
ሲታሰብ ወይንም በትምህርት ሂደት፣ አይነት፣ እንቅስቃሴ፣ ወይንም የትምህርት ሂደት ላይ ከፍተኛ እና
1
ቀጣይነት ያለው ስጋት ወይንም የማስተጓጎል ችግር ይፈጥራል ተብሎ ሲታመን የሚወሰድ ተማሪውን
በድንገት ከትምህርት የማስወገድ እርምጃ ነው።
ድንተኛ የማባረር እርምጃ — “ድንተኛ የማባረር እርምጃ” ማለት በሌሎች ተማሪዎች፣ ወይንም በትምህርት-
ቤቱ ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ እና ቀጣይነት ያለው አደጋ ሊያስከትል ይችላል ተብሎ ሲታሰብ ወይንም
ብትምህርት ሂደት፣ አይነት፣ እንቅስቃሴ፣ ወይንም የትምህርት ሂደት ላይ ከፍተኛ እና ቀጣይነት
ያለው ስጋት ወይንም የማስተጓጎል ችግር ይፈጥራል ተብሎ ሲታመን የሚወሰድ ተማሪውን በድንገት
ከትምህርት ቤት ተሳትፎው በማባረር እስከ (10) ተከታታይ የትምህርት ቀናቶች ከትምህርት እንዲርቅ
የማድረግ እርምጃ ነው። ተማሪው ለአስር (10) ተከታታይ የትምህርት ቀናት ተባሮ ከቆየ በኋላ በድንገት
የማባረር ቅጣቱ ያበቃል ወይንም ወደ ሌሎች የቅጣት አይነቶች ይቀየራል።
ወላጅ ወይንም ሞግዚት — ማንኛውም በተፈጥሮ፣ በማደጎነት፣ ወይንም በሕጋዊ አሳዳጊነት ወይንም
በሞግዚትነት ህጻኑን ወላጅ ሆኖ የማሳደግ መብት ያለው አካል። በአብዛኛው የዕድሜ ክልል የሚገኙ
ተማሪዎች ወላጅ አሳዳጊ የማግኘት መብት አላቸው።
የትምህርት ቀን — ሁሉም ወይንም የተወሰኑት የዲስትሪክቱ ተማሪዎች በተጨባጭ በዲስትሪክቱ ብቁ
ሰራተኞች በሚታገዱ፣ ቁጥጥር በሚደረግባቸው እና በሚከናወኑ ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎች የመሳተፍ
ዕድል የሚያገኙባቸው ከትምህርት-ቤት በአላት ውጪ ያሉ የስራ ቀናቶች።
የትምህርት-ቤት የስራ ቀን — ከቅዳሜ እና እሁድ እና በስቴት እና በፌዴራል ሕጎች የትምህርት-ቤት በአላት
ተብለው ከተያዙ ቀናቶች ውጪ ያሉ የትምህርት-ቤቱ ከፍተኛ ሀላፊ ለህዝብ ክፍት የሚሆንባቸው
ሁልም ቀናቶች። የከፍተኛ ሀላፊው ጽሕፈት-ቤት በሚዘጋት ሰአት የትምህርት የስራ ቀን ያበቃል።
አካዳሚያዊ ተርም — ለ 90 የትምህርት ቀናት የሚዘልቅ አንድ ሰሚስተር።

የሚጠበቅ የተማሪ ስነምግባር እና ተገቢ እገዳዎች


{ከፖሊሲ #3300 የተቀነጨበ፣ የሚጠበቅ የተማሪ ስነምግባር እና ተገቢ እገዳዎች}
የተማሪ ጸባይ ደንቦች
ተማሪዎች በዚህ ፓሊሲ ወይም በሌሎች ፓሊዎች ውስጥ የትምህርትቤቱ አስተዳደር በስራ ላይ
ላዋላቸው የጸባይ ደንቦች ተገዥ ይሆናሉ። ይህንን በተግባር አለማዋል ለእርማት አርምጃዎች መሰረት
ይሆናል። ደንቦቹ በትምህርትቤት ባለስልጣናት በተግባር መዋል አለባቸው፦
• በትምህርትቤት መጫወቻ ስፍራ ላይ ከትምህርት ሰዓታት በፊት እና በኋላ፤
• ትምህርት-ቤቱ በትምህርት-ቤቱ በትምህርት ቤቱ መጫወቻ ቦታዎች ቡድን(ኖች) ወይንም
ለትምህርት ቤት ስራ በተያዘበት በማናቸው ሌላ ጊዜ ;
• ከትምህርት ቤት መጫወቻ ስፍራ ውጭ በትምህርት ቤት እንቅስቃሴ፣ ስራ ወይም
ዝግጅት ላይ፤
• ከትምህርት-ቤቱ ውጪ፣ የተማሪው ተግባሮች በተጨባጭ የትምህርት ሂደቱ ወይንም
የድስትሪክቱ ተግባራትን የሚያውኩ ከሆነ; እና
• በትምህርት-ቤት ማጓጓዣ አገልግሎቶች ወይንም ተማሪዎች በትምህርት-ቤቱ ሰራተኛ
ክትትል ስር በሚሆኑበት ማናቸውም ቦታዎች።

2
የኮከብ ምልክት (*) የተደረገባቸው ደንቦች የሚወክሉት ልዩ ያልተገባ ባህሪይን ነው እና ከጥምር የዜጎች ኮሚቴ
ጋር በመሆን ብይን የተሰጠባቸው ሲሆን የሚያከናውኑትም (ሀ) እንዲህ ያሉት ተደጋጋሚ፣ ምንም እንኳን
ከዚህ ቀደም እንዲህ ያለውን ያልተገባ ባህሪይ በሌሎች ተመሳሳይ የእርማት እርምጃዎች ለመቆጣጠር በተደረገ
ሙከራ፣ ወይም (ለ) በተፈጥሮው በጣም ከባድ የሆነ እና/ወይም በትመህርት ቤቱ ክንውን ላይ አስቸጋሪ
ውጤት ያለው ሲሆን እነኝህን ደንቦች በመጣሳቸው ምክንያት የትምህርት ቤቱ ከዚህ በቀደም ተመሳሳይ
ያልተገባ ባህሪይ ያላቸው ተማሪዎች ላይ ሌላ አይነት የእርማት እርምጃ ተወስዶ ባያውቅም የትምህርት ቤቱ
አስተዳዳሪዎች የአጭር ጊዜ ወይም የረዥም ጊዜ እግድን በተግባር ሊያውሉ ይችላሉ። እንዲህ ያለው ያልተገባ
ባህሪይ መባረርን ወይም በፍጥነት መባረርን ሊያስከትል ይችላል ይህም ለ WAC 392-400-275 እና
392-400-295 ተጠሪ ነው። ይሁን እንጂ፣ However, neither long-term suspension nor non-emer-
gency expulsions will be imposed in response to student misconduct in a manner that consti-
tutes “discretionary discipline,” as that term is used in RCW 28A.600.020.
1. ልኮል/የኬሚካል ንጥረ ነገሮች* – አልኮልን ወይም ህገወጥ ዕፆችን ይዞ መገኘት፣ መጠቀም፣ ማሰራጨት፣
እንደተጠቀሙ ምልክቶች ማሳየት፣ መሸጥ፣ ማሻሻጥ ወይም ለሽያጭ ማስተባበር የተከለከለ ነው። የአደንዛዥ
እፅ መሳሪያ ወይም ማንኛውም እንደዚህ ያለ የተከለከለ ነገር። በትምህርት ቤት ውስጥ ተሳትፎ ወይም
በትምህርት ቤት ስፓንሰር በተደረገ ዝግጅት፣ ተማሪዎች እንዲህ ያሉ እንቅስቃሴዎች በሚከሰቱ ጊዜ በፍጥነት
ራሳቸውን ማስወገድ አለባቸው። ተማሪዎች በእራሳቸው እና በሌሎች ተማሪዎች ወይም የግዛት ህግጋትን፣
የአስተዳደር ፓሊሲን እና የትምህርት ቤት መሪዎች ቁርጠኛ የሚሆኑለትን ደንብ እንዲሁም ማንኛውም
ለጤንነታቸው ወይም ለደህንነታቸው አደገኛ ሁኔታን የሚያመጣ ነገር ሪፓርት ማድረግ እንዳለባቸው
ማህበረሰቡ እንደሚያበረታታቸው ተማሪዎች ይረዳሉ።
2. የቅጅዎች ማሻሻል* – ትምህርት ማስረጃዎችን አስመስሎ መሰራት፣ መለወጥ ወይም ማንኛውንም
ግንኙነቶችን ከቤትና ከትምህርት ቤት መጥፋት የተከለከለ ነው.
3. ተቀጣጣይ* – ሆን ብሎ እሳት ማስነሳት ወይም እሳት ሊያስነሱ የሚችሉ መሳሪያዎችን መያዝ የተከለከለ
ነው።
4. ጥቃት/ማስፈራራት/ማንጓጠጥ* – ጥቃት አከላዊ ወይም በቃል ማሰፈራራት ተብሎ ይገለጻል እናም ክልክል
ነው። ማንጓጠጥ እንደ የሰዎች ጥቃት ተብሎ ይገለጻል እናም ክልክል ነው።
5. መገኘት – በግዛቲቱ ህግና በአውራጃው መመሪያ መስረት የተመዘገቡ ተመሪዎች የቀን ተቀን መገኘት አስፈላጊ
ነው። ተገኝተዋል ተብለው ለመቆጠር ተማሪዎቹ ቢያንስ የሶስት ኮርሶቸን የትምህርት ቀን 50 ፕረሰንት
ወይም ተመጣጣኙን መገኘት አለባቸው። ተማሪዎች በኦፈሻል በተመደበው(በተመደቡት) ሰው (ሰዎች)
እስካልተፈቀደላቸው ድረስ በመደበኝነት የተያዘላቸውን ትምህርቶችና እንቅስቃሴዎች ላይ ይሳተፋሉ።
ተማሪዎችና ወላጆች ያለበቂ ምክንያት/ለበርካታ ቀን መቅረት ምክንያቱም ምንም ይሁን ምን ክሬዲቶቹ
ውድቅ እንዲደረጉ እና/ወይም ቀሪ ባልሆነበት ጊዜ ምንም እንኳ አማካይ ወይም ከአማካይ በላይ ቢሰራም
ተመጣጣኝ ርምጃ እንዲወሰድ ሊያደርግ ይችላል።
6. ዘረፋ* – ለመስረቅም ይሁን ለለሌ ጉዳይ ትመህርት ቤት ሰብሮ መግባት የተከለከለ ነው.
7. ማታለል* – ማታለል የተከለከለ ነው። ማንኛውም ተማሪ እያወቀ/ች የሌሎችን ስራ እንደራሱ ወይም
እንደራሷ አድረጎ/ጋ ማቅረብ እንደማታለል ይቆጠራል። ማታለል በተጫማሪ የሌሎችን ማጋዝ እና በማሳሳት፣
በመለወጥ ወይም የተማሪውን መዝገብ በማንኛውም ምንገድ ማስወገድን የሚያታልሉትን፣ ማገዝንና
መሸፈንን ያካትታል።

3
8. ዝግ/ክፍት ካምፖች – ከ K እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ትመህርት ቤት ከደረሱበት በኦፊሴል
እስከሚሰናበቱት ድረስ በትመህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ መቆየት አለባቸው። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች
በየካምፓሱ የተቀመጠውን የካምፓስ ዝግ/ክፍት መመሪያዎች እንዲከተሉ ይጠበቅባቸዋል። በሃላፊነት ይህን
በጎ ፈቃድ የማይጠቀሙ ወይም በትምህርት ቤቱ አጠገብ በሚገኙ የተከለከሉ ቦታዎች የሚገኙ ተማሪዎች
ይህን በጎ ፈቃድ ሊነጠቁ ይችላሉ። የክፍት ካምፓስ በጎ ፈቃዳቸው ከተሰረዘ በኋላ ካምፓሱን ለቀው የሚሄዱ
ተማሪዎች እገዳ ወይም መባረርን ጨምሮ ለተጨማሪ የስነስርአት እርምጃ ይዳረጋሉ።
9. ኮርፖሬሽነ በትመህርት ቤት ሰራተኛ፣ በትመህርት ቤት ደንቦች፣ ወይም በአውራጃ ፖሊሲዎች ውስጥ * –
ተማሪዎች የትምህርት ቤቱን ህጋዊ መመሪያዎች መከተል አለባቸው.
10. የወንጀል ባህሪ * – በትምህርት ቤት ውስጥ፣ ከትምህርት ቤት ውጪ በወንጀል ድሪጊቶች የሚሳተፉ
ተማሪዎች፣ የወንጀል ተግባራቱ ትመህርት ቤቱን ወይም አውራጃውን በማስከበርና በማኪያሄድ ላይ ዋሳኝ
ተጽእኖ ሲኖራቸው የማስተካከያ ርምጃ በትምህርት ቤቱ ይወሰዳል እንዲሁም በህግ ሊያስከስስ ይችላል።
11. የተጠራቀሙ ጥሰቶች – በትምህርት ቤት ማህበረሰብ፣ ተማሪዎች የተለያዩ የትመህርት ቤት ፖሊሰዎች፣
ደንቦች እና መተዳደሪዎችን የሚጥሱባቸው መጠኖች አብዛኛውን ጊዜ ከግል ጥሰቶች እኩል ወይም የበለጡ
ተጠያቂነት ይፈጥራሉ። ስነስርአተ የእነዚህ ተግባራት ጥርቅም ውጤት ነው።
12. ልብስና አቀራረብ – ልብሰና አቀራረብ የጤና ወይም የደህንነት ችግሮችን የሚያሳይ ወይም በ #3224, የተማሪ
ልብስ ፖሊሲ መሰረት ረብሻ የሚፈጠር መሆን የለበትም.
13. የረብሻ ተግባር* – በቁስ እና በግልጽ የትመህርት ሂደቱ ላይ ጣልቃ መግባት የተከለከለ ነው።
14. አደንዛዥ እጾች (ህገወጥ)* – ፍቺውን በ“አልኮልና ኬሚካል ንጥረነገሮች” ንጥል ቁጥር #1 ስር ይመልከቱ.
15. የሚፈነዱ* – ባለቤት መሆን፣ መጠቀም፣ ወይም በትመህርት ቤተ ቅጥር ግቢ ወይም በትምህርት ቤት –
የሚዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ የመፈንዳት ማስፈራሪያ የተከለከለ ነው.
16. ባይል መንጠቅ፣ አስፈራርቶ መቀበል፣ ወይም አሰገድዶ መቀበል* – ገንዘብ ወይም ንብረት በሃይል ወይም
በሃይል በማስፈራራት፣ ወይም አንድ ሰው አንድ ነገር እንዲያደርግ በሃይል ወይመ በማስፈራራት ማስገደድ
የተከለከለ ነው።
17. የሃሰት ውንጀላ/ስም ማጥፋት* – ተማሪዎች እውነተ ያልሆኑ የመጥፎ ተግባር ክሶች ወይም ሌሎች ስም
የማጥፋት መግለጫዎች ማድረግ የለባቸውም.
18. መደባደብ* – አካላዊ ንክኪ ያካተት ጸብ ላይ መሳተፍ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
19. አሰመስሎ መስራት* – በጽሁፍ የሌላን ሰው መጻፍ ወይም ሰአቶችን፣ ቀኖችን፣ ውጤቶችን አድራሻዎችን፣
ወይም ሌላ በትምህረርት ቤት ቅጾች ላይ የማጭበርበር ተግባር መፈጸም የተከለከለ ነው.
20. ቁማር – የቁማር ተግባር ወይም ሌሎች እንዲቆምሩ ማመቻቸት የተከለከለ ነው። “ቁማር መጫወት”
በጫወታ ውጤት ምክንያት ተሸንፎ ዋጋ የሚያወጡ ነገሮችን አሳልፎ መስጠት ወይንም አሸናፊው አካል
በጨዋታው በሚያገኘው ውጤት መሰረት አሁንም ይሁን ለወደፊቱ የሆነ ዋጋ ያለው ነገር ከተሸናፊው
የሚወስድበት ጨዋታ ላይ መሳተፍ።
21. የዱሩዬ ተቀጽላ/ምልክቶች* – የዱሩዬ ተግባራት ወይም የዱሩዬ ተቀጽላ ምልክቶችን ማሳያት የተከለከለ
ነው። “ወንበዴ” ሶስት ወይም ከዚያ በላይ ሰዎችን ይይዛል፣ ሊለይ የሚችል አመራር አለው፣ እናም የማያቋርጥ
እንቅስቃሴ አለው፣ በመደበኛነት ያሴራል እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜ ለወንጀል አለማ ጠንካራ ርምጃዎችን
ይወስዳል። የወንበዴ ምልክቶች የእጅ ምልክቶችን፣ የእጅ ጽሁፍ እና/ወይም የልብስ፣ ጌጣጌጥ፣ ተቀፅላዎች፣
ተንጠልጣዮች ይኖሯቸዋል፣ ወይም የአለባበስ ሁኔታ በቀለም፣ በአደራደር፣ የንግድ ምልክት፣ ምልክት
በመለወጥ የሚለይ፣ ወይም ሌላ ማንኛውም መለያ የወንበዴው አባልነት የሚገልጽ ይጠቀማሉ።

4
22. ትንኮሳ/ማስፈራራት/በጉልበት ሌላውን ማጥቃት/በኢንተርኔት መዛት* – ተማሪዎች ትንኮሳ/ማስፈራራት/
በጉልበት ሌላውን ማጥቃት/በኢንተርኔት መዛትን በሚከለክለው ፖሊሲ 3308 ላይ እንደተገለጸው በ
“ትንኮሳ/ማስፈራራት/በጉልበት ሌላውን ማጥቃት/በኢንተርኔት መዛት” (HIB) መሳተፍ፣ ለመሳተፍ ማሴር
ወይን ሌሎችን ለማሳተፍ ማሴር የለባቸውም። ትንኮሳ፣ ጥቃት ወይም ስድብ» ማለት በኤሌክትሮኒክስ
መሳሪያ የሚተላለፍን ጨምሮ ሆን ተብሎ የሚፃፍ መልዕክት ወይም ምስል፣የቃል ወይም የአካል ድርጊት
ምንም እንኳን በዚህ ብቻ ባይወሰነም በ RCW 9A.36.080(3)፣ (ዘር፣ ቀለም፣ የትውልድ ስፍራ፣ (ቋንቋን
ጨምሮ)፣ ፆታ፣ የፆታዊ ግንኙነት የስርዓተ ፆታን መለያ ጨምሮ፣ እምነት፣ ሃይማኖት፣ ዕድሜ፣ የአርበኝነት
ወይም ወታደራዊ ሁኔታ፣ አካል ጉዳተኝነት፣ ወይም አካል ጉዳተኞች የሚጠቀሙበት የሰለጠነ ውሻ
አጠቃቀም ወይም መመሪያ) ወይም ሌሌች የተለዩ ባህሪያት ማለት ነው፣ ተግባሩ በሚከተለው መልኩ;
በዋነኛነት በተማሪው ትምህርት ላይ ጣልቃ የመግባት ውጤት የሚኖረው ድርጊት መፈጸም፤ ፍርሀት እና
ስጋት ሰፈነበት የትምህርት ሁኔታ የሚፈጥር፣ ወይንም የትምህርት-ቤቱን ሰላማዊ እንቅስቃሴ የማደናቀፍ
አቅም ያለው የከፋ፣ ቀጣይነት ያለው እና ዘላቂ ከሆነ። የተከለከለ HIB ማጉደፍ፣ አሉባልታዎች፣ ወሬዎች፣
ቀልዶች፣ አልባልታዎች፣ አዋራጅ አስተያየቶች፣ ስእሎች፣ ካርቱኖች፣ ፕራንኮች፣ ምልክቶች፣ ጥቃቶች፣
ዛቻዎች፣ ወይንም ሌሎች በጽሑፍ፣ በቃላት ወይንም በአካል የሚገለጹ ተግባራት እና ሌሎችን ያካትታል።
23. ራስን መግለጽ – ሁሉም ሰው በትምህርት ቤት ህንጻ፣ ቅጥር ግቢ፣ወይም በትምህርት ቤት በሚዘጋጁ
ዝግጀቶች ላይ አግበብ ባለወ የትምህርት ቤት ባለስልጣን ሲጠየቅ ራሳቸውን መግለጽ አለባቸው.
24. ሌዘር እና ተመሳሳይ መሳሪያዎች – ቀድሞ ለትምህርት ቤት ባለስልጣናት ያላሳወቁትን ሌዘር ወይም ተመሳሳይ
መሳሪያዎችን መጠቀም የተከለከለ ነው.
25. ማበላሸት – በጋራ በታዎች ላይ መወርወር፣ መጣል፣ ማከማቸት፣ ወይም ቆሻሻ መጣል የተከለከለ ነው።
26. መንቀዋለል – ተማሪዎች ትምህርት-ቤት ከሚከፈትበት ጊዜ ከሰላሳ (30) ደቂቃ በፊት ቀድመው መድረስ
አይጠበቅባቸውም እንዲሁም ሌላ ትምህርታዊ ስራ ከሌላቸው በስተቀር ከትምህርት-ቤቱ መውጪያ ሰአት
በኋላ ትምህርት-ቤቱ ላይ መቆየት የለባቸውም።
27. አደገኛ ጉዳቶች* – ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ ወይም የአንድን ሰው ንብረት ያለፈቃዱ/ዷ መንካት
የተከለከለ ነው።
28. የሞተር ተሽከርካሪ ጥሰቶች – ምንም እንኳ ወደትምህርት ቤት የሞተር ተሸከርሪዎችን ተጠቅሞ መምጣት
ቢቻልም፣ የሚበረታታ አይደለም። ወደትምህርት ቤት የሞተር ተሸከርካሪዎችን ይዘው መምጣት የሚፈልጉ
የሚከተሉትን ማክበር አለባቸው፡ – ሀ) በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢና በትምህርት ቤት ዙሪያ ሁሉንም
የጥንቃቄ አነዳዶችን ልብ ማለት፤ ለ) በህንጻ አሰተዳዳሪዎች በተወሰነ ቦታ ላይ ብቻ ማቆም፤ እና (ሐ) በህንጻ
አሰተዳዳሪዎች ሊጠየቁ የሚችሉ ማናቸውንም የምዝገባ ቅደም ተከተሎችን መክበር፤ እነዚህን ሁኔታዎችን
አለማክበር በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስየ የማቆም ፈቃድ መነጠቅ እና/ወይም ሌሎች የስነስርአት
እርምጃዎች ሊያስወስድ ይችላል።
29. ያለሃኪም ትእዛዝ የሚሸጡ/ቁጥጥር የሚደረግባቸው ንጥረ ነገሮች/በሃኪም የሚታዘዙ መድሃኒቶች* –
ያለሃኪም ትእዛዝ የሚሸጡንና ቁጥጥር የሚደረግባቸው ንጥረ ነገሮች ያለአግባብ መጠቀም የተከለከለ ነው.

5
30. ዘረፋ* – ከግለሰበብ በሃይል ወይም በማስፈራራት መስረቅ የተከለከለ ነው።
31. ወሲባዊ ትንኮሳ* – በግለሰቡ ሰነ ጾታ ምክንያት ትንኮሳ፣ እንደሌሎች አይነቶች ትንኮሳ የተከለከለ ነው። ወሲባዊ
ትንኮሳ የሚከተሉትን ሊያካትት ይቻላል፣ ሆነም በዚህ የተወሰነ አይደለም፡ – የወሲባዊ ውለታ መጠየቅ
ለአድሎአዊ መስተንግዶ ወይም እሴት ያለው ነገር ለመቀበል፤ ለቀረበለት/ላት የወሲብ ጥያቄ አዎንታዊ መልስ
ካልሰጠ/ች አንድ ነገር እንደሚያጣ/እንደምታጣ መናገር፤ ለወሲባዊ ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ ባለመሰጠት
ምክንያት መቅጣት ወይም ለፈጸመ ጥቅማ ጥቅም መስጠት፤ በጎ ያልሆኑ፣ ሰብእና የሚነኩ ተገቢ ያልሁኑ
ወሲባዊ ጠቋሚ አስተያቶች፣ ገጽታዎች፣ ወይም ቀልዶች ወይም ሰለሰው አቋም፣ ስነጾታ፣ ወይም ምግባር
የወሲብ በህሪ ያላቸው አስተያየቶች መስጠት፤ አሸሟጣጭ የወሲብ ፊቺዎችን ለሰዎች መጠቀም፤ በጣም ጠጋ
ብሎ መቆም፣ ያልተገባ ንክኪ፣ መሄጃ ማሳጣት፣ ወይም በአንድ ቦታ ማፈን፤ ወሲባዊ ጽሁፍ፤ ወይም ስብእናን
የሚነኩ ወይም ተገቢ ያልሆኑ ወሲባዊ ገለጻዎች በትምሀርት ቤት ንብረቶች ላይ ማስፈር፤ ማንኛውም ተማሪ
ለወሲባዊ ትንኮሳ ተጋልጫለሁ ብሎ ወይም ብላ ያመነ ወይም ያመነች ወይም በማንኛውም ሰው፣ ተማሪዎችንና
ሰራተኞችን ጨምሮ ጥቃድ አድረሰውብኛል ብሎ ያመነ ወይም ያመነች ወዲያውኑ የህንጻ አማካሪውን ወይም
አሰተዳዳሪ ያነጋግሩ። (ፖሊሲ 3209 ይመልከቱ፣ ተማሪዎች: ጾታዊ ትንኮሳ፣ እና ፖሊሲ 5013፣ ሰራተኞች:
ጾታዊ ትንኮሳ።)
32. ተምባሆ ማጨስ/ማኘክ* – ተማሪዎች በትምህርት-ቤቱም ሆነ በትምህርት-ቤቱ አቅራቢያ ተምባሆ መያዝ፣
መሸጥ፣ ወይንም መጠቀም አይፈቀድላቸውም። በትምህርት ቤት ዙሪያ ፍቺው በትምህርት ቤቱ አቅራቢያ
በአይን ሊታይ በሚችል ማለት ነው።
33. የተማሪ አገላለጽ ጥሰት* – የተማሪ ራስን የመግለጽ ነጻነት የአውራጃው የትምህርት ፕሮግራም አካል ነው።
ይሁን እንጂ፣ የተማሪው አገላለጽ፣ ብልግና፣ ጸያፍ ቃላት፣ በሀፍረተቢስ አነጋገር የታጨቀ ወይንም በግላጭ
አስቀያሚ አለያም የትምህርት ሂደቱ ለማስተጓጎል እና የሌሎችን መብቶች ለመጋፋት የተደረገ መሆን የለበትም።
ከትምህርት-ቤቱ የገንዘብ እገዛ የሚደረግለት አገላለጽ በተገቢ ትምህርታዊ እሳዎች ምክንያት የበለጠ ቁጥጥር
ይደረግበታል። (ፖሊሲ 3220 ይመልከቱ፣ የመናገር ነጻነት)።
34. አርፋጅነት – ተማሪዎች ወደትምህርት ቤት ሲመጡ እና በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሰአት አክባሪዎች
መሆን ይጠበቅባቸዋል።
35. የቴሌኮሙኒኬሽን አውታረ መረብ ጥሰት* – ያልተፈቀደ፣ ህገወጥ ወይም ተገቢ ባልሆነ መንገድ የአውራጃውን
ቴሌኮሙኒኬሽን አውታረ መረብ ስርአትን፣ ኤሌክትሮኒክ መሳሪያውችን ወይም የተመሪ የግል መሳሪያዎችን
መጠቀም የተከለከለ ነው.
36. ስርቆት – መስረቅ የተከለከለ ነው.
37. መተላለፍ – ባልተፈቀደ ቦታ ቆሞ መገኘት ወይም ቦታውን እንዲለቁ ሲጠየቁ በመቃወም አለመልቀቅ
የተከለከለ ነው።
38. ህገወጥ ጣልቃገብነት በትምህርት ቤት ባለስልጣናት ላይ* – አሰተዳዳሪዎች ወይም መምህራን በህግ
የተፈቀደላቸውን ስልጣን ለመጠቀም ሲሞክሩ ጣልቃ መግባት የተከለከለ ነው.
39. ጋጠወጥነት* – የትምህርት ቤት ንብረት ማውደም የተከለከለ ነው። (በግዛቲቱ ህግ መሰረት የተማሪ ውጤት
ወይም ዲፕሎማ ሊያዝ ይችላል።)
40. የብልግና ወይም አጸያፊ ምግባር* – ማንኛውም አጸያፊ፣ ተገቢ ያልሆነ፣ ጸረ ሃይማኖት፣ ወይም የብልግና ተግባር
የተከለከለ ነው።
41. የጦር መሳሪያዎችና ሌሎቸ አደገኛ መሳሪያዎች* – ተመሪዎች በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ወይም
በትምህርት ቤት በሚዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ የጦር መሳሪያዎች፣ ሌሎች አደገኛ መሳሪያዎች ወይም ማንኛውም ጎጂ
ሊሆን የሚችል ነገር ሽጉጦች፣ ቢላዎች፣ ዱላዎች፣ የብረት ናክልስ፣ ስለቶች፣ ወደሰውነት የሚገቡ ኬሚካሎች፣ ወይም

6
ማንኛውም ጉዳት ሊያደረሱ የሚችሉ ቁሶች ጨምሮ ነገር ግን በእነዚህ ያልተገደበ ባለቤት መሆን፣ ማሳየት፣ መያዝ፣
ወይም ማዘዋወር የተከለከለ ነው። ማንኛውም ከላይ ከተገለጸው የተለየ ግልጽ የሆነ ፈቃድ ያስፈልገዋል።
ፈቃድ ምናልባት ድራማዊ ስራዎች እና ለኤግዚቢሽን ሊሰጥ ይችላል። ፈቃድ የሚሰጠው እያንዳንዱን የፈቃድ ጥያቄ
በዲስትሪክቱ የትምህርት ማቴርያሎች ኮሚቴ ሲታይ እና ተቀባይነት ሲያገኝ ነው።
ከ18 አመት በላይ እና ከ 14-18 አመት ያሉ ሰዎች በወላጆች ወይም በአሳዳጊዎች ፈቃድ ራስን ለመከላከል አላማ
በትምህርት ቤት ወስጥ ስፕሬይ መሳሪያዎችን መያዝ ሊፈቀድላቸው ይችላል። ከ 14 አመት በታች ወይም ማንም ከ
14-18 አመት ሆኖ የወላጅ ፈቃድ የለሌው ሰው ምንም የስፕሬይ መሳሪያ ላያደርስ ይችላል። የስፕሬይ መሳሪያዎች
ራስን ከመከላከል ውጪ ጥቅም ላይ ላይውሉ ይችላሉ በግዛቲቱ ህግ ላይ እንደተገለጸው። በሌላ በማንኛውም ሁኔታ
ራስን የመከላከያ ስፕሬይ መሳረያዎች መያዝ፣ ወይም መጠቀም የአውራጃዎን ፖሊሲ መተላለፍ ነው።

የእርምት ርመጃ አወሳሰድ


ሀ. በአጠቃላይ ተግባራዊ የሚሆኑ ድንጋጌዎች
1. እያንዳንዱ ብቃቱ የተረጋገጠ መምህር፣ የትምህርት-ቤት አስተዳዳሪ፣ የትምህርት-ቤቱ ባስ ሹፌር፣ እና
ማንኛውም በዳሬክተሮች ቦርድ የተመደበ ሌላ የትምህርት-ቤቱ ተቀጣሪ ሰራተኛ የሚከተሉትን የማድረግ
ስልጣን አለ: (1) በኣሰራር ቁጥር 3240P የሚገኙ የዲስትሪክቱ ደንቦችን የሚጥሱ ስነምግባር ጉድለቶች ያሳየ
ተማሪ ላይ የዲሲፕሊን ቅጣት የመጣል እና ለተማሪዎች እና ለወላጆች አመታዊ “የተማሪዎች ግዴታዎች እና
መብቶች መግለጫ” የመስጠት ሀላፊነት አለበት; እንዲሁም (2) በዚሁ አሰራር መሰረት ተማሪን ከመማርያ
ክፍሊ፣ ጉዳይ፣ ወይን ከትምህርት እንቅስቃሴ በድንገት የማስወገድ ስልጣን ኣለዉ።
2. የዳሬክተሮች ቦርድ ለርእሰ-መምህሩ እና/ወይንም ለተወካዩ(ዮቹ) የዲስትሪክቱ ደንቦችን የሚጥሱ
የስነምግባር ጉድለቶች የታዩበት ተማሪ የማገድ እና የማባረር ቅጣት የመጣል ስልጣን ሰጥተዋቸዋል።
እያንዳንዱ ብቃቱ የተረጋገጠለት መምህር ለተፈጸመው የስነምግባር ጉድለት ያስፈልጋል ብሎ ያመነበትን
የማገድም ሆነ የማባረር ቅጣት መጠቆም ይችላል።
3. አንድ አስተማሪ ትምህርት እየሰጠ ባለበት ሰአት የትምህርት-ቤቱ የድሲፕሊን ደንቦችን በመተላለፍ የመማር
ማስተማር ሂደቱ የሚያደናቅፍ የስነምጋር ጉድለት ያሳየ ተማሪውን የትምህርት ክፍለጊዜው እስኪጠናቀቅ
ወይንም ከክፍለጊዜው ለተወሰነ ጊዜ ማግለል ይችላል፣ ይህ የሚሆንው ጉዳዩ በ RCW 28A.600.020 መሰረት
ርእሰ-መምህሩ ወይንም ተወካዩ በጉዳዩ ዙርያ እስኪነጋገሩ ድረስ ነው። “በድንገት የማስወገድ እርምጃ”
በሚለው አርእስት ስር ከተገለጸው የድንገተኛ ሁኔታዎች ውጪ፣ አስተማሪው መጀመሪያ አንድ ወይንም
ከአንድ በላይ እንደ አማራጭ የሚወሰዱ የእርምት አይነቶችን መመኮር አለበት። በተጨማሪ፣ተማሪው
አስተማሪው ሳይፈቅድለት በፈጸመው ስነምግባር ጉድለት ምክንያት ከመማርያ ክፍል በታገደበት ጊዜ ውስጥ
ተመልሶ የመግባት ምብት የለዉም።
4. አካላዊ ቅጣት ማለት ማንኛውም ሆን ተብሎ የሚደረግ በተማሪው አካል ላይ ህመም የሚያስከትል ቅጣት
ሲሆን፣ በስቴት ሕግ እና በቦርድ በሊሲ መሰረት ፈጽሞ የተከለከለ ነው። ልዩ ሁኔታዎች WAC 392-400-235
ላይ ተብራርተዋል።
5. በፖሊሲ 3317 እና አሰራር ቁጥር 3317P ላይ እንደተገለጸው፣ ሁሉም ተማሪዎች ተገቢ ካልሆነ ክልከላ፣
የክልከላ መሳሪያዎች፣ መገለል፣ እና ሌሎች የአካል ቅጣቶች ነጻ መሆን አለባቸው።

7
6. ሁሉም ፈቃድ የተሰጣቸው የስታፍ አባላት አስቀድሞ ከተገለጸው በተጨማሪ የሚከተሉትን የማድረግ
ስልጣን አላቸው:
ሀ. ተማሪዎች የተማሪ ስነምግባር ደንቦች እንዲያከብሩ መጠበቅ።
መ. ቢያንስ በአአመት አንድ ጊዜ የትምህርት-ቤቱ የዲሲፕሊን ስተነዳርዶችን ማዘጋጀት እና/
ወይንም መገምገም እንዲሁም እነዚህን ስተንዳርዶች በእኩልነት ማስፈጸም።
ሐ. በትምህርት-ቤቱ ደንቦች መሰረት ለጥሰቶች የእርምት ቅጣቶችን መጣል።
መ. በከፍተኛ ደረጃ የተረጋጋ የመማር ማስተማር አካባቢ ሁኔታን ያስጠብቃል።
ሠ. በክፍል V ላይ በተገለጹት ሁኔታዎች ላይ በመመስረት ተማሪ ክትምህርት በኋላ
ኣግቶ ማቆየት።
ረ. ለእርምት ቅጣት ምክንያት የሆነው ክስተት መግለጽ እና ኮንፈረንስ ከተዘጋጀ በኋላ ቅሬታ
ከሚያቀርበው አካል ጋር መነጋገር።
g. በዲስትሪክቱ ፖሊሲ 3317 እና የአሰራር ቁጥር 3317P መሰረት የክልከላላ ማግለል፣ እና ሌሎች
ተገቢ የኃይል እርምጃዎች መውሰድ ተማሪው በራሱ ላይ፣ በሌሎች ተማሪዎች ላይ፣ ወይንም
በሌሎች ላይ ልያደርስ ከሚችለው የአካል ጥቃት ወይንም ጉዳት ለመከላል ያስችላሉ።
7. ሁሉም የጠፈቀደላቸው ስታፍ አባላት የሚከተሉትን የማድረግ ሀላፊነት ይኖርባቸዋል:
ሀ. የተማሪዎችን መብቶች መከታተል።
መ. የተማሪዎች የስነምግባር ደንቦችን በፍትሐዊነት፣ በእኩልነት እና ከአድልዎ በጸዳ መልኩ
ማስፈጸም።
ሐ. በርእሰ-መምህሩ ወይንም በሌላ አስተዳዳሪ ጥያቄ ሲቀርብ የማይናቁና ተደጋጋሚ የሖኑ
ጥሰቶች እና/ወይንም ተከታታይ ረብሻዎችን እየመዘገቡ መያዝ።
መ. በመማሪያ ክፍል፣ በአዳራሹ መንገዶች፣ እና በማጫወቻ ቦታዎች ወይንም በሌሎች የቤት-
ትምህርቱ የጋራ ቦታዎች፣ እንዲሁም በባስ ወይንም በሌላ የማጓጓዣ ዘዴዎች (የጉብኝት ጉዞዎችን
ጨምሮ) ተገቢ ሰላማዊ ሁኔታ ማስጠበቅ።
ሠ. ተገቢ የተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ መዝገብ መያዝ እና ሁሉም ከትምህርት የመቅረት
አጋጣሚዎችን ሪፖርት ማድረግ።
ረ. ጥሩ ስነምግባር አርአያ መሆን እና የማንኛውም ተማሪ ስብእና ወይንም የተማሪዎች የቡድን
ክብር የሚነኩ አነጋገሮችን ከመጠቀም መቆጠብ።
የዋሺንግተን አስተዳደራዊ ኮድ (WAC) 392-400-230, -235 እና የተሸሻለው የዋሽንግተን ኮድ (RCW) 28A.600.020 ይመልከቱ።

ለ. በዲስፕሊን ላይ ተግባራዊ የሚሆኑ ድንጋጌዎች


የዲስትሪክቱ ደንቦች የጣሰ ተግባር የፈጸመ ተማሪ ሲኖር ከላይ እንደተገለጸው የዲሲፕሊን ቅጣት ሊጣልበት
ይችላል። ተማሪው ላይ የሚጣለው የዲስፕሊን ቅጣት ተማሪውን አካዳሚክ የትምህርት ደረጃ፣ አይነት፣
ወይንም የምረቃ መስፈርት ከማሳካት የሚያግደው መሆን የለበትም።
የዋሽንግተን አስተዳዳረዊ ኮድ (WAC) 392-400-235 ተመልከት።

8
ሐ. በሁሉም እገዳዎች ላይ ተግባራዊ የሚሆኑ ድንጋጌዎች
1. ተማሪዎች የዲስትሪክት ደንቦች በመጣሳቸው እገዳ ሊጣልባቸው ይችላል። የጥሰቱ ሁኔታ ባህሪይ ከግምት
ውስጥ ሊገባ ይገባል እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የረዥም ጊዜ እግድ ማስጠንቀቂያን መስጠት ይገባዋል
እንዲሁም የተጣለው እግድ ርዝመትም ሊገለፅ ይገባል።
2. ልዩ የስነምግባር ጉድለት ተብለው ከተቀመጡት ውጪ (የአሰራር ቁጥር 3241P ተመልከት)፣ ተማሪው
ከዚህ በፊት ፈጽሞት ለነበረ ተመሳሳይ ጥሰት ለማሻሻል ሲባል ሌላ ተስተካካይ የእርምት ቅጣት ካልተጣለበት
በስተቀር እግድ ሊጣልበት አይችልም።
3. መዋእለህጻናት ላይ የሚማር ተማሪ በአንድ የትምህርት አመት በድምሩ ከአስር (10) የትምህርት ቀናት
በላይ የሚዘለቅ የአጭር ጊዜ እግድ ሊጣልበት አይችልም። ማንኛውም የዚህ አይነት ተማሪ የረዥም ጊዜ
እግድ ሊጣልበት አይችልም። እነዚህ ተማሪዎች በእግድ ምክንያት የትምህርት ደረጃ ወይንም ክረዲት
ሊያመልጠው አይችልም።
የአምስተኛ ደረጃ ተማሪ በአንድ ሰሚስተር ውስጥ በድምሩ ከአስራአምስት (15) የትምህርት ቀናቶች በላይ
የሚዘልቅ የአጭር ጊዜ እግድ ሊጣልበት አይችልም፣ እንዲሁም ተማሪው በአንድ የትምህርት አመት ውስጥ
ከአንድ ሰሚሰተር በላይ አካዳሚያዊ ደረጃ ወይንም ክረዲት እንዲያጣ የሚያስገድድ የረዥም ጊዜ እገዳ
ሊጣልበት አይገባም።
4. መወገድ በተጨማሪ የትምህርት ቤቱ ንብረት የሆኑ፣ የተከረዩ ወይም ቁጥጥ ስር ያለ እውነተኛ እና የግል
ንብረቶች ውስጥ መመዝገብ ወይም መገባትን ማገድን ሊያካትት ይችላል። በተጨማሪ ተማሪ ከአንድ
የትምህርት ክፍለጊዜ ወይንም እንቅስቃሴ ሊታገድ ይችላል።
5. ተማሪዎች በእገዳ ወቅት የትምህርት አገልግሎቶች የሚያገኙባቸው እድሎች ይሰጡዋቸዋል።
6. ሁሉም እገዳዎች እና የእገዳዎቹ ምክንያቶች እገዳው ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ በ 24 ሰአታት ውስጥ በጽሑፍ
ለርእሰ-መምህሩ ወይንም ለተወካዩ ሪፖርት መደረግ አለባቸው።
7. ማንኛውም የታገደ ተማሪ በማንኛውም ሰዓት ዳግም ተመልሶ ለመግባት ማመልከቻ ማስገባት
ይፈቀድለታል። (ካታች ያለው ክፍል IV ይመልከቱ)
8. ትምህርት ቤቱ በቅጥር ግቢ ውስጥ እገዳውን ማኪያሄድ ከፈለገ፣ የትምህርት ቤቱ ፕርንሲፓል ከሌሎች
በአውራጃው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ፖሊሲዎችና አፈጻጸሞች ጋረ የሚመሳሰል የትምህርት ቤት ውስጥ
እገዳ መመሪያ ሊያወጣ ይገባል።
የዋሽንግተን አስተዳደራዊ ኮድ (WAC) 392-400-245, -260 ይመልከቱ።

መ. በአጭር ጊዜ እገዳዎች ላይ ብቻ ተግባራዊ የሚሆኑ ድንጋጌዎች


1. ማንኛው ተማሪ የአጭር ጊዜ እግድ ከመሰጠቱ በፊት ከተማሪው ጋር በሚከተለው መሰረት ስብሰባ
ይከናወናል፦
ሀ. የስነምግባር ጉድለቱ መግለጫ፣ ክሱን የሚያጠናክር ማስረጃ፣ እና ሊወሰድ የሚችለው
የእርምት እርምጃ በቃል ወይንም በጽሑፍ ለተማሪው ይገለጻል።
ለ. ተማሪው/ዋ ማብራሪያ እንዲሰጥ/ትሰጥ እድል ይሰጠዋል/ታል።

9
2. የአጭር ጊዜ እግዱ ከአንደ የቀን መቁጠሪያ ቀን በሚያልፍ ጊዜ የተማሪው/ዋ ወላጅ(ጆች) ወይም
አሳዳጊ(ዎች) የእግዱ ምክንያት እና የእግዱ የጊዜ ገደብ በቃል እና/ወይም በዩናይትድ ስቴትስ ፓስታ ቤት
በኩል ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ በደብዳቤ ይገለፅላቸዋል። እንዲሁም ማሳወቂያው ለወላጅ ወይም
ለአሳዳጊ ከ WAC 392-400-255 በማስከተል መደበኛ ያልሆነ ስብሰባን የሚያሳውቅ ነው እንዲሁም
በስብሰባው ምክንያት የእግዱ ጊዜ የሚቀንስበት ሁኔታም ሊኖር ይችላል።
3. ማንኛውም የአጭር ጊዜ እግድ የተጣለበት ተማሪ፣ በእግድ ላይ በነበረበት ጊዜ ያመለጡት ፈተናዎች
ወይንም ስራዎች በተማሪው ሰሚስተር ውጤት ላይ የማይናቅ ጫና የሚያሳድሩ ከሆነ ወይንም እነዚህ
ፈተናዎች ወይንም ስራዎች ሳይሰራ መቅረቱ የኮርሱ(ሶቹ) ክረዲት ከመቀበል የሚያስቀሩት ከሆነ፣ እነዚህን
ፈተናዎች እና ስራዎች የሚያካክስበት እድል ይሰጠዋል።
የዋሽንግተን አስተዳደራዊ ኮድ (WAC) 392-400-245, -250 ይመልከቱ።

ሠ. በረዥም ጊዜ እገዳዎች እና ማባረሮች ላይ ብቻ ተግባራዊ የሚሆኑ ድንጋጌዎች


1. የረዥም ጊዜ እገዳዎች ወይንም የማባረር እርምጃዎች የሚቆዩበት ጊዜ በግልጽ መገለጽ ያለበት ሲሆነ ከአነድ
አካዳሚያዊ ተርም (90 የትምህርት ቀናት) የሚረዝሙ ግን መሆን የለባቸውም።
2. የረዥም ጊዜ እግዶች ወይንም የማባረር እርምጃዎች “እነደ አማራጭ እርምት” መወሰድ አይችሉም፣ ይህ
ማለት በአሰራር ቁጥር 3240P እና “የተማሪዎች ግዴታዎች እና መብቶች መግለጫዎች” ናይ የተቀመጡ
የተማሪ ስነምግባር ደንቦችን የጣሰ ተማሪ ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ አይችሉም ማለት ነው። እንደአማራጭ
የሚወሰድ የእርምት እርምጃ ተማሪው የሚከተሉት ጥሰቶች በሚፈጽምበት ጊዜ የሚደረጉ አይደሉም:
ሀ. በ RCW 28A.600.420 መሰረት የተከለከለ በትምህርት-ቤት ውስጥ የጦር መሳሪያ ይዞ
መገኘት;
ለ. በ RCW 13.04.155 የተዘረዘረ የወንጀል ሕግ ጥሰት;
ሐ. የ RCW 9A.46.120 (በቡድን ማስፈራራት), RCW 9.41.280 (አደገኛ የጦር መሳሪያዎችን
ትምህርት-ቤት ውስጥ ይዞ መገኘት), RCW 28A.600.455 (የቡድን ወንጀል ላይ መሳተፍ),
RCW 28A.635.020 (ሆን ብሎ ለትምህርት-ቤቱ አስተዳዳሪዎች አልገዛም ማለት ወይንም ከትምህርት-ቤት
አልወጣም ማለት), ወይንም RCW 28A.635.060 (የትምህርት-ቤት ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ) የመሳሰሉ
በሶስተ አመት ውስጥ ሁለት ወይንም ከሁለት በላይ ጥሰቶችን መፈጸም; ወይንም
መ. የሌሎች ተማሪዎች ወይንም የትምህርት ስታፍ ጤንነትን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ባህርይ።
በንኡስ ክፍል (a)-(d) ለተገለጹ ባህርይዎች፣ የረዥም ጊዜ እግድ ወይንም የማባረር እርምጃ ከመወሰዱ በፊት፣
ዲስትሪክቱ እንደ አማራጭ የሚወሰዱ የእርምት ቅጣቶችን ግምት ውስጥ ያስገባል።

3. አንድ ተማሪ ለረዥም ጊዜ ከትምህርት ገበታ ላይ ከመታገዱ ፊት፣ ለአቤቱታ እድል የሚሰጥ በፅሁፍ የቀረበ
ማሳወቂያ በአካል ወይም ምዝገባው በተረጋገጠ ፓስታ ለተማሪው እና ለወላጅ(ጆች) ወይም አሳዳጊ(ዎች)
እንዲደርሳቸው ይደረጋል። ይህ ማስታወቂያ ተማሪው እና የተማሪው/የተማሪዋ ወላጅ(ጆች) ወይንም
ሞግዚት (ቶች) አብዝተው በሚናገሩት ቋንቋ ይቀርብላቸዋል። ማስታወቂያው የሚከተሉትን ብግልጽ
ያስቀምጣል:
ሀ. ተደረገ የተባለው የስነምግባር ችግር እና የጣሳቸው የትምህርት-ቤት ደንቦች;
ለ. ይወሰዳል የተባለው የእርምት እርምጃ;

10
ሐ. መ. ተፈፀመ የተባለውን ጥፋት ለመከራከር የተማሪ የተማሪ ወላጅ አሳዳጊ የመሰማት
መብት); እና
መ. በሶስት (3) የትምህርት ስራ ቀናቶች ውስጥ በማስታወቂያው ላይ ስሙ/ስምዋ
ለተጠቀሰው የዲስትሪክቱ ሰራተኛ ወይንም ወደ ጽሕፈት ቤቱ በጽሑፍ ወይንም በቃል የክስ
መስማት ሂደት ጥያቄ ካልቀረበ፣ ክስ የመስማት ሂደቱ ይቀር እና የቀረቡት የእርምት ቅጣት
ሀሳቦች ተግባራዊ ይሆናሉ።
የዲስትሪክቱ ትምህርት-ቤት በጽሑፍ ከቀረበው ማስታወቂያ ጋር ተያይዞ ሊቀርብ የሚችል ክስ የመስማት
ሂደትን ለማስተናገድ የሚያስችል “የትምህርት-ቤቱ የስራ ቀናት” የጊዜ ሰሌዳ ማካተት አለበት።
4. የተማሪው/ተማሪዋ ወላጅ(ጆች) ወይንም ሞግዚት(ቶች) የእርምት እርምጃዎችን የሚገልጽ ማስታወቂያ
ከተቀበሉበት ቀን አንስቶ በሶስት (3) የትምህርት-ቤቱ የስራ ቀናቶች ውስጥ የክስ መስማት ሂደትን መጠየቅ
ይችላሉ። የክስ መስማት ሂደት ጥያቄ በጊዜው ካልቀረበ፣ የተማሪው ወላጅ(ጆች) ወይንም ሞግዚት(ቶች)
ይግባይ የመጠየቅ መብታቸው መጠቀም እንዳልፈለጉ በመውሰድ፣ ዲስትሪክቱ የእርምት ቅጣቶቹን
የሚገልጸው ማስታወቂያ ከተቀበሉበት ቀን አንስቶ በአራተኛው ቀን ላይ ቅጣቶቹን ተግባራዊ ያደርጋል።
5. ርእሰመምህሩ ወይንም ምክትል ርእሰመምህሩ ተማሪው ላይ የረዥም ጊዜ እግድ ወይንም ድንገተኛ ያልሆነ
የማባረር እርምጃ ከተወሰደበት ቀን አንስቶ፣ ተማሪው ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ ይጠይቅ አይጠይቅ
ግምት ውስጥ ሳይከት፣ እና በማንኛውም መንገድ ተማሪው ወደ ትምህርት-ቤት ከመመለሱ ከአምስት (5)
ቀናቶች አስቀድሞ፣ በ (20) ቀናቶች ውስጥ ከተማሪው እና የተማሪው ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች) ጋር
ተማሪው እንደገና ትምህርት ላይ ማሳተፍን በተመለከተ ምክክር ያደርጋል። እነዚህ የተማሪው ተመልሶ
ትምህርት መጀመርን የሚመለከቱ ውይይቶች ወደ ትምህርት-ቤት እንዲመለስ የሚጠይቀውን አቤቱታ
አይተኩም። (ካታች ያለው ክፍል IV ይመልከቱ)
6. ተማሪውን ለረዥም ጊዜ እገዳ ወይንም የማባረር እርምጃ ያጋለጠው ክስተት ጭምር ግምት ውስጥ
በመክተት ከተማሪው ግላዊ አጋጣሚዎች ጋር የሚሄድ የዳግመ ማሳተፍ እቅድ ይዘጋጃል። በተጨማሪ እቅዱ
ተማሪው ለእገዳ ወይንም ለማባረር እርምጃ አጋልጦት የነበረውን ሁኔታ ለማረም ለሚወስዳቸው አስፈላጊ
እርምጃዎች አጋዥ በሆነ መንገድ ነው መዘጋጀት ያለበት። የመልሶ ማሳተፍ እቅዱ ሲዘጋጅ፣ ተማሪው ታግዶ
ወይንም ተባሮ የሚቆይበት ጊዜ ማሳጠር፣ ሌሎች የእርምት ቅጣት አይነቶች፣ እና የተማሪው አካዳሚያዊ
ስኬት የሚያግዙ እና ተማሪው ለመመረቅ የሚያስችለው ውጤት እንዲያስመዘግብ የሚረዱ ደጋፊ
እንተርቨንሽኖችን ከግምት የከተተ መሆን አለበት። ተማሪው እና የተማሪው ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች)
በሚዘጋጀው የባህል ስስነት እና የባህል ፍላጎቶች ምላሽ ያካተት የመልሶ ማሳተፍ እቅድ ላይ ይሳተፋሉ፣
አስፈላጊ ግብኣት ያቀርባሉ።
የዋሺንግተን አስተዳደራዊ ኮድ (WAC) 392-400-260, -275, -420 እና የተሻሻለው የዋሺንግተን ኮድ
(RCW) 28A.600.015, .022 ይመልከቱ።

ረ. የማባረር እርምጃ ላይ ብቻ የሚተገበሩ ደንጋጌዎች


1. ተማሪዎች የዲስትሪክቱ ደንቦች በመጣሳቸው ሊባረሩ ይችላሉ። የሕግ ጥሰት ሁኔታ እና ፀባይ የተማሪ
መባረር ችግርን አስመልክቶ ዋስትናመስጠት አለበት።
2. ተማሪው ፀባዩን እንዲያስተካክል አስፈላጊ የማስተካከያ እርምጃ ወይም ቅጣት ተሰጥቶ በዚህ መታረም
ካልቻለ በስተቀር ወይም ሌሎች አስፈላጊ የማስተካከያ እርምጃ ወይም ቅጣት ተጥሎ ተማሪው ሳይታረም
ካልቀረ በስተቀር ምንም አይነት ተማሪ አይባረርም።

11
3. መወገድ በተጨማሪ የትምህርት ቤቱ ንብረት የሆኑ፣ የተከረዩ ወይም ቁጥጥ ስር ያለ እውነተኛ እና የግል
ንብረቶች ውስጥ መመዝገብ ወይም መገባትን ማገድን ሊያካትት ይችላል። በተጨማሪ ከአንድ የትምህርት
አይነት ክፍለጊዜም ሊባረር ይችላል።
4. ተማሪዎች ተባረው በሚቆዩበት ጊዜ የትምህርት አገልግሎቶች የሚያገኙበት እድል ሊሰጣቸው ይችላል።
5. ሁሉም የማባረር እርምጃዎች እና ምክንያቶቻቸው የማባረር እርምጃው በተወሰደ በ 24 ሰአታት ውስጥ
ለርእሰ-መምህሩ ወይንም ለተወካዩ ሪፖርት መደረግ አለባቸው።
6. ማንኛውም ከትምህርት ቤት የተባገረ ተማሪ በማንኛውም ጊዜ ለመልሶ ቅበላ ማመልከት ይችላል። (ከታች
ያለው ክፍል IV ይመልከቱ።)
7. የህንጻው ርእሰ-መምህር ወይንም ምክትሉ የማባረር እርምጃው መራዘሙ የህዝቡ ጤና እና ደህንነት
ከስጋት የሚታደግ በመሆኑ ከአንድ የትምህርት ተርም (90 የትምህርት ቀናቶች) በላይ እንዲራዘም ለከፍተኛ
ሀላፊው አቤቱታ ማቅረብ ይችላል።
ሀ. አቤቱታው ድንገተኛ ያልሆነው የማባረር እርምጃ በተጣለበት የመጨረሻው ቀን እና የማባረር
ቅጣቱ የሚበቃበት የመጨረሻው ቀን መካከል በማንኛውም ጊዜ ሊቀርብ ይችላል።
ለ. አቤቱታው የግድ WAC 392-400-410 ላይ የተዘረዘሩት ነጥቦችን ያካተተ መሆን አለበት።
ሐ. አቤቱታው ግልባጭ በአካል ወይንም ሕጋዊ እውቅና ባለው ፖስታ ቤት አማካኝነት
ለተማሪው እና ለተማሪው/ተማሪዋ ወላጅ(ጆች) ወይንም ሞግዚት(ቶች) መቅረብ አለበት።
መ. ተማሪው እና ለተማሪው/ተማሪዋ ወላጅ(ጆች) ወይንም ሞግዚት(ቶች) አቤቱታው
ከተቀበሉበት ቀን አንስቶ በ (10) የትምህርት-ቤቱ የስራ ቀናቶች ውስጥ ለአቤቱታው በጽሑፍ ወይንም በቃል
ምላሽ መስጠት ይችላሉ።
ሠ. ተማሪው በአንድ የአካዳሚክ ተርም (90 የትምህርት ቀናት) ውስጥ ወይንም በኋላ ወደ
ትምህርት ቢመለስ የህዝቡ ጤና ወይንም ደህንነት አደጋ ውስጥ ይከታል የሚለው
አቤቱታ በአሳማኝ ማስረጃ የታጀበ እስከሆነ ድረስ ከፍተኛ ሀላፊው የእርምጃው መራዘም የሚጠይቀው
አቤቱታ የማጽደው ስልጣኑ ተጠቅሞ ሊያራዝመው ይችላል። ከፍተኛ ሀላፊው አቤቱታው ለተማሪው
እና ለተማሪው/ተማሪዋ ወላጅ(ጆች) ወይንም ሞግዚት(ቶች) ከቀረበበት ቀን አንስቶ ባሉት አስራአንድ
(11) ቀናቶች ውስጥ ወይንም በጣም ዘገየ ቢባል በሃያ (20) የትምህርት-ቤት ስራ ቀናት ውስጥ የማራዘም
አቤቱታው ተቀባይነት ማግኘቱ ወይንም ውድቅ መሆኑን ያሳውቃል። ውሳኔው በ WAC 392-400-310 እና
-315 ስር የሰፈሩት የሁሉም መብቶች እና የይግባኝ አሰራሮች መገልጫ ጭምር የያዘ መሆን አለበት።
ረ. አቤቱታው ከጸደቀ፣ የተማሪው እና የተማሪው ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች) ውሳኔውን
በመቃወም በአስር (10) የትምህርት-ቤቱ የስራ ቀናቶች ውስጥ ለዳሬክተሮች ቦርድ ይግባኝ ማለት
ይችላል።
የዋሺንግተን አስተዳደራዊ ኮድ (WAC) 392-400-275, -410 እና የተሻሻለው የዋሺንግተን ኮድ (RCW) 28A.600.015, .020
ይመልከቱ።

G. በድንገት የማባረር እርምጃ ላይ ብቻ ተግባራዊ የሚሆኑ ድንጋጌዎች


1. የአንድ ተማሪ መማርያ ክፍል ውስጥ መኖር በተማሪዎች፣ የትምህርትቤቱ ሰራተኞች፣ የሚፈጥረው
ቀጥተኛና ቀጣይነት ያለው አደጋ፣ ወይም በትምህርትቤቱ የትምህርት ሂደት ላይ ሊፈጥረው የሚችል

12
ቀጥተኛና ቀጣይነት ያለው የማስተጓጎል ስጋት መኖሩ የሚያሳዩ ምልክቶች ካሉ አስተማሪው ተማሪውን
ከከፍል ማስወጣት ይችላል።
2. ከክፍል ማስወጣቱ የሚቀጥለው: (ሀ) አደጋው ዛቻው እስከሚያቆም; መ) ርእሰመምህሩ ወይም
ትምህርትቤቱ የወከለው አካል የእርምት እርምጃ ይወስዳል።
3. የተመደበው የትምህርት-ቤቱ ባለስልጣን ከተማሪው ጋር በፍጥነት መገናኘት ያለበት ሲሆን፣ ግን በፍጹም
ማስወጣቱ ተጠነናቆ ትምህርት ከተጀመረ በኋላ መሆን የለበትም፣ ከዛ አስፈላጊው የእርምት እርምጃ
መውሰድ አለበት።
4. ተማሪው ወደ መማሪያ ክፍል፣ የትምህር አይነት፣ ወይንም እንቅስቃሴ ከመመለሱ በፊት፣ የተመደበው
የትምህርት-ቤቱ ባለስልጣን ተማሪውን ላባረረው አስተማሪ ወይንም አስተዳዳሪ ያሳውቃል።
የዋሺንግተን አስተዳደራዊ ኮድ (WAC) 392-400-290.

H. በድንገት የማባረር እርምጃ ላይ የሚተገበሩ ድንጋጌዎች


1. የተማሪው በትምህርት-ቤት መኖር በተጨባጭ በተማሪው፣ በሌሎች ተማሪዎች፣ ወይንም በትምህርት-ቤቱ
ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ እና ቀጣይነት ያለው አደጋ ሊያስከትል ይችላል ተብሎ ሲታሰብ ወይንም በትምህርት
ሂደት፣ አይነት፣ እንቅስቃሴ፣ ወይንም የትምህርት ሂደት ላይ ከፍተኛ እና ቀጣይነት ያለው ስጋት ወይንም
የማስተጓጎል ችግር ይፈጥራል ተብሎ ሲታመን ተማሪው በቀጥታ በከፍተኛ ሀላፊው/ተወካዩ አማካኝነት
ሊባረር ይችላል።
2. ተማሪው ለአስር (10) ተከታታይ የትምህርት ቀናት ተባሮ ከቆየ በኋላ በድንገት የማባረር ቅጣቱ በከፍተኛ
ሀላፊው/ተወካዩ አማካኝነት ያበቃል ወይንም ወደ ሌሎች የቅጣት አይነቶች ይቀየራል። የማባረር ቅጣቱ ወደ
ሌሎች የቅጣት አይነቶች ሲቀየር ከዚሁ የቅጣት አይነት ጋር የሚያያዘው ማስታወቂያ እና የሂደቱ መብቶች
አብረው መቅረብ አለባቸው።
3. ተማሪው እና የተማሪው ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች) በድንገት የማባረር እርምጃው ይነገራቸዋል እንዲሁም
የይግባኝ እድል እንዳላቸው እንዲያውቁ ይደረጋል: (a) ለወላጁ(ጆቹ) ወይንም ሞግዚቱ(ቶቹ) በሀያ አራት
ሰአት (24) ውስጥ በድንገት የማባረር እርምጃውን በተመለከተ በአካል ወይንም በጽሁፍ ማስታወቂያ
ይደርሳቸዋል፣ እንዲሁም ለወላጁ(ጆቹ) ወይንም ሞግዚቱ(ቶቹ) ማስታወቂያው መቀበላቸውን በፊርማቸው
ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል; ወይንም (b) በድንገት የማባረር እርምጃው ከተወሰደ በሃያአራት (24) ሰአታት
ውስጥ ማረጋገጫ የተደረገላቸው ደብዳቤ(ዎች) በፖስታ ቤት በመላክ፣ እንዲሁም በተቻለ ፍጥነት መሰረት
ለተማሪው እና የተማሪው ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች) በስልክ ወይንም በአካል ለማሳወቅ ተገቢ ሙከራዎችን
ማድረግ።
4. ይህ የጽሑፍ ወይንም የቃል ማስታወቂያ ተማሪው እና የተማሪው ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች) አብዝተው
በሚጠቀሙት ቋንቋ መቅረብ ያለበት ሲሆን የሚከተሉትን ምግለጽ አለበት:
ሀ. የተማሪው መኖር በተማሪዎች፣ የትምህርትቤቱ ሰራተኞች፣ የሚፈጥረው ቀጥተኛና ቀጣይነት
ያለው አደጋ፣ ወይም በትምህርትቤቱ የትምህርት ሂደት ላይ ሊፈጥረው የሚችል ቀጥተኛና ቀጣይነት ያለው
የማስተጓጎል ስጋት መኖሩ የሚያሳዩ ምክንያቶች በግል ተለይተው መቅረብ አልባቸው;

13
ለ. አስቸኳይ መባረሩ የሚጀመርበትና የሚያበቃበት ቀን በግልጽ መቀመጥ አለበት;
ሐ. የተፈፀመውን ድርጊት በተቻለ መጠን በአስቸኳይ ለመከላከል ተማሪው እና/ወይም የተማሪው
ወላጅ (ጆች) አልያም አሳዳጊ (ዎች) ለችሎቱ የሚያቀርቡትን ማስቀመጥ;
መ. የይግባኝ ጥያቄ ማስታወቂያው ከተቀበሉበት ቀን አንስቶ በሶስተኛው የትምህርት-ቤቱ የስራ
ቀን በጽሑፍ ወይንም በቃል ለተመደበው የዲስትሪክቱ ሰራተኛ መቅረብ አለበት;
ሠ. ጥያቄው በሶስት (3) የትምህርት-ቤቱ የስራ ቀናቶች ውስጥ ካልደረሰ፣ በድንገት የማባረር
እርምጃው በአጠቃላይ ለአስር (10) የትምህርት-ቤቱ የስራ ቀናቶች ይቀጥላል; እንዲሁም
ረ. በድንገት የማባረር እርምጃው በአስር (10) የትምህርት-ቤቱ የስራ ቀናቶች ውስጥ ወደ ማባረር፣
የአጭር ወይንም የረዥም ጊዜ እግድ፣ ወይንም ሌላ የእርምት እርምጃ ሊቀየር ይችላል፣ ከዛም
የተቀየረው እርምጃ እና ይግባኝ የመጠየቅ መብት የሚገልጽ ማስታወቂያ ይቀርባል።
የዋሺንግተን አስተዳደራዊ ኮድ (WAC) 392-400-295.

I. ተቀባይነት በሌላቸው ማርፈዶች እና ከትምህርት መቅረቶች ላይ የሚተገበሩ የእርምት እርምጃ ድንጋጌዎች


1. በምዕራፍ 28A.225 RCW መሰረት ትምህርት-ቤት ላይ የመማር ግዴታ ያለበት ተማሪ ያለአሳማኝ
ምክንያት አንድ ወይንም ሁለት ጊዜ ክትምህር ቢቀር፣ የተማሪውን ባህሪ ለማስተካከል ይረዳሉ ተብሎ
የሚታመንባቸው የእርምት እርምጃዎች ይወሰዱበታል። ዲስትሪክቱ በእንድ ወይንም ከንድ በላይ ተገቢ
ያልሆኑ ክትምህርት የመቅረት አጋጣሚዎች የእርምት እርምጃ ከወሰደ፣ የሚከተሉትን ማድረግ ይጠበቅበታል:
ሀ. ለተማሪው እና የተማሪው ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች) በእንግሊዘኛ፣ ወይንም ዋናው
ቋንቋቸው ሌላ ከሆነ በሌላ ቋንቋ ማስታወቂያ መስጠት
ይህ ማስታወቂያ ተማሪው ያለአሳማኝ ምክንያት ከትምህርት መቅረቱን ለወላጁ(ጆቹ) ወይንም
ለሞግዚቱ(ቶቹ) ያሳውቃል;
ለ. ከተማሪው ቤተሰብ / ቤተሰቦች ወይም አሳዳጊ / አሳዲጊዎች ወይም ሞግዚት / ሞግዚቶች
መርሃ ግብር የተያዘ ስብሰባ / ስብሰባዎች እንዲሁም ተማሪው ለሁሉም የሚመች ጊዜ እና ሰአት
የተማሪ የትምህርት ቤት መቅረት ምርመራን ጨምሮ እንዲሁም ለልዩ ትምህርት ወይም ሌላ
ልዮ ፕሮግራም ትኩረት መስጠት የሚገባ እና የማይገባ መሆኑን ለመወሰን የሚደረግ ምርመራን
ጨምሮ፤ እና
ሐ. የተማሪውን/ዋን ከትምህርት ቤት መቅረት ለመቀነስ አርምጃዎች ተወስደዋል፣ እርምጃዎቹም
የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፣ አግባብ በሚኖረው ጊዜ፣ በትምህርት ቤት ውስጥ ባሉ ባለስልጣናት ውሳኔ እና
በሚቻል ጊዜ ከተማሪ፣ ከወላጅ (ጆች) ወይም ከአሳዳጊ(ዎች) ወይም በህጋዊ መልኩ ላስጠጉዋቸው አሳዳጊ
ወላጅ(ጆች) በመወያየት፣ የተማሪው/ዋ ከትምህርት ቤት መቅረትን ለማካካስ የተማሪን የትምህርት ቤት
ፕሮግራም ወይም የትምህርት ቤት ኮርስ መደባን አልያም ለተማሪ ወይም ለወላጅ አጋዥ አገልግሎቶችን
እንዲያገኙ ማገዝ።
2. እነድ ተማሪ በአንድ የተምህርት አይነት የሚያመጣው አካዳሚያዊ ውጤት ወይንም ክረዲት ወደ
ትምህርት አርፍዶ በመድረስ ወይንም ከትምህርት በመቅረት በእጅጉ ሊጎዳ የሚችለው:

14
ሀ. የተማሪው ተሳትፎ ከትምህርት አይነቱ አላማዎች ወይንም ግቦች ጋር ግንኙነት ሲኖረው;
መ. አስተማሪው በዲስትሪክቱ ፖሊሲ መሰረት የተማሪው የትምህርት ተሳትፎ ሙሉ በሙሉ
ወይንም በተወሰነ ደረጃ ግሩድ አሰጣጥ ላይ ግምት ውስጥ እንደሚገባ ካስቀመጠ; እንዲሁም
ሐ. ተማሪው ወደ ትምህርት-ቤት እንዳይሄድ የሚያደናቅፉት ሁኔታዎችም ግምት ውስጥ ይጋሉ፣
ማለት ማርፈዱ ወይንም ከትምህርት መቅረቱ በክፍል 504 የመልሶ ማቋቋም ድንጋጌ 1973፣ አርእስት II
ወይንም አካል ጉዳተኛ አሜሪካኖች ድንጋጌ፣ ወይንም የአካል ጉዳተኞች ትምህርት ድንጋጌ በተቀመጠው
መሰረት በቀጥታ ከአካል ጉዳቱ ጋር ግንኙነት ያለው እንደሆነ ይፈተሸል።
3. አንድ ተማሪ ሳይፈቀድለት በማርፈዱ ወይንም ከትምህርት በመቅረቱ ምክንያት ለረዥም ጊዜ ሊታገድ
ወይንም ሊባረር አይችልም።
የዋሺንግተን አስተዳደራዊ ኮድ (WAC) 392-400-233።

የእርምት እርምጃዎችን የመቃወም አሰራሮች


ሀ. የዲስፕሊን እና የአጭር ጊዜ እገዳዎች ቅሬታ አቀራረብ አሰራር
ማንኛውም በእርምት እርምጃው ወይንም በአጭር ጊዜ እግዱ የማይስማማ ተማሪ ወይንም ወላጅ/ሞግዚት
ከህንጻው ርእሰ-መምህር ወይንም ተወካይ ጋር መደበኛ ባልሆነ መንገድ በመገናኘት ቅሬታውን የማቅረብ
መብት አለው። አቤቱታ የሚቀርብበት ሰራተኛ ምክንያታዊ በሆነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ስለ አቤቱታውን
በተመለከተ እንዲያውቅ/እንድታውቅ ይደረጋል። በዚህ ስብሰባ ጊዜ፣ ተማሪው እና የተማሪው ወላጅ(ጆች)
ሞግዚት(ቶች) በርእሰ-መምህሩ ወይንም በምክትሉ የመጤቅ እንዲሁም እነሱም ጉዳዩን ለሚመለከተው
ሰራተኛ ጥያቄ የማቅረብ መብት አላቸው።
ከዚህ በትምህርት-ቤት ደረጃ የሚደረገው ስብሰባ በኋላም ይህ ቅሬታ መፍትሄ ሳያገኝ ከቀረ፣ ተማሪው እና
የተማሪው ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች)፣ ወደ ከፍተኛ ሀላፊው ጽሕፈት-ቤት አቤቱታዎ ከማቅረብዎ በፊት
ሁለት (2) የስራ ቀናቶችን በመስጠት፣ ቅሬታዎ በጽሑፍ እና/ወይንም በቃል ለከፍተኛ ሀላፊው ወይንም
ለተወካዩ ማቅረብ ይቻላላ።
ችግሩ በዛ ደረጃም ቢሆን ሊፈታ ካልቻለ፣ ተማሪው እና የተማሪው ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች)፣ ወደ
ከፍተኛ ሀላፊው ጽሕፈት-ቤት አቤቱታዎ ከማቅረብዎ በፊት ሁለት (2) የስራ ቀናቶችን በመስጠት፣ ቅሬታዎ
በጽሑፍ እና/ወይንም በቃል በቀጣዩ የቦርዱ መደበኛ ስብሰባ ወቅት ለዳሬክተሮች ቦር ማቅረብ ይቻላላ።
ቦርዱ ከስብሰባው ቀን በኋላ በአስር የስራ ቀናት ውስጥ የአቤቱታውን ምላሽ ለተማሪው/ዋ፣ ለወላጅ፣ ወይም
ለአሳዳጊ ያቀርባል።
ርእሰ-መምህሩ ወይንም የእሱ/የእስዋ ምክትል እርምጃውን እንዲቋረጥ ካላዘዘ በስተቀር፣ ቅሬታው
በሚታይበት ሂደትም የአጭር ጊዜ እግዱን ተግባራዊ ሆኖ ይቀጥላል።
የዋሺንግተን አስተዳደራዊ ኮድ (WAC) 392-400-240, -255።

ለ. የረዥም ጊዜ እግድ፣ የመባረር እርምጃ፣ እና ድንገተኛ የማባረር እርምጃ በመቃወም ይግባኝ የመጠየቅ
ሂደት
ማንኛውም የረዥም ጊዜ እግዱ ወይንም የማባረር እርምጃውን የሚቃወም ተማሪው እና የተማሪው

15
ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች) ውሳኔውን ለማስቀየር ክስ መመስረት ይችላል። የከፍተኛ ሀላፊው ጽሕፈት-ቤት
የእርምት እርምጃው የተወሰነበት ቀን የሚያሳውቀው ማስታወቂያ ከተቀበሉበት ቀን በሶስት (3) የምህርት-
ቤቱ የስራ ቀናቶች የይግባኝ ጥያቄ ሊቀርብለት ይገባል። የይግባኝ ጥያቄ በወቅቱ ከቀረበ፣ ዲስትሪክቱ የይግባኝ
ጥያቄው በዲስትሪክቱ እጅ ከገባበት ቀን አንስቶ ባሉት ሶስት (3) የስራ ቀናቶች ውስጥ (በድንግት የማባረር
እርምጃ ከሆነ ደግሞ በሁለት (2) የትምህርት-ቤቱ የስራ ቀናቶች ውስጥ) ክሱን ለማየት የሚያስችል የጊዜ
ሰሌዳ ያስቀምጣል።

ተማሪው በሕግ አማካሪ የመወከል፣ ለምስክሮች በጥያቄዎች የማፋጠት፣ ተፈጸመ የተባለው ስነምግባር
ጉድለት መግለጫ የማቅረብ፣ እንዲሁም አስፈላጊ ማስረጃዎችን የማቅረብ መብት አለው።
ተማሪውም ሆነ የዲስትሪክቱ ተወካይ ችሎቱ ከመከፈቱ በፊት ተቃራኒው ወገን ለክሱ ሂደት የሚያቀርባቸው
የሰነድም ሆነ የሰው ማስረጃዎችን የመፈተሸ መብት አላቸው።
ክሱን ለመስማት በዲስትሪክቱ የቀረበው ሀላፊ ምስክር ሊሆን አይችልም፣ የተጠቀሱት የስነምግባር ጉድለቶቹ
እውነትነት በችሎቱ ላይ በሚቀርቡ ማስረጃዎች ብቻ ነው የሚረጋገጠው።
በቴፕ የተቀረጸ ወይም የቃል ሪከርድ መስሚያ ይዘጋጃል። ክስ የሚሰማው ሀላፊ የተገኙት እውነታዎች፣
ድምዳሜዎች፣ እና የእርምት እርምጃው ባህሪ እና ቆይታ ግምት ውስጥ በማስገባት ውሳኔውን በጽሑፍ
ማሳወቅ ይችላል። ለረዥም ጊዜ የእግድ እና የማባረር እርምጃዎች፣ ይህ በጽሑፍ የተዘጋጀ ውሳኔ ለተማሪው
የሕግ አማካሪ፣ ወይንም ለተማሪው እና የተማሪው ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች) መስጠት አለበት። በድንገት
የማባረር እርምጃዎች በሚመለከት ደግሞ፣ ውሳኔው የግድ: (1) ችሎቱ ከተዘጋበት ቀን አንስቶ በአንድ
የትምህርት-ቤቱ የስራ ቀን ውስጥ መውጣት አለበት; (2) ማረጋገጫ የተደረገበት ደብዳቤ ፖስታ ውስጥ
በመክተት ለተማሪው እና የተማሪው ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች) ወይንም ለተማሪው የሕግ አማካሪ መሰጠት
አለበት; (3) በተማሪዎች፣ የትምህርትቤቱ ሰራተኞች፣ የሚፈጥረው ቀጥተኛና ቀጣይነት ያለው አደጋ፣ ወይም
በትምህርትቤቱ የትምህርት ሂደት ላይ ሊፈጥረው የሚችል ቀጥተኛና ቀጣይነት ያለው የማስተጓጎል ስጋት
ማብቃቱን መግለጽ አለበት; እንዲሁም (4) በድንገት የማባረር እርምጃው በሌላ እርምት ቅጣት የሚቀየር
ስለመሆኑ እና አለመሆኑ መግለጽ አለበት።
የይግባኝ ጥያቄ ካልቀረበ በስተቀር፣ ማንኛውም በክስ ሰሚው ሀላፊ የተወሰነው የረዥም ጊዜ እግድ ወይንም
ድንገተኛ ያልሆነ የማባረር እርምጃ የክስ ሰሚው ሀላፊ ውሳኔ የተሰጠበት ቀን ተከትሎ በሚቀጥለው
የትምህርት-ቤቱ የስራ ቀን ተግባራዊ ይሆናል።
የዋሺንግተን አስተዳደራዊ ኮድ (WAC) 392-400-265, -270, -280, -285, -300, -305 ይመልከቱ።
ሐ. የክስ ሰሚው ሀላፊ የረዥም ጊዜ እግድ፣ ማባረር፣ ወይንም በድንገት የማባረር እርምጃ ውሳኔ በመቃወም
ይግባኝ ማቅረብ

ተማሪው እና የተማሪው ወላጅ(ጆች) ሞግዚት(ቶች) የክስ ሰሚው ሀላፊ የረዥም ጊዜ እግድ፣ ማባረር፣
ወይንም በድንገት የማባረር እርምጃ ውሳኔ በመቃወም ወደ ዳሬክተሮች ቦርድ ይግባኝ ማቅረብ ይችላሉ።
ተማሪው የሀላፊውን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ መጠየቅ እንደሚፈልግ የሚገልጽ ማስታወቂያ የሀላፊውን
ውሳኔ ማስታወቂያ ከተቀበሉበት ቀን አንስቶ በሶስት (3) የትምህርት-ቤቱ የስራ ቀናቶች ውስጥ በቃል ወይንም
በጽሑፍ ለከፍተኛ ሀላፊው ጽሕፈት-ቤት ወይንም ለክስ ሰሚው ጽሕፈት-ቤት ማስረከብ ያስፈልጋል።

ወቅቱ የጠበቀ ይግባኝ ለቦርዱ ከቀረበ፣ እግዱ ወይንም ድንገተኛ ያልሆነው የማባረር እርምጃው የይግባይ

16
ጥያቄው ውሳኔ እስኪያገኝ ለአስር (10) ተከታታይ የትምህርት ቀናቶች ይጸናል። ማናቸውም ይግባኝ ጥያቄው
ውሳኔ ከማግኘቱ በፊት ተማሪው የታገደባቸው ቀናቶች ከተወሰደው የእግድ ወይንም የማባረር እርምጃ ላይ
ይደመራሉ፣ እናም የእግድ ወይንም የማባረር እርምጃውን ማሳነስም ሆነ ማስፋት አይችሉም። ማንኛውም
ታግዶ የነበረ እና የይግባኝ ጥያቅው ውሳኔ ሳይሰጠው ወደ ትምህርት የተመለሰ ተማሪ በእግድ ላይ በነበረበት
ጊዜ ያመለጡት ፈተናዎች ወይንም ስራዎች በተማሪው ሰሚስተር ውጤት ላይ የማይናቅ ጫና የሚያሳድሩ
ከሆነ ወይንም እነዚህ ፈተናዎች ወይንም ስራዎች ሳይሰራ መቅረቱ የኮርሱ(ሶቹ) ክረዲት ከመቀበል
የሚያስቀሩት ከሆነ፣ እነዚህን ፈተናዎች እና ስራዎች የሚያካክስበት እድል ይሰጠዋል።
የይግባኝ ጥያቄ በወቅቱ ከቀረበ፣ ቦርዱ የይግባኝ ጥያቄው ከቀረበበት ቀን አንስቶ ባሉት ሶስት (10) የስራ
ቀናቶች ውስጥ ጉዳዩን ለመገምገም በደመኛ ያልሆነ ኮንፈረንስ ያዘጋጃል። የስብሰባው አላማ ለይግባኙ
መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችሉ ተገቢ ዘዴዎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መምክር ነው።
ተማሪው ወይም የተማሪው ወላጅ (ጆች) ወይም አሳዳጊዎች አልያም ህጋዊ አማካሪዎች የመስማት መብት
ይሰጣቸዋል፣ እንዲሁም ቦርደ በሚፈልገው ሁኔታ መሰረት ይህንን የሚያረጋግጡላቸውን ምስክሮች
የማቅረብ እድል ይሰጣቸዋል። ቦርዱ ከቀጠሮ በፊት ከዚህ በታች የተገለጹትን ሂደቶች ያስማማል፦
1. የቀረቡትን የተሰማው ጉዳይ ሪከርድ ሌላ ነገርን ያጠናል እንዲሁም ከአስቸኳይ ስብሰባ ባሉት አስር
የትምህርት ቀናት ውሳኔን ይሰጣል;
2. በቦርዱ ሪከርድ መሰረት ተጨማሪ ክርክሮችን ለመስማት ቀጠሮ በመያዝ ስብሰባን ይጠራል እንዲሁም
ከአስቸኳዩ ስብሰባ ቀን በኋላ ባሉት አስራ አምስት የትምህርት ቀናት ጊዜ ውስጥ ውሳኔን ይሰጣል; ወይም
3. ጉዳዩን ሰምቶ ውሳኔ ለመስጠት ካስቸኳይ የስብሰባ ቀናት በኋላ ባሉት አስር የትምህርት ቤት ቀናት በኋላ
ቀጠሮ በመያዝ ስብሰባን ይጠራል።
Iቦርዱ ይግባኙን ከመጀመሪያው ለመስማት በሚመርጥበት ጊዜ፣ ተማሪው በችሎቱ ፊት ከሚቀርቡት አካላት
ጋር እኩል መብት አለው።

ለቦርዱ የሚቀርበው የይግባኝ ጥያቄ በ WAC 392-400-310, -315, and -320 መሰረት ነው የሚካሄደው።
ማንኛውም በተማሪው ላይ የተወሰነው የዲሲፕሊን ቅጣት፣ እግድ ወይንም የማባረር እርምጃ ለማጽናት፣
ለመቀየር፣ ወይንም ለማሻሻል በቦርዱ የተሰጠ ውሳኔ፣ ማስረጃዎችን በሰሙ ወይንም ባነበቡ የቦርዱ
አባላት፣ እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ምስክር ሆነው ባልቀረቡ የቦርዱ አባላት እንዲሁም የቦርዱ ምልአተጉባኤ
በተረጋገጠበት በአብላጫ የቦርዱ አባላት ድምጽ ነው የሚወሰነው።
የቦርዱን ውሳኔ ከተቃወሙ ወደ ፍርድቤት ነው ይግባኝ ማለት የሚችሉት። ቦርዱ ይህ የይግባኝ ጥያቄ
በሂደት ባበት ጊዜ የእርምት እርምጃውን ለጊዜው እንዲቋርጥ ማድረግ ይችላል።
የዋሽንግተን አስተዳደራዊ ኮድ ይመልከቱ (WAC) 392-400-310, -315, -317, -320።

በእግድ ወይንም የማባረር እርምጃ በተወሰደበት ጊዜ መልሶ ትምህርት መጀመር

17
ማንኛውም የታገደ ተማሪ በማንኛውም ሰዓት ዳግም ተመልሶ ለመግባት ማመልከቻ ማስገባት ይፈቀድለታል።
ማመልከቻው ተማሪው ሊማርበት ለሚፈልገው ትምህርት ቤት ርእሰመምህር ይገባል። ማመልከቻው ማካተት ያለበት
ሀ. ተማሪው መመለስ የፈለገበትን እና ጥያቄ መጤን የሚኖርበትን ምክንያት
መ. ጥያቄውን የሚያጠናክር ማስረጃ;
ሐ. ተማሪዎቹን ከደገፉት ወላጆች ወይም ሌሎች አካሎች የድጋፍ መግለጫ;
መ. ተማሪው ትምህርቱ ለመቀጠል ጥረቶች እያደረገ መሆኑ የሚያሳዩ ማስረጃዎች;
ሠ. ለጥፋቱ ማካካሻ በበጎ ፈቃድ ስራዎች እና ጥረቶች ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየቱን የሚገልጽ ማስረጃ; እና
ረ. የማባረር እርምጃው ከአደንዛዥ ዕጽ ወይንም ከአልኮል ጋር የተያያዘ ከሆነ፣ የአደንዛዥ ዕጽ እና የአልጎል ግምገማ
ቅጂ እና በግምገማው ላይ የቀረቡ ምክረሀሳቦች ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ።
ርእሰመምህሩርእሰመምህሩ ማመልከቻውን መቀበል፣ ከበላይ ሃለፊ ጋር መወያየት እና ውሳኔውን ለወላጆች እና
ለተማሪ በጽሁፍ ማመልከቻውን በተቀበለ በአምስት (5) የትምህርት ቤት የስራ ቀናት ውስጥ ማሳወቅ አለበት። ዳግም
ምዝገባ ርእሰመምህሩ በሚያቀርባቸው በማናቸውም ምክንያታዊ ሃሰቦች ላይ የተመሰረተ ነው።
ወደ ትምህርት የመመለስ ሂደቱ በስቴት ሕግ ምእራፍ ከተቀመጠው በዲስትሪክቱ የሚካሄዱ የመልሶ መግባባት
ስብሰባዎች 28A.600 RCW ፈጽሞ የተለየ ነው። (ከላይ ያለው ክፍል II ይመልከቱ።)

መታሰር
ለጥቃቅን የትምህርት ቤት ህግ፣ መመሪያዎች መተላለፍ፣ ወይም መጠነኛ ጥፋት ሰራተኛው ተማሪውን የትምህርት
ሰአት ከበቃ የቅድሚያ የወላጅ ፈቃድ ሳይጠየቅ በኋላ ከሁለት ሰአት ላልበለጠ ጊዜ መቆየት ይችላል። ወላጆች
ተማሪዎች ለእርማት ርምጃ ከትምሀርት ሰአት በኋላ በእስራት ከቆዩ በኋላ አስፈላጊውን መጓጓዣ ለተማሪው/ዋ
እንዲያዘጋጁና የእስራቱን አለማ እንዲረዱ ለወላጀች ሳይነገር እስራት መጀመር የለበትም (ለአቅመ አዳም የደረሱ
ተምሪዎቸ ካልሆኑ በቀር)።
እንደዚህ አይነት የማስተካከያ ርምጃ በሚወሰድበት ጊዜ ቅጣት የተላለፈበትን የጥፋቱን ባህሪ እና ጥሰቱ የተከሰተበትን
ትክክለኛ ተግባር ሰራተኛው ለተማሪው ማሳወቅ አለበት። ተማሪው/ዋ ሰለድርጊተ/ቷ ለሰራተኛው እንዲያስረዳ/
እንድታሰረዳ እድል መሰጠት ይገባል። ለእርምት ርምጃ የታሰረ በሰራተኛ ወይም ሌላ ባለሞያ የሆነ የስራ በልደረባ
ቀጥታ ክትትል ስር መሆን አለበት። ተማሪው በእነዚህ የእርምት እርምጃዎች የሚያሳልፈው ጊዜ አናጺ በሆነ መንገድ
ጥቅም ላይ ይውላል።

በትምህርት ቤት ውስጥ እገዳ


ትምህርት ቤቱ በቅጥር ግቢ ውስጥ እገዳውን ማኪያሄድ ከፈለገ፣ የትምህርት ቤቱ ፕርንሲፓል ከሌሎች
በአውራጃው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ፖሊሲዎችና አፈጻጸሞች ጋረ የሚመሳሰል የትምህርት ቤት ውስጥ እገዳ

18
መመሪያ ሊያወጣ ይገባል።

ሌሎች ፓሊሰዎች
የልጅ ሞግዚት
{የፓሊሲ ቁጥር #3610 ካልሆነ፣ የልጅ ሞግዚት}
የዳይሬክተሮች ቦርድ በትምህርት ቤት ልጅን የሚያስመዘግብ ግለሰብ ተማሪው አብሮ የሚኖረው ወላጅ እንደሆነ
ከግምት ውስጥ ያስገባል። ፍርድ ቤቱ ካልገለጸው በስተቀር ተማሪው አብሮ የሚኖረው ወላጅ ለተማሪው የእለት
ተእለት ጥበቃ እና ቁጥጥር የማድረግ እና ውሳኔዎችን የመውሰድ ሃላፊነት እንዲሁም ተማሪውን የመንከባከብ
ብሎም የመቆጣጠር ሃላፊነት አለበት። ወላጆች፣ ሞግዚት/አሳዳጊዎች፣ ወይም ሌሎች ቤተሰቦች ከትምህርት ቤት
ሪከርድ ውስጥ ያሉና ስለ ልጃቸው የተቀመጠ መረጃ ለሌላ ግለሰብ እንዳይሰጥ ወይም ለወላጅ በተሰጠው ስልጣን
መሰረት እንዳይተላለፍ ድርብ መብት አላቸው።

ቦርዱ ካልተነገረው በስተቀር የቤት ወላጆች መብትን አስመልክቶ ለተማሪ የትህርት ቤት፣ የስራ እንቅስቃሴ እና
ችሎን አስመልክቶ እንደ ቤተሰብ ማድረግ እንዲችሉ ገደብ አይጥልም። በፍርድ ቤት የተጣሉ ገደቦች ከሌሉ
በስተቀር አንድ ላይ የማይኖሩ ወላጅ ቤተሰብ በጥያቄያቸው መሰረት የተማሪን ውጤት ሪፓርት፣ የትምህርት
ቤት ስራዎች ማሳሰቢያ፣ የዲሲፒሊን እርምጃዎች፣ የመምህር፣ የርዕሰ መምህር ማጠቃለያ ማሳሰቢያዎች
ይሰጣቸዋል። ገደቦች በዘመድ ወይም በማንኛውም ሌላ ወላጅ ላይ ከተጣለ አብሮ የሚኖር ወላጅ እንዚህ
መብቶች ስለመሰጠጡ የሚገልፅ ከፍርድ ቤት የተሰጠ የተረጋገጠ ትዕዛዝ ፎቶ ኮፒ እንዲያቀርብ ይጠየቃል።
እነዚህ መብቶች አብሮ በማይኖር ቤተሰብ አማካኝነት ጥያቄ ከተነሳባቸው ጉዳዩ እልባት የሚያገኘው ፍርድ ቤት
ወይም የህግ ባለስልጣን ቀርቦ ይሆናል።
አለማዳላት
{ከፖሊሲ #3210 የተወሰደ ጽሑፍ፣ አለማዳላት}
ዲስትሪክቱ ዘር፣ እምነት፣ የቆዳ ቀለም፣ ብሄራዊ መሰረት፣ ከመከላከያ ሰራዊት በክብር መሰናበትን፣ ፆታ፣ ፆታዊ
ባህርይ፣ የፆታ መገለጫ ወይንም ማንነት፣ ማንኛውም የስሜት ህዋስ፣ አእምሮ፣ ወይንም የአካል ጉዳት፣ የአካል
ጉዳተኛ የሰለጠነ መሪ ውሻ መጠቀም ወይንም አገልግሎት ሰጪ እንስሳ መጠቀም መሰረት ያደረገ አድልዎ
ሳያደርግ ለሁሉም ተማሪዎች እኩል የትምህርት እድል መስጠት እና በእኩልነት ማስተናገድ ይኖርበታል።
በዩናይትድ ስቴትስ ኮድ ምእራፍ 36 የአርበኞች ማህበረሰብ ተብሎ በተገለጸው መሰረት ዲስትሪክቱ ለ Boy
Scouts of America እና ለሁሉም የወጣት ቡድኖች በትምህርት ተቋማቱ እኩል የትምህርት እድሎችን
ይሰጣል። የዲስትሪክቱ ፕሮግራሞች ጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ ከሁሉም ሕገወጥ ትንኮሳዎች የጸዱ መሆን
አለባቸው።

19
የተማሪ ረከርዶች
{ከፓሊሲ እና አሰራር #3600፣ በስተቀር የተማሪ ረከርዶች}
አስተዳደሩ የተማሪን የትምህርት መመሪያ ወይም ደህንነት ሁኔታ ለትክክለኛ የትምህርት ቤት ስራ ሲባል ህጉ
በሚፈቅደው መሰረት ይጠብቃል። ሁሉም ከተማሪዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው መረጃዎች በሚስጥር እና
ሞያው በሚጠይቀው መሰረት ይያዛሉ። የክልል እና የፌደራል ህጎችን መረጃ በሚለቀቅበት ወቅት አስተዳደሩ እና
የአስተዳደር ሰራተኞች በቸልተኝነት ወይም በመጥፎ መንፈስ የተነሳ ካልሆነ በስተቀር ለሲቪል ሃላፊነት ተጠያቂ
አይሆኑም። የተማሪ ሪከርዶች የአስተዳደር ንብረት ይሁን እንጂ ለተማሪች እና ለተማሪዎች ወላጆች በአግባቡ
እና በጊዜ ይቀርባሉ። የተማሪ ወላጅ ወይም ጎልማሳ ተማሪ ትክክለኛ ያልሆነ፣ የሚያሳስት ወይም የተማሪን የግል
ወይም ሌሎች መብቶች የሚጥስ የተማሪ ሪከርድ መረጃ አለ ብሎ ካመነ መከራከር ይችላል።
የተማሪ ሪከርዶች በሚቀርበው ጥያቄ መሰረት ለሌሎች ትምህርት ቤት ኤጀንሲዎች ሊቀርቡ ይችላሉ። ለሁለተኛ
ደረጃ ትምህርት ቤት ሃላፊ የተማሪን ትራንስክሪብት የሚመረምሩ ሰራተኞች ለመወከል በአስተዳደሩ ባለስልጣን
ሊሰጠው ይችላል። አስተዳደሩ የተማሪን ሪከርዶች ከትምህርት ቤቱ ኤጀንሲ ወይም ድርጅት ከመልቀቁ በፊት
ወይም በህግ ካልተሰጠ በስተቀር ሪከርዱ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት የቤተሰብ ስምምነት ያስፈልጋል። አዋቂ ተማሪ
ከቤተሰቡ ከግማሽ በታች ድጋፍ የሚያገኝ ከሆነ በዚህ ፓሊሲ መሰረት ለቤተሰብ የሚሰጠው የስምምነት እና
መብቶች ጥያቄ ለተማሪው ብቻ ይሆናል።
ሪፓርት ካርድ፣ ትራንስክሪብት፣ ዲፕሎማ የትምህርት ቤቱ እቃዎች እና ቁሳቁሶች በመውደማቸው እና
በመጥፋታቸው ተማሪው ያጠፋውን እስኪተካ ድረስ ሊያዙ ይችላሉ። ስለ ተማሪ የአካዳሚ ብቃት፣ ልዩ ምደባ፣
የዲሲፒሊን እርምጃዎች፣ ሪከርዶች፣ ለመዝጋቢ ትምህርት ቤት ብቻ ይላካል። የእነዚህ ሪከርዶች ይዘት በሁለት
የትምህር ቤት የስራ ቀናት ጊዜ ለመዝጋቢ አስተዳደር ይገለፃል። የሪከርዶች ፎቶ ኮፒ በተቻለ መጠን በአስቸኳይ
ይላካል። የተማሪው ትራንስክሪብት ቀሪ ክፍያ ወይም ቅጣት እስከሚከፈል ድረስ አይለቀቅም። መዝጋቢ ትምህርት
ቤት ያልተከፈለ ክፍያ ወይም ቅጣት በመኖሩ የተማሪ ትራንስክሪብት የተያያዘ ስለመሆኑ ይገለጽለታል።
የቤተሰብ የትምህርት መብቶች እና የግል ህግ (FERPA) የተማሪ ትምህርት ሪከርዶችን አስመልክቶ ለቤተሰቦች እና
ከ18 በላይ ለሆኑ (ብቁ ተማሪዎች) ተማሪዎች የተወሰነ መብት ይሰጣል። መብቶቹም፦
1) የተማሪውን የትምህርት ሪከርድ ጥያቄው የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በ 45
ቀናት ጊዜ ውስጥ ለመመርመር እና ለመከለስ።
2) ተማሪው ወይም ቤተሰቡ የተማሪው የትምህርት መረጃ ትክክል አይደለም ወይም የተሳሳተ ነው ብለው
የሚያምኑ ከሆነ እንዲታረምላቸው የመጠየቅ መብት አላቸዉ።
3) ያለ ስምምነት FERPA የሚከለክለው ካልሆነ በስተቀር በተማሪው የትምህርት ሪከርዶች ውስጥ
የተያዙትን የግል መረጃዎች ለሌላ ለመግለፅ የመስማማት መብት።
4) ከ FERPA መስፈርቶች መሰረት ለመሄድ የተጣሱ ነገሮችን አስመልክቶ ለዩኤስ የትምህርት መምሪያ
ቅሬታ የማቅረብ መብት አላቸው።

20
የወሲብ ጥቃት
{ፓሊሲ #3209 ካልሆነ በስተቀር፣ ፆታዊ ትንኮሳ}
የትህርት ቤቱ አስተዳደር ፆታዊ ትንኮሳን ጨምሮ ትምህርት ቤቱ ከማንኛውም አድልዎ ነፃ የሆነ እና
አወንታዊ እንዲሁም ውጤት ተኮር ትምህርት የሚሰጥበት የስራ ቦታ ለማድረግ በቁርጠኝነት ይሰራል።
የትምህርት ቤት አስተዳደሩ የተማሪዎችን፣ የሰራተኞችን፣ የሌሎች የትምህርት ቤት ወረዳ ስራዎችን የፆታ
ትንኮሳን አይፈቅድም።
የፆታዊ ትንኮሳ የሚከናወነው በሚከተለው መልኩ ነው፦
1. ለትምህርት፣ የስራ እድል ወይም ለሌላ ጥቅም ሲባል ይህንን ለማሟላት የግብረ ስጋ ግንኙነት
ጥያቄ ሲቀርብ
2. በአካዳሚ ትምህርት፣ በስራ ወይም ግለሰብን በሚነኩ የትምህርት ቤት ውሳኔዎች ላይ የግብረ
ስጋ ግነኙነት ጥያቄ ማቅረብ ወይም መተው፤ ወይም
3. በተማሪ ግል ስራ ላይ የሚቀርበው ትክክለኛ ያልሆነ ጾታ ነክ ፀባይ ወይም ግንኙነት፣ ትንኮሳ ጸብ
ወይም ሌላ ነገር ያመጣል።

ፆታዊ ትንኮሳ ከጎልማሳ ሰው ለተማሪ፣ ከተማሪ ለጎልማሳ፣ ከተማሪ ለተማሪ፣ ከጎልማሳ ለጎልማሳ፣ ከወንድ ወደ
ሴት፣ ከሴት ወደ ወንድ፣ ከወንድ ወደ ወንድ፣ ከሴት ወደ ሴት ሊቀርብ ይችላል።

ወረዳው እነዚህ ሪፓርቶች፣ ቅሬታዎች፣ የፆታ ትንኮሳ ሁኔታዎች በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆነ
በሚቀርቡበት ወቅት አስፈላጊው እና ትክክለኛውም የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል። የወንጀል ጥፋት
ለህግ አስከባሪ አካል ሪፓርት ያደርጋል፣ በልጅ ላይ ጥቃት አድርሷል ተብሎ የተጠረጠረ ግለሰብ ለህግ
አስከባሪ ወይም ህፃናት ጥበቃ አገልግሎት ሪፓርት ይደረጋል። የፆታ ትንኮሳ የደረሰባቸው ግለሰቦች
አግባብ ያለው የትምህርት ቤት አስተዳደራዊ አገልግሎት ማግኘት አለባቸው፣ የደረሰባቸው የፆታ ጥቃትም
ተመርምሮ እና ተገምግሞ አግባብ ያለው አስፈላጊው ውሳኔ ይሰጥባቸዋል።

በፆታዊ ትንኮሳ ላይ የተሳተፈ ጥፋተኛ ተማሪ አስፈላጊው የዲሲፒሊን እርምጃ ወይም ማዕቀብ
እንዲጣልበት ያደርጋል። ማንኛውም የትምህርት ቤት ንብረት ንብረት ወይም ከትምሀርት ቤት ስራ ጋር
ተያያዥነት ያላቸው እንዲሁም እንደ አስፈላጊነታቸው ስራዎች በእነሱ በመገደባቸው፣ በፆታ ትንኮሳ ስራ
ላይ መሳተፍ።

በፆታ ትንኮሳ ቅሬታ ላይ ምስክር በሆነ ወይም ባረጋገጠው ግለሰብ ላይ ማንኛውንም ድርጊት መፈጸም
የተከለከለ ሲሆን ተደርጎ ከሆነ አስፈላጊው የዲሲፒሊን እርምጃ ያስከትላል። የትምህርት ቤቱ አስተዳደሩ
በዚህ ስራ ላይ የሚሰማሩ ሰዎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስፈላጊውን አርምጃ ይወስዳል።

የተሳሳተ የፆታ ትንኮሳ ሪፓርት አውቆ ማስገባት እንደ ፓሊሲ ጥሰት ይቆጠራል። ሆን ብለው ሪፓርት
እንዲቀርብ የሚያደርጉ ወይም ሃሰተኛ ሪፓርት አቅርቦት ላይ የሚተባበሩ ግለሰቦች ተገቢ የሆነ የዲሲፒሊን
እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

21
የትንኮሳ፣ የጥቃት፣ እና የስድብ/በኢንተርኔት ላይ መሳደብ ክልከላዎች
{ፖሊሲ#3308፣ የጥቃት፣, ማንጓጠጥ/የወል ማንጓጠጥን፣ ማስጨነቅ፣ እና ክልከላ፣ ይመልከቱ}
የ Shoreline School አስተዳደር ሁሉም ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞች፣ እና የልገሳ ስራ፣ ደህንነታቸው በተጠበቀ
ሁኔታ የሚማሩበት እንዲሁም በማንኛውም ትንኮሳ ወይም የስድብ/በኢንተርኔት ላይ መሳደብ የማይሳተፉበት ቦታ
ለማድረግ በቁርጠኝነት ይሰራል። «ትንኮሳ፣ ጥቃት ወይም ስድብ» ማለት በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ የሚተላለፍን ጨምሮ
ሆን ተብሎ የሚፃፍ መልዕክት ወይም ምስል፣የቃል ወይም የአካል ድርጊት ምንም እንኳን በዚህ ብቻ ባይወሰነም በ
RCW 9A.36.080(3)፣ (ዘር፣ ቀለም፣ የትውልድ ስፍራ፣ (ቋንቋን ጨምሮ)፣ ፆታ፣ የፆታዊ ግንኙነት የስርዓተ ፆታን
መለያ ጨምሮ፣ እምነት፣ ሃይማኖት፣ ዕድሜ፣ የአርበኝነት ወይም ወታደራዊ ሁኔታ፣ አካል ጉዳተኝነት፣ ወይም አካል
ጉዳተኞች የሚጠቀሙበት የሰለጠነ ውሻ አጠቃቀም ወይም መመሪያ) ወይም ሌሌች የተለዩ ባህሪያት ማለት ነው፣ ተግባሩ
በሚከተለው መልኩ፦
• በተማሪ ላይ የአካል ጉዳት ማድረግ ወይም የተማሪን ንብረት ማውደም፤ ወይም
• በዋነኛነት በተማሪው ትምህርት ላይ ጣልቃ የመግባት ውጤት የሚኖረው ድርጊት መፈጸም፤ ወይም
• ጥላቻን የሚፈጥር እና ከባድ ጥቃት የሚኖርበት ወይም አስፈሪ የትምህርት ሁኔታን መፍጠር፤ ወይም
• በዋነኛነት የትምህርት ቤቱን ስርዓት የጠበቀ ክንውን የሚያውክ ድርጊት።
ጥቃት የደረሰበት ተማሪ ለትንኮሳ፣ ለጥቃት ወይም ስም ማጥፋት መሰረት የሆኑ ጸባያት እንዲኖረው በዚህ ክፍል ውስጥ
የሚያደርግ አይኖርም። «ሌሎች መለያ ጸባያት» ምንም እንኳን በዚኅ ብቻ ባይወሰነም የሚከተሉ ሊሆኑ ይችላል፦ አካላዊ
እይታ፣ አለባበስ ወይም ሌሎች ማሳያ፣ የማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ፣ የስርዓተ ፆታ መለያ፣ አና የጋብቻ ሁኔታ ናቸው።
ትንኮሳ፣ ጥቃት ወይም ስድብ/በኢንተርኔት ላይ መሳደብ ከዚህ በታች የተገለጹትን ጨምሮ በተለያዩ ሁኔታዎች ይታያሉ፦
ሃሜት፣ ወሬ፣ ቀልድ፣ አስተያየት፣ ስዕል፣ ካርቱን፣ ፕራንክ፣ አካላዊ እንቅስቃሴ፣ ጥቃት፣ ስጋት፣ ወይም ሌሎች የቃል ወይም
አካላዊ ድርጊቶች። «ሆን ተብሎ የሚደረጉ ድርጊቶች» በድርጊቱ የተነሳ የሚከሰት ነገር ሳይሆን በዚህ ድርጊት(ቶች) ላይ
የሚሳተፉ ግለሰቦችን ይመለከታል።
በድርጊቱ ሁኔታ እና መጠን መሰረት፣ ጣልቃ ገብነት ምክር፣ ማስተካከያ፣ ወይም ወደ ህግ ተግባራዊነት ሊመራ ይችላል።
ማንኛውም የትምህርት ቤቱ ሠራተኛ፣ ተማሪ ወይም በጎ ፈቃደኛ በማንኛውም ቅሬታ አቅራቢ ላይ ተመሳሳይ የሆነ ምላሽ
ወይም ሃሰተኛ ውንጀላ ማቅረብ አይኖርበትም። ይህም ትንኮሳ፣ ስብዕና የሚነኩ ሁኔታዎች ወይም ልፊያ መሰል ፀቦችን
ያጠቃልላል። በቀል ፈፅሞ የተከለከለ ሲሆን ይህ ሆኖ ከተገኘ አስፈላጊው የሥነ-ሥርዓት እርምጃ የሚወሰድበት ይሆናል።
ትንኮሳ፣ ስብዕና የሚነካ ሁኔታን ወይም ልፊያን የሚጠቁም ግለሰብ ማስፈራራት ወይም ለመጉዳት መሞከር የህግ ጥሰት
ነው። ሆንብሎ ሃሰተኛ የትንኮሳ፣ ስብዕና የሚነካ ወይም በሰው ላይ የመቀለድ ተግባር መፈፀም የክልሉን ፖሊሲ ጥሰት ነው።
ተማሪዎች ወይም ሠራተኞች በመልካም መነሳሳት ሪፖርት ቢያደርጉ የሥነ-ሥርዓት እርምጃ አይወሰድባቸውም። ሆኖም
ግን ሆን ብሎ ሃሰተኛ የሆነ ሪፖርቶችን ወይም ውንጀላዎችን የሚያቀርብ ግለሰብ የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ይወሰድበታል።
ማንኛውም የትምህርት ቤቱ ሠራተኛ፣ ተማሪ ወይም በጎ ፈቃደኛ ሆኖ ተማሪው ትንኮሳ፣ የስብዕና መጉደፍ ወይም የማንጓጠጥ
ተግባር በአካልም ሆነ በቃል ሲደርስበት የተመለከተ ሁኔታውን ለሚመለከተው የትምህርት ቤት ኃላፊ እንዲያቀርብ
ይበረታታል። ማንኛውም ሪፖርት የተደረገ ሁኔታ ሪፖርት አድራጊው ለሚወሰድበት ማንኛውም እርምጃ መዘግየት ምንም
አይነት ኃላፊነት አይወስድም። የሾርላይን ትምህርት ዞን የትንኮሳ , ማስፈራራት እና ማዋከብ ሪፖርት ማድረጊያ ቅጽን
ለማግኘት እባክዎ የሚከተለውን ድር ጣቢያ ይጎብኙ: http://www.shorelineschools.org/HIBReportingForm

የአቤቱታ መኮንንን፡ – Bailey Bertram, Harrassment, Intimiadation እና Compliance, 18560 1st Ave. NE,
Shoreline, WA 98155, 206.393.4213

22
አድሎአዊ ያልሆነና ቅሬታ/አቤቱታ አካሄድ
ሾርላይን የህዝብ ትምህረትቤቶች እኩል የትምህርት እና የስራ እድል ያቀርባል ዘር፣ እምነት፣ ቀለም፣ የዜግነት
መሰረት፣ ጾታ፣ አካል ጉዳት፣ የሰነጾታ አመለካከት የጾታ አገላለጽ ወይም መታወቂያን ጨምሮ፣ ሃይማኖት፣
እድሜ፣ የጠሩተኛ ወይም የውትድርና ደረጃ፣ አካል ጉዳተኛ የሆ ሰዎች የሰለጠነ ውሻ ወይም የአገልግሎት
እንስሳት መጠቀም፣ ሳይመለከት ለቦይስካውት እና ሌላ የወጣቶች ቡድኖች እኩል እድል ይሰጣል።
አውራጃው ተግባራዊ ከሆኑ ከሁሉም የግዛትና የፌደራል ደንቦችና መመሪያዎች ጋር በሁሉም አውራጃ
ፕሮግራሞች፣ ኮርሶች፣ እንቅስቃሴዎች፣ ተጫመሪ የካሪኩለም እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ፣ አገልግሎቶች፣
ተቋማት ላይ መድረስ፣ ወ.ዘ.ተ. ይሰማማል።
የሾርላይን ትምህርት ቤት አውራጃ በክፍት ምዝገባ ፖሊሲው ስር በበርካታ ሙያዎችና የቴክኒክ
ትምህርቶች ፕሮግራም ትምህርቶች ያቀረባል። በተለይ፣ የሾርላይን ትምህርት ቤት አውራጃ በምርጫ
መስፈርቶች (ለምሳሌ ቅድመ ሁኔታ የሚሹ ከፍተኛ ምዝገባ ፕሮግራሞች) በተለየ አካሄድ ሆኖም
አደሎዋዊ ያልሆኑ ምዝገባዎች ያቀርባል። ሰለ ምዝገባና የተለዩ ኮርሶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣
ሾርላይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (206.393.4286) ወይም ሾርውድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤት (206.393.4372) የምዝገባ ቢሮውን ያናግሩ። ለሙያና ቴክኒካዊ ትምህርቶች እንግሊዘኛ ቋንቋ
ለምዝገባና ለተሳትፎ መስፈርቶች ውስጥ አይደለም። ይህ ማሳወቂያ 206.393.4365 በማነጋገር
ለብሄራዊ መሰረት ላላቸው ማህበረሰቦች በተገቢው ቋንቋ ሊቀርብ ይችላል። የሚከተሉት ሰዎች
ሰለአድሎአዊ ስላልሆኑ ፖሊሲዎች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን እንደሚልሱ ተመደበዋል፡-

የ IX ሹመት ያለው መኮንንና ግዛት ህግ (RCW 28A.640/28A.642) የስምምነት አስተባባሪ በአጠቃላይ የመከታተልና
ስምምነቱ የሚከተሉትን መሆኑን ማረጋገጥ፡-

Title IX Officer እና የአዋቂዎች ትንኮሳ፣ ማስፈራራት እና በጉልበት ጫና የመፍጠር ሁኔታ:


Bailey Bertram, የሰው ሀብት/የተመደቡ ሰራተኞች ዳይሬክተር
18560 1st Avenue NE, Shoreline, WA 98155
206.393.4776

የተማሪ ትንኮሳ፣ ማስፈራራት እና በጉልበት ጫና የመፍጠር ሁኔታ:


Don Dalziel, ትንኮሳ፣ ማስፈራራት እና በጉልበት ጫና መፍጠር ችግሮችን ማስከበር
18560 1st Avenue NE, Shoreline, WA 98155
206.393.4213

ADA ተሰማሚነት መኮንንና ክፍል 504 ተሰማሚነት መኮንን


አሚ ቮዮቪቸ
የተማሪዎች አገልግሎት ዴሪክተር
18560 1st Avenue NE, Shoreline, WA 98155
206.393.4117
በማናቸውም የዲስትሪክቱ ትምህርታዊ ፕሮግራሞች፣ እንቅስቃሴዎች፣ አገልግሎቶች፣ ወዘተ፣ አድልዎ
ተፈጽሞብናል ብለው የሚያምኑ ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ አማካኝነት ቅሬታቸውን
ማቅረብ ይችላሉ።

23
የተፈቀደና ያልተፈቀደ ቀሪነት
{የፖሊሲና አኪያሄዶች ጥቅስ #3122, የተፈቀደና የልተፈቀደ ቀሪነት}
ማስታወሻ: ህንጻን መሰረት ያደረጉ ስለተለዩ በትምህርት ቤት የመገኘት ፖሊሲዎች ለማወቅ የትምህርት ቤት
የራሱን ህትመቶች ያንብቡ
በመደበኛነት በትምህርት ቤት መገኘት በአውራጀው ለሚገኙ ተማሪዎች ሰለሚቀርበው ትምህርት እወቀት
ለማግኘት አስፈላጊ ነው። ተማሪዎች አንዳንድ ጊዜ በተገቢው ሁኔታ ከክፍል ሊቀሩ ይችላሉ። የሚከተሉት ጽነሰ
ሃሳቦቸ በአውራጃው ውስጥ በትመህርት ቤት የመገኘት አካሄድ መሳደግና ማስተዳደር ይመራል፡-
1. ቀሪ በህመም ወይም በጤና ሁኔታ ምክንያት መቅረት፤ የሃይማኖት ስርአት፤ በትመህርት ቤት የተፈቀደ
እንቅስቃሴ የቤተሰብ ድንገተኛ ጥሪ፤ እና፣ በህግ እንደሚጠየቀው፣ የስነስርአት እርምጃዎች ወይም አጭሪ
ጊዜ እገዳዎች ይቅርታ ሊደረግላቸው ይገባል። በተጨማሪ፣ ርእሰመምህሩ በወላጅ በሚቀርብለት ጥያቄ
መቀረቱ የተማሪውን የትመህርት እድገት በማይጎዳ መልኩ ፈቃድ ሊሰጥ ይቻላል፤
2. በፈቃድ በሚቀርበት ጊዜ ተማሪዎች በተገቢ ጊዜ ያቀረባቸውን ስራዎች ከክፍል ውጪ እንዲያሟሉ
ይደረጋል ስራው በተሳትፎ የሚሰራ ከሆነ በቀሩ ጊዜ ያመለጣቸውን ትምሀርት ለማካካስ የትርፍ ጊዜ
ድጋፍ ለመስጠት በመምህሩ የተቻለው ጥረት ይደረጋል፤
3. በፈቃድ መቅረት በወላጅ፣ አዋቂ ተማሪ (ከአስራስምነት አመት በላይ የሆኑ) ወይም ራሱን የቻለ ተማሪ
(ከአስራስድስት አመት በላይ የሆኑና በፍርድ ቤት ነጻ የሆኑ)፣ ወይም ለመቅረቱ ተጠያቂ የሆነው
የትምህርት ቤት ባለስልጣን ማረጋገጥ አለበት። (አስራአራት አመት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ በግብረስጋ
ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ለመመርመር ወይም ለመታከም ከትምህርት ቤት መውጣት ከፈለጉ
የራሳቸውን ቀሪነት ማረጋገጥ ይቸላሉ እና የቀሩበትም ምክንያት በሚስጥር ይያዛል።)፡-
4. የሃላፊነትና የግል ተጠያቂነት ላይ እሴቶችን ለመጨመር ያለፈቃድ የቀረ ተማሪ የሚከተለውን ቅጣት
መቀበል አለበት/አለባት። ደረጃ የሚስጠው እንቅስቃሴ ወይም ስራ ተማሪው በቀረበት ጊዜ ከተሰጠና
ተማሪው ካልተሰራ የተማሪው ውጤት ተጽእኖ ሊያርፍበት ይችላል፤
5. ተማሪው አሁን ባለው የትመህርት አመት ውስጥ በወር ያለፈቃድ ከአንድ ቀን በላይ በሚቀርበት ጊዜ
ትምህርት ቤቱ የተማሪውን ወላጅ/አሳዳጊ ማሳወቅ ይኖርበታል። ማስታወቂያው ተጨማሪ ያለፈቃድ
መቅረት የሚያመጣውን መካተት ይኖርበታል። በአመት ውስጥ በማንኛውም ወር ያለፈቃድ ሀለት ቀን
ከቀሩ ከወላጅ/አሳዳጊ ጋር ኮንፍረንስ መካሔድ አለበት።
ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት የሚያስቀራቸውን ችግር ለመፍታት የእርምት እርምጃዎችን ለመወሰን
የኮንፍረነስ ቀጠሮ መያዝ አለበት ቤተሰብ ኮንፈረንሱን ካልተካፈሉ፣ የተማሪዎችን ቀሪ ለመቀነስ
የትምህርት ቤት አውራጃ ሊወስድ ስላሰበው እርምጃ ለወላጆች መገለጽ ይኖረበታል።

24
ተማሪዎች በአንድ ወር ውስጥ ከአምስት በላይ ቀን ያለፈቃድ ከቀሩ አውራጃው ከተማሪዎችና
ወላጆች ጋር የትምህርት ቤት መምጣት መስፈርቶች ስምምነት ውስጥ መግባት ይኖርበታል፣
ተማሪዎችን ወደየቀሪ ቁጥጥር የማህበረሰብ ቦርድ መምራት፣ ወይም ማመልከቻ ማስገባትና
በወጣቶች ፍርድቤትRCW 28A.225.010 በመተላለፍ ክስ ዋስ መጠየቅ።
ይህ እርምጃ ካልተሳካ፣ በትምህርት አመቱ በማንኛውም ወር ያለፈቃድ ለሰባት ቀናት ወይም
በአስረኛው ቀን አውራጃው በወጣቶች ፍርድቤት በወላጆች፣ ተማሪዎች ወይም በወላጆችና
ተማሪዎች RCW 28A.225.010 በመተላለፍ ክስ ማመልከቻ ማስገባት ይኖርበታል።

ተማሪዎች የተመደበላቸውን እያንዳንዱን ክፍለጊዜ መከታተል አለባቸው። መምህራን የቀሪ እና የአረፋጅ መዝገብ
መያዝ ይኖርባቸዋል። የሚከተሉት ለመቅረትና ለማርፈድ ተቀባይነት ያላቸው ምክንያቶች ናቸው። ያለፏቸው የቤት
ሰራዎች እና እንቅስቃሴዎች በመምህሩ በሚሰጥ ሊካካሱ ይችሉ ይሆናል።
1. በትምህርት ቤት በተፈቀደ እንቅስቃሴ መሳተፍ. ፈቃድ ለማግኘት፣ ይህ ቀሪ በሰራተኛ መፈቀድ አለብት
በግልጽ የማይቻል ካልሆነ በሰተቀር መምህሩም በቅድሚያ ሊገለጽለት ይገባል፤
2. ቀሪ በህመም፣ ጤና ሁኔታ፣ በቤተሰብ ድንገተኛ ጥሪ፣ ወይም በሃይማኖታዊ ምክንያት. በሚቻልበት
ጊዜ፣ ወላጅ ወይም አዋቂ/ነጻ የወጣ ተማሪ በሚቀርበት ቀን ትምህርት ቤቱን ማሳወቅ ይጠበቅበታል
እንዲሁም የተፈረመ የማብራሪያ ማሰታወሻ በተማሪው/ዋ ወደትምህርት ቤት በሚመለሱበት ጊዜ
መላክ አለበት። አዋቂ ተማሪዎች (ከአስራስምነት አመት በላይ የሆኑ) እና ነጻ የወጡ ተማሪዎች
(ከአስራስድስት አመት በላይ የሆኑ በፍርድ ቤት እርምጃ ነጻ የሆኑ) ሰለመቅረታቸው በተፈረመ
ማስታወሻ ማብራሪያ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል። አስራ አራት አመት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ተማሪዎች
በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ለመመርመር ወይም ለመታከም ከትመህርት ቤት የቀሩበት
የተፈረመበት ማስታወሻ ሰለመቅረታቸው በማብራራት ትምህርት ቤቱን ማሳወቅ ያስፈልጋቸዋል እና
የቀሩበትም ምክንያት በሚስጥር ይያዛል። አስራሶስት አመት ወይም ከዚያ በላይ የሆናቸው ተማሪዎች
ለአእምሮ ጤና፣ እፅ፣ ወይም አልኮል ህክምና በተመሳሳይ ማድረግ ይችላሉ፤ እናም ሁሉም ተማሪዎች
ለቤተሰብ እቅድና ለጽንስ ማስወረድ መብት አላቸው ወላጅ ተማሪዎች የሃይማኖታዊ በአላት ለማክበር
ከትምህርት ቤት እንዲቀሩ መጠየቅ ይችላሉ።
በተጨማሪ፣ ተማሪው/ዋ በወላጅ ጥያቄ የቀኑን ገሚሱን ሃይማኖታዊ መመሪያን ለመካፈል ሊቀሩ
ይችላሉ ፕሮግራሙ በትመህርት ቤት ውስጥ የሚኪያሄድ እስከሆነ ድረስ።
3. በወላጅ ይሁኝታ ሊቀሩባቸው የሚችሉ ጉዳዮች። ይህ አይነት መቅረት በርእሰመምህሩ እና በወላጅ
ለተስማሙባቸው ጉዳዮች የሚፈቀድ ይሆናል። መቅረት ተማሪው የትምህርት እድገት ላይ ጎጂ
ተጽእኖ የሚያሳድር ከሆነ ላይፈቀድ ይችላል። በተሳትፎ የሚከናወኑ ትምህርቶች ላይ (ለምሳሌ፡-የሆነ
ሙዚቃ፣ የሰይንስ ቤተ ሙከራ፣ እና የአካል ብቃት ትምህርቶች) በመቅረታቸው ምክንያት ተማሪዎች
የክፍሉን አላማ ለመቀበል አይችሉ ይሆናል። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ፣ በወላጅ የተረጋገጠ መቅረት
በተማሪዎች የትምህርት እድገት ላይ ጎጂ ተጽእኖ ሊፈጥርና በኋላም በኮርሱ ውጤት ላይ ተጽእኖ
ሊያሳድር ይችላል።

25
የስቴት ሕግ ትምህርት የመማርን ግዴታ ያስቀምጣል
•• የስቴት ሕግ ዕድሜያቸው ከ 8 እስከ 17 አመት የሆናቸው ልጆች ትምህርት እንዲማሩ ያስገድዳል።
•• ትምህርት-ቤት ላይ ተመዝግበው የሚገኙ ዕድሜያቸው 6- ወይንም 7 አመት የሆናቸው ህጻናትም
ትምህርት የመማር ግዴታ አለባቸው።
•• የ 16 አመት ወይንም ከዚህ የሚበልጡ ልጆች የተወሰኑ መስፈርቶችን ማሟላት ከቻሉ ትምህርት-ቤት
የመሄድ ግዴታ ሊነሳላቸው ይችላል። ስለነዚህ መስፈርቶች መወያየት ከፈለጉ እባክዎ የትምህርት-
ቤትዎ ጽሕፈት-ቤትን ያናግሩ።
ተማሪዎ ከትምህርት-ቤት የሚቀር ከሆን እባክዎ አስቀድመው ከትምህርት-ቤትዎ ጽሕፈት-ቤት ጋር
ይነጋገሩ።

*ያለፍቃድ ከትምህርት-ቤት መቅረትን የሚመለከተው ደንብ “RCW 28A.225” ጎግል ላይ በመጻፍ እና


የመጀመሪያውን ምርጫ በመምረጥ ማየት ይችላሉ።

ተማሪው ከትምህርት በሚቀርበት ጊዜ ትምህርት-ቤቱ የሚወስዳቸው እርምጃዎች


•• ልጅዎ በወር ሁለት ጊዜ በድንገት ከትምህርት-ቤት ቢቀር፣ ከእርስዎ እና ከልጅዎ ጋር ስብሰባ
እንድንቀመጥ የስቴት ሕግ (RCW 28A.225.020) ያስገድደናል።
•• በአንደኛ ደረጃ ትምህርት-ቤት በአንድ ወር ውስጥ አምስት ቀን ወይንም በአመት አስር አለያም
ከአስር ቀን በላይ ከትምህርት ቢቀር እና በትምህርት-ቤቱ ይቀር ቢባል፣ የዲስትሪክቱ ትምህርት-ቤት
ከእርስዎ ጋር ተገናኝቶ መነጋገር እንዳበት ሕጉ ያስገድዳል። ልጅዎ ለመቅረቱ ምክንያት የሓኪም
ወረቀት ካቀረበ፣ ወይንም ከትምህርት እንደሚቀር አስቀድሞ በጽሑፍ ያሳወቀ ከሆነ፣ እና ልጅዎ
በትምህርት ወደኋላ እንዳይቀር የተዘጋጁለት እቅዶች ካሉ ኮንፈረንስ ማድረግ አያስፈልግም።
•• ልጅዎ በአንድ ወር ውስጥ አምስት ቀን ወይንም በአመት አስር አለያም ከአስር ቀን በላይ ከትምህርት
ቢቀር እና ትምህርት-ቤቱ ይቅር ሳይለው ቢቀር፣ ትምህርት መማር የሚደነግገው ሕግ RCW
28A.225.010 መጣሱን መሰረት በማድረግ ህጻናት ፍርድ-ቤት ላይ ክስ መመስረት ይጠበቅብናል።
እርስዎ ከልጅዎ ጋር የህጻናት ፍርድ-ቤት ላይ ሊቀርቡ ይችላሉ።

26
የሚከተለውን ያውቃሉ?
•• ሁልጊዜ ትምህርት-ቤት በሰአት መድረስ ልጅዎ ከከፍተኛ ትምህርት-ቤት የመመረቅ እድሉን ከፍ
ያደርግለታል።
•• ከመዋእለ ህጻናት ጀምሮ፣ በወር በአማካይ 2 ቀናቶች ከትምህርት መቅረት፣ ይቅር የሚባልም ይሁን
የማይባል፣ ልጅዎ ሶስተኛ ደረጃ ሲደርስ የሒሳብ እና የንባብ ኣካዳሚያዊ ስተንዳርዶችን ሳያሟላ
የመቅረት እድሉ ከፍተኛ ነው።
•• 6ኛ ደረጃ ላይ፣ ከትምህርት መቅረት ተማሪ የከፍተኛ ትምህርቱን ሊያቋርጥ ከሚችልባቸው ሶስት
ምልክቶች አንዱ ነው።
•• ከትምህርት መቅረት የተማሪውን የትምህርት ፍላጎት ማጣት፣ የትምህርት ስራዎች እየከበዱት
መሆኑ፣ ጉልበተኞች እያስፈራሩት መሆኑ ወይንም የተወሰኑ ሌሎች ከባድ ችግሮች እያጋጠሙት
ስለመሆኑ ምልክት ሊሆን ይችላል።
•• 9ኛ ደረጃ ላይ፣ በመደበኛነት በመማሪያ ክፍል መገኘት ከ 8ኛ ክፍል የፈተና ውጤት በላይ ከከፍተኛ
ትምህርት የመመረቅ መጠንን ያመላታል።

ማድረግ ያለብዎ ነገር


•• ልጅዎ እውነት መታመሙን ካላረጋገጡ ማለትም ትኩሳት፣ ተውከት፣ ተቅማጥ፣ ወይንም ተላላፊ
እከክ ካላዩበት በስተቀር ከትምርት-ቤት እንዲቀር አይፍቀዱለት።
•• በትምህርት ጊዜ ቀጠሮዎችን እና ጉዞዎችን አያቅዱ።
•• የልጅዎ የትምህርት ተሳትፎ እየመዘገቡ ይያዙ። ይቅር ቢባልም ባይባልም፣ ከ 9 ቀናት በላይ
ከትምህርት መቅረት፣ ልጅዎ በትምህርቱ ወደኋላ ሊያስቀረው ይችላል።
•• በጊዜ ያስተኙት፣ በጠዋት መነሳት ያስለምዱት እንዲሁም ወደ ትምህርት-ቤት ስሄድ የምይዛቸው
ነገሮችን አዘጋጅተውለት ይደሩ።
•• የሆነ ነገር ካጋጠምዎ የቤተሰብዎ አባላት፣ ገረቤቶችዎ፣ ወይንም ሌሎች ወላጆች ልጅዎን
ከትምህርት-ቤት እንዲያደርሱልዎ ያድርጉ።
*የትምህርት-ቤት ተሳትፎ የሚመለከት ጠቃሚ መረጃ ከሚከተለው ድረገጽ ማግኘት ይችላሉ:
www.attendanceworks.org

ልጅዎ ወደ ትምህርት-ቤት ለመላክ እየተቸገሩ ከሆነ፣ አስፈላጊ መፍትሄዎችን ለማምጣት እኛ ልንረዳዎ


ዝግጁ ነን። እባክዎ የልጅዎን ተሳትፎ በሚመለከት ከትምህርት-ቤትዎ ጽሕፈት-ቤት ጋር ለመወያየት
ያለምንም ማመንታት ቀጠሮ ያስይዙ።

27
ስነምግባርና ሃቀኝነት
{ጥቅስ ከፖሊሲ #3302, ስነምግባርና ሃቀኝነት}
ፖሊሲ 3302, ስነምግባር እና ሀገኝነት፣ ላይ ጥሰት የፈጸሙ ተማሪዎች የሚከተሉት ቅጣቶች ይጣልባቸዋል:
(1) በፖሊሲ 3300 (“ከተማሪ የሚጠበቁ ስነምግባሮች እና ተገቢ እግዶች”), ፖሊሲ 3310 (“በተማሪዎች
የስነምግባር ጉድለት ላይ የሚወሰዱ የዲሲፕሊን እና የእርምት እርምጃዎች”), እና በማስፈጸሚያ አሰራሮቻቸው
መሰረት የእርምት ቅጣት ይጣልባቸዋል; እንዲሁም (2) አስተማሪው የተማሪው ጥረቶች እና ውጤቶች ላይ
አሉታዊ ነጥብ ያስቀምጣል። እንደየሁኔታው የሚመደበው የቅጣት ውሳኔ በጥፋቱ ይዘት መሰረት የሚለያይ
ሲሆን የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ወይም እግድ ይተላለፋል። ማንኛውም የሚያጭበረብር ተማሪ ከልጁ እድሜ እና
ባህሪ ጋር ሊሄድ የሚችል የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ይወሰድበታል።

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከዚህ እንደሚከተለው የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

1ኛ ጥፋት: 1 ኛ ላይ የቀረበው ወንጀል፡ ተማሪው ወደ ርዕሰ መምህሩ/ወኪሉ ይላካል፣ የተማሪውን የቤት ስራ


አፈፃፀም /ወይም ሌላ የትምህርት ነክ ተግባር/ 0 እንዲሆን ይደረጋል። ወላጆችም በአስተዳዳሪው አማካይነት
ስለ ጉዳዩ እንዲያውቁ ይደረጋል።

2 ኛ ላይ የቀረበው ወንጀል: ተማሪው ከአስር (10) የትምህርት-ቤቱ የስራቀናት ላልበለጠ ጊዜ አጭር እግድ
ተጥሎበታል። (ማስታወሻ፡ አሁን የሚሰጠው የመማሪያ ክፍል ቀደም ሲል ጥፋት ከፈፀመበት ክፍል የተለየ ነው።)
ስለ ጉዳዩ ማሳወቅን በተመለከተ አስተዳዳሪዎቹ በህግ የተቀረፁትን የማገጃ የሥራ ሂደቶች ተከትለው ይሰራሉ።

3rd ጥቃት: ተማሪው ከአስር (10) የትምህርት-ቤቱ የስራቀናት ላልበለጠ ጊዜ ከሁሉም ክላሶች እንዲርቅ አጭር
እግድ ተጥሎበታል። ከወላጆች ጋር ግንኙነት ይፈጠርና አግባብነት ያለው የስራ ሂደት መብቶች የሚሰጡ ይሆናል።

በሁሉም ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎች ከእድሜያቸው ጋር በሚሄድ ሁኔታ ዋናውን ስራቸውን እንዲያከናውኑ እና


በእያንዳንዱም ዓመት ሠራተኞች ስለሚወሰዱ የእርምት እርምጃዎች ባህሪ እና መጠን በቅድሚያ እንዲያውቁ
የሚያደርጉ ሲሆን እንደ አጠቃላይ ህግም ፖሊሲዎቹን በመጣሳቸው ምክንያት የሚጣልባቸውንም ቅጣት
በተመለከተ ያሳውቋቸዋል። የመለስተኛ 1ኛ ደረጃ ተማሪዎች ስለዋናው ስራ፣ ምንጮችን በማህደር ማስቀመጥ
ማደራጀት እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ሲማሩ የ2ኛውን መመሪያዎች ያካተቱትን እስከሚደርሱ ድረስ በተከታታይ
ስነ-ስርዓት ሊይዙ ይችላሉ። የተለያዩ ሁኔታዎችን የሚያካትቱ ለየት ያሉ ነገሮች እንዲሰጡ ለአስተዳደሮች እና
ትኩረት ሰጪ ኦፊሰሮች ይፈቀዳል።

አንድ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተማሪዎች የስነ- ምግባር ወይም የታማኝነት ፖሊሲዎች መጣሳቸውን በመምህራን
ምክንያታዊ ጥርጣሬ ካደረባቸው ከተጨማሪ ስራ/ዎች በስተቀር መምህራኑ በተለያየ ዘዴዎች ተማሪዎቹን
መፈተን/መገምገም ይችላሉ። የፖሊሲዎች ጥሰት እና ተመሳሳይ ጥፋቶች በመፈጸም የተጠረጠሩ ተማሪዎችን
እንዲያጋልጡ ሌሎች ተማሪዎች በመምህራኖቻቸው ወይም አስተዳደሮች ከተጠየቁ ለምርመራው እና
ለማጣራቱ ሂደት ተማሪዎቹ መተባበር አለባቸው።

28
ኢንተርኔት መጠቀም
{ፖሊሲ ቁጥር 2314 ፒን ሳይጥሱ ተማሪዎች በመረጃ መረቦች እና ምጮች የመጠቀም መብት ይኖራቸዋል}
ተቀባይነት ያለው የመረጃ መረብ አጠቃቀም
የመረጃ መረቦቹ ለትምህርታዊ እና ሙያዊ ፋይዳዎች ብቻ ያገለግላሉ። በተጠቃሚዎች ተቀባይነት ያለው
የመረጃ መረብ አጠቃቀም የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡-
• ለትምህርታዊ እና አስተዳደራዊ አላማዎች የመረጃ መረብ ምንጮችን በመጠቀም ፋይሎችን መክፈት፣
የፕሮጀክት ፋይሎች፣ የቪዲዎ ፋይሎችን፣ የመረጃ ዌቦች ገጾች እና ፖድካስቶችን መጠቀም።
• በጡመራ፣ በዊኪ የመፅሄት ቦርዶች፣ በማህበራዊ አውታረመረብ ጣቢያዎች እና ቡድኖች እንዲሁም ይዘቶችን
ትምህርትን እና ጥናትን ለመደገፍ አላማ ይውሉ ዘንድ ለኢሜይል እና የድር ገፆችን በመፍጠር መሳተፍ፤
• በቤተሰባዊ/ወላጅ ፈቃድ ትምህርታዊ ይዘት ያላቸው በአየር ላይ የተለቀቁ ህትመቶችን መጠቀም፣
ከትምህርት ጋር የተያያዙ ማቴሪያሎችን እና የሌሎች ተማሪዎች ስራዎች መጠቀም፣ ከመመሪያ ክፍሎች ውጭ
ያሉትን ምንጮች በተገቢ ሁኔታ ማመላከት አለበት።
• ሰራተኞች የግል ጉዳዮች ሊጠቀሙ የሚችሉ ሲሆን ይህም በትርፍ ሰዓት እና በአካባቢዎች ፖሊሲዎች እና
መመሪያዎች መሰረት መሆን አለበት።
ተቀባይነት የመረጃ መረብ አጠቃቀም
ተቀባይነት የመረጃ መረብ አጠቃቀም ወይም ተጠቃሚዎች መጠቀም የሌለባቸው በእነዚህ ብቻ ባይገደብም
የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡-
• ለግል ጥቅም፣ ለንግድ ስራ እና ለማንኛውም አይነት የካሣ ክፍያ ጥያቄ ኢንተርኔት መጠቀም አይቻልም፤
• በአካባቢው/ወረዳው ላይ እዳ ወይም ወጪ የሚያስከትል አጠቃቀም፤
• ከመረጃ መረብ ፕሪንት ማድረግ፣ መረጃ መረቡ ላይ መጫን፣ ጌሞችን መጫወት፣ ኦዲዮ ፋየሎችን፣ ቪዲዮ፣
ሌሎች ፋይሎችን ከትምህርት አገልግሎት አላማ ወጭ የሆኑትን (መጋራት እና ነጻ አጠቃቀም ጨምሮ)
በኢንፎርማሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ፈቃድ ሳያገኙ ከላይ የተጠቀሱትን መጠቀም፤
• የአመጽ እርምጃዎች በመደገፍም ሆነ በመቃወም እንዲሁም የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴዎች
በተመለከተ እጩዎችን ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም በኢንተርኔት መጠቀም የማይቻል መሆኑን፣
• በሐርድዌር፣ በሶፍትዌር እና ማንኛውንም የሞኒተሪንግ መሳሪያዎች ላይ የቫይረስ ስርጭት ወይም ጥቃት
የሚያስከትሉ አጠቃቀሞች፣
• ያልተፈቀዱ የኮምፒዩተር ክፍሎች፣ የመረጃ መረቦች እና የመረጃ ስርዓቶችን መክፈት እና መገልገል፣
• በኢንተርኔት ላይ መሳደብ፣ የጥላቻ ኢሜይል መላክ፣ ስም ማጥፋት፣ ማንኛውም አይነት ትንኮሳ፣ የሚያገሉ
ቀልዶች እና አስተያየቶች፤
• ሌሎችን የሚጎዱ አየር ላይ የተለቀቁ፣ የተላኩ፣ በመረጃ መረቦች ተከማችተው የሚገኙ (ለምሳሌ የቦምብ
መስራት ቀመር እና አደንዛዥ እጾችን ለማምረት የሚያስችሉ መረጃዎችን) በትምህርትቤቱ ኢንተርኔት መረጃ
መረብ መጠቀም፤
• የተለያዩ ህገ-ወጥ የሆኑ እንደ የግብረ ስጋ ግንኙነት አይነት ወይም ስለ ግብረስጋ ግንኙት የሚያብራሩ ወይም
የሚያሳዩ ማቴሪያሎችን መጫን፣ ከፍቶ ማየት፣ መላላክ እና ማሰራጨት፤ እና
• በወረዳው/ አካባቢው/ ህገ-ወጥ የሆኑ መሳሪያዎችን መጫን/ማያያዝ ናቸው። እንደዚህ አይነት የተጫኑ/
የተያያዙ መሳሪያዎች ከመረጃ መረቡ ላይ እንዲጠፉ ይደረጋል።
የአጠቃቀም ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች ጥሰት የመረጃ መረብ የመጠቀም መብትን ይከለክላል፤ እንዲሁም
በወረዳው ኮምፒተሮች እንዳይጠቀም እገዳ ይጣልበታል። በተጨማሪም ሌሎች የትምህርትቤቱ የስነ-ስርዓት
እርምጃዎች በተገቢው ሁኔታ እንዲወሰድበት እና /ወይም ተገቢ የሆነ የህግ እርምጃ እንዲወሰድበት ያደርጋል።
ጥሰቶቹ ጥቅማ ጥቅም ከማግኘት የመነሳት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፣ የአስተዳደር ኮምፒውተር ከመጠቀም
መታገድን እንዲሁም ሌሎች የትምህርት ቤቱ የዲሲፒሊን እርምጃ፣ እና/ወይም አግባብ ያለው ህጋዊ እርምጃን
የሚያስከትሉ ይሆናሉ። ተለይቶ የሚታወቁ የስነ-ስርዓት እርምጃዎች የሚወሰኑት በየኬዞቹ ሁኔታ ላይ
ተመርኩዞ ነው።

29
የተማሪ ስነምግባር በባሶች
{ከፖሊሲ #8123P፣ የተማሪ ስነምግባር በባሶች ላይ የተወሰደ አጭር ጽሑፍ}
ተማሪው ማንኛውም በባሱ ሹፌር ወይንም ተቆጣጣሪ ለበጎ በሰላማዊ የባሱ እንቅስቃሴ ላይ እክል
ይፈጥራል ተብሎ የሚታመን የስነምግባር ጉድለት ቢፈጽም፣ ርእሰ-መምህሩ የተማሪውን የትራንስፖርት
አገልግሎት የማግኘት መብት ላይ እግድ ሊጥል ይችላል።
የባስ ተጠቃሚ ተማሪዎች የስነምግባር ደንቦች የሚከተሉት ናቸው:
1. ተማሪዎች ለማንኛውም በዲስትሪክቱ የሚመደብ የባሱ ሹፌር ወይንም ረዳት ተገዢ መሆን አለባቸው።
የባሱ እና የተሳፋሪዎች ሙሉ ሀላፊነት በሹፌሩ እጅ ነው፣ ስለዚህ ሊከበር ይገባዋል። ዲስትሪክቱ ባሱ ላይ
ተባባሪ ባለሙያ ቢመድብ፣ የተሳፋሪዎቹን ስነምግባር የመቆጣጠር ሀላፊነት የእሱ/እስዋ ይሆናል። ክፍል
ሙሉ ተማሪዎች ወይንም ቡድኖች በማጓጓዝ ጊዜ ደግሞ የተማሪዎቹን ስነምግባር የመከታተል ሙሉ
ሀላፊነት በአስተማሪው ወይንም አሰልጣኙ ላይ የወደቀ ይሆናል። ተማሪዎች ሹፌሩን፣ አስተማሪውን፣
አሰልጣኙን፣ ወይንም ሌላ የስታፍ አባልን ማክበር ይኖርባቸዋል። የበስ ሹፌሩ የመጨረሻ ስልጣን
ወይንም ሀላፊነት ይኖረዋል።
2. K-8 ተማሪዎች ከተመደበላቸው ባስ ውጪ መጠቀም የሚችሉት ከትምህርት-ቤቱ ባለስልጣናት
የጽሑፍ ፈቃድ ከተሰጣቸው ብቻ ነው።
3. K-8 ተማሪዎች ከትምህርት-ቤቱ ባለስልጣናት የጽሑፍ ፈቃድ ካልተሰጣቸው በስተቀር ከቋሚ
ፌርማታቸው ውጪ ከባሱ እንዲወርዱ ሊፈቀድላቸው አይገባም።
4. ተማሪዎች ከሹፌሩ ፈቃድ ሳያገኙ በፍጹም ከተመደበላቸው መቀመጫ ውጪ መቀመጥ የለባቸውም።
5. ተማሪዎች በባስ በሚጓዙበት ጊዜ የመማሪያ ክፍል የስነምግባር ደንቦችን መርሳት የለባቸውም።
ሹፌሩን የሚረብሽ ጫጫታ መኖር የለበትም። ተማሪዎች የብልግና ወይንም ክብር የሚነኩ ቃላቶች
ወይንም ምልክቶች ከመጠቀም መቆጠብ አለባቸው።
6. ተማሪዎች መለኮሻ (lighters)፣ ክብሪቶች፣ ወይንም ሌሎች እሳት የሚፈጥሩ ነገሮችን ባስ ውስጥ
ከማስጨስ ወይንም ከመለኮስ መቆጠብ አለባቸው።
7. ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ ካልተፈቀደላቸው እና በአስተማሪ፣ አሰልጣኝ፣ ወይንም ሌላ የስታፍ አባል
ካልታጀቡ በስተቀር ባሶች ላይ ምግብ መብላት የለባቸውም። ባሶች ንጽህናቸው የተጠበቀ መሆን አለበት።
8. ተማሪዎች ሱፌሩ ሳይፈቅድላቸው የባሱን መስኮት መክፈት የለባቸውም።
9. ተማሪዎች በማናቸውም ጊዜ የሰውነታቸው ክፍል በባሱ መስኮት በኩል ወደ ውጭ ማውጣት የለባቸውም።
10. ተማሪዎች ባስ ውስጥ ተማሪዎች ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮችን ይዘው መጓዝ የለባቸውም።
እነዚህ ነገሮች የሚከተሉት እና ሌሎችን ያካትታሉ; ብርጭቆ ወይንም ሌሎች ተሰባሪ መያዣዎች;
የጦር መሳሪያዎች፣ ተተኳሸ መሳሪያዎች፣ ከልብሶች የሚገኙ መቆለፊያዎች እና ስፒሎች; በእግሮች
መካከል ወዘተ ሊቀመጡ የማይችሉ ትልልቅ፣ ከባድ ነገሮች። መጽሐፍቶች ወይንም የግል መገልገያዎች
ከመተላለፊያው ውጪ ነው መቀመጥ ያለባቸው።
11. ተማሪዎች ከመሪ ውሾች በስተቀር ባስ ውስጥ ሌላ እንስሳ ይዘው መግባት አይችሉም።
12. ተማሪ በሹፌሩ ወንበር ላይ ወይንም በሹፌሩ ቀኝ እና ግራ በኩል መቀመጥ አይችሉም።
13. እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ካልተገኘ በስተቀር ተማሪዎች ሹፌሩን ከማነጋገር መቆጠብ ይኖርባቸዋል።

30
14. ተማሪዎች ሹፌሩ ሌላ መመሪያ ካልሰጣቸው በስተቀር ወደ ባስ እንደገቡ ወድያውኑ መቀመጫቸው
ላይ መቀመጥ እና ሳይነሱ መቆየት ይኖርባቸዋል።
15. ተማሪዎች ሹፌሩ ወይንም የተመደበው የትምህርት-ቤት ደህንነት ተቆጣጣሪ የሚሰጡዋቸው
መመሪያዎች በመከተል ወደ ባሱ ሲሳፈሩ እና ከባሱ ሲወርዱ በሰልፍ ነው መሆን ያለበት። ወደ ባስ
ሲገቡም ሆነ ከባስ ሲወርዱ መጎታተት እና መጋፋት የለባቸውም። ተማሪዎች ከባሱ ከወረዱ በኋላ
የእግረኞችን ደንብ አክብረው መጓዝ አለባቸው።
16. ተማሪዎች ከእግረኞች መሻገሪያ ወይንም ከትራፊክ መብራቶች ውጪ ከባስ ጀርባ ተከለልለው
መንገድ ማቋረጥ የለባቸውም።
17. ተማሪዎች ባስ ወደ ማቆሚያ ቦታ በሚቀርብበት ወይንም ከማቆሚያ ቦታ በሚነሳበት ጊዜ ከመንገዱ
ከርቭ መራቅ አለባቸው።
18. ከባሳቸው እና ወደ ባሳቸው ማቆሚያ ቦታ የሚሄዱ ተማሪዎች የመንገዱ ግራ ይዘው ነው መጓዝ
ያለባቸው። ተማሪዎች ከባስ ከወረዱ በኋላ በቀጥታ ወደ ቤታቸው ነው መሄድ ያለባቸው።
19. ተማሪዎች ባሱ ውስጥ የደህንነት ቀበቶ ካለ ማሰር አለባቸው።
20. ተማሪዎች ሹፌሩ በሚሰጣቸው መመሪያዎች መሰረት የአደጋ ጊዜ መውጫ በሮችን መጠቀም አለባቸው።
21. ተማሪዎች ከአደጋ ጊዜ መውጪያ በር ወይንም መሳሪያ ጋር መታገል የለባቸውም።
22. ተማሪዎች ባሱ ላይ ጉዳት ካደረሱ ወላጆቻቸው የደረሰው ጉዳት ማሰሪያ የሚሆን ግፍያ ይከፍላሉ።
ጉዳቱን ያደረሱ ተማሪዎች ከማጓጓዣው ምናልባትም ከትምህርት-ቤት ሊታገዱ ይችላሉ።
23. ተማሪው ያሳየው ስነምግባር ጉድለት ክብደት ማጓጓዣ ከመጠቀም መብቱ ለማገድ በቂ መሆን
መቻል አለበት።
ተማሪዎች ባስ ሲጠብቁ ወይንም ወደ ባስ ማቆምያ ስሄዱ እና ከባስ ማቆምያ ስሄዱ፣ ለአዋቂዎች ለተዘጋጁ
ማህበራዊ እና ሕጋዊ ደንቦች ተገዢ የመሆን ግዴታ አለባቸው። በግልም ሆነ በመንግስት ንብረት ላይ
ጉዳት ማድረስ የለባቸውም; የብልግና ቃላትም ይሁን ምልክቶች መጠቀም የለባቸውም; በፍጹም በወንጀል
ተግባራት መሳተፍ የለባቸውም። እነዚህን ደንቦች ማክበር ባለመቻላቸው በመደበኛ መንገድ ከዜጎች ቅሬታ
ቢቀርብ ይህ ቅሬታ ወደ ርእሰ-መምህር ይተላለፍ እና አስፈላጊ የእርምት ቅጣት ይጣልባቸዋል።
አስፈላጊ ከሆነ፣ የእርምት እርምጃ በመላ ዲስትሪክቱ እንደሚከተለው ተመሳሳይ መሆን አለበት:
1. ማስጠንቀቂያ: ተማሪው ያሳየው የስነምግባር ጉድለት በባህሪው ቀላል የሚባል እና የሌሎች ተማሪዎች
ደህንነት ወይንም የባሱ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ጉዳት የማያደርስ ሆኖ ከተገኘ።
2. እገዳ: ተማሪው ያሳየው የስነምግባር ጉድለት የተሳፋሪዎት ደህንነት እና የባሱ እንቅስቃሴ ላይ እክል
የሚፈጥር ከሆነ፣ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ስነምግባር ጉድለቶቹን ማረም ሳይችል ከቀረ፣
ወይንም ተማሪው ባሱ ላይ ጉዳት ካደረሰ።
3. ማባረር: የተማሪው የስነምግባር ጉድለት ሆን ተብሎ የተደረገ እና በባህሪው የባሱ እንቅስቃሴ እና/
ወይንም የተሳፋሪዎች ደህንነት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የከተተ ከሆነ (ለምሳሌ፣ ሹፌሩ ላይ ጥቃት
ያደረሰ ተማሪ)።
የተማሪው ወላጅ/ሙግዚት ወይንም ተማሪው ራሱ እገዳውን በመቃወም ቅሬታቸውን በጽሑፍ ወደ
ከፍተኛ ሀላፊው ማቅረብ ይችላሉ።

31
ክልከላ፣ ማግለል እና ሌሎች ተገቢ ኃይሎችን መጠቀም
{ከፖሊሲ #3317 የተወሰደ ጽሑፍ፣ ክልከላ እና ማግለል መጠቀም}

ዲስትሪክቱ ሁሉንም ተማሪዎች በክብር በመያዝ ደህንነቱ የተጠቀበቀ የትምህርቲ አካባቢ ማስቀጠል
አለበት። የግል ፍላጎት መሰረት ያደረገየትምህርት ፕሮግራም (IEP) ወይንም በመልሶ ማቋቋም ሕግ 1973
ክፍሊ 504 መሰረት የተዘጋጀ እቅድ ውስጥ የሚሳተፉ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም ዲስትሪክቱ ውስጥ
የሚገኙ ተማሪዎች ተገቢ ካልሆነ ክልከላ፣ የክልከላ መሳሪያዎች፣ መገለል፣ እና ሌሎች አካላዊ ኃይሎች
የመጠቀም ሁኔታዎች ነጻ የመሆን መብት አላቸው። እነዚህ ዘዴዎች በማንኛውም ሁኔታ እንደ እርምት
ወይንም የቅጣት እርምቻ ማገልገል የለባቸውም።

በ RCW 70.96B.010 እና በምዕራፍ 392-172A WAC ላይ በተገለጸው መሰረት እና ይህንን ፖሊሲ


በሚደግፈው አሰራር ላይ በተብራራው መሰረት፣ ተማሪው “ከፍተኛ የሆነ ከባድ አደጋ ጉዳት የማስከተል
ስጋት ያለው” ልቅ ባህሪ በሚያሳይበት ጊዜ ይህንን ለመቆጣጠር ክልከላ እና ማግለል ጥቅም ላይ ሊውሉ
ይችላሉ። ከባድ ጉዳት ሲባል በራስ ላይ፣ በሌሎች ላይ፣ ወይንም በሲስትሪክቱ ንብረት ላይ የሚደርስ
አካላዊ ጉዳትን ያጠቃልላል። ተማሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል ሰራተኞች በቅርበት ክትትል
ያደርጋሉ፣ የተማሪዎች እና የሰራተኞች ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል አነስተኛ የክልከላ እና የማግለል
መጠን ጥቅም ላይ ያውላሉ። ከባድ ጉዳት የማድረስ ስጋቱ ከተወገደ በኋላ የክልከላ እና የማግለል
እርምጃው ያበቃል።

ተማሪዎች ላይ አካላዊ ቅጣት መፈጸም በፍጹም የተከለከለ ነው። አካላዊ ቅጣት ማለት ማንኛውም ሆን
ተብሎ የሚደረግ በተማሪው አካል ላይ ህመም የሚያስከትል ቅጣት ሲሆን መዠለጥ ወይንም መምታትን
ያጠቃልላል። አካላዊ ቅጣት የሚከተሉትን አያጠቃልልም:

1. ከላይ እንደተገለጸው ተገቢ ጉልበት መጠቀም;


2. ለአትሌቲክስ ውድድር በሚሰጥ ስልጠና ወይንም ተማሪው በፍለጎቱ በሚሳተፍበት የመዝናኛ
እንቅስቃሴ ምክንያት የሚፈጠር አካላዊ ህመም ወይንም አለመመቸት;

3. በአስተማሪ የሚሰጡ አካላዊ ድካምን ሊያስከትሉ የሚችሉ የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት


እንቅስቃሴዎች፣ የጉብኝት ጉዞዎች፣ ወይንም የሙያ ትምህርት ፕሮጀክቶች እና ሌሎችም

ከፍተኛ ሀላፊው ወይንም የተመደበው ሰው ይህንን ፖሊሲ ለማስፈጸም የሚያስችሉ አሰራችን


ያዘጋጃል። በተጨማሪ፣ ከፍተኛ ሀላፊው ወይንም የተመደበው ሰው ኃይል ወይንም ማግለል እና ክልከላ
የተስተዋሉባቸው አጋጣሚዎችን በየአመቱ ለቦርዱ ሪፖርት ያደርጋል።

32
ክልከላ፣ ማግለል እና ሌሎች ተገቢ የኃይል እርምጃዎችን መጠቀም
{አሰራር 3317P}

I. ክልከላ፣ ማግለል እና ሌሎች ተገቢ የኃይል እርምጃዎችን መጠቀም


የዲስትሪክቱ ስታፍ ከባድ አደጋ ጉዳት የማስከተል ስጋት ያለው ልቅ ባህሪ በሚታይበት ጊዜ ይህንን
ለመቆጣጠር ተገቢ ነው ብሎ በሚያምንበት ጊዜ ይህ አሰራር ተግባራዊ ይሆናል። አሰራሩ ከ RCW
28A.600.485, RCW 9A.16.020, RCW 9A.16.100, RCW 28A.155.210, WAC 392-400-235፣
እና፣ IEP ላላቸው ተማሪዎች ደግሞ ከምዕራፍ 392-172A WAC ደንቦች ጋር በማይጣረስ መልኩ
መተርጎም ይኖርበታል።

ትርጓሜዎች:

• ማረጋጋት: እራሱን መቆጣጠር ላልቻለ፣ ሕግ ማክበር ያልቻለ ወይንም ተቀባይነት የሌላቸው


ባህሪዎችን የሚያሳይ ተማሪ ለማረም አወንታዊ የባህሪ እርምጃዎች እና ሌሎች በዲስትሪክቱ የጸደቁ
ስትራቴጂዎችን መጠቀም። እነዚህ ስትራጂዎች ለአደገኛ፣ አስቸጋሪ ወይንም የተማሪዎችን ወይንም
የሌሎችን የመማር ሂደት የሚያደናቅፉ ባህሪዎች መፍትሄ ይሰጣል።

• አይቀሬ: የአነድ ሁኔታ የመከሰት እድል የማይቀር ሊባል በሚችል ደረጃ እጅግ ቅርብ ሲሆን።

• ማግለል: ትማሪው መውጣት ከማይችልበት ክፍል ወይንም ሌላ የተዘጋ ቦታ ውስጥ ለብቻው


ማቆየት። ይህ ተማሪው በገዛፈቃዱ ጸጥታን በመምረጥ ጸጥ ባለ ቦታ ለብቻው መቀመጥን፣ ወይንም ተገቢ
አወንታዊ የባህሪ ኢንተርቨንሽን እቅድ ለመተግበር ሲባል ተማሪውን ከመደበኛ ትምህርት ክፍሉ ነጥሎ
ባልተቆለፈ ቦታ ውስጥ ማቆየትን አያካትትም።

• የከባድ ጉዳት የመከሰት ሁናቴ: በተማሪ ይፈጸማል ተብሎ የሚታመን የአካል ጉዳት ስጋት:
o በራሱ ላይ እራሱን የማጥፋት ሙከራ ወይንም በራሱ ላይ አካላዊ ጉዳት የማድረስ ሙከራ
ሊያደርግ እንደሆነ ማስረጃ ሲቀርብ;
o በሌሎች ሰዎች ላይ እነዚህን ጉዳች የማድረስ ስጋት መኖሩ የሚያሳይ በቂ ማስረጃ ሲኖር;
o በሌሎች ንብረት ላይ ከባድ ኪሳራ ወይንም ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ባህርይ ሲያሳይ; ወይንም
o ተማሪው የሌሎችን አካላዊ ደህንነት ላይ አደጋ ለማድረስ ሲያስፈራራ እና ከዚህ በፊት ተመሳሳይ
ችግሮች ፈጥሮ እንደነበር የኋላ ታሪኩ የሚያሳይ ከሆነ።

• ኣወንታዊ የባህርይ ኢንተርቨንሺኖች: ለፈታኝ ባህርይዎች አማራጮችን ለማቅረብ፣ አስፈላጊ


ባህርይዎችን ለመገንባት፣ እና የፈታኝ ባህርይዎች መደጋገም እና አደገኛነት ለማስወገድ የሚተገበሩ
ስትራቴጂዎች እና ትምህርቶች ናቸው። አወንታዊ የባህርይ ኢንተርቨንሺኖች ለፈታኝ ብህርይ
መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ አካባቢያዊ ምክንያቶችን መፈተሽ እና ተማሪው የራሱን ባህርይ መቆጣጠር
የሚችልባቸውን ክህሎቶች ማስተማር ያጠቃልላል።

33
• ክልከላ: ተማሪውን ለመቆጣጠር ከልካይ ወይንም አጋጅ መሳሪያ መጠቀምን የሚያካትት አካላዊ
ኢንተርቨንሽን ወይንም ኃይል የመጠቀም አሰራር። ተማሪው ሚዛኑ የጠበቀ የሰውነት አቋቋም፣ ክብደት
ወይንም ቁመና እንዲኖረው ወይንም ተማሪው እንቅስቃሴዎ ላይ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እንዲሳተፍ
ለማድረግ የሚሰጡ በሐኪም የታዘዙ የሕክምና፣ ኦርቶፔዲክ ወይንም ወይንም ቴራፒቲክ መሳሪያዎችን
አያካትትም።

የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ ፕሮቶኮሎች


ከላይ እንደተገለጸው “ከባድ ጉዳት የማድረስ አቅም ያላቸው” ድንገተኛ አደጋዎች በሚከሰቱ ጊዜ ጥቅም
ላይ የሚውሉ የድንገተኛ አደጋ ፕሮቶኮሎጅ በወላጅ እና በዲስትሪክቱ ሊዘጋጁ ይችላሉ። የድንገተኛ
አደጋ ምላሽ አሰጣጥ ፕሮቶኮሎች፣ከተዘጋጁ፣ የግድ 1) ወደ ተማሪዎ IEP መካተት አለባቸው; 2) የእንደ
ግብ የተያዘው ባህርይ ለመቀየር፣ ለመተካት፣ ለማሻሻል፣ ወይንም ለማጥፋት የተዘጋጀውን የባህርይ
ኢንተርቨንሽን እቅድ ተክቶ ጥቅም ላይ መዋል የለበትም; እንዲሁም 3) ለሚከተሉት ሁናዎች እና
ውስንነቶች ተገዢ መሆን አለበት:

ሀ) የተማሪው ወላጅ ወይንም ሞግዚት አስቀድሞ በሚዘጋጀው የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ
ፕሮቶኮል መስማማቱ የሚገልጽ ጽሑፍ ማቅረብ መቻል አለበት:

መ) የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ ፕሮቶኮሎች:

(i) ማግለል፣ ክልከላ፣ ወይንም የክልከላ መሳሪያዎች ጥቅም ላይ የሚውሉባቸው የድንገተኛ አደጋ
ሁኔታዎች ለይቶ ያስቀምጣል;

(ii) ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸው የማግለል፣ ክልከላ፣ እና/ወይንም የክልከላ መሳሪያዎች


አይነቶች ይዘረዝራል;

(iii) ተማሪው ላይ የማግለል፣ ክልከላ፣ እና/ወይንም የክልከላ መሳሪያ እንዲጠቀሙ የተፈቀደላቸው


ስታፍ ወይንም ኮንትራት የወሰዱ አካላት እንዲሁም የማግለል፣ ክልከላ፣ እና/ወይንም የክልከላ መሳሪያ
(ዎች) እንዲጠቀሙ የተሰጣቸው ስልጠና;

(iv) ሌሎች ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸው ማናቸውም ልዩ ቅድመጥንቃቄዎች።

ሐ) ማንኛውም የማግለል፣ ክልከላ፣ እና/ወይንም የክልከላ መሳሪያ(ዎች) መጠቀም ከባድ ኩዳት


የመፈጠር ስጋቱ ከተወገደ በኋላ ወድያውኑ መቋረጥ አለበት።

መ) ማንኛውም የማግለል፣ ክልከላ፣ እና/ወይንም የክልከላ መሳሪያ(ዎች) እየተጠቀመ የሚገኝ ስታፍ


አባል ወይንም አዋቂ፣ የማግለል፣ ክልከላ፣ እና/ወይንም የክልከላ መሳሪያ(ዎች) መጠቀም የሚመለከት
ስልጠና የወሰደ እና የብቃት ማረጋገጫ የተሰጠው መሆን አለበት።

34
የድህረ ክስተት ማስታወቂያ እና ግምገማ ከወላጅ/ሞግዚት ጋር:
ተማሪው ላይ ክልከላ ወይንም ማግለል ተግባራዊ ከተደረገ በሀያ አራት (24) ሰአታት ውስጥ፣ ርእሰ-
መምህርሩ ወይንም የሚመለከተው አካል ለተማሪው ወላጆች ወይን ሙግዚት በቃል ለማሳወቅ ተገቢውን
ጥረት ማድረግ አለበት። ርእሰ-መምህርሩ ወይንም የሚመለከተው አካል እርምጃው ተግባራዊ ሲሆን
ወድያውኑ የጽሑፍ ደብዳቤ መላክ ያለበት ሲሆን፣ ይህ ደብዳቤ ከአምስት (5) የስራ ቀናት ባላነሰ
ጊዜ ውስጥ መድረስ ይኖርበታል። ትምህርት-ቤቱ በተለምዶ ለተማሪው ወላጅ ወይንም ሙግዚት
የሚያደርሳቸው መረጃዎች በእግሊዘኛ ሳይሆን በሌላ ቋንቋ ከሆነ የሚያዘጋጅላቸው፣ የተጻፈው ሪፖርትም
በዚሁ ቋንቋ ነው ለወላጅ ወይንም ለሞግዚቱ መቅረብ ያለብት።

ርእሰ-ምምህረሩ ወይንም የተመደበው አካል:


• ዘዴውን ለመጠቀም ምክንያት የሆነው ባህርይ እና የምላሹ ተገቢነት በሚመለከት ከተማሪው ወላጅ
ወይንም ሞግዚት (በአንድ ጊዜ አስፈላጊ ባይሆንም) ጋር ሆኖ ይገምግማል።

• የማግለል ወይንም የክልከላ እርምጃውን ተግባር ላይ ካዋሉት የስታፍ ሰዉ(ዎች) እርምጃዎቹ ተገቢ
አሰራሮችን ስለመከተላቸው እና ተማሪውን ተመሳሳይ ባህሪዎችን እንዲያስወግድ ለመርዳት ምን አይነት
የስታፍ ስልጠና ወይንም እገዛ እንደሚያስፈልግ ይወያያል።

የክስተት ሪፖርት:
በአሰራሩ ላይ እንደተገለጸው በትምህርት-ቤት የገንዘብ እገዛ በሚሰጡ ትምህርቶች ወይንም
እንቅስቃሴዎች ላይ በማንኛውም ተማሪ ላይ የማግለል ወይንም የመከልከል ተግባር የሚያከናውነው
ማንኛውም የትምህርት-ቤቱ ተቀጣሪ ሰራተኛ ወይንም የትምህርት-ቤቱ ደህንነት ሀላፊ፣ ለርእሰ-
መምህሩ ወይንም ለተመደበው ሰው ወድያውኑ ያሳውቃል እንዲሁም በሁለት (2) የስራ ቀናቶች ውስጥ
የክስተቱ ሪፖርት በጽሑፍ ለዲስትሪክት ጽሕፈት-ቤቱ ያቀርባል። በጽሑፍ የሚዘጋጀው ሪፖርት ብያንስ
የሚከተሉትን ማካተት አለበት:

• ክስተቱ የተፈጠረበት ቀን እና ሰአት;

• የመከልከል እና የማግለል ተግባሩን ያስተዳደረው የስታፍ አባል ስም እና ስለጣን;

• ለክልከላ እና ማግለል እርምጃው መነሻ የሆነው ክስተት መግለጫ;

• ተግባራዊ የተደረገው የክልከላ እና የማግለል አይነት እና የቆየበት ጊዜ;

• ክልከላ ወይንም ማግለል ባስከተለው ክስተት ተማሪው ላይ ወይንም የስታፍ አባሉ ላይ ያጋጠመ
አካላዊ ጉዳት ካለ;

• ለተማሪው ወይንም ለስታፍ አባሉ የተሰጠ ማንኛውም የሕክምና እንክብካቤ; እንዲሁም

• እንዲሁም ማናቸውም ተመሳሳይ ክስተቶችን ለማስወገድ የሚያስችሉ ተማሪው ወይንም ስታፍ


አባሉ የሚጠቀምባቸው የሪሶርሶች ባህሪ እና መጠን ላይ ለውጥ ለማድረግ የሚያስችሉ ምክሮች።

35
የመከልከል፣ ማግለል እና ሌሎች ተገቢ ኃይሎችን መጠቀም የሚመለከት ፖሊሲ ለወላጆች/
ሞግዚቶች መስጠት:
ዲስትሪክቱ የመከልከል፣ ማግለል እና ሌሎች ተገቢ ኃይሎችን መጠቀም የሚመለከት ፖሊሲ ለሁሉም የተማሪ
ለወላጆች/ሞግዚቶች ይሰጣል። ተማሪው IEP ወይንም የ 504 እቅድ ካለው፣ ዲስትሪክቱ መነሻ ወይንም
አመታዊ IEP ወይንም የ 504 እቅድ በሚዘጋጅበት ጊዜ ለወላጆች/ሞግዚቶች የፖሊሲው ቅጂ ይሰጣል።

የስታፍ ስልጠና መስፈርቶች:


ሁሉም ስልጠናዎች አወንታዊ የተማሪ ባህርይ አያያዝ፣ የባህል ስስነት፣ ረባሽ ወይንም አደገኛ ባህርይ
ለማስወገድ ወይንም ለማቀዝቀዝ የሚያስችል ውጤታማ ኮሚዩኒኬሽን እንዲሁም ደህንቱ የተጠበቀ
እና ተገቢ የኃይል፣ ማግለል እና መከልከል አጠቓቀም ትምህርቶችን ያካተተ ይሆናል። አስተዳዳሪዎች
በየአመቱ ለሁሉም የስታፉ አባላት የዲስትሪክቱ የተገቢ ኃይል አጠቃቀም ፖሊሲ እና አሰራሮች
ይሰጡዋቸዋል።

ሁሉም የስታፍ አባላት ነገሮችን የማብረድ እና ተገቢ አካላዊ እርምጃ የመውሰድ አሰራሮችን ማወቅ
ይገባቸዋል። የሚመለከታቸው የስታፍ አባላት እና አካላዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚሰማሩ ሰዎች አካላዊ
እርምቻ አወሳሰድ የሚመለከት ስልጠና ይሰጣቸዋል።

ተጠቃሽ ፖሊሲዎች እና አሰራሮች


# 2314 - በኔትዎርክ የቀረቡ የመረጃ ሀብቶችን እና ኮሚኒኬሽኖችን በተመለከተ ለተማሪዎች ያላቸው
ተደራሽነት
# 3209 - ተማሪዎች፡- የወሲብ ጥቃት
# 3210 - የማግለል
# 3122 - ምህረት የሚደረግለት እና የማይደረግለት ቀሪ
# 3300 - የተማሪዎች ባህሪ እና ለውጥ የማስተካከያ እርምጃ
# 3302 - ስነ-ምግባር እና ታማኝነት
# 3308 - የጥቃት/ ትንኮሳ - ጋጠወጥነት እና የድብድብ ድርጊቶች ላይ የመወሰን እርምጃ
# 3310 - Discipline and Corrective Action for Student Misconduct
# 3600 - የተማሪዎች ሪከርዶች
# 3610 - የሕጻናት አሳዳጊ
# 8123 - በሰርቪስ ባሶች ላይ የተማሪ ባህሪ
እንዲሁም የሚከተሉት ይመለከታል፡- ፖሊሲ # 2151 የትምህርታዊ አትሌትኪሶች ትብብር/ የተማሪዎች
አትሌቲክሲ ባህሪ

36
ማሳሰቢያዎች
ከጦር መሳሪያ ነጻ የሆኑ ዞኖች
• በRCW 9.41.28 መሰረት ማንኛውም ትምህርትቤት ከጦር መሳሪያ ነጻ የሆነ አካባቢ ነው። በRCW 9.41.28
መሰረት በተገለጸው መሰረት ማንኛውም ትምህርትቤት ከማንኛውም የጦር መሳሪያ ወይም በሌሎች ላይ
ጉዳት የሚደርሱ ስለት መሳሪዎች ነጻ የሆነ አካባቢ ነው። ተማሪውን ለማባረር እና ለሕግ አስፈጻሚ አካላት
ሪፖርት ለማድረግ መሰረት የሚሆኑ የደንብ ጥሰቶች

• የትምህርትቤት ንብረት በሆነው ቅፅር ጊቢ ውስጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ለወላጆች በማሳወቅ ለአንድ
አመት ከትምህርትቤት የማስወገድ እርምጃ የሚወሰድበት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በህግ አስፈጻሚ አካላት
ጉዳዩ እንዲቀርብ ይደረጋል። (በRCW 28ኤ.600.420)

አዳኝ ውሻ ማፈላለግ
• በህግ እንደተወሰነው እና እንደተቀመጠው በትምህርትቤት ውስጥ አደንዛዥ እጽ ወይም ኮንትሮባንድ
የያዙ ተማሪዎች መኖራቸው ከተጠረጠረ በትምህርትቤት ጊቢ ውስጥ እነዚህን አዳኝ ውሾችን በመጠቀም
ማፈላለግ እና እንዲያዙ ማድረግ ይቻላል።
(መቆለፊያዎችን ጨምሮ.

ህፃን ልጅ ማፈላለግ
{ለ Shoreline የሕዝብ ትምህርት ቤቶች}
ልጅህ በሁለንተናዊ አኳሃኑ በንግግር እና ቋንቋ ችሎታው፣ በራኢው እና በመስማት ችሎታው፣ ለክህሎቶቹ፣ በተሰጦ እና
በውስጣዊ ችሎታቸው ወይምወይም በማህበራዊ ስሜት እንዲበለጽጉ ወይም እንዲያድጉ ትፈልጋለህ?
ሕጻናትን የማግኛ ማጣሪያ የተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ በወር አንድ ጊዜ ሲሆን ይህም ከመስከረም ወር አንስቶ እስከ ግንቦት ወር
ሲሆን ስፍራውም በሜሪዲያን ፓርደክ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትቤት አድራሻው 17077ሜሪዲያን ጎዳና የሆነ N,
Shoreline. የህንጻን ልጅ ችሎታ ፈለጋ አመራረጥ በትምህርትቤቱ ከፍተኛ ባለሙያዎች (በንግግር እና በቋንቋ መምህራን
በስነ-ልቦና በስራና አካላዊ ቴራፒስቶች እና ስነ-ልቦና ባለሙያዎች) ይካሄዳል።
የልጅነት ትምህርት ጥሪ በ(206) 393-4250 ለተጨማሪ መረጃ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

37
ጸረ-ተባይ አጠቃቀም
ይህ ማስታወቂያ በትምህርትቤቱ ቅፅር ጊቢ ውስጥ ለአንዳንድ ቦታዎች ጸረ- አረም ለምንጠቀምበት ምክር
እንዲሆን የተዘጋጀ ነው። ላለፉት ብዙ አመታት በጥሩ ሀኔታ በተቀናጀው የተባይ አስተዳደር እቅዳችን
አማካኝነት ጸረተባይ መጠቀም የቀነስን ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ ፍላጎቱ አለንቨ በማንኛውም መልኩ በየጊዜው
ጸረ- አረም አንጠቀምም። ቢሆንም በአንዳንድ ቦታዎች (በተለይ ለአጥር መስመር ስር፣ ኮንክሪቶች ስር)
ልንፈልግ እንችላለን። ፀረ ተባይ የምንጠቀመው በተመሰረተው የሾርላይን ወረዳ አሰራር መሰረት ሲሆን ይህም
ለተቀመጠው የፀረ ተባይ አጠቃቀም እርምጃዎችን የምንጠቀምበት ነው። የዋሽንግተን ስቴት የተፈቀደላቸው
የወረዳው ሰራተኞች ብቻ ወይም ትክክለኛ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ብቻ ፀረ ተባይን ይጠቀማሉ። ስለ ፀረ ተባይ
አጠቃቀም አስመልክቶ የምንጠቀማቸው መረጃዎች በአመታዊ ማጠቃለያ የሚወጡ የአጠቃቀሞች መረጃ
የሚያጠቃልል ሲሆን እነዚህም ደግሞ በየአመቱ መጨረሻ ማጠቃለያዎች ሾርላይን ማእከል ላይ ይገኛሉ።
ቀጥሎ የተመለከቱት በሕጉ መሰረት መጠቀም የሚችለው መጠን ሲሆን በተለይ ደግሞ በዋሽንግተን ስቴት
በRCW (17.21.415) መሰረት በተገለጸው የአጠቃቀም አሰራሮች መሰረት በትምህርትቤቱ ወረዳ ግዛት ውስጥ
የአጠቃቀሙን ሂደት ካስተዋወቅን በኋላ ተግባራዊ እናደርገዋለን። ት/ቤት የሚለው ቃል የሚያመለክተው
የትምህርትቤት ወረዳ ግዛት መሆኑን ብቻ እንጂ አንድ በተጨባጭ የታወቀውን ትምህርትቤት ብቻ
የማያመለክት ያለመሆኑን እና በአጠቃላይ ት/ቤቶች ውስጥ ሕጋዊ ኃላፊነት ያለባቸው አሰራሮች የሚተገበሩበት
መሆኑን ሊያውቁ ይገባል።
በመጨረሻም በወረዳችን ውስጥ የፀረ ተባይ አጠቃቀም ልምድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የአጠቃቀም ሁኔታን
የሚተገበረው የአጠቃቀም ሁኔታ በክረምት እና በሌሎች የትምህርትቤት እረፍት ጊዜ ይሆናል። ሆኖም ግን
አንዳንድ ጊዜ የግድ በትምህርት ወቅት የምንጠቀምባቸው ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ።
RCW 17.21.415 ትምህርትቤት የሚከተሉትን ነገሮች እንዲያከናውን ይፈልጋል፡-
1. ፀረ ተባይ ለመጠቀም ሁኔታዎች በሚያስገድዱበት ጊዜ ቢያንስ የተማሪዎችን ወላጆች ወይም አሳዳጊዎቻቸውን
እንዲሁም የትምህርትቤቱ ሰራተኞች ቢያንስ ከ48 ሰዓት በፊት የማሳወቅ ስርዓት ስራ ላይ ይውላል።
2. እነዚህ ማስታወቂያ ስርዓቶችን የሚያካትቱት ማስታወቂያዎችን የሚለጠፉት በጣም ግልጽ በሆነ እና
በሚታይ ቦታ በትምህርትቤቱ ዋና መ/ቤት አካባቢ ይሆናል።
3. ሁሉም ለወላጆች፣ ለአሳዳጊዎች እና ለሰራተኞች የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች በሙሉ ከላይ «ማስታወቂያ»
የሚል ርዕስ ይኖረዋል። የፀረ ተባይ አጠቃቀም እና ቢያንስ መገለጽ ያለበት፡-
(ሀ) የምንጠቀመው የፀረ ተባይ አምራች ስም፣
(ለ) ለመጠቀም የታሰበው ቀንና ሰዓት፣
(ሐ) ፀረ ተባዩ የምንጠቀምበት ቦታ፣
(መ) ለመቆጣጠር የተፈለጉ ተባዮች እና
(ሠ) በትምህርትቤት ውስጥ ጉዳዩ የሚመለከተው ግለሰብ ስምና ስልክ ቁጥር
4. በትምህርትቤት ውስጥ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች ማመቻቸት ፀረ ተባዩን ለመጠቀም ከታሰበው ጊዜ እና
ሰዓት በፊት ቢያንስ 48 ሰዓት ቀደም ተብሎ በማስታወቂያው ውስጥ መካተት ያለበት ሲሆን የማስታወቂያው
ሂደትም እንደገና በድጋሚ ይገለጻል።
5. ትምህርትቤቱ ፀረ ተባይ በሚረጭበት ጊዜ አስፈላጊ የሆኑትን ምልክቶች በሙሉ የሚጠቀም ሲሆን
አልፎ አልፎ ግን በተፈለገው አካል ብቻ መለጠፍ የሚያስፈልግ ከሆነ የተገደበ ይሆናል፤ ይህም በስምምነት
RCW17.21.410 (አይ) (ዲ) መሰረት ነው።
(ሀ) ለፀረ ተባይ መርጨት የምልክቶች ማስታወቂያ በትምህርትቤቱ ውስጥ የሚደረጉ ምልክቶች
በትምህርትቤቱ ሰራተኞች የሚከናወኑ ሲሆን እነዚህ ምልክቶችም አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆኑ እንደ
ትምህርትቤቱትምህርትቤቱ መግቢያ አካባቢ ይደረጋሉ። የምልክቶቹ መጠን ቢያንስ 4ኢንች መሆን ያለበት
ሲሆን አስፈላጊ ሲሆንም እስከ 5ኢንች ሊደርስ ይችላል። ይህም የተካተቱትን ቃላቶች ያጠቃልላል። «ይህ ቦታ
ከዚህ ቀደም ፀረ ተባይ በት/ቤታችሁ የተረጨ ሲሆን» እንደ ርዕስ መጠቀም ይቻላል። እንዲሁም ለበለጠ መረጃ
በካፒታል ሌተሮች የተጻፉትን እንደ ፉተር መጠቀም ይቻላል። ፉተሩ በትምህርትቤት ውስጥ የሚመለከተው
አካል ስምና ስልክ ቁጥርን የያዘ ይሆናል።

38
እባክዎ ሊያውቁት የሚገባ፡- የመጀመሪያው የትምህርትቤቱ መግቢያ የተባለው ሁሉም አካላት በእግርም
ሆነ በተሽከርካሪ ወደ ትምህርትቤቱ ቅጥር ግቢ የሚገቡበት በር ይሆናል።
(ለ) የአጠቃቀሙ ምልክቶች ከትምህርትቤቱ ቅጥር ግቢ ይልቅ ፀረ ተባዩ መድሐኒት የሚረጭበት
ተጨባጭ ቦታ ላይ ይለጠፋል። የዚህ መጠንም ቢያንስ 8.5x11ኢንች ይሆናል። እና እነዚህም ማስታወቂያ
የሚለውን ርዕስ ያጠቃልላል። የፀረ ተባይ አጠቃቀም እና ቢያንስ መገለጽ ያለበት፡-
(i) የሚረጨው ፀረ ተባይ መድሐኒት ምርት ስም፣
(ii) የሚረጭበት ቀንና ጊዜ
(iii) ፀረ ተባዩ መድሐኒት የሚረጭበት ተጨባጭ ቦታ፣
(iv) ለመቆጣጠር ወይም ደግሞ እንዲጠፋ የተፈለገው ተባይ፣ እና
(v) ከትምህርትቤቱ ጉዳዩ የሚመለከተው ግለሰብ ስልክ ቁጥር እና ስም ናቸው።
(ሐ) የማስታወቂያው ምልክቶች መድሐኒቱ ከሚረጭበት ቦታ በተቃራኒ የሚታይ ቀለም የታተመ
መሆን አለበት።
(መ) ይህ ማስታወቂያ መድሐኒቱ ከተረጨ በኋላ ቢያንስ ለ24 ሰዓት በቦታው መቆየት ያስፈልጋል።
የመድሐኒቱ አጠቃቀም ሁኔታ እና ኃይሉ ከዚህ በላይ ከ24 ሰዓት በላይ እንዲቆይ የሚያስፈልግ ከሆነ
እንደሚያስፈልገው ሁኔታ ማስታወቂው በቦታው ከዚህ በበለጠ ጊዜ እንዲቆይ ይደረጋል። እነዚህ
ማስታወቂያዎች የሚገነጥሉ ሕገ-ወጥ ለሆኑ ሰዎች ትምህርትቤቱ መጋለጥ የለበትም።
6. ትምህርትቤት ውስጥ የምንጠቀማቸው ፀረ ተባይ መድሐኒቶች ሌሎች አይነት ፀረ ማይክሮቢያል
ፀረ ተባይ አይነቶች ወይም ሌሎች አይነቶች አደገኛ የሆኑ እና ሕጻናት መድረስ የሚችሉበት አካባቢ
እንድንጠቀም አይደረግም።
7. የዚህ ክፍል ቅድመ ማሳወቂያ ከማመልከቻው በኋላ ትምህርት ቤቱ ቢያንስ ለሁለት ተከታታይ ቀናት
የትምህርት ቤት አቅርቦት ማመልከቻዎች ከቀረቡ በስራ ላይ አይውሉም።
8. የዚህ ክፍል ቅድመ ማሳወቂያ መስፈርቶች በማንኛውም የድንገተኛ የትምህርት ቤት አቅርቦት
ማመልከቻዎች ላይ በስራ ላይ አይውሉም ይህም ማንኛውንም በሰው ልጅ ጤና ላይ እክል የሚያስከትሉ
ነፍሳቶችን ለመቆጣጠር ወይም፣ እንደ ጎጂ ነፍሳት ያሉ ለደህንነት ስጋት ነገሮችን ለመቆጣጠር በሰራ ላይ
የሚውሉ አይነቶቹን ነው። ድንገተኛ የትምህርት ቤት ተግባራዊ ክንውን በሚደረግ ጊዜ፣ ከትምህርት
ቤቱ የማሳወቂያ ስርዓት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ማሳወቂያ ወዲያውኑ በስራ ላይ ይውላል። ሌላ ሰው በባሱ
ውስጥ በትምህርትቤቱ ወረዳ ተመድቦ ከተገኘ የተመደው ሰው ለተሳፋሪዎቹ ባህሪያት ኃላፊነት አለው።
9. በዚህ ምዕራፍ ስር በሚፈለገው መሰረት ለትምህርትቤቱ ፋሲሊቲዎች በሚያስፈልገው መሰረት
ትምህርትቤቱ አጠቃላይ የፀረ ተባይ መርጨት ስራዎችን ይተገብራል። እነዚህም አመታዊ የማጠቃለያ
ሪፖርቶችን እንዲሁም ለሚመለከተው ግለሰብ በሚያገኝ መሰረት ዝግጁ መሆናቸውን ያጠቃልላል።
10. ትምህርትቤቱ ማስታወቂያዎቹን የሚገነጥሉ ወይም ምልክቶቹን የሚያጠፉ ለሕገ-ወጥ ግለሰብ
መጋለጥ አለበት። በዚህ ክፍል ውስጥ የሚካተተው ትምህርትቤት ግለሰብ ንብረቶችን ለማበላሸት
አይጋለጥም ወይም ደግሞ ማንኛውም በሰውነት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ያደርጋል። ወይም በምልክቶቹ
ምክንያት አደጋዎች እና የተለያዩ ብልሽቶች እንዳይደርሱ ጥንቃቄ ያደርጋል።

39
የአስቤስቶስ አመራር እቅድ
የአካባቢ ጥበቃ ኤጀነሲ ትምህርት-ቤቶች ላይ የሚያደርገው የአስቤስቶስ ቁጥጥር መሰረት በማድረግ፣
የዲስትሪክት ትምህርት-ቤቶች የአስቤስቶስ አያያዝ እቅድ መዘጋጀቱን ለወላጆች፣ ለአስተማሪዎች እና
ለሰራተኞች ድርጅቶች ማሳወቅ እንዳባቸው ይጠይቃል።

የሾርላይን ዲስትሪክት ትምህርት-ቤት (Shoreline School District) በተቋሞቹ የሚተገበር የአስቤስቶስ


አያያዝ እቅድ ያወጣው በ 1988 ነበር። እነዚህ እቅዶች በእያንዳንዱ ተቋም የሚገኙ አስቤስቶስ የያዙ
ቦታዎችን መዝግበው ይይዛሉ። የሁሉም ስልጠናዎች፣ ማስታወቂያዎች፣ ፍተሻዎች፣ ዳግመ-ፍተሸዎች
ሰነዶች እንዲሁም የአስቤስቶስ ስራ ወይንም የአስቤስቶስ አወጋገድ እንቅስቃሴዎች አጫጭር መረጃዎች
ጠ 18560 1st Ave N.E., Shoreline, Washington በሚገኘው የሾርላይን ዲስትሪክት ትምህርት-ቤት
የጥገና ዲፓርትመንት (Shoreline School District Maintenance Department) ተቀምጠው
ይገኛሉ። እያንዳንዱ የ Shoreline School District የአስቤስቶስ አያያዝ እቅድ በህዝባዊ ትምህርት
ሀላፊው ፋይል ተደርጎ የተቀመጠ ሲሆን በእያንዳንዱ የትምህርት-ቤት ቦታ አስተዳደር ጽሕፈት-ቤት
እና በሾርላይን ዲስትሪክት ትምህርት-ቤት የጥገና ዲፓርትመንት ይገኛል። አንድ የተቆጣጣሪ መስፈርት
ለሁሉም በትምህርት-ቤት ህንጻ ላይ የሚሰሩ የአጭር ጊዜ ሰራተኞች የአስቤስቶስ አያያዝ እቅድ መኖሩ
የሚገልጽ ማስታወቂያ መስጠትን ያካትታል። በእያንዳንዱ ቦታ የሚገኙ የጽሕፈት-ቤቱ ሰራተኞች
የአስቤስቶስ አያያዝ እቅዱን ለሁሉም ህንጻው ላይ የግንባታ ወይንም የጥገና ስራ የሚሰሩ የአጭር ጊዜ
ሰራተኞች መስጠት ይጠበቅባቸዋል። የአስቤስቶስ አያያዝ እቅዱ የሽፋን ገጽ የትኞቹ የግንባታ እቃዎች
አስቤስቶስ ይዘው እንደሚገኙ ያብራራል፣ ምዕራፍ V ደግሞ እያንዳንዱ እቃ እና የሚገኝበት ቦታ
በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይሰጣል።

40
Shoreline School District
ለድንገተኛ አደጋዎች፣

ሪፖርትያድርጉ!
እባክዎ በ 911 ይደውሉ!

911!

በሚከተሉት ላይ የሚቀርብ
የትምህርት-ቤቶች ደህንነት (SafeSchools) መረጃ:
የማንቂያ ደወል የዲስትሪክታችን መረጃ ሪፖርት
ማድረጊያ አገልግሎት ነው። ደህንነታችን ላይ • ሰው መምታት
ስለተደቀነ አደጋ መረጃ ካለዎት ሪፖርት በማድረግ • ማስፈራራት
የበኩልዎን ይወጡ! ይህ ሲያደርጉ ስምዎ • ጥቃት
አለመጥቀስ እንደሚችሉ ያስታውሱ።
• የጦር መሳሪያዎች
• አደንዛዥ ዕፆች
4 ቀላል መንገዶች • ሌላ
http://1261.alert1.us
1261@alert1.us
206.317.5768
መረጃዎ ወደ 206.317.5768
በጽሑፍ ይላኩ

ለድንገተኛ አደጋዎች፣ ሁልጊዜም በ 911 ይደውሉ። ሁሉም ወደ የትምህርት-ቤቶች ደህንነት ማንቂያ ደወል ስርአታችን የተላኩ መረጃዎች ተገቢው ትኩረት በማድረግ አስፈላጊ ምላሽ ይሰጥባቸዋል። እባክዎ መረጃ ሲያቀብሉ ሀላፊነት በተሞላበት መንገድ ይሁን

41

Вам также может понравиться