Вы находитесь на странице: 1из 125

የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

1
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት
የተማሪ መማሪያ መጽሐፍ
አምስተኛ ክፍል

አዘጋጆች
ጀማል ጌታሁን
ቸርነት ታደሰ
አዝማች አዋጎ

አርታኢዎችና ገምጋሚዎች
ተስፋዬ አቤ
ወንድአለ ሥጦቴ
አዶንያስ ገ/ሥላሴ
ውብዓለም በየነ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ


2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
© በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ
አዲስ አበባ
2014 ዓ.ም
ማውጫ ገጽ

ምዕራፍ አንድ
ዘመናዊ የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ እና ስፖርት�������������������������������������������������������������� 1
1.1 የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ምንነት������������������������������������������������������������ 2
1.2 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ደህንነት����������������������������������������������������������������������� 4
1.3 በኢትዮጵያ ታዋቂ የሆኑ ስፖርተኞች������������������������������������������������������������������������ 6

ምዕራፍ ሁለት
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ በማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ትምህርት ���������������������������������� 14
2.1. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለራስ ግንዛቤ እና የአመራር ክህሎት ማሻሻል������������������� 15
2.2. የአካል እንቅስቀሴ ለመልካም ግንኙነት ክህሎት መሻሻል���������������������������������������� 18
2.3.የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሀላፊነት ለተሞላበት ዉሳኔ አሰጣጥ����������������������������������� 20
2.4 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለተሻለ የጋራ ����������������������������������������������������������������� 24
መግባባት ክህሎት�������������������������������������������������������������������������������������������������������� 24

ምዕራፍ ሶስት
ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች������������������������������������������������������������������������������ 30
3.1- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ�������������������������������������������������������������������������������������� 31
3.2- የልብና የአተነፋፈ ስብርታትን የሚያሻሽሉ እንቅስቃሴዎች ������������������������������������������� 32
3.3 የጡንቻ ብርታት የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች������������������������������������������������������������ 38
3.4- መዘርጋትናመተጣጠፍ /Felexibility/�����������������������������������������������������������������������42
3.5- ቅልጥፍና������������������������������������������������������������������������������������������������������������ 46
3.6. አበረታች ቅመም ምንድን ነው?��������������������������������������������������������������������������������49

ምዕራፍአራት
አትሌቲክስ������������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 53
4.1- ሩጫ������������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 54
4.2. ውርወራ��������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 59
4.3 ዝላይ�������������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 61
4.3 የከፍታ ዝላይ�������������������������������������������������������������������������������������������������������� 62

I
ምዕራፍ አምስት
ጅምናስቲክ������������������������������������������������������������������������������������������������������������������ 66
5.1 ያለመሳሪያ የሚሰሩ የጅምናስቲክእንቅስቃሴዎች�������������������������������������������������������� 67
5.2 በመሳሪያ የሚሰሩ ጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎች����������������������������������������������������������� 73
5.3 ተከታታይነት ያከው የጅምናሰቲቸ እንቅስቃሴ ጅምናስቲክ������������������������������������������ 77
ምዕራፍ ስድስት
በኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ የማቀበል እና ������������������������������������������������������������������ 82
የመቀበል ክህሎት�������������������������������������������������������������������������������������������������������� 82
6.1 የኳ ስአያያዝ���������������������������������������������������������������������������������������������������������� 83
6.2 ኳስ በአየር ማቀበል������������������������������������������������������������������������������������������������ 84
6.3 በክንድ ኳስ ማቀበል����������������������������������������������������������������������������������������������� 87
6.4 ኳስ ማንሳት እና ማቀበል��������������������������������������������������������������������������������������� 89
6.5 በዉስጥ የጎን እግር ኳስን ማቀበል�������������������������������������������������������������������������� 91
6.6 በዉጭየጎንእግርኳስንማቀበል���������������������������������������������������������������������������������� 93
6.7 በአነስተኛ ጨዋታ ጊዜ በውስጥ እና በውጭ የጎን እግር አጨዋወት������������������������� 95
6.8 ኳስ በደረት ማቀበል���������������������������������������������������������������������������������������������� 97
6.9 በእጅ ኳስ እና በቅርጫት ኳስ ጨዋታ ጊዜ ኳስን በማንጠር ማቀበል������������������������� 99
6.10- አነስተኛ ጨዋታ.����������������������������������������������������������������������������������������������� 101
ምዕራፍ ሰባት
በአዲስ አበባ ደረጃ የሚገኙ የኢትዮጵያ ባህላዊ እንቅስቃሴዎች እና ጨዋታዎች��������������� 104
7.1. ባህላዊ እንቅስቃሴዎች����������������������������������������������������������������������������������������� 105
7.2. በአዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ የተወሰኑ
የኢትዮጵያ ባህላዊ እንቅስቃሴዎች (ክፍልአንድ)����������������������������������������������������� 106
7.3. ባህላዊ ጨዋታዎች���������������������������������������������������������������������������������������������� 109
7.4 በአዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ባህላዊ ጨዋታዎች������������������� 110

II
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

መግቢያ
ትምህርት ብቁ ዜጋን ለማፍራት የሚያስችል የማንኛውም ሀገር ተግባር ነው::
ብቁ ዜጋ ሲባል በአዕምሮ፣ በአካል፣ በስነ- ልቦናና በማህበራዊ ግንኙነት ጤናማ
ትውለድ መፍጠር ማለት ነው፡፡

የሀገራችንም የመጀመሪያ የትምህርት ግብ ይህ ሲሆን ይህንን ግብ ለማሳካት


አስተዋፅኦ ካላቸው ግባዓቶች ውስጥ ዋናው ሥርዓተ ትምህርት ነው፡፡ የሥረዓተ
ትምህርት አንዱ አካል የሆነው የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ብቁ ዜጋን
ለማፍራት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ዓላማ
ለአንድ ሀገር እደገት ልማትና ብልፅግና ወሳኝ የሆነ በአዕምሮ፣ በአካል፣ በሰነ-ልቦናና
በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀ ዜጋን መፍጠር ነው፡፡

የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርትን ልዩ የሚያርገው ሁሉንም የሰው ልጅ


አካል ሰለሚያዳብር ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት
በከተማችን ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት በሁሉም
የትምህርት ደረጃዎች ላይ ይሰጣል፡፡

የአምስተኛ ክፍል የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ዋና ትኩረት አጠቃላይ


የእንቅስቃሴ ክህሎቶችን እና ፅንሰ ሀሳብን በማስጨበጥ፣ ለቀጣዩ ክፍል ዝግጁ ማድረግ
እና በትምህርት መስኩ በህይወታቸው የሚያበረክቷቸውን ጥቅሞች ማስገንዘብ
በሚል መሰረታዊ ንድፈ ሀሳብ ላይ ነው፡፡ ይህንን ስረዓተ ትምህርት መሰረት
በማድረግ የአምስተኛ ክፍል የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት የተማሪው መፃህፍ
ተዘጋጅቷል፡፡

ይህ የተማሪው መፅሐፍ በዚህ የክፍል ደረጃ ላይ ዓላማዎችን ከግብ ለማድረስና


ለማሳካት አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ሰባት ምዕራፎችን ይዟል፡፡እነሱም ዘመናዊ የጤናና
ሰዉነት ማጎልመሻና ስፖርት፣ የሰዉነት ማጎልመሻ በማህበራዊና ስነልቦናዊ ትምህርት፣
ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች፣ አትሌቲክስ፣ ጅምናስቲክ፣ የኳስ ጨዋታዎች
መሰረታዊ የማቀበልና የመቀበል ክህሎት እናበአዲስ አበባ ደረጃ የሚገኙ የኢትዮጵያ
ባህላዊ እንቅስቃሴና ጨዋታዎች ናቸው፡፡

III
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ምዕራፍ አንድ
ዘመናዊ የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ እና ስፖርት
መግቢያ
ዘመናዊ የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ለአንድ ሀገር ዕድገት መሰረት
መሆኑ እውን ነዉ፡፡ ከሚሰጡት ጥቅሞች ውስጥም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካላዊ
እና ስነ ልቦናዊ እንዲሁም ስብዕናዉ የተሟላ ዜጋን ለመፍጠር ያለው አስተዋፅኦ
ከፍተኛ ነዉ፡፡

ዘመናዊ የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት እና ስፖርት በእንቅስቃሴዎች እና


በውድድራዊ ክንዋኔዎች ላይ ክህሎትን እና አካላዊ ብቃትን ለማዳበር በትምህርት
መስኩ መሰረታዊ ንድፈ ሀሳቦች አማካኝነት ግንዛቤ አግኝተዋል፡፡ እንዲሁም የእርስ
በርስ ግንኙነታቸው ጤናማ እንዲሆን የረዳቸዋል

በዚህ መሰረት ይህ ምዕራፍ የሚያተኩረው በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና ኑሮ ላይ


ተግባራዊ ሊደርጉ የሚገቡ ጠቃሚ ንድፈ ሀሳቦች ላይ ነዉ፡፡

ምዕራፉ አራት አበይት የትምህርት ይዘቶችን ሲይዝ እነሱም፣ የሰዉነት ማጎልመሻ


ትምህርት ምንነት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ደህንነት፣ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን
ስፖርተኞች ፣ የኦሎምፒክ ጨዋታ አጀማመር እና ዕድገት የሚሉ ይዘቶችን አካቷል::

የመማር ዉጤቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ


• ዘመናዊ የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ እና ስፖርት ፅንሰ ሀሳብን ታውቃላችሁ፡፡

• ዘመናዊ የጤናና የሰዉነት ማጎልመሻ እና ስፖርት ጽንሰ ሀሳብን ታደንቃላችሁ::

1
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡

• የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ምንነትን ትገልጻላችሁ::

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


1. የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ዓላማዎች ምንምን ናቸዉ?

2. ከጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ጥቅሞችንመካከል ሶስቱን ጥቀሱ?

1.1 የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ምንነት


ዘመናዊ የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ማለት የሰው አዕምሮን፣ ማህበራዊ
ግንኙነትንና ስሜትን የምናዳብርበት፤ በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የሚሰጥ የትምህርት
አይነት ነዉ፡፡

የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት አብዛኛዉን ጊዜ በተግባር የሚሰጥ ሆኖ አጠቃላይ


የጤናን ደረጃ የምናሳድግበት የትምህርት ዓይነት ነዉ፡፡

የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት የአራት ቃላቶች ጥምረት ሲሆንእነሱም፡-

1.ጤና 2. ሰዉነት 3. ማጎልመሻና 4. ትምህርት ናቸው

1. ጤና ማለት ከበሽታ ነፃ መሆን ብቻ ሳይሆን በአካል፣ በአዕምሮ፣ በማህበረዊ


ግንኙነት እና በስሜት የዳበረ ማለት ነው፡፡

2. ሰዉነት ማለት አጠቃላይ ውስጣዊና ውጫዊ የሰዉነት ክፍሎችን አዋቅሮ የያዘ


ክፍል ነዉ፡፡ ለምሳሌ፡- ጡንቻዎች፣ አጥንቶች፣ ደም ወዘተ ናቸዉ፡፡

3. ማጎልመሻ ማለት ደግሞ ማዳበር፤ማሳደግ፤ማበልጸግ ማለት ነዉ፡፡

4. ትምህርት ማለት ሂደታዊ ሲሆን ጽንሰ ሀሳቦችን፣ ዋና ዋና ህግጋትን


የሚያጠቃልልና የሚተነትን ዘመናዊ ንድፈ ሀሳብ እና ተግባር የሚያጠና የሰው
ልጆችን አስተሳሰብ የሚያበለጽግ ፍሬ ነገር ማት ነዉ፡፡

ስለዚህ የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት የሰው ልጅ ጤንነትን፣ ምርታማነትን


እና አስተሳሰብን የሚያሳድግ የትምህርት ዘርፍ ነዉ፡፡

2
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የስፖርት ምንነት
ስፖርት ማለት የተቀናጀ ውድድራዊ ጨዋታ ማለት ነው፡፡ ስፖርት የራሱ የሆነ
አለማቀፋዊ ህግጋትን ያካተተና በውድድር መልክ የሚተገበር ነው፡፡ ስፖርት ያለ
ውድድር ትርጉም የለውም፡፡ ለምሳሌ፡- አለም አቀፍ የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣
የቅርጫት ኳስ ውድድርና አለም አቀፍ የኦሎምፒክ ጨዋታ ወ.ዘ.ተ…መጥቀስ
ይቻላል፡፡ ነገር ግን አለም አቀፍ የውድድር ህግጋትን የማያሟላ ውድድር ስፖርት
ልንለው አንችልም፡፡ የዚህ ዓይነት ጨዋታ በውድድር መዝናናት ልንለው እንችላለን::
ለምሳሌ፡- ስድስት ስድስት ሆነው የእግር ኳስ ጨዋታ በትንሽ ሜዳ ትምህርት ቤት
ከትምህርት ቤት ውድድር ቢያደርጉ ይህ ምሳሌ በውድድር መዝናናትን የሚገልፅ
ነው እንጂ ስፖርትን አይገልፅም፡፡ ምክኒያቱም አለም አቀፍ የውድድር ህግጋትን
ስለማያሟላ ነው፡፡

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትን ስፖርት ልንለው እንችላለን


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትን በተግባር ለመተርጎም ከሚያገለግሉት ዋነኛ
ዘርፍች አንዱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በተወሰነ የስፖርት
ዓይነት መለማመድንና መወዳደርን የሚመለከት በመሆኑ ሰዉነትን በማዳበርና ጤናን
በመጠበቅ አኳያ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ሰለዚህ ስፖርትና የሰውነት ማጎልመሻ
ትምህርት ተመጋጋቢ ናቸው እንጂ በቀጥታ አንድ ዓይነት አይደሉም፡፡

የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት አራት አላማዎች አሉት፡


1. አካላዊ እድገት

2. አዕምሮዊ እድገት

3. ማህበራዊ እድገት

4. የነርቭና የክህሎት ዕድገት (motor and skill development)

1. አካላዊ እድገት፡- የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ


አማካኝነት የሰዉ ልጅን አካል የሚያሳድግ ሲሆን በተጨማሪም ጡንቻን የማጠንከርና
የውስጥ አካል ክፍሎችን ስራ የሚያሻሽል ስለሆነ በዚህ ምክንያት የሰዉነት ማጎልመሻ
ትምህርት መሰረታዊ ዓላማ ነዉ፡፡

3
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

2. አዕምሯዊ እድገት፡-የአካል ብቃትም ሆነ ማንኛዉም እንቅስቃሴ በምንሰራበት


ጊዜ ማሰብን የሚጠይቅ ስለሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት ደግሞ የሰዉነትን
የመስራት አቅም ስለሚያየሳድግ፤ ያደገ አካል ደግሞ የበቃ አዕምሮን የስገኛል፡፡
ለምሳሌ:- ጠንካራ የአካል ክፍል የበለጸገ አስተሳሰብን ይፈጥራል፡፡ደካማ ጡንቻ ወይም
ደካማ የአካል ክፍል ካለን ለአዕምሮ ደካማ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ በዚህ ምክንያት
ጠንካራ አዕምሮአዊ እድገት እና የአካል ክፍል እንዲኖረን ከተፈለገ የአካል ብቃት
እንቅስቃሴ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

3. የማህበራዊ ግንኙነት እድገት፡- የማህበራዊ ግንኙነት እድገት ማለት ጤናማ


የእርስ በርስ ግንኙነትን ማዳበር ማለት ነው፡፡ በሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ዉስጥ
የቡድን እንቅስቃሴዎች እና ጨዋታዎች በትምህርት ተካተዉ ስለሚሰጡ የቡድን
ጨዋታ ደግሞ ማሸነፍ እና መሸነፍ ያለዉ ስለሆነ ለማሸነፍ መግባባት ያስፈልጋል፡፡
መግባባት ደግሞ ማህበራዊ እድገትን ያስገኛል፡፡

4. የነርቭና የክህሎት እድገት፡- ማንኛዉንም እንቅስቃሴ ለማከናወን የነርቭ እና


የጡንቻ መቀናጀትን ይፈልጋል፡፡ የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት በምንማርበት
ወቅት የተሻለ እንቅስቃሴ ይኖረናል፤ የተሻለ እንቅስቃሴ ደግሞ የተሻለ የነርቭና
የክህሎት ቅንጅት ይኖረናል ማለት ነዉ፡፡ ለምሳሌ፡- አንድን ነገር ወርውሮ እንዳይወድቅ
ለመያዝ እጅ፣ አይን፣ ጡንቻና አዕምሮ መቀናጀት አለባቸዉ፡፡

የግምገማ ጥያቄዎች
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ማለት ምን ማለት ነዉ?

ጤናና የሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት እንዴት ጤናማ ግንኙነት ሊያዳብር

ይችላሉ?

1.2 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ደህንነት

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚረዱ የደህንነት ህጎችን ትዘረዝራላችሁ፣

4
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄ

የጥንቃቄ መርሆችን መከተል የሚሰጠውን ጥቅም ጥቀሱ?

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የጥንቃቄ መርሆች


የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከመስራታችን በፊት የተለያዩ የአካል ጉዳቶች እንዳያጋጥሙ
ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ በመቀጠል የተዘረዘሩት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
የጥንቃቄ መርሆች ናቸው፡፡

እነሱም ፡-

ሀ. በተስተካከለ ሜዳ መስራት ( ወጣ ገባ ያልሆነ፣ ስለታማ ነገር የሌለው)

ለ. አደጋን ከሚያስከትሉ ነገሮች በራቀ ቦታ ላይ መስራት (ኤሌክትሪክ ሽቦ፣


ተቀጣጣይ ነገሮች የሌሉበት)

ሐ. ለእንቅስቃሴ ተገቢ የሆነ አለባበስን እና መሳሪያዎችን መጠቀም


ለምሳሌ፡- ቱታ፣ ጫማ ወዘተ…

መ. የጤና ደረጃን እና የአካል ብቃት ደረጃን ማወቅ

ሠ. በእንቅስቃሴ ወቅት የአካል ጉዳቶች እንዳይፈጠሩ መከላከል

ረ. ከአምስት እስከ አስር ደቂቃ የሰዉነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎችን መስራት::


ለምሳሌ ፡- የእጅ እንቅስቃሴ ⇨ የወገብ እንቅስቃሴ ⇨ የእግር እንቅስቃሴ ⇨
ማሳሳቢያ መስራት፡፡

ሰ. በእንቅስቃሴው መጨረሻ ላይ ከሶስት እስከ አምስት ደቂቃ የተለያዩ የሰውነት


ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴዎችን መስራት፡፡

የግምገማ ጥያቄዎች
1. የአካልብቃት እንቅስቃሴ ከመስራታችን በፊት ሆነ በምንሰራበት ሰዓት
ከሚወሰዱ የጥንቃቄ መርሆች ውስጥ ቢያንስ ሶስት ዘርዝሩ?

2. የጥንቃቄ መርሆችን አለመከተል የሚያመጣው ጉዳት ምንድን ነው?

5
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

1.3 በኢትዮጵያ ታዋቂ የሆኑ ስፖርተኞች


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• በኢትዮጵያ ታዋቂ የሆኑ ስፖርተኞችን ትገልጻላችሁ

የመነሻ የማነቃቂያ ጥያቄ


1. በኢትዮጵያ ታዋቂ ከሆኑ ስፖርተኞች መካከል ጥቂቶችን ዘርዝሩ?

በኢትዮጵያ የሚታወቁ ታዋቂ ስፖርተኞች


ኢትዮጵያ የብዙ ብርቅዬ አትሌቶች መፍለቂያ ሀገር ናት፡፡ ለምሳሌ አበበ ቢቂላ፣
ማሞ ወልዴ፣ ምሩፅ ይፍጠር፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ደራርቱ ቱሉ ገዛኽኝ አበራ ወዘተ…
መጥቀስ ይቻላል፡፡ በዚህ የክፍል ደረጃ የሁለት ወንድ አትሌቶችን ታሪክ እናያለን፡፡

ቀነኒሳ በቀለ
ቀነኒሳ በቀለ በ1974ዓ.ም በኦሮሚያ
ክልልአርሲዞን በቆጂ በተባለች የገጠር
ከተማ ተወለደ፡፡ ቀነኒሳ ከመነሻው በልዩ
የአትሌቲክስ የተፈጥሮ ክህሎት የታጀበ
በመሆኑ አቅሙን ለመለየት ለአሰልጣኞች
በጣም ቀላል ነበረ፡፡

ቀነኒሳ እስካሁን በሁለቱም በ5000


ሜትር እና በ10,000 ሜትር ያለው
የዓለም ሪኮርድ እና የኦሎምፒክ ሪኮርድ
በእጁ ይገኛል፡፡ እንዲሁም የ31 ሜዳሊያ
ባለቤት ነው፡፡ በ2004 እ.ኤ.አ. አቴንስ
ኦሎምፒክ በ10,000 ሜ የወርቅና እና
በ5000 ሜትር በብርሜዳሊያ አሸናፊ
ሆናል፡፡ እንዲሁም በ 2008 እ.ኤ.አ.
የበጋ ቤጂንግ ኦሎምፒክ በ 5000ሜ እና
10,000 ሜትር ውድድሮች በሁለቱም ስዕል 1.1 ቀነኒሳ በቀለ
የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል፡፡

6
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ቀነኒሳ በቀለ ለአምስትተከታታይ ዓመታት ከ 2002 እስከ 2006 እ.ኤ.አ ድረስ


አትሌቲክስ ፍዴሬአለም አቀፉ ሽን (በአይኤ ኤፍ) የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና
ውድድር ውስጥ ሁለቱንም አጭር (4 ኪ.ሜ) እናረዥም (12 ኪ.ሜ) ውድድሮችን
የግሉ አድረጓል፡፡

እ.አ.አ. በ2003፣ 2005፣ በ2007 እና በ2009 በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዎና 10,000


ውድድር በተከታታይ አሸንፏል፡፡ ቀነኒሳ በቀለ እ.አ.አ .ከ2003 እስከ 2011 ድረስ
ባደረጋቸው የዓለም ሻምፒዮናዎች ማጠናቀቅ ሳይችል የቀረው 2011ን ብቻ ነው.

ቀነኒሳ በቀለ እ.አ.አ.በ 2009 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5000 እና 10,000


ሜትር በአንድ ሻምፒዮና በማሸነፍ የመጀመሪያው ወንድ አትሌት ለመሆን በቃ ፡፡
የዓለም ሻምፒዮና ነሐስ (2003)፣ሁለትየአፍሪካ ሻምፒዮና ወርቃማ ድሎችን እና አንድ
መላው አፍሪካ ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፈዋል፡፡እ.አ.አ.በ2006 በዓለም የቤት
ውስጥ ሻምፒዮናዎች በ3000 ሜትር አሸናፊ ሆነ፡፡እ.አ.አ. መስከረም 25 ቀን 2016
ቀነኒሳ እ.አ.አ .በበርሊን ማራቶን በ 2:03:03 አዲስ የግል ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ
ሶስተኛውን የማራቶን ፈጣን ሰዓት አምጥቶአሸናፊሆነ።

ቀነኒሳ በቀለ እ.አ.አ. መስከረም 29 ቀን 2019 በበርሊን ማራቶን የ 2018 በርሊን


ማራቶን ከተመዘገበው በ 2:01:39 ጊዜ ውስጥ ውድድሩን በድጋሚ አሸነፈ፡፡ብዙዎች
ቀነኒሳ በቀለ በአገር አቋራጭ፣ በትራክ እና በጎዳና ላይ ውድድር ያስመዘገባቸውን
ውጤቶች ሲመለከቱ እርሱ በዓለማችን ከሁሉም የሚበልጥ ታላቅ ሯጭ ነው ብለው
ይመሰክራሉ /ያረጋግጣሉ፡፡

በአጠቃለይ ቀነኒሳ በቀለ በዓለም አትሌቲክስ ውድድር ያገኛቸው ውጤቶች


እንደሚከተለው ተጠቃለው ቀረበዋል፡-

የቀነኒሳ የሩጫ ውጤት


የውድድሩ ዓይነት ወርቅ ብር ነሃስ
በኦሎምፒክ ውድድር 3 1 0
የዓለምአትሌቲክስሻምፒዮና 5 0 1
በዓለምየቤትውስጥሻምፒዮና 1 0 0
የአፍሪካ አትሌቲክስሻምፒዮና 2 0 0
መላው የአፍሪካ ጨዋታ 2 0 0
የዓለምአገር አቋራጭ ሻምፒዮናውድድር 11 1 0
አለም ዓቀፍ ማራቶን 2 1 1
አጠቃላይ 26 3 2

7
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ገዛኸኝ አበራ
ገዛኸኝ አበራ ሚያዝያ 15
1970 ዓ.ም በቀድሞው
አርሲ ጠቅላይ ግዛት በአሁኑ
ኦሮሚያ ክልል ልዩ ስሙ
ኢተያ በምትባል የገጠር
ከተማ ተወለደ፡፡ ገዛኸኝ
አበራ ዕድሜው ለትምህርት
ሲደርስ በውስጡ በተፈጥሮ
የታመቀውን የአትሌቲክስ
ሀብት በትምህርት ቤት
ለማሳየት ብዙ ጊዜ
አልወሰደበትም፡፡ ከዚያም ስዕል 1.2 ገዛኸኝ አበራ
በየደረጃው በወረዳ፤ በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ ስራው፣ ብቃቱና ውጤቱ ደመቅ
እያለ መጣ፡፡

ገዛኸኝ አበራ የመጀመሪያው የዓለም አቀፍ ውድድር እ.አ.አ. በ1999 ሎስ አንጀለስ


ማራቶን ሲሆን ከሶስት ኬንያውያን ቀጥሎ አራተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡ ይህ ውጤት
ወጣቱን አትሌት በ1999 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዎና በ ኢትዮጵያ ቡድን እንዲታቀፍ
አደረገው፡፡ በውጤቱም ገዛኸኝ የአስራ አንደኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ፡፡ በዚያው ዓመት
የመጨረሻ ወራት ገዛኸኝ አበራ የመጀመሪውን ኢንተርናሽናል ማራቶን በፎኮካ በማሸነፍ
ድሉን ጀመረ፡፡ ከዚያም በ2001 እና 2002 በፎኮካ ድሉን ደጋገመ፤ በቦስተን ማራቶን
ደግሞ በሁለተኛነት ማጠናቀቅ ችሏል፤

እ.አ.አ. በ 2000 የበጋ ሲድኒ ኦሊምፒክ የማራቶን ውድድር በሁለት ኢትዮጵያውያን


ገዛኸኝ እና ተስፋዬ ቶላ እና ኬንያዊ ኤሪክ ዌይንያና ፉክክሩ ተቀጣጠለ ፡፡ ወደ 37ኛው
ኪሜ ምልክት ሲደርሱ ኬንያዊው ኤሪክ ዌይንኔይ ሁለቱን ለመቁረጥ ከፍተኛ ጥረት
ያደረገ ቢሆንም ከ 2 ኪ.ሜ በኋላ የ22 ዓመቱ ወጣት ገዛኸኝ አበራ መሪነቱን በመያዝ
ወደ መጨረሻው መስፈንጠር ጀመረ፡፡ ይህ ዕድሜ ዣን ካርሎስ ዛባላ እ.አ.አ. በ
1932 በሎስ አንጀለስ ከተወዳደረበት ዕድሜ ቀጥሎ የተገኘው ወጣት የማራቶን ሯጭ
ያደርገዋል ፤ውድድሩንም በሚያስገርም ብቃት በአንደኛነት ጨርሷ፤ ይህ ከማሞ
ወልዴ ሜክሲኮ ኦሊምፒክ አሸናፊነት በኃላ የተገኘ ልዩና ድንቅ ድል ሆኖ ተመዘገበ፡፡

ገዛኸኝ አበራ እ.አ.አ. በ 2001 ዓለም ሻምፒዎና ከኬንያዊውን ሲሞን ቢዎትን በሴኮንዶች

8
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

በማሸነፍ የመጀመሪያውን በኦሊምፒክ ቀጥሎ በአለም ሻምፒዮና ማራቶን ሁለት ጊዜ


በተከታታይ በማሸነፍ የመጀመሪያው ሰው ለመሆን በቃ፤ እ.አ.አ. በ2003 ገዛኸኝ አበራ
የሎንደን ማራቶንን በ2:07:56 አሸነፈ፡፡ እ.አ.አ. በ 2003 የዓለም ሻምፒዮናዎ ላይ
ገዛኸኝ አበራ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ውድድሩን መተው ነበረበት፣ ሆኖም ግን በ
2004 የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ውስጥ ተመርጧል:: ነገር ግን ጉዳቱ ስለባሰበት
ከውድድሩ መቅረት ግድ ሆነበት ፡፡ ገዛኸኝ በተደጋጋሚ ጊዜያት በደረሰበት ጉዳቶች
ምክንያት በለጋ ዕድሜው ከሚወደው ሩጫ መውጣት ግድ ሆኖበታል፡፡

የግመምገማ ጥያቄዎች
1. በኢትዮጵያ የሚታወቁ ሶስት ስፖርተኞችን ሥም ፃፉ?

2. ቀነኒሳ በቀለ መቼ እና የት ተወለደ?

3. ገዛኽኝ አበራ በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው መቼና የት በተካሄደው


የኦሎምፒክ ጨዋታ ነበር?

የኦሎምፒክ ጨዋታዎች አጀማመር እናዕድገት

አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• የኦሎሚፒክ ጨዋታዎች አጀማመር ትገልጻላችሁ፡፡

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


¾ ስለ ኦሎምፒክ ጨዋታ የምታውቁትን ተናገሩ?

የኦሎምፒክ ጨዋታ
የኦሎምፒክ ጨዋታ በአለማችን ካሉ ስፖርታዊ ውድድሮች ሁሉ ትልቁና ዋንኛው
ነው:: ምክንያቱም ብዙ የውድድር ዓይነቶችን፣ ተወዳዳሪዎችንና ሀገራትን፣ ስለሚያሳትፍ
ነው፡፡ የኦሎምፒክ ጨዋታ በአራት አመት አንዴ ይካሄዳል፡፡

9
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የኦሎምፒክ ጨዋታ አጀማመር


የኦሎምፒክ ጨዋታ በውድድር መልክ የተጀመረው
ለመጀመሪያ ጊዜ በ 776 ዓመተ ዓለም ላይ ሲሆን
በጥነንታዊ የግሪክ ከተማ በሆነችው ኦሎምፒያ
በተባለች ከተማ ውስጥ ነበር፡፡ ይህ ውድድር የግሪክ
የጣኦት ንጉስ የሆነው Zeus/ዘስ/ የተባለ አምልኳቸውን
ለማመስገን በአራት አመት አንድ ጊዜ የተለያዩ
ስፖርታዊ ውድድሮችን በማካሄድ ይከበር እንደነበር
ታሪክ ያስረዳል፡፡ቀስ በቀስ የበዓሉ ታዳሚዎች ቁጥር
እየጨመረ በመምጣቱ የስፖርት ሜዳ (ስታዲየም)
መገንባት ችለዋል፡፡ በወቅቱ ይካሄዱ የነበሩ የውድድር
ስዕል 1.3 ባሮን ፔሬ ዴ ኩበርቲን ዓይነቶች የዲስከስ፣ አሎሎና ጦር ውርወራ ፣ ርዝመት
ዝላይ፣ ትግል፣ የሰረገላ ውድድር፣ የፈረስ ውድድር የመሳሰሉት ናቸው:: በውድድሩም
ያሸነፈ ተወዳዳሪ የወይራ ዝንጣፊ ጉንጉን ይሸለም ነበር፡፡

በሂደት እያደገ መጥቶ ዘመናዊ ኦሎምፒክ በፈረንሳያዊው Baron Pierre de Cou-


bertin ሀሳብ አመንጭነት እንደ አዲስ በ1896 እ.ኤ.አ በግሪክ አቴንስ ከተማ
ለመጀመሪያ ጊዜ ኦሎምፒክ ለሁሉም፣ ለሰላም፣ ለወንድማማችነት በሚልሊጀመር
ችሏል፡፡ ዘመናዊ የኦሎምፒክ ጨዋታ ልክ እንደ ጥንታዊ ኦሎምፒክ በአራት
ዓመት አንድ ጊዜ ይካሄዳል፡፡ከ1896 እ.ኤ.አ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እየተካሄደም
ይገኛል፡፡ የኛም ሀገር በኦሎምፒክ መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው ዘመናዊ
የኦሎምፒክ ጨዋታ ከተጀመረ ከ60 ዓመት በኋላ ማለትም በ1948 ዓ.ም (በ1956
እ.ኤ.አ) በሜልቦርን ኦሎምፒክ ነበር፡፡

የግምገማ ጥያቄዎች
1. የጥንታዊ ኦሎምፒክ ጨዋታ መቼ፣ የት እናበማን ተጀመረ?

2. ዘመናዊ የኦሎምፒክ ጨዋታ ዓላማ ምንድነው?

3. የኦሎምፒክ ጨዋታ በየስንት ዓመት ይካሄዳል?

10
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የምዕራፉ ማጠቃለያ
ዘመናዊ የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት አንዱ የትምህርት ዘርፍ በመሆኑ
በአካል ብቃት፣ በክህሎት፣ አዕምሯዊ እድገትን በማዳበርና የማህበራዊ
ተሳትፎን አቅም በማጎልበት ያለው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

የሰውነት ማጎልመሻ ትምህረት ይዘቶች በአብዛኛው የሚተረጎሙት በአካላዊ


እንቅስቃሴ ተሳትፎ ነው፡፡ የአካል እንቅስቃሴ ለመስራት ሁሌም በምንሰራበት
ወቅት ምቹ ሜዳና በምቹ አለባበስ እንዲሁም በተዘጋጀ ሰዉነት መሆን
አለበት፡፡

ኢትዮጵያ ብዙ ታዋቂ ስፖርተኞችን በተለይ በሩጫው ዘርፍ ያፈራች ሀገር


ናት፡፡ እነዚህ ታዋቂና እንቁ አትሌቶች የሀገራችንን ባህልበአለማቀፍ መድረክ
አስተዋውቀውልናል:: ከብዙዎቹ አትሌቶች መካከል አበበ ቢቂላ፣ ምሩፅ ይፍጠር፣
ማሞ ወልዴ፣ ሃይሌ ገብረስላሴ ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ገዛኸኝ አበራ፣ ደራርቱ ቱሉ፣
ፋጡማ ሮባ፣ ጥሩነሽ ዲባባ ወዘተ ማንሳት ይቻላል፡፡

የኦሎምፒክ ጨዋታ በ776 ዓመተ ዓለም በግሪክ ኦሎምፒያ ከተማ በግሪክ ዜጎች
ብቻ ይደረግ እንደነበርና በ1896 እ.ኤ.አ ደግሞ በዘመናዊ አስተሳሰብ በአዲስ
መልክ ተጀምሯል፡፡

11
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የማጠቃለያ ጥያቄዎች
ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማንበብ ከተሰጡት አማራጮች መካከል
ትክክለኛውን መልስ ምረጥ/ጭ

1. ጤና ማለት ከበሽታ ነፃ መሆን ብቻ ማለት ነው?

ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

2. የጤናና የሰዉነት ማጎልመሻ ጥቅም የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ደስተኛ ሆኖ ለመኖር ሐ. ንቁና ቀልጣፋ ለመሆን

ለ. ጤናማ ለመሆን መ. ሁሉም

3. -------------- የተቀናጀ የውድድር ጨዋታ ዓይነት ነው?

ሀ. የሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ሐ. የአካል ብቃት

ለ. ስፖርት መ. ሁሉም

4. ዘመናዊ ኦሎምፒክ የት ተጀመረ?

ሀ. ቻይና ለ. አቴንስ ሐ. ቶኪዮ መ. ሮም

5. ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው መቼ ነው?

ሀ. በ1960 እ.ኤ.አ ሐ. በ1956 እ.ኤ.አ

ለ. በ1896 እ.ኤ.አ መ. በ1948 እ.ኤ.አ

ለ. የሚከተሉትን በ ሀ ስር የተዘረዘሩትን የሰዉነት ማጎልመሻ ዓላማዎች


ከ ለ ስር ካሉ ሃሳቦች ጋር አዘምዱ
ሀ ለ
1. የአካል ዕድገት ሀ. ጤናማ የእርስ በርስ ግንኙነት

2. የአዕምሮ ዕደገት ለ. የአካል ክፍሎች ስራ መሻሻል

3. የማህበራዊ ዕድገት ሐ. የነርቭና የጡንቻ ቅንጅት

4. የነርቭ ክህሎት ዕድገት መ. የማሰብ መሻሻል

12
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ሐ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ስጡ

1. የጤናናሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ማለት ምን ማለት ነው?


2. የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትና ስፖርት ያላቸው አንድነትና ልዩነት ምንድነው?
3. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሲሰራ ልንከተላቸው የሚገቡ ከጥንቃቄ መርሆች ውስጥ
ሶስቱን ዘርዝሩ?
4. ታዋቂ የኢትዮጵያ ስፖርተኞች መካከል ቢያንስ ሶስት ጥቀሱ?
5. የኦሎምፒክ ጨዋታ መቼ እና የት እንደተጀመረ ጥቀሱ?
6. የኦሎምፒክ ጨዋታ ጥንታዊ እና ዘመናዊ ዓላማውን

13
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ምዕራፍ ሁለት
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ በማህበራዊ እና
ስነ-ልቦናዊ ትምህርት
መግቢያ
ማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ትምህርት ከዕለት ተዕለት ሥራዎች እና ችግሮች ጋር
በብቃት እና በሥነ ምግባር ለማከናወን ችሎታዎችን፣ አመለካከቶችን እና ባህሪያትን
በማቀናጀት የተማሪዎችን አቅም ያጠነክራል፡፡ እነዚህን ችሎታዎች ለማሳደግ አካላዊ
እንቅስቃሴዎችን በመለማመድ ማህበራዊ ንቁ አካባቢ ለመፍጠር ያስችላል፡፡ በተለያዩ
በእንቅስቃሴ የተደገፉ ጨዋታዎችን በመጫወት የቡድን ስራን በመስራት ማህበራዊ
ግንኙነትንና ስሜትን ለመግለፅ ያስችላል፡፡ ይህ ምዕራፍ አምስት አበይት ንዑስ ርዕሶችን
አካቷል፡፡ እነሱም፡-

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለራስ ግንዛቤና የአመራር ክህሎት መሻሻል፣

የአካል እንቅስቀሴ ለመልካም ግንኙነት ክህሎት መሻሻል፣

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሀላፊነት ለተሞላበት ዉሳኔ አሰጣጥ፣

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለተሻለ አስተሳሰብና

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለተሻለ የጋራ መግባባት ክህሎት ናቸው፡፡

የመማር ዉጤቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ


• የጎደኞቻቸዉን ችግር እንደራሳቸዉ በማየት ግምት ዉስጥ ታስገባላችሁ፣

14
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

2.1. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለራስ ግንዛቤ እና


የአመራር ክህሎት ማሻሻል

አጥጋቢ የመማር ብቃት:- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ

• የተለያዩ ችግሮች ሲጋጥሙ የችግሮችን ባህሪያትና ምልክት ትለያላችሁ፣

• የችግር አፈታት ዘዴን ተግባራዊ ታደርጋላችሁ፣

የመነሻ እና የማነቃቂያ ጥያቄዎች፡


• ራስን ማወቅ እና ራስን መምራት ማለት ምን ማለት ነው?

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለራስ ግንዛቤ /self-awareness/


የራስ ግንዛቤ ማለት የራስ ስሜትን፣ ሀሳብን እና እሴትን በትክክል የመለየት ችሎታ
ማለት ነው፡፡ የራስ ግንዛቤ ፍሬ ሃሳቦች የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡-

ስሜቶችን መለየት

በጤናማ ሁኔታ ራስን ማስተዋል

ጥንካሬን ማወቅ

በራስ መተማመንና

የራስ ውጤታማነትን ያመለክታል፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሰው ልጅ አእምሯዊ እና አካላዊ እድገትን ለማምጣት


የሚረዳ የእንቅስቃሴ አይነት ነው፡፡ የግንዛቤ ክህሎትንበአካል ብቃት እንቅስቃሴ
ለማሳደግ የሚከተሉትን ዋና ነጥቦችን ማየት እንችላለን፡፡

በጋራ እንቅስቃሴ ወቅት የአጋሮቻቸውን የስሜት ደረጃ ማወቅ እና መረዳት፣


የስሜት መነሻዎችን ምን አንደሆኑ መለየት፣
የስሜት ደረጃ መረዳት እና ሌሎች እንዴት እንደሚጎዱ መገመት መቻል፣

15
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ውስጥ የስሜት የአስተሳሰብ እና የባህሪ ግንኙነትን የመረዳት


ክህሎትን ማዳበር

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የመስራት ፍላጎት እና ጥቅም በተሻለ ደረጃ ወዘተ ማወቅ፣

ራስን የመምራት ክህሎት /self-management/


ራስን መምራት ማለት ባህርያችን፣ ስሜታችን እንዲሁም ሀሳባችን በጥሩ ሁኔታ
የመቆጣጠር ብቃት ሲሆን፤ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችውስጥ ምን መስራትና
እንዴት መስራት እንዳለብን፣ ጭንቀትን መቆጣጠር፣ ራስን ማነቃቃት እና ራስን
ለማስተዳደር ያስችላል፡፡ ራስን ለመምራት የሚከተሉትን ዋና ዋና ሃሳቦች መተግበር
አለብን፡-

1. ጭንቀትን መቀነስ 4.የራስ ተነሳሽነት .

2. የራስ ተግሳፅ 5.ግብማስቀመጥና

3. የስሜትግፊትንመቆጣጠር6 ክህሎትን ማቀናጀት ናቸው


የራስ ግንዛቤ እና ራስን የመምራት እንቅስቃሴዎችን የምናሻሽለው፡-

ሀ. አካላዊ እንቅስቃሴ መስራት

ለ. ሌሎች ሰዎችን በማስተዋል

ሐ. ጥዋት ፀጥ ባለና ማራኪ በሆነ ቦታ የእግር ጉዞ በማድረግ

መ. ተጨማሪ መፃህፍ በማንበብ

ሠ. በንቃት መተንፈስን በመለማመድ


ተግባር አንድ፡- በሶስት እግር የመሮጥ ውድድር

የጨዋታው ዓላማ፡-ራስን ማወቅና ራስን የመምራት ክህሎት ማሻሻል


የሚያስፈልግ መሰሪያ፡- የእግር ማሰሪያ(ሪቫን)

የአሰራር ቅደም ተከተል

• ሁለት ሁለት ተማሪዎች በመሆን ሶስት ቡድን መፍጠር፡፡


• የአንዱን ተማሪ ቀኝ እግር ከሌለው ተማሪ ግራ እግር ጋር ማሰር፡፡

16
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• ሁሉንም ቡድኖች ተዘጋጅተው ሲጨርሱ እሰከ አሰራ አምስት ሜትር


በፍጥነት መሮጥ፡፡
• በሶስት እግር መሮጥን ደጋግሞ መስራት
• ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸውን ተማሪዎች ለነሱ የሚሆን እንቅስቃሴ
ማሰራት ፡፡

ስዕል 2.1 በሶስት እግር የመሮጥ ውድድር

አጠቃላይ እንቅስቃሴውን በብቃት ለማከናወን ራስን ማወቅና መምራት፣ እንቅስቃሴዎችን


መለማመድ፣ ሌሎች ሰዎችን ማስተዋል፣ አካላዊ እንቅስቃሴ መስራት ወዘተ---
አለባችሁ፡፡

የግምገማ ጥያቄዎች
1. የችግሮች ባህሪያት በምን መንገድ መለየት ይቻላል?

2. የራስ ግንዛቤ ማለት ምን ማለት ነው?

3. ራስን የማወቅ እና ራስን የመምራት እንቅስቃሴዎች ከምንላቸው ውስጥ


ሁለቱን ጥቀሱ?

4. በሶስት እግር ሩጫ ስትሰሩ ያጋጠማችሁ ችግር ምንድን ነው? እንዴት


በመለየት ፈታችሁት?

17
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

2.2. የአካል እንቅስቀሴ ለመልካም ግንኙነት


ክህሎት መሻሻል
አጥጋቢ የመማር ብቃት:- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ

• የችግር አፈታት ክህሎትን ተግባራዊ ታደርጋላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


• ማህበራዊ ግንኙነት የሚያዳብሩ ክህሎቶችን ዘርዝሩ?

• ግጭቶችን እንዴት መቀነስ እንችላለን?

ማህበራዊ ግንኙነት ማለት የሌሎችን አመለካከት የመያዝ እና የመተሳሰብ ችሎታ


ባህል ነው፡፡ ማህበራዊና ስነ-ምግባራዊ ደንቦችን የመረዳት እና ቤተሰብን፣ ትምህርት
ቤትን እና የማህበረሰብ ሀብቶች ዕውቅና መስጠት ነው፡፡ ሌሎችን የመረዳትና መተሳሰብ
ችሎታን ያካትታል በተለይ ከራሳቸው ይልቅ ከተለያዩ ቦታ እና ቤተሰብ የሚመጡ
ሰዎች ለመልካም ግንኙነት ክህሎት መሻሻል እና ግጭቶችን ለመቀነስ የስችላል ፡፡
መልካም ግንኙነትን የሚያዳብሩ ከህሎቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ. ርህራሄን እና አዘኔታን ማሳየት

ለ. አሳቢነትን ማሳየትና መረዳት

ሐ. ምስጋናን ማቅረብ

መ. የሌሎች ጥንካሬን ማወቅና ከነሱ መማር

ሠ. ማህበራዊ ሕጎችን መለየት

የግንኙነት ከህሎቶች ንደሚሰማዎችን


በንቃት ማዳመጥ እና የግጭት አፈታት ችሎታዎችን በተለያዬ ዘዴዎች አወንታዊ
የሆኑ ግንኙነቶች የመገንባት ችሎታ ነው፡፡ እነዚህ ክህሎቶች ግፊትን የመቋቋም
ችሎታን የመፈለግና እርዳታ የመስጠት ችሎታንም ያጠቃልላል፡፡

18
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የግንኑኙነት ክህሎት ሊሻሻል የሚችለው


1. የቡድን ስራን በመስራት፣

2. መልካም ግኑኙነትን በማዳበር፣

3. ወንድማማችነትን በማስቀደም፣

4. የቡድን ስራንና ትብብርን በማጠንከር፣

5. ለሌሎች መብት በመቆም ናቸው፡፡

ስለዚህ የአካል እንቅስቃሴን በጋራ በመስራት ከላይ የተጠቀሱትን እና ሌላ ክህሎትን


ማዳበር ይቻላል፡፡
ተግባር፡- በቡድን የእግር ኳስ አራት አራት ሆነው መጫወት

በዚህ ጨዋታ ላይ በሰላም ተጫውቶ ለመጨረስ

1. እርስ በርስ መግባባት

2. የጋራ የሚያድርጋቸውን ነገር አምኖ መቀበል ለምሳሌ የጋራ የሚያደርጋቸው


ኳስና ሜዳ ስለሆነ ለምን ኳስ ትመታለህ የሚል ግጭት አይነሳም፡፡

3. ህግን አክብሮ መጫወት ይህን በሚያደርጉበት ጊዜ

• የተቃራኒውን ቡድንን መብት መጠበቅ

• መከባባር

• ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን ማስቀደምን መለማመድ አለባቸው፡፡


(ለምሳሌ፡- ያለ አግባብ ተቃራኒ ቡድን ላይ በመጉዳት ጎል ማስቆጠር ወንድማማችነትን
እና እህትማማችነትን ማስቀደም ማለት አይደለም)

የግምገማ ጥያቄ
1. የግንኙነት ክህሎት ውጤታማ የሚሆነው ምን ምን ስናከናውን ነው?

19
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

2.3.የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሀላፊነት ለተሞላበት


ዉሳኔ አሰጣጥ
አጥጋቢ የመማር ብቃት:- ተማሪዎች ይህንን ትምህርት ከተማራችሁ በኃላ

• በሌሎች የሚደርስ ችግር ሲያጋጥም እንደራስ በማየት አፈታትን


ታሳያላችሁ፣

• በራስና በሌሎች የሚወሰን ዉሳኔ የሚያስከትለዉን ዉጤት ትገመግማላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄ


ኃላፊነት የተሞላበት ውሳኔ አሰጣጥ ማለት ምን ማለት ነው ?

ኃላፊነት የተሞላበት ውሳኔ አሰጣጥ ማለት መቼ፣ እንዴትና የት እንደሚንቀሳቀሱ


መወሰን ማለት ነው፡፡ ትክክለኛ ውሳኔ አሰጣጥ ባሉ ተጨባጭ መረጃዎች ላይ ተመርኩዞ
ኃላፊነት በጤናና ሰዉነት መማልመሻ ትምህርት የውሳኔ አሰጣጥ የችግር አፈታት
ደረጀዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

• ውሳኔው መቼ እንደሚያስፈልግ መለየት፣


• ተያያዥ አማራጮችን ማሰብ፣
• አማራጮችን መገምገም፣
• ስልቶችን መምረጥ፣
• እንዴት እንደሚሰራ ማስቀመጥ፣
ተግባር 1 ኳስን ወደ ግብ አልሞ የመምታት ጨዋታ

• በዚህ ጊዜ ኳሳን ለመምታት ከመሄድ በፊት በየትኛው ሰዓት፣ የት፣ እንዴት


እንደሚመታ አዕምሮው ውስጥ ማሰብ መቻል

• በየትኛው እግር መምታት እንዳለባቸው መወሰን ፣

• ራስን ለውሳኔ ማዘጋጀት

• መወሰን ( በቀኝ በኩል ወይስ በግራ፣ በቅርብ ርቀት ተንደርድሮ ወይስ ከሩቅ
ርቀት ተንደርድሮ፣ በየትኛው የእግር ክፍል)

20
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• አልሞ መምታትን ውሳኔ መስጠት ላይ መሰረት በማድረግ በየተራ መለማመድ፣

• ልዩ እገዛ የሚያስፈልጋቸውን ተማሪዎች ለእነሱ ሚሆነውን እንቅስቃሴበማዘጋጀት


ማስራት
ተግባር 2 ኳስ የማቀበል ጨዋታ

የጨዋታው ዓላማ፡- ኳስን ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ለጓደኛ ማቀበል

የአሰራር ቅደም ተከተል

• በቅድሚያ ተማሪዎችን ማሟሟቂያ ማሰራት

• ክብ በመሥራት ከአምስት(5) እስከ ሰባት(7) ተማሪዎች ሆኖ መቆም

• ኳስ በመያዝ እና በመወርወር ማቀበል፣

• ኳስ በአየር ላይ በመቀባበል እንዳይወድቅ ማድረግ፣

• ኳሱን በትክክል ያላቀበለ ወይም የጣለ ክቡ መሀል ይገባል፡፡ አስፈላጊ ሲሆን ክቡ


ውስጥ የገባውን ተማሪ በኳስ መምታት፤ ከሳተው ግን መቺው ይገባል፡፡

• መሀል የገባው ወይም የገባችው ኳስን በተቀመጡበት ከቀለቡ ወደ ጨዋታው


ይቀላቀላሉ፡፡

• ጨወዋታው ሁለት ተማሪ እስከሚቀር ይጫወቱና ሁለቱ ሲጫወቱ ካጠፉ


ጨዋታው እንደገና ይጀምራል፡፡

• በቡድን በመሆን ከላይ የተጠቀሰውን አሰራር በመከተል ልምምድ ማድረግ፡፡

ልዩ እገዛ የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ለእነሱ በሚሆናችው እንቅስቃሴ ላይ ባላቸው


አቅም መሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡

የግምገማ ጥያቄዎች
1. የችግር አፈታት ሂደቶችን ጥቀሱ?

2. ኳስን በ የማመቀበል ጨዋታ ምንን የሚያዳብር ክህሎት ነው?

3. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለተሻለ አስተሳሰብ

21
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

አጥጋቢ የመማር ብቃት:- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ

• በቡድን በመሆን ሲጫወቱ ያላቸዉን ሚና ትገነዘባላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


1. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለተሻለ አስተሳሰብ ማለት ምን ማለት ነው?

2. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በራስና በሌሎች የሚወሰኑ ውሳኔዎች ላይ ምን ዓይነት


ተፅዕኖ ያስከትላል?

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለተሻለ አስተሳሰብ ማለት እንቅስቃሴዎች ለምንወስናቸው


ውሳኔዎች እና እናኃላፊነቶች የምናፈልቅባቸው የተሻለ የሀሳብ መረጃ የማመንጨት
ሂደት ነው፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለተሻለ አስተሳሰብ ማለት ዕውቀት፣ የማመዛዘን
ችሎታ፣ ራስን የመቆጣጠር እና ትምህርት ለማሻሻል እንዲረዳ የሀሳብ መረጃ
የማመንጨት ሂደት ነው፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተፈጥሯዊ ባህሪ አዲስ ስልት ተግባራዊ ለማድረግ፣


እንቅስቃሴን ለመሞከርና የሚገኘውን ውጤት ለመገምገም ይረዳል፡፡ በወሳኝ ሁኔታ
ለማሰብ፣ ለማብራራት እና ሊከላከል የሚችል ምክንያታዊ ውሳኔ ለማድረግ ከተለያዩ
ምንጮች እና ግንዛቤዎች የተሰበሰቡ መረጃዎችን ማሰብ ይጠይቃል፡፡
ተግባር፡- በአራት እግር የመሮጥ ውድድር

• ሶስት ሶስት በመሆን ቡድን መመስረት

• ሶስቱም በተርታ ከቆሙ በኋላ መሀል የሚገኘውን ተማሪ ቀኝ እግሩን ከሌላው


ተማሪ ግራ እግር ጋር እንዲሁም ግራ እግሩን ከቀሪው ተማሪ ቀኝ እግር ጋር
ማሰር፣

• ሁሉም ቡድኖች ከተዘጋጁ በኋላ ጨዋታውን መጀመር እና እስከ 10 ሜትር


በቀስታ መሞከር፣

• ሁሉም ቡድኖች ጨዋታውን መጀመር እና እስከ 15 ሜትር በፍጥነት መሮጥ፣

22
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• የላይኛውን እንቅስቀሴ በደንብ ደጋግማችሁ ከሰራችሁ በኋላ እስከ 20 ሜትር


በፍጥነት መሮጥ፣

• ልዩ እገዛ የሚያስፈልጋቸው ተሚሪዎች በ እንቅስቃሴ ላይ ባላቸው አቅም


መሳተፍ ይኖርባቸዋ፡፡

• በምን ዘዴ ብንሮጥ እናሸንፋለን ብለው በማሰብ መወያየት ይኖርባችኃል


ይኖርባቸዋል፡፡

ስዕል 2.2 በአራት እግር የመሮጥ ውድድር

የግምገማ ጥያቄዎች
1. በጨዋታው የነበራቸው ሚና ምንድን ነው?

2. ያሸነፉት ምን በማድረግ ሊያሸንፉ ቻሉ ?

23
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

2.4 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለተሻለ የጋራ


መግባባት ክህሎት
አጥጋቢ የመማር ብቃት:- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ

• ሀሳባቸዉን ለማካፈል ከሌሎች ጋር ይገናኛሉ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች፡


• የመግባባት ትርጉምን አብራሩ?
• የትብብር ጥምረት ማለት ምን ማለት ነው?

መግባባት
መግባባት ማለት መረጃ በመለዋወጥ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት ማለት ነው፡፡
የተሻለ የጋራ መግባባት ክህሎት ማለት ልዩነትን በማጥበብ ወደ አንድ የተሻለ ውሳኔ
መምጣት ነው፡፡

ለተሻለ መግባበትና ግንኙነት አምስቱ ደረጃዎች

1.ማዳመጥ 3. የሰዉነት ቋንቋን መረዳት

2.እራስን መግለፅ 4. ልዩነቶችን ማወቅና ግጭትን መፍታት ናቸው፡፡


የትብብር ጥምረት
የትብብር ጥምረት ማለት የትብብር ውጤት ሁኔታን ለማራመድ የመረጃና የነገሮች
መለዋወጥ ማለት ነው፡፡

መግባባትና የትብብር ውጤት ግብን ለማሳካት ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ ነገር ግን


ያለመግባባት የትብብር ጥምረት ሊያድግ አይችልም፡፡ ስለዚህ መግባባት እና መተባበር
አንድ አይነት ናቸው መሆናቸውን መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡ በመግባባት ግንኙነቶች
እንዲሠሩ ያስችላቸዋል፡፡ በእነዚህ ግንኙነቶች አፈፃፀም ትብብር እንዲከሰት ብቻ ሳይሆን
ፍሬያማ እንዲሆን ያስችላል።

24
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የትብብር ደረጃዎች
ለስኬታማ ትብብር ሊከተሏቸው የሚችሉት አምስት ደረጃዎች አሉ፡፡እነሱም፡-

• ዓላማውን መግለፅ
• ትክክለኛ ሰዎችን ማሳተፍ
• ገዢ ሃሳብን መምረጥ
• የትብብር ባህሪን ማበረታታት
ተግባር 1 ኳስን የመሰብሰብ ጨዋታ /ball collection/

የጨዋታው ዓላማ፡- የተሻለ የጋራ መግባባት

የሚያስፈልግ ቁሳቁስ፡- ቅንብቢት ወይም ትናንሽ ኳስ

የአሰራር ቅደም ተከተል

• ሰባት ሰባት ተማሪዎች ቡድን መመስረት

• ተማሪዎችን ማሟሟቂያ እንድሰሩ ማድረግ

• ፊት ለፊት ሰባት ሰባት ሆነው መሰለፍ

• ከመጀመሪያው ተሰላፊ አራት ሜትር ርቆ የተደረደረ አስር አስር ሳህን(ቅንብቢት)


ለሁለቱም ቡድን ማስቀመጥ፣ ከሰባተኛው ተጨዋች አራት ሜትር ርቆ የሚገኝ
ለአያንዳንዳቸው አንድ አንድ መደርደሪያ ማዘጋጀት

• ምልክቱን በመቀባበል ወደ ማጠራቀሚያ ቦታ ማድረስ

• ምልክቱ በተደረደረበት ቦታ አቅራቢያ ያለው ልጅ ምልክቱን አምጪ ሲሆን


ሌሌች ተደርድረው የቆሙ ጓደኞቹ ምልክቱን በመቀባበል የመጨረሻው ልጅ ጋር
ሲደርስ በተዘጋጀለት ቦታ እየተመላለሰ ይደረድራል፡፡

• አምጪው ወይም ደርዳሪው ልጅ ልክ አስቀምጦ እንደጨረሰ ምልክት ለማምጣት


ይሮጣል፡፡

• ምልክቱን ሁሉም የቡድኑ አባላት በመንቀሳቀስ እየተቀባበሉ ማለፍ አለባቸው፡፡

• ምልክቱ ያለበት ቦታና ምልክቱ የሚደረደርበት ቦታ እኩል ርቀት ያለው መሆን


አለበት፡፡

25
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• ልዩፍላጎት ለሚያስፈልጋቸው ለነሱ የሚሆን እንቅስቃሴ ላ ባላቸው አቅም መሳተፍ


ይኖርባችኋል ይኖርባቸዋል፡፡

• በዚህ ሂደት ተባብሮ በፍጥነት ምልክቱን የጨረሰ ቡድን አሸናፊ ይሆናል፡፡ ተግባሩን
በጋራ መስራት የተሻለ ውጤት ያመጣል፡፡ ማህበራዊ ግንኙነትንም ያዳብራል፡፡
ተግባር 2 የጓደኛን ንብረት ማዳን

የጨዋታው ዓላማ፡- የተሻለ የጋራ መግባባት መፍጠር


የአሰራር ቅደም ተከተል:-

y አምስት አምስት በመሆን ቡድን መፍጠር፣

y ተማሪዎችን ማሟሟቂያ እንዲስሩ ማድረግ፣

y አራቱ ትከሻ አካባቢ በእጅ በመያያዝ ክብ መስራት፣

y አንዱ ልጅ ከተያያዙት ልጆች ውጭ ሆኖ ይቆማል፤

y አንደኛው ልጅ ጀርባው ላይ ጨርቁን ማንጠልጠል፣

y የተንጠለጠለዉን ጨርቅ ለመንካት ውጭ ያለው ልጅ ወደ ተንጠለጠለበት


ጨርቅ ይሄዳል፣

y አራቱ ልጆች በጋራ ነኪው በመጣበት ተመሳሳይ አቅጣጫ እየተዟዟሩ ላለማስነካት


ይሞክራሉማለት ነው፡፡ ከተነካ ግን ጨርቁን በጀርባው የያዘው ልጅ አባራሪ
ይሆናል፡፡

y ልዩ ፍላጎት ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ለነሱ የሚሆን እንቅስቃሴ ላይ ባላቸው


አቅም መሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡

የግምገማ ጥያቄዎች
ለረጅም ጊዜ ጨርቁን ሳታስነኩ ከቆያችሁ እንዴት መቆየት ቻላችሁ?

ከተነካባቸው ለምን ተነካባችሁ?

26
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የምራዕፉ ማጠቃለያ
ማህበራዊ እና ስሜታዊ ትምህርት በተለያዩ እንቅስቃሴ የተደገፉ ጨዋታዎችን
በመጫወት የቡድን ስራን በመስራት ማህበራዊ ግንኙነታቸውንና ስሜታቸውን
እንዲገልፁ ያስችላቸዋል፡፡

የራስ ግንዛቤ ፍሬ ሃሳቦች የሚያካትታቸው ስሜቶችን መለየት፣ በጤናማ ሁኔታ


ራስን ማስተዋል፣ ጥንካሬን ማወቅ፣ በራስ መተማመንና፣ የራስ ውጤታማነት
ያመለክታል፡፡ ራስን መምራት ማለት ባህርያችን፣ ስሜታችን እንዲሁም ሀሳባችን
በጥሩ ሁኔታ የመቆጣጠር ብቃት ነው፡፡

መልካም ግንኙነት የሚያዳብሩ ከህሎቶች ለሌሎች በቃልና በአካል ምን


አንደሚሰማቸው በመለየት፣ ርህራሄን ፣ አዘኔታን፣ አሳቢነትን መረዳትን፣
ምስጋና ማቅረብን፣ የሌሎችን ጥንካሬ ማወቅና ከነሱ መማር እና ማህበራዊ
ሕጎችን መለየት ናቸው፡፡

በ ጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት አሰጣጥ ውስጥ ውሳኔ ለመሰጠት እና


መምህራን ተማሪዎችን በራስ ተነሳሽነት፣ በራስ መተማመን፣ እንዲኖራቸው
እና ውሳኔያቸው ላይ ሀላፊነት እንዲወስዱ ዕድል መስጠት አለባቸው፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በጨዋታ እና በውድደር መልክ የሚሰጥ ሲሆን


አምስቱን የማህበራዊና የስሜት ብስለት ትምህርትን የሚያዳብር ዋንኛ መሳሪያ
ነው፡፡

27
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የምዕራፉ የማጠቃለያ ጥያቄዎች


ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ የያዘዉን ፊደል በመምረጥ መልሱ

1. ያለ መግባባት የትብብር ጥምረት ሊያድግ አይችልም?

ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

2. መግባባት ማለት፡-

ሀ. መረጃ መለዋወጥ ሐ. ማዳመጥ

ለ. ለሌሎች ሀሳብን ማካፈል መ.ሁሉም

3. ማህበራዊና ስሜታዊ ትምህርት የተማሪዎችን ----------ያጎለብታል?

ሀ. ችሎታን ለ. ባህሪን ሐ. አመለካከትን መ.ሁሉም

4. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለራስ ግንዛቤ እና ራስን የመምራት ክህሎት የሚገልፀው


የትኛው ነው?

ሀ. ችግሮችን መፍታት ሐ. አለመግባባት

ለ. መበሳጨት መ. ግንኙነትን ማባባስ

5. -------ማለት የራስን ስሜቶች ሀሳቦች እና እሴቶች በትክክል የመለየት ችሎታ ነው?

ሀ. ራስን መምራት ሐ. ማህበራዊ ግንኙነት

ለ.የራስን ግንዛቤ መ. መልስ የለም

6. ------ የሌሎችን አመለካከት የመያዝ እና የመተሳሰብ ችሎታ ባህል ነው?

ሀ. ራስን ማወቅ ሐ. ማህበራዊ ግንኙነት

ለ. ራስን መምራት መ. ውሳኔ መስጠት

28
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ለ. በ ሀ ስር የተዘረዘሩትን ሐረጋት ከ ለ ስር ካሉ ሃሳቦች ጋር አዘምዱ

ሀ ለ

1. የራስ ግንዛቤ ሀ. ራስን በትክክል የማየት ችሎታ

2. መልካመ ግንኙነት ለ. ተጨባጭ መረጃን በመጠቀም የመወሰን ሂደት

3. ውሳኔ መስጠት ሐ.መረጃን በመለዋወጥ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት

4. የተሻለ አስተሳሰብ መ. የተሻለ የሃሳብ መረጃ ሂደት

5. የጋራ መግባባት ሠ. አውንታዊ ግንኙነት የመመስረት ችሎታ

ሐ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ስጡ

1. መልካም ግንኙነትን የሚያዳብሩ ክህሎቶች እነማን ናቸው?

2. የችግር አፈታት ዘዴዎችን ዘርዝሩ?

3. በአራት እግር መሮጥ የትኛውን የአካል ክፍል ያዳብራል?

4. ኳስ የመሰብሰብ ጨዋታ የሚያዳበረውን ክህሎት ዘርዝሩ?

29
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ምዕራፍ ሶስት
ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች
መግቢያ
ጤና ማለት ከበሸታ ነፃ መሆን ብቻ ሳይሆን በአካል፣ በአእምሮ፣ በማህበራዊ ግንኙነት
እና በስሜት የዳበረ ማለት ነው፡፡ ጤና የሚሻሻለው የተመጠነ እንቅስቃሴና የተመጠነ
የአመጋገብ ስርዓትን በመከተል ነው፡፡ ስለዚህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጤናን ለማሻሻል
እና ለማዳበር ዋነኛ መሳሪያ ነው፡፡

የአካል ብቃት ማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴ ወይም ውድድር ያለምንም ድካም ወይም
ችግር የማከናወን ችሎታ ነው፡፡ ሁሉም ሰዎች ብቁ ሆነው ለመገኘት ሊኖራቸው
የሚገባ የጤና፣ የሥራ ችሎታ፣ የመግባባትና የመተጋገዝ ስሜት መታሰብ አለበት፡፡
ብቃት አዕምሮአዊ፣ አካላዊ፣ ማህበራዊና ሥነ-ልቦናዊ እሴቶችን ያጠቃልላል፡፡

አንድ ተማሪ ስምንት ክፍለ ጊዜ ተምሮ ለመጨረስ አካሉ፣ አእምሮው፣ ማህበራዊ ስነ


ልቦናው ብቁ ሆኖ መገኘት አለበት፡፡ የአካል ብቃት በዳበረ ቁጥር የአንድ ሰው ጤንነት፣
ቁመና በህይወት ዘመን ደስተኛ ሆኖ የመኖር ሁኔታዎችን ያሻሽላል፡፡ የአካል ብቃት
የግለሰቡ ብቃት ሲሆን ከግለሰብ ግለሰብ በዕድሜ፣ በፆታ፣ በዘር ፣ በአመጋገብ ሁኔታ
ይለያያል፡፡

የአካል ብቃት የሚዳብረው ዘወትር አቅዶ በመስራት ብቻ ነው፡፡ በዚህ የክፍል ደረጃ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ የልብና የአተነፋፈስ ብርታትን የሚያሻሽሉ እንቅስቃሴዎች፣
የጡንቻ ብርታት የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች፣ መዘርጋትና መተጣጠፍ፣ ቅልጥፍና
እና አበረታች ቅመም የሚል ርዕስ ተካተዋል፡፡

ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸውን የአካል ክፍላቸውን በመጠቀም የአካል ብቃት


እንቅስቃሴዎችን በመስራት የአካል ብቃት ደረጃቸውን ማሻሻል ይኖርባቸዋል፡፡

30
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የመማር ዉጤቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ


• የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የሚያሻሽሉ እንቅስቃሴዎች ትገነዘባላችሁ፣
• ዕድሜን ያገናዘበ ትክክለኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመሥራት የአካል
ብቃትን ታሻሽላላችሁ፣
• በተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለመሳተፍ አዎንታዊ የሆነ አመለካከት
ታሳያላችሁ፣
• የአበረታች ቅመሞች ምንነትን ታውቃላችሁ፣

3.1- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ

• የአካል ብቃት ምንነትን ትገልጻላችሁ፣

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄዎች


1. የአካል ብቃት ማለት ምን ማለት ነው?

2. የአካል ብቃት ዘርፎች ስንት ናቸው? አብራሩ?

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማለት የሰው ልጅ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን ያለምንም


ችግር ለማከናወን የሚያደርገው የእንቅስቃሴ ዓይነት ነው፡፡

የአካል ብቃት ሁለት ዘርፎች አሉት፡፡


1. ጤና ተኮር እና
2. ውድድር ተኮር የአካል ብቃት ናቸው፡፡

ጤና ተኮር የአካል ብቃት


ጤና ተኮር የአካል ብቃት ማለት ጤናችን ለመጠበቅና የጤና ደረጃችን ለማሻሻል
የሚሰሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ናቸው፡፡ ጤና ተኮር የአካል ብቃት አምስት
እንቅስቃሴዎችን ያካተተ ሲሆኑ እነሱም፡- የልብና የአተነፋፈስ ብርታት፣ የጡንቻ
ጥንካሬ፣ የጡንቻ ብርታት፣ የመዘርጋትና የመተጣጠፍ ናቸው፡፡ ተማሪዎች ጤናቸውን
ጠብቀው የመማር ማስተማሩ ሂደት በተሻለ ለማከናወን ከላይ የተጠቀሱትን ጤና
ተኮረ እንቅስቃሴዎችን ማዘወተር ይኖርባቸዋል፡፡

31
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ውድድር ተኮር የአካል ብቃት


ውድድር ተኮር የአካል ብቃት ማለት ለውድደር የሚጠቅሙ የእንቅስቃሴ ዓይነቶች
ናቸው፡፡ ውድድር ተኮር የአካል ብቃት ከክህሎት ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ውድደር ተኮር ስፖርታዊ ብቃቶች የሚባለት ፍጥነትን፣ ሀይልን ፣ ሚዛን የመጠበቅ


ችሎታን፣ የሰውነት ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ ፣ ቅልጥፍናንና አፀፋ የመመለስ ችሎታን
የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ጤና ተኮር የአካል ብቃት ለማንኛውም ጤናን ለማዳበር የሚያስፈልግ


ሲሆን ወድድር ተኮር ግን ውድድርን በብቃት ለመወጣት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ
ማንኛውም ማህበረሰብ ማዘውተር ያለበት ጤና ተኮር የአካል ብቃት እንቅስቃሴን
ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የክፍል ደረጃ ተማሪዎች ጤናቸውን ለማዳበር የሚከተሉትን
የአካል ብቃት ዘርፎች በልምምድ እንዲሰሩ ቀርበውላቸዋል፡፡

የግምገማ ጥያቄዎች
1. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ምንነትን ግለፁ?

2. የአካል ብቃት ጥቅሞችን ፃፉ?

3. ጤና ተኮር የአካል ብቃት ዘርፎችን ዘርዝሩ?

3.2- የልብና የአተነፋፈ ስብርታትን የሚያሻሽሉ


እንቅስቃሴዎች
አጥጋቢ የመማር ብቃቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ

• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዴት የልብና የአተነፋፈስ ስርአት


እንደሚያሻሽል ትገልጻላችሁ፣

• የልብና የአተነፋፈስ ስርአት የሚያሻሽሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን


ትሰራላችሁ፣

• ለልብና አተነፋፈስ ሥርዓት የሚሰሩ የአካል ብቃትን እንቅስቃሴዎች


ጥቅም ታደንቃላችሁ፣፣

32
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄዎች


1. የልብና የአተነፋፈስ ብርታት ማለት ምን ማለት ነው?

2. ለልብና አተነፋፈስ ሥርዓት የሚሰሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ጥቅምን


ዘርዝሩ?

የልብና የአተነፋፈስ ብርታት


የልብና የአተነፋፈስ ብርታት ማለት በልብ፣ በሳንባ፣ በደምና በደም ቧንቧ አማካኝነት
ኦክስጅንና ምግብን ለሚሰራው የአካል ክፍል በብቃት የማድረስ ችሎታ ነው፡፡ በዚህ
መሰረት አራት የአካል ክፍሎች መዳበር እና ብቁ መሆን አለባቸው፡፡

የዳበረ ልብ በአንድ ጊዜ ብዙ ደም ለተለያዩ የአካል ክፍሎች በቀላሉ በመርጨት


ማድረስ ይችላል፣ የዳበረ ሳንባ ለሰዉነት የሚያስፈልገውን በቂ ኦክስጅን በቀላሉ
ማምረት እና በሰዉነት ውስጥ የተቃጠለ አየር በብቃት ለማስወገድ ያስችላል፣ የደም
ዋንኛ አገልግሎት ምግብና ኦክስጅንን ተሸክሞ ወደ ተፈለገው የሰዉነት አካል ማድረስና
የተቃጠለውን የአየር ክፍል መመለስ ሲሆን የደም ቧንቧ ደግሞደም በትክከለኛው
መንገድ እንዲዘዋወር የሚረዳ ነው፡፡ የልብና የአተነፋፈስ ብርታት በጣም ብዙ የጤና
ጥቅሞች አሉት ለምሳሌ የልብ ጡንቻ፣ የደም ቧንቧ እና የሳንባ ጤንነትን ይጠብቅልናል::

የልብና የአተነፋፈስ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች


የሚከተሉትን እንቅስቀቃሴዎችን ለረጅም ሰዓታት በመስራት ማዳበር ይቻላል፡፡
ለምሳሌ፡-
• ደረጃ መውጣት እና መውረድ
• ረጅም ርቀት ሩጫ
• መሬትበመንካትመዝለል
• ሶምሶማ ሩጫ
• ገመድ ዝላይ

ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ በዚህ የክፍል ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎችሁለት የልብና


አተነፋፈስ ብርታትን እንቅስቃሴዎች እንድትሰሩ ተመርጠዋል፡፡

33
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ተግባር 1 ደረጃ መውጣትና መውረድ(Step-up)፡-

ይህን እንቅስቃሴ በሳምንት ቢያንስ ሶስት ቀን ቢሰራ የልብና የአተነፋፈስ ብርታትን


ያሻሽላል፡፡ የልብ ምትን በመቁጠር መገምገም እንችላለን፡፡ ለምሳሌ በአስር ሰከንድ
አስራ አምስት ከተቆጠረ በአንድ ደቂቃ ስንት እደሚመታ ማስላት ይቻላል፡፡ ይህንን
እንቅስቃሴ ያለማቋረጥ ቢያንስ በሳምንት ሶስት ጊዜ ቢሰራ የእንቅስቃሴው የልብ
ምትና የአተነፋፈስ ስርዓት እየቀነሰ ይመጣል፡፡ ስለዚህ የልብና የአተነፋፈስብቃት ደረጃ
እያደገ መጣ ማለት ነው፡፡

ስዕል 3.1 የልብ ምት መለካት

የእንቅስቃሴው ዓይነት፡- ደረጃ መውጣትና መውረድ


የሚያስፈልገው መሳሪያ፡- ከፍ ያለ ደረጃ (ከ20ሴ.ሜ. እስከ 30 ሴ፣ሜ.)
የሚወስደው ጊዜ ፡- ሶስት ደቂቃ
የሚሰጠው ጥቅም፡- የመተንፈሻ ክፍሎችና የልብ ስራን ማሻሻል

ደረጃ ለመውጣትን ለመውረድ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ነጥቦች


• የእግር ክፍሎችን የሚያዘጋጁ የሰዉነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎችን መስራት፣

• ከመሬት ከሃያ እስከ ሰላሳ ሴንቲ ሜትር ከፍታ ባለው ደረጃ ላይ እንቅስቃሴውን
ለመስራት ተዘጋጅቶ አጠገቡ መቆም፣

• መሪ እግርን እና ተከታይ እግርን በማንሳት ወደ ደረጃ ማውጣት፣

34
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• ሙሉ አካልን ወደ ደረጃ ማንሳትን፣

• የወጣውን እግር ወደተነሳበት መመለስ፣

• ይህ እንቅስቃሴ በሚሰራበት ጊዜ ጀርባ ቀጥ ማለት አለበት፣

• እግር ደረጃ ላይ በትክከል ማረፉን እርግጠኛ መሆን አለብን፣

ስዕል 3.2 ደረጃ ላይ መውጣት እና መውረድ


የአሰራር ቅደም ተከተል

• ቀስ በቀስ እንቅስቃሴውን መሞከር

• ቀስ በቀስ እንቅስቃሴውን ሳያቋርጡ ለ40 ሰከንድ ደረጃ ላይ መውጣት መውረድ


መለማመድ
• በመካከለኛ ፍጥነት ለ40 ሰከንድ ደረጃ መውጣትና መውረድን መለማመድ

• እንቅስቃሴውን በመካከለኛ ፍጥነት ለአንድ ደቂቃ መስራት

• እንቅስቃሴውን በፍጥነት ለሁለት ደቂቃ ሳያቋርጡ በመስራት ምን ያህል ጊዜ

እንደወጡና እንደወረዱ መቁጠርና እራሳቸውን ከጓደኞቻቸው ጋር ማነፃፀር እና

እንዴት እንደሚሻሻል መወያየት፡፡

• እንቅስቃሴውን ሳያቋርጡ ለሶስት ደቂቃ መስራት እና ለውጡን መገምገም፡፡

35
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ማስታወሻ፡- በየእንቅስቃሴው መካከል ሰላሳ ሰከንድ እረፍት መወሰድ(ይህ ማለት


ግን ሙሉ ለሙሉ መቀመጥ ሳይሆን የተለያዩ ማሳሳቢያ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ)

የግምገማ ጥያቄዎች
1. ትክክለኛ የደረጃ መውጣት እና የመውረድን አሰራር ሰርታችሁ አሳዩ?

2. ይህንን እንቅስቃሴ ስትሰሩ ምን ምን ጥቅም ታገኛላችሁ?

የቤት ስራ
1. ከላይ የተጠቀሱ እንቅስቃሴዎችን የአሰራር ሂደትን በመከተል ከቤታችሁ ባለው
ደረጃ በሳምንት ሶስት ቀን ተለማመዱ?

2. የልብ ምታችሁን ከእንቅስቃሴ በፊት እና በኋላ ያለውን ለውጥ በአንድ ደቂቃ ምን


ያህል ጊዜ እንደሚመታ መዝግቡ እና ለውጡን ገምግሙ?
ተግባር 2 መሬት በመንካት መዝለል

የእንቅስቃሴው ዓይነት፡- መሬት በመንካት መዝለል

የሚወስደው ሰዓት፡- ሁለት ደቂቃ

የሚሰጠው ጥቅም፡- የመተንፈሻ ክፍሎችና የልብ ስራን ማሻሻል

መሬት በመንካት ለመዝለል የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ነጥቦች

• እግርን በትከሻ ስፋት ልክ መከፈት

• ጉልበት አጠፍ ማድርግ እና ከእግር ጣቶች ጋር ቀጥታ ማድረግ(90ድግሪ)

• እጅ ዘና ባለ ሁኔታ መሬትን በመንካት ለመዝለል መዘጋጀት

• መሬትን በመጫን ወደ ላይ መነሳት

• ወደ መሬት ስናርፍ እግር ትንሽ ከትከሻ ስፋት በበለጠ መከፈት እና ቁጢጥ ባለ


ሁኔታ መሆን አለበት፡፡

36
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ስዕል 3.3 ቁጢጥ ብሎ መሬት በመንካት መዝለል


የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• በትከሻ ስፋት ልክ እግርን በመክፍት ቀስ ብሎ ቁጢጥ ማለት እና መመለስ ቢያንስ


ለአምስት ጊዜ መሞከር

• በትከሻ ስፋት ልክ በመቆም ወደ ላይ እጅን ዘርግቶ መዝለል ለአምስት ጊዜ


መስራት

• ቁጢጥ በማለት እጅን ዘና ባለ ሁኔታ መሬትን በመንካት ወደ ላይ መዝለል እና


ወደ ተነሱበት መመለስ ለአስር ጊዜ መስራት

• ሙሉ እነቅስቃሴውን መሞከር ቢያንስ ለአስር ጊዜ በቀስታ መስራት

• ሁለት ሁለት ተማሪዎች በመሆን እንቅስቃሴውን በመስራት ወደ ላይ በመዝለል


እጅን ማነካካት አምስት አምስት ለሶስት ጊዜ መስራት

• ሁለት ሁለት ተማሪዎች በመሆን እንቅስቃሴውን በመስራት ወደ ላይ በመዝለል


እጅን ማነካካት ስድስት ስድስት ለሶስት ጊዜ መስራት

• በሁለት ደቂቂ ውስጥ እንቅስቃሴውን ምን ያህል ጊዜ እንደሰራችሁ መቁጠርና


ከጓደኛ ጋር ማነፃፀር

37
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ማስታወሻ፡- በየእንቅስቃሴው መካከል ሰላሳ ሰከንድ እረፍት መወሰድ (ይህ ማለት


ግን ሙሉ ለሙሉ መቀመጥ ሳይሆን የተለያዩ ማሳሳቢያ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ)

ልዩ ፍላጎት የሚያስፈክጋቸው ካሉእንደ ጉዳታቸው መጠን የልብና የአተነፋፈስ


ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች በመምረጥ መሳተፍ አለባቸው፡፡

የግምገማ ጥያቄዎች
1. ትክክለኛ መሬት በመንካት መዝለል አሰራሩን በመግለፅ ሰርታችሁ አሳዩ?

2. ይህንን እንቅስቃሴ ስትሰሩ ምን ምን ጥቅም ታገኛላችሁ?

3. የልብና የአተነፋፈስ ስርአትን በትክክል የሚያሻሽሉ የአካል ብቃት


እንቅስቃሴዎችን ፃፉ?

የቤት ስራ
1. ከላይ የተጠቀሱ እንቅስቃሴዎችን የአሰራር ሂደትን በመከተል በቤታችሁ ወይም
ሰፈራችሁ ባለው ሜዳ በሳምንት ሶስት ቀን ተለማመዱ?

2. ሌሎች የልብና የአተነፋፈስ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን በመለየት ስሩ?

3.3 የጡንቻ ብርታት የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ

• የጡንቻ ብርታትን የሚያሻሽሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ትሰራላችሁ፣

የመነሻና ማነቃቂያ ጥያቄዎች፡


1. የጡንቻ ብርታት ማለት ምን ማለት ነው?

2. የጡንቻ ብርታትን የሚያሻሽሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ምንምን ናቸው?

የጡንቻ ብርታት
የጡንቻ ብርታት ማለት ጡንቻዎቸ በህብረት ሆነው ለረጅም ጊዜ የመስራት ችሎታ
ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ ጡንቻዎች ለረጅም ጊዜ ያለ ድካም የሚያወጡት ኃይል

38
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ነው፡፡ ጡንቻ ስንል በዚህ የክፍል ደረጃ አጥንት ላይ ተደርቦ የሚገኘውን የስጋ ክፍል
ማለታችን ነው፡፡ ለመጥቀስ ያህል የእግር፣ የሆድ፣ የደረት፣ የእጅ፣ የጀርባ ጡንዎች
ወዘተ… ናቸው፡፡ ጡንቻ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመንቀሳቀስ፣ ከብደት ያለው
ነገር ለማንሳት፣ ለመግፋት ለመሮጥ በአጠቃላይ የአካል እንቅስቃሴ ለማድረግ ከፍተኛ
አስተዋፅኦ አለው፡፡

የጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች የሚከተሉት ናቸው እነሱም፡-

1. በደረት ተኝቶ እጅ መሬትን በመግፋት መመለስ (push up)

2. በጀርበ ተኝቶ ከወገብ በላይ እግርን አጥፎ መነሳት፣

3. በጀርበ ተኝቶ ከወገብ በላይ እግርን ዘርግቶ መነሳት፣

4. በጀርበ ተኝቶ እግርን ማንሳት፣

5. በሆድ ተኝቶ ከደረት በላይ ያለውን የአካል ክፍል ማንሳትና በተጨማሪም እጅና
እግርን ሳንመልስ አዛው ማቆየት፣

6. ተንበርክኮ በእጅ መዳፍ መሬትን መግፋት እና መነሳት /knee push-up/

7. ወደጎንመነሳት (Side Hop)


ተግባር 1 ተንበርክኮ በእጅ መዳፍ መሬትን መግፋት እና መነሳት

የእንቅስቃሴው ዓይነት፡- ተንበርክኮ በእጅ መዳፍ መሬትን መግፋት እና መነሳት

የሚሰራው ቁጥር፡- (30) ሰላሳ

የሚሰጠው ጥቅም፡- የእጅና የደረትን ጡንቻን ብርታት ማሻሻል

ዋና ዋና ነጥቦች፡-

• መንበርከክ

• ክንድን መዘርጋት አና የእጃችን ስፋት በትከሻ ስፋት ልክ መሬት ማስቀመጥ፣

• እጅ በጣም ወደፊትም ሆነ ወደ ኃላ አለማድረግ(በብብት ቀጥታ ማስቀመጥ)

• ጀርባችንና መቀመጫችን ቀጥ ማድረግ፣

• መሬት የሚነካው እጅና ጉልበት ብቻ መሆን አለበት፣

39
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• እጅን ማጠፍና መዘርጋት መለማመድ

ስዕል 3.4 ተንበርክኮ በእጅ መዳፍ መሬትን መግፋትና መነሳት


የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• የእጅ እንቅስቃሴ የበዛበት የሰዉነት ማሟሟቂያ መስራት፣

• መንበርከክን መለማመድ(ከጉልበት መካከል ትንሽ ከፈት አድርጎ)፣

• በመንበርከክ እጅ በትክከለኛው ቦታ ማስቀመጥን መለማመድ፣

• በሆድ በመተኛት በእጅ መሬትን ተጭኖ መነሳት እግር ከኃላ ተነስቶ መሬት
ሳይነካ (አምስት አምስት ጊዜ በሁለት ዙር)

• ተንበርክከው በመዳፍ መሬትን በመግፋት መነሳት መለማመድ ሶስት ጊዜ አስር


አስር

• ተንበርክከው በመዳፍ መሬትን በመግፋት መነሳት(knee push-up) ሁለት ሁለት


ሆነው ሲነሱ እጅ ተራ በተራ ማነካካት አስራ አምስት ጊዜ በሁለትምስትትአስራ
ዙር መስራት

• ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው ካሉ ለእነሱ የሚሆናቸው የጡንቻ ብርታትን


የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች በመምረጥ መሳተፍ አለባቸው፡፡

40
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የግምገማ ጥያቄዎች
1. የጡንቻ ብርታት የሚያሻሽሉ እንቅስቃሴዎችን ቢያንስ ሶስት ጥቀሱ?

2. የጡንቻ ብርታት የሚያሻሽሉ እንቅስቃሴዎችን አሰራር ሰርታችሁ አሳዩ?

የቤት ሥራ
ተንበርክኮ በእጅ መዳፍ መሬትን መግፋትና መነሳት /knee push-up/ን እስከ 36
በሶስት ዙር ስሩ?
ተግባር 2 ወደ ጎን መነሳት (side hop):-

የእንቅስቃሴው ጥቅም፡- ከወገበ በታች የሚገኙ ጡንቻዎችን ብርታት ማሻሻል(የባት


ጡንቻ፣ የእግር ጡንቻ፣ የዳሌ ጡንቻ)
የእንቅስቃሴው ዓይነት፡- ወደ ጎን መነሳት
የሚሰራው ስራው መጠን፡- አስራ ስድስት በሁለት ድግገሞሽ ጠቅላላ ሰላሳ ሁለት

ዋና ዋና ነጥቦች፡-

• እግርን በዳሌ ስፋት ልክ ከፍቶ መቆም፣


• ቁጢጥ ወይም ሸብረከ ማለት፣
• እጅን ዳሌ ላይ ማድረግ፣
• ወደ ጎን ለመዝለል በቂ ቦታ መኖሩን ማረጋገጥ፣
• ዝቅ በማለት ከጉልበትና ከዳሌ በመታጠፍ ወደ ጎን መዝለል፡፡

ስዕል 3.5 ዝቅ በማለት ከጉልበትና ከዳሌ በመታጠፍ ወደ ጎን መዝለል

41
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• እግርን በትከሻ ልክ ከፍቶ መቆም

• ሁለት እግርን በማንሳት ወደ ቀኝ ጎን ዘሎ መቆም (አምስት ጊዜ በሁለት ዙር)

• ሁለት እግርን በማንሳት ወደ ግራጎን ዘሎ መቆም (አምስት ጊዜ በሁለት ዙር)

• ከመቆም ቁጢጥ ማለትን ከዛም በቆሙበት መነሳት መለማመድ (አምስት ጊዜ


በሁለት ዙር)

• ቁጢጥ ብሎ ባላችሁበት ወደ ቀኝና ወደ ግራ መነሳትን መለማመድ

• ከቁጢጥ በመነሳት ከቀኝ ወደ ግራ ከግራ ወደ ቀኝ መዝለልን መለማመድ

• ከፍ ያለ ነገር በማስቀመጥ ከቀኝ ወደ ግራ እና ከግራ ወደ ቀኝ ስምንት ወደ ቀኝ


እና ስምንት ወደ ግራ በሁለት ዙር መስራት፣

• ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው ካሉ ለእነሱ የሚሆናቸውን የጡንቻ ብርታትን


የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች በመምረጥ መሳተፍ አለባቸው፡፡

የግምገማ ጥያቄ
ወደ ጎን መነሳት የትኛውን የጡንጫ ክፍል ያሻሽላል?

የቤት ሥራ
• የላየይኛውን እንቅስቃሴ እና ሌሎች የጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች
በቤት ወይም በሰፈር ተለማመዱ?

3.4- መዘርጋትናመተጣጠፍ /Felexibility/


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ

• ዕድሜን ያገናዘበ የመተጣጠፍና የመዘርጋት እንቅስቃሴ በትክክል


ትሰራላችሁ፣

42
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች፡


1. የመተጣጠፍና የመዘርጋት እንቅስቃሴ ማለት ምን ማለት ነው?

2. የመተጣጠፍና የመዘርጋት እንቅስቃሴዎች ምንምን ናቸው?

የሰዉነት መተጣጠፍና መዘርጋት ማለት የሰዉነት የመገጣጠሚያ ክፍሎችን መጠን


ሰፊ በሆነ ተፈጥሮአዊ የእንቅስቃሴ መጠን /range of motion/ የማንቀሳቀስ ችሎታ
ነው፡፡ እያንዳንዱ የሰዉነት መገጣጠሚያ የተለያየ የሰዉነት መተጣጠፍ መጠን ወይም
ደረጃ አለዉ፡፡ ስለዚህ የመተጣጠፍ እንቅስቃሴዎችን በምንሰራበት ወቅት የተለያየ
የአካል ክፍሎች የሰዉነት መተጣጠፍ ደረጃ ከግምት ዉስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነዉ፡፡
ተግባር 1 እግርን ዘርግቶ በመቀመጥ በእጅ የእግር ጣቶችን መንካት፡-

የእንቅስቃሴው ጥቅም፡- የወገብ፣ የእግርና ደረት አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎችና


መገጣጠሚያዎችን የመተጣጠፍና የመዘርጋት ችሎታን ያሻሽላል፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• ከተቀመጡ በኋላ እግሮችን አንድ ላይ በማድረግ ወደ ፊት ዘርግቶ ማስቀመጥ፡፡

• እግሮች ከጉልበት ሳይታጠፉ ወደ ፊት በማጎንበስ እጆችን ዘርግቶ የእግሮችን


ጣቶች በመንካት እየደጋገሙ መስራት ይሆናል፡፡

• የእግር ጣት በመንካት ወደ ቀኝና ወደ ግራ እየተጠማዘዙ መልሶ የእግር ጣትን


መንካት፣ደጋግሞ መስራት

ሰዕል 3.6 እግርን ዘርግቶ በመቀመጥ በእጅ የእግር ጣቶችን መንካት


43
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ተግባር 2 ሰውነትን ወደ ግራና ቀኝ ማዘንበል፡-

የእንቅስቃሴው ጥቅም፡- የሽንጥንና የወገብ ጎን አካባቢን የመሳሳብ ችሎታን ለማሻሻል፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• እግሮችን በትከሻ ስፊት ልክ ከፍተው በመቆም የቀኝ እጅን በመጠኑ ከክርን አጠፍ
በማድረግ ከራስ በላይ መያዝ፡፡

• ከዚህ ሁኔታ በዝግታ ወደ ግራ በማዘንበል መጠነኛ ሕመም ስሜት እስኪሰማ


ማዘንበል፡፡

• ይህንኑ በቀኝ በኩል በተመሳሳይ ሁኔታ ማከናወን

ሰዕል 3.7 ሰውነትን ወደ ግራና ቀኝ ማዘንበል

44
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ተግባር 3 አንገትና እጅን አንድ ላይ ማጠማዘዝ፡-

የእንቅስቃሴው ጥቅም፡- የአንገት ጡንቻንና ውጫዊ ዳሌን መሳሳብ ችሎታን ያሻሽላል፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• የቀኝ እግርን በመዘርጋት መቀመጥ

• ግራ እግርን በማጠፍ በቀኝ እግር ከጉልበት በላይ አሳልፎ ማስቀመጥ

• የቀኝን እጅ በግራ እግር በኩል ማስቀመጥ

• እግርን በቀኝ እጅ በመጫን ወደ ተቃራኒ በመግፋት ከወገብ በላይ ያለውን ሰውነት


ወደ ግራ ማጠማዘዝ

• ይህንኑ እንቅስቃሴ የተዘረጋዉን በማጠፍ የታጠፈውን በመዘርጋት ማሰራት

• ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው ካሉ ለእነሱ የሚሆናቸውን መዘርጋት


እና መተጣጠፍን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን በመምረጥ መሳተፍ አለባቸው፡፡

ሰዕል 3.8 አንገትና እጅን አንድ ላይ ማጠማዘዝ

45
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የግምገማ ጥያቄ
የመዘርጋትናመተጣጠፍ እንቅስቃሴን ማዘወተር የሚሰጠውን ጥቅም ግለፁ?

የቤት ሥራ
የተለያዩ የማሳሳብና የመጠማዘዝ ችሎታን የሚያዳብሩ እንቀስቃሴዎችን በመምረጥ
ሥሩ?

3.5- ቅልጥፍና
የመነሻና የመነቃቂያ ጥያቄ
ቅልጥፍናን የሚያደብሩ እንቅስቃሴዎች የትኞቹ ናቸው?

ቅልጥፍና ማለት አንድን ተግባር በፍጥነት የማከንወን ችሎታ ማለት ንው ፡፡የተሰጠን


ስራ ቶሎ ቶሎ የመስራት ችሎታን ያካብትልናል ፡፡ የቅልጥፍና ችሎታ በብዙ የስፖርት
ውድድሮች ጎልቶ ይታያል፡፡ በዚህ ዕድሜ ደረጃ በሚገባ መጀመር የሚችል በመሆኑ
ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እንቅስቃሴዎች የቅልጥፍና ችሎታን
የሚያሻሽሉ ናቸው፡፡
ተግባር 1 መስመር የመንካት ውድድር

የእንቅስቃሴው ጥቅም፡- ፍጥነትንና ቅልጥፍናን ማሻሻል፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• የሰዉነት ማሟሟቂያ መስራት

• የመነሻ መስመር ማስመር

• ከመነሻው መስመር ቀጥሎ በአምስት ሜትር ስፋት ማስመር

• ከአንደኛዉ መስምር ቀጥሎ አራት ሜትር ስፋት ማስመር

• ከሁለተኛዉ መስመር ቀጥሎ ሶስት ሜትር ስፋት ማስመር

• ከመነሻ መስመር በመነሳት የመጀመሪያውን አምስት ሜትር ነክቶ በመመለስ


የተረኛን እጅ በመንካት ከኋላ መሰለፍ

46
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• የመጀመሪያዉ አምስት ሜትር ውድድር ካለቀ በኋላ ሁለተኛው ዙር ውድድር


የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን አራት ሜትር ጨምረው ሮጠው በመመለስ
ተረኛን ይልካሉ፡፡

• የመጀመሪያው ዙር ካለቀ በኋላ ሶስቱንም ምለክቶች እየነኩ መመላለስ

ሰዕል 3.9 መስመር የመንካት ውድድር

ተግባር 2 ምልክትን የመዞር እንቅስቃሴ

የእንቅስቃሴው ጥቅም፡- ፍጥነትንና ቅልጥፍናን ማሻሻል፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል

• የመነሻ መስመር ምልክት ማስቀመጥ

• ከመነሻ መስመሩ በአምስት አምስት ሜትር ርቀት ላይ ስፋታቸው ሁለት ጫማ


የሆነ ሁለት ምልክቶችን በየርቀቱ ማስቀመጥ፡፡ በአጠቃላይ ሶስት ቦታዎች ምልክት
ማስቀመጥ

• በሰልፍ በመሆን ምልክት ሲሰጥ ወደ ፊት መሮጥ ከዚያም የመጀመሪያውን ምልክት

47
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

በመዞር ወደ ሰልፉ መመለስ እና ተረኛን መላከ

• ሁሉም ከተዳረሱ በኃላ የመጀመሪያውን ስራ በመድገም ወደ ሁለተኛው ምልክት


በመሮጥ ማሳደግ፣ ከዚያም ወደ ሶስት ማሳደግ

• ምልክቱን ሲዞር ግን ወደፊት ከሮጡ በኃላ ወደ ኃላ መመለስ ላይ በጀርባ በመሆን


ከዚያ ወደ ፊት በመሮጥ ወደ ቀጣይ ምልክት ማምራት ያስፈልጋል

• ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው ካሉ ለእነሱ የሚሆናቸውን ቅልጥፍና የሚያዳብሩ


እንቅስቃሴዎች በመምረጥ መሳተፍ አለበት/ባት፡፡

ሰዕል 3.10 ምልክትን የመዞር እንቅስቃሴ

የግምገማ ጥያቄዎች
1. ቅልጥፍና ማለት ምን ማላት ነው?

2. የቅልጥፍና እንቅስቃሴን ለህይወታችን የሚሰጠውን ጥቅም ዘርዝሩ?

3. የቅልጥፍና እንቅስቃሴዎችን ሰርታችሁ አሳዩ?

የቤት ሥራ
የልብና የአተነፋፈስ ብርታትን፣ የጡንቻ ብርታት፣ የመጠጣጠፍ ችሎታ እና ቅልጥፍናን
የሚያሻሽሉ ሁለት እና ከዚያ በላይ እቅስቃሴዎችን ለእያንዳንዱ ሥሩ?

ማስታወሻ፡- የሰራችሁትን የቤት ሥራ በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ ለመምህሩ/ሯ አሳዩ፡፡

48
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

3.6. አበረታች ቅመም ምንድን ነው?


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ

• የአበረታች ቅመሞችን (Doping) ምንነት ትገልፃላችሁ፣

የመነሻ ጥያቄዎች
ስለ አበረታች ቅመሞች (Doping) የምታውቁትን ግለፁ?

አበረታች ቅመሞች (Doping) ማለት ስፖርተኞች ብቃትን ለማሻሻል የሚወስዱት


ህገ ወጥ ንጥረ ነገር ነው ወይም ቅመሞች ማለት ነው፡፡ በስፖርታዊ ውድድሮች
ወይም እንቅስቃሴዎች ወቅት ሁለንተናዊ ብቃትን የሚጨምሩ የተከለከሉ አበረታች
ቅመሞችን መውሰድ ማለት ነው

ይህ አበረታች ንጥረ ነገር ተወዳዳሪው ወይም አትሌቱ ብርታቱን ከፍ ለማድረግ ሲባል


በመርፌ፣ በኪኒን፣ በምግብና በመጠጥ መልክ ይወስዳቸዋል፡፡ አትሌቱ የራሱ ያለሆነ
ማለትም በተፈጥሮና በስልጠና ያላመጣውን ብቃትና ሃይል ይሰጠዋል፡፡ ይህ ደግሞ
በውድድር ተቋማት ዘንድ ህገ ወጥ ስለሆነ በአለም አቀፉ አበረታች ቅመም ተቋም
ያስጠይቃል፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ668 በስፖርት አበረታች ቅመሞችን መጠቀም የተጀመረው


እንደነበር መዛግብት ያወሳሉ፡፡ በ1967የአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የስፖርት
አበረታች ቅመሞች መጠቀምን በመከልከል በስሩም የህክምና ኮሚሽን አቋቋመ፡፡
በ1999 ዓ.ምአለም አቀፍ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ተቋቋመ፡፡ በ1999 ዓ.ም
አገራችን ኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች የአለም አቀፍ ስምምነቶችን ተቀበለች፡፡
2009 ዓ.ምየኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት በሚኒስትሮች ም/ቤት
ደንብ ቁጥር ስራውን በይፋ ጀመሯል፡፡አበረታች ቅመም ወስዶ የተገኘ አትሌት ወይም
ተወዳዳሪ ከውድድር አለም ይታገዳል፡፡

የግምገማ ጥያቄ
ስለ አበረታች ቅመም ምንነት ግለፁ?

49
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የምዕራፉ ማጠቃለያ
ዘመናዊ የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት አቀራረብ ከጤና ተኮር እንቅስቃሴዎች
ጋር በቀጥታ እንዲገናኝ የተደረገ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት በምዕራፉ ውስጥ የጤና
ተኮር አካላዊ ብቃት መሰረቶች የሆኑት የልብና የአተነፋፈስ ብርታት፣ የጡንቻ
ብርታት፣ የመተጣጠፍ፣ የመዘርጋት እና የቅልጥፍና ችሎታ እንዲካተቱ
ተደርጓል፡፡

ብርታትን የተመለከቱት እንቅስቃሴዎች የልብ፣ የደም ዝውውርና አተነፋፈስ


ሥርዓትን የሚያጠቃልሉ በመሆናቸው የህልውና መሰረት በሆኑት ውስጣዊ
አካላችን ላይ ተጽእኖ የሚያሳርፉ ናቸው፡፡

የጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች ተንበርክኮ በእጅ መዳፍ መሬትን


መግፋት እና መነሳት ወደጎን መነሳት ወዘተ የመሳሰሉትን በመስራት ማዳበር
ይቻላል፡፡

መተጣጠፍና መዘርጋት ማለት የሰዉነት የመገጣጠሚያ ክፍሎችን መጠነ ሰፊ


በሆነ ተፈጥሮአዊ የእንቅስቃሴ መጠን የማንቀሳቀስ ችሎታ ነው፡፡ ቅልጥፍና
ማለት ደግሞ አንድን የተሰጠን ስራ ቶሎ ቶሎ የመስራት ችሎታ ሲሆኑ
ቅልጥፍናን የሚያዳብሩ መስመር የመንካት ውድድርና ምልክትን የመዞር
እንቅስቃሴዎች ናቸው፡፡ እነዚህን እንቅስቃሴዎች ያለ ማቋረጥ በሳምንት ሶስት
ቀን ከሰራን የጤና ደረጃችን በእጀጉ እንደሚሻሻል ጥርጥር የለውም፡፡ አበረታች
ቅመምን መጠቀም ለተወዳዳሪዎች በሕግ እነደተከለከለው ተማሪዎችም ከዚህ
የምትማሩት በአቋራጭ ሳይለፉ መኮረጅን በሕግ እንደሚያስቀጣ ልምዱን
መለማመድ አለባችሁ፡፡ የተከለከሉ ነገሮችንም ከማድረግ መቆጠብ አለባችሁ፡፡

50
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የማጠቃለያ ጥያቄዎች
ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል የሆነዉን እዉነት ያልሆነዉን ሀሰት በማለት
መልሱ

1. ጤና ማለት ከበሽታ ነፃ መሆን ማለት ነዉ፡፡

2. ጤና የሚዳበረዉ በተመጠነ እንቅስቃሴ እና በተመጠነ አመጋገብ ስርዓትነዉ፡፡

3. የአካል ብቃት የሚያዳብረዉ የሰዉነት ክፍልን ብቻ ነዉ፡፡

4. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚዳብረዉ በተከታታይ በመስራት ነዉ፡፡

5. አካል ብቃት እንቅስቃሴ በአራት ዘርፎች ይከፈላል፡፡

ለ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛዉን መልስ በመምረጥ መልሱ

1. ከሚከተሉት ዉስጥ አንዱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጥቅም ነዉ?

ሀ/ የአካል ዕድገት ሐ/ የተስተካከለ ቁመና

ለ/ የአዕምሮ ዕድገት መ/ ሁሉም

2. ከሚከተሉት ውስጥ ጤና ተኮር የአካል ብቃት ዘርፍ የሆነዉ የቱ ነዉ?

ሀ/ ፍጥነት ለ/ ቅልጥፍና ሐ/ የጡንቻ ብርታት መ/ ሁሉም

3. ከሚከተሉት አንዱ የክህሎት (የዉድድር) ተኮር ነዉ?

ሀ/ የጡንቻ ጥንካሬ ለ/ ቅልጥፍና ሐ/ የጡንቻ ብርታት መ/ ሁሉም

4. ከሚከተሉት አንዱ የአበረታች ቅመም ጉዳት ነዉ?

ሀ/ የጤና ጉዳት ለ/ የአዕምሮ ጉዳት ሐ/ የአካል ጉዳት መ/ ሁሉም

5. ከሚከተሉት እንቅስቃሴዎች አንዱ የልብና የአተነፋፈስ ብርታትን የሚያዳብር ነዉ?

ሀ/ የገመድ ዝላይ ለ/ ክብደት ማንሳት ሐ/ ፑሽ አፕ መ/ ሁሉም

51
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ሐ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከትክክለኛዉ መልስ ጋር አዛምዱ

ሀ ለ

1. የልብና የተነፋፈስ ብርታት ሀ/ የቅልጥፍና ችሎታ

2. የጡንቻ ብርታት ለ/ የጤና ደረጃን ለማሻሻል የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች

3. መተጣጠፍ እና መዘረጋት ሐ/ በሶምሶማ ሩጫ የሚዳብር

4. ጤና ተኮር የአካል ብቃት መ/ ወደ ግራና ወደ ቀኝ የመዞር ችሎታ

5. ክህሎት /ዉድድር/ ተኮር ሠ/ ተንበርክኮ መሬትን በመግፋት የሚዳብር

መ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛዉን መልስ ጻፉ፤

1. የጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ዘርዝሩ?

2. የቅለጥፍና ችሎታን የሚያዳብሩ እንቀስቃሴዎችን ቢያንስ ሁለት ፃፉ?

52
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ምዕራፍ አራት
አትሌቲክስ
መግቢያ
የሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርትን በአግባቡ ለመተግበርና ለማሳደግ አትሌቲክስ በአንድ
ምዕራፍ ሊቀርብ ችሏል፡፡ አትሌቲክስ በመምና በሜዳ ተግባራት የሚከናወን ሲሆን
በውስጡም ሩጫ፣ ውርወራና ዝላይ አጠቃሎ የያዘ ነው፡፡ አትሌትክስ በአብዛኛው
የተፈጥሮ ስፖርት በመባል ይታወቃል፡፡ ሰዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን
ለማከናወን ሲሉ አትሌቲክስን መተግበር የግድ ይላቸዋል፡፡ ከሚፈልጉት ቦታ ለመድረስ
መፍጠን ይኖርባቸዋል፡፡ ለመፍጠን መሮጥ፣ ዕቃ ለማቀበል መወርወር፣ ጎድጎድ
ያለ ቦታ ሲያጋጥም መዝለል እና ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ መራመድ ያስፈልጋል::
በዚህ ምክንያት አትሌቲክስ የተፈጥሮ እንቅስቃሴ ሊባል ችሏል፡፡ ጥንታዊ ሰዎች
ደግሞ ምግባቸውን ለማዘጋጀት እንስሳትን በማደንና ፍራፍሬ በመልቀም ይኖሩ
ነበር:: ለማደንና ፍራፍሬ ለመልቀም ደግሞ መሮጥ ፣ መወርወር እና መዝለል ዋነኛ
ተግባሮች ነበሩ፡፡ ስለዚህ አትሌቲክስ ሰዎች በዚህ ምድር መኖር ከጀመሩ ጀምሮ አብሮ
የነበረ እንቅስቃሴ ነው፡፡

የአትሌቲክስ ከህሎትን ለማዳበር በትምህርት ቤት ውስጥ በሰዉነት ማጎልመሻ


ትምህርት በመሳተፍ በትክክል መሮጥ ፣ መዝለልን እና መወርወርን እንቅስቃሴን
ለመማር መሠረት ይሆናቸዋል እንዲሁም ትክክለኛ ዕድገትን ማግኘት ይቻላል፡፡
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ሩጫ፣ ዉርወራ እና ዝላይ ይዘቶች ተካተዋል፡፡

53
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የመማር ዉጤቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ


• በጣም ፈጣን የሆነ የሩጫ ምንነትን ታስረዳላችሁ፣

• በተሰጠዉ ዉስን ሰዓት ዉስጥ የመሮጥ ችሎታን ታሻሽላላችሁ፣

• በሁለት እጆች ወደፊት ዉርወራ ጊዜ ትክክለኛዉ የእጅና የላይኛዉ የሰውነት


አካል እንቅስቃሴን ታሳያላችሁ፣

• በመቆም የሽቅብ ዝላይ፣ የእጅንና የእግርን አቋቋም ትገልፃላችሁ፣ በክህሎት


ልምምድ ጊዜ በትብብር ከጓደኞቻችሁ ጋር ትሰራላችሁ፣

• በክህሎት ልምምድ ጊዜ በትብብር ከጓደኞቻቸዉ ጋር ይሰራሉ፣

4.1- ሩጫ
አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማሩ በኋላ፡-

• በመምህሩ/ሯ እገዛ የዝቅተኛ ፍጥነት ሩጫን በመንደፍ ትሰራላችሁ፣


• በከፍተኛ ፍጥነት መሮጥን ታሳያላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


1. የፍጥነት ሩጫ ዓላማን ጥቀሱ?

2. ፈጣን ሯጭ ለመሆን ምን ምን መሟላት አለበት?

ሩጫ የተፈጥሮ እንቅስቃሴ ሲሆን በሩጫ ጊዜ ግን ከእያንዳንዱ መመንጠቅ በኃላ ለአጭር


ጊዜ በአየር ላይ መንሳፈፍ የሚገኝበት ሁኔታ ነው፡፡ መሄድና መሮጥ የሚከናወኑት
በሁሉም የሰውነት መንቀሳቀሻ አካለት ቢሆንም ዋናውን ሚና የሚጫወተው እግር
ነው፡፡ ሩጫ የርምጃዎች ውጤት ሲሆን አንዴ በቀኝ አንዴ በግራ በማፈራረቅ የሚደረግ
ተመሳሳይ የእግር እንቅስቃሴ ነው፡፡
ሩጫ በስታዲየም ውስጥ እና ከስታዲየም ውጪ ይካሄዳል፡፡ ሩጫ አጭር ፣ መካከለኛ
እና ረጅም ርቀት ተብሎ በሶስት ይከፈላል፡፡ አጭር ርቀት ሩጫ የሚያካትታቸው
100 ሜትር፣ 200 ሜትር፣ 400 ሜትር፣ 4x100ሜትር፣ 4x400ሜ ዱላ ቅብብል
እንዲሁም 100ሜትር፣ 110ሜትርና 4x400 ሜትር መሰናከል ናቸው፡፡ በዚህ ክፍል
ደረጃ ለፍጥንት መሮጥ የሚል የተግባር ትምህርት ቀርቧል፡፡

54
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ለፍጥነት መሮጥ
ለፍጥነት መሮጥ አንድን የተወሰነ ርቀት በአጭር ጊዜ መጨረስ ማለት ነው:: በፍጥነት
ሮጦ ለመጨረስ እና አጭር ሰዓት ለማስመዝገብ አነሳስ ፣ የእጅና የእግር ቅንጅት
አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ለፍጥነት መሮጥ ዋና ዓላማው አንድን እንቅስቃሴ
በፈጣን ሰዓት መጨረስ ነው፡፡
ተግባር 1 ከ30 እስከ 50 ሜትር በፍጥነት መሮጥ

የሩጫው ዋና ዓላማ፡- አጭር ሰዓት ማስመዝገብ ነው፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-


• ከወገብ በላይ ያለውን የሰዉንት ክፍል ወደ ፊት በማዘንበል ፈጣን የእግር
እንቅስቃሴ በመጠቀም እጅን ከእግር ጋር በማቀናጀት በእርምጃ እስከ አስራ
አምስት(15) ሜትር ድረስ መለማመድ፣
• በዝግታ ሩጫ እስከ ሃያ(20) ሜትር ድረስ መለማመድ
• ይህንን እንቅስቃሴ ሰላሳ(30) ሜትር ድረስ በጥንድ በመሆን እርስ በርስ እየተፎካከሩ
በፍጥነት መሮጥና መለማመድ
• የእንቅስቃሴውን ርቀት በመጨመር ከ40 እስከ 50 ሜትር አራት አራት በመሆን
መወዳደር

ሰዕል 4.1 (ከ30 እስከ 50 ሜትር የፍጥነት ሩጫ


55
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ተግባር 2 ከስልሳ (60) እስከ ሰባ (70) ሜትር በፍጥነት መሮጥ

የሩጫው ዋና ዓላማ፡- አጭር ሰዓት ማስመዝገብ ነው፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• ከወገብ በላይ ያለውን የሰዉንት ክፍል ወደ ፊት በማዘንበል ፈጣን የእግር


እንቅስቃሴ በመጠቀም እጅን ከእግር ጋር በማቀናጀት በመካከለኛ ፍጥነት እስከ
ሃያ አምስት(25) ሜትር ድረስ መለማመድ፣

• በፍጥነት ሩጫ እስከ ሃምሳ (50) ሜትር ድረስ መለማመድ

• ይህንን እንቅስቃሴ ሰልሳ (60) ሜትር ድረስ በጥንድ በመሆን እርስ በርስ
እየተፎካከሩ በፍጥነት መሮጥና መለማመድ

• የእንቅስቃሴውን ርቀት በመጨመር ከስልሳ(60) እስከ ሰባ (70) ሜትር አራት


አራት በመሆን በፍጥነት ሩጫ መወዳደር

ለሰዓት መሮጥ
ለሰዓት መሮጥ የአካል ብቃት ደረጃን ለመጠበቅ፣ በሩጫ ደሰታን ለመጨመር፣ ያማረ

ጊዜን ለማሳለፍ እና በተቀመጠልን ሰዓት ረጅም ርቀትን ለመሸፈን ይጠቅማል፡፡

ተግባር 3 በዝቅተኛ ፍጥንት ሳያቋርጡ ከ50 እስከ 60 ሰከንድ መሮጥ

ዋናው ዓለማ፡- በተሰጠው ሰዓት ምን ያህል ርቀት መሮጥ መቻል ነው፣

• ለሰዓት መሮጥ የእግር አነሳስ፣ የእርምጃ ስፋት እና የእጅ ውዝዋዜ መሠረታዊ


የአሯሯጥ ስልቶች ናቸው፡፡

56
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ስዕል 4.2 (በዝቅተኛ ፍጥንት ሳያቋርጡ ከ50 እስከ 60 ሰከንድ መሮጥ)

የአሰራር ቅደም ተከተል

• በመምህራችሁ በመታገዝ በሁለት ረጅም መስመሮች መሰለፍ፣

• በቆማችሁበት ቦታ ላይ ለ30 ሰከንድ ሳታቋርጡ የእጅና የእግር ቅንጅት በመጠቀም


መሮጥ

• በራሳችሁ አሯሯጥ ዘዴ ለ35 ሰከንድ በዝቅተኛ ፍጥነት ሳታቋርጡ መሮጥ፣

• መምህሩ/ሯ ምልክት ሲያሳይ/ስታሳይ ትክክለኛ የአሯሯጥ ስልትን በመጠቀም


በዝግታ ለ40 ሰከንድ መሮጥ፣

• በመምህሩ/ሯ እገዛ እሰከ 50 ሰከንድ ሳታቋርጡ በዝቅተኛ ፍጥነት መሰረታዊ


የአሯሯጥ ሂደቶችን በመከተል መሮጥ፣

• ሁለት ሁለት ሆናችሁ በመሮጥ አንዱ ሲሰራ ሌላው እየተከተለ ስህተቱን በማረም
ለ50 ሰከንድ መሮጥ፣

• ሁለት ሁለት በመሆን ትክክለኛ የአሯሯጥ ስልቶችን በመጠቀም ለ60 ሰከንድ


በዝቅተኛ ፍጥነት መሮጥ፣

• ሶስት ሶስት በመሆን ትክክለኛ የአሯሯጥ ስልትን በመጠቀም ለ60 ሰከንድ በዝቅተኛ
ፍጥነት መሮጥ፣

57
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ተግባር 4 በዝቅተኛ ፍጥነት ሳያቋርጡ ከሁለት ደቂቃ እስከ አራት ደቂቃ መሮጥ

ዋናው ዓለማ፡- በተሰጠው ሰዓት ምን ያህል ርቀት መሮጥ መቻል ነው፣

• ለሰዓት መሮጥ የእግር አነሳስ፣ የእርምጃ ስፋት እና የእጅ ውዝዋዜ መሠረታዊ


የአሯሯጥ ስልቶች ናቸው፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል

• በመምህራችሁ በመታገዝ በሁለት ረጅም መስመሮች መሰለፍ፣

• በቆማችሁበት ቦታ ላይ ለአንድ ደቂቃ ሳታቋርጡ የእጅና የእግር ቅንጅት በመጠቀም


መሮጥ

• በራሳችሁ አሯሯጥ ዘዴ ለሁለት(2) ደቀቃ በዝቅተኛ ፍጥነት ሳታቋርጡ መሮጥ፣

• መምህሩ/ሯ ምልክት ሲያሳይ/ስታሳይ ትክክለኛ የአሯሯጥ ስልትን በመጠቀም


በዝግታ ለሶስት(3) ደቂቃ መሮጥ፣

• ሁለት ሁለት ሆናችሁ በመሮጥ አንዱ ሲሰራ ሌላው እየተከተለ ስህተቱን በማረም
ለአራት(4) ደቂቃ መሮጥ፣

• ሶስት ሶስት በመሆን ትክክለኛ የአሯሯጥ ስልትን በመጠቀም ለአራት(4) ደቂቃ


በዝቅተኛ ፍጥነት መሮጥ፣

• የግምገማ ጥያቄዎች

• ትክክለኛ የአሯሯጥ ስልትን በመጠቀም በፍጥነትና በዝግታ የአሯሯጥ ሁኔታውን


ሰርታችሁ አሳዩ?

ማስታወሻ
በተለያዩ ምክንያት መሮጥ የማትችሉ ተማሪዎች ለመምህር በመንገር እንቅስቃሴውን
በሚመቻችሁ ሁኔታ መስራት አለባችሁ፣
በአካቢባያችሁ የሩጫ እንቅስቃሴ በምትሰሩበት ሰዓት ትክክለኛውን የእግረኛ መንገድ
በመጠቀም የትራፊክ አደጋን ከግምት ውስጥ በማስገባት መስራት ይጠበቅባችኋል፡፡

58
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

4.2. ውርወራ
አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ

• በሁለት እጅ ወደፊት ከባድ ዕቃዎችን /medicine ball/ ለመወርወር የላይኛዉን


የሰዉነት አካል አቋቋምን ታሳያላችሁ

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


ውርወራ ለመወርወር መሠረታዊ ነገሮች ምን ምን ናቸው?

ውርወራ የተፈጥሮ እንቅስቃሴ በመሆኑ በየእለቱ የሚከናወን ድርጊት ነው፡፡ ይህ


የተፈጥሮ እንቅስቃሴ በውድድር ጊዜ የሚያካትታቸው አራት የውርወራ ዓይነቶችን
ነው፡፡ እነሱም አሎሎ፣ ዲስከስ፣ ፣ ጦር እና መዶሻ ውርወራ ሲሆኑ በውርወራ
በመሳተፍ የሰዉነት ኃይል፣ ጥንካሬን፣ የመተጣጠፍ ችሎታን ከፍ ያደርጋል፡፡ ሁሉም
የውርወራ ዓይነቶች በጋራ የሚጠይቁት ከህሎት፡-

• የእጅ፣ የእግርና የዓይን ቅንጀት

• የርቀት መጠን

• የጊዜና የኃይል ግንዛቤ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ይህ ርዕስ ትኩረት ያደረገው እነዚህን መሠረታዊ ነገሮች በማዳበር ላይ ነው፡፡ በዚህ


የክፍል ደረጃ ለርቀት መወርወር የሚል የውርወራ እንቅስቃሴ ቀርቧል፡፡

ለርቀት መወርወር
ለርቀት ለመወርወር፡- የእጅና የእግር እንቅስቃሴ

• የሰዉነት አቋቋም

• የውርወራ አቅጣጫዎች

• የአያያዝ መሠረታዊ ክህሎቶች ናቸው፡፡

59
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ተግባር ትናንሽ ክብደት ያላቸውን ኳሶች በርቀት መወርወር

የእንቀስቃሴው ዓላማ፡- ለርቀት መወርወር

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• የኳስ አያያዝ፣ የእጅና የእግር እንቅስቃሴ፣ የሰዉነት አቋቋም የውርወራ አቅጠጫ


እና ርቀት ናቸው፡፡

• በመጀመሪያ በሁለት እጅ ከበድ ያለ ኳስ ወደ ላይ በመወርወር መያዝን መለማመድ፣

• ፊትን ወደ ሚወረወርበት አቅጣጫ በማድረግ መቆምና ኳሱን በሁለት እግር ጭን


መካከል መያዝ፣

• ሁለት እግርን በትከሻ ስፋት በመክፈት ሸብረክ ማለትን እና ጀርባችን ቀጥ


ማደረግን መለማማድ፣

• በሁለት እጅ በትክክል የአያያዝ ስልትን እና የሰዉነት አቋቋም በመጠቀም ኳሱን


ለተወሰነ ርቀት ወደ ፊት በመግፋት መወርወር፣

• ከበድ ያለን ኳስን ራቅ ብሎ ለቆመ ጓደኛ በሁለት እጅ ወደ ፊት በመወርወር


ማድረስ፣

• አንድ እርምጃ በመንቀሳቀስ ከበድ ያለውን ኳስ ለጓደኛ መወርወር፣

• ቀስ በቀስ በሁለት እርምጃ ርቀትን በመጨመር ከበድ ያለ ኳስን ወደ ፊት በሁለት


እጅ ለቆመ ጓደኛ ማድረስ እና መልሶ መቀበል፣

• አራት አራት በመሆን አራት መአዘን በመሥራት በተመሳሳይ ርቀት በመቆም


ከባዱን ኳስ በውርወራ የመጀመሪያው እስከ ሁለተኛው ድረስ፣ ሁለተኛው እስከ
ሶስተኛው፣ ሶስተኛው እስከ አራተኛው በመወርወር የኳሱን ዙረት ካሬ ቅርፅ
እንዲይዝ በማድረግ መለማመድ፣

60
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ስዕል 4.3 ትናንሽ ክብደት ያላቸውን ኳሶች በርቀት መወርወር

የግምገማ ጥያቄ
• ከበድ ያለ ኳስን በርቀት በመወርወር የእጅና የላይኛው የሰዉነት አካል
እንቅስቃሴን አሳዩ?

4.3 ዝላይ
አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• ቁጢጥ ብሎ የመዝለል አስተራረፍን በትክክል ታሳያላችሁ፣

• ከአንድ ቦታ በመቆም ሽቅብ ለመዝለል ትክክለኛዉ የታችኛዉን የሰዉነት


ክፍል አቀማመጥን ታሳያላችሁ፣

• የላይኛዉና የታችኛዉ የሰዉነት እንቅስቃሴን በማቀናጀት ሊያጋጥሙ


የሚችሉ ችግሮችን ትፈታላችሁ፣

61
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


የከፍታ ዝላይ ለመዝለል የምንከተላቸው ሂደቶች ዘርዝሩ?

4.3 የከፍታ ዝላይ


ዝላይ እንደ ሩጫና ውረወራ የተፈጥሮ እንቅስቃሴ ሲሆን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ሰዎች
ማንኛውንም መሰናክል በመዝለል የሚያልፉበት ተግባር ነው፡፡ የዝለይ ክህሎት ለተለያዩ
ስፖረቶች በተለይ ለመረብ ኳስ፣ ለቅረጫት ኳስ ወዘተ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡
፡ ዝላይ በእለታዊ ሕይወታችን ውስጥ ለሚያጋሙን መሰናክሎች የምንወጣበት
የእንቅስቃሴ ክህሎት ነው፡፡ ሁለት የዝላይ ዓይነቶች አሉ እነሱም የርዝመት ዝላይና
የከፍታ ዝላይ በመባል ይታወቃሉ፡፡ በዚህ የክፍል ደረጃ የከፍታ ዝላይ አንድትለማመዱ
ቀርቧል፡፡የዝላይ ሂደቶች የሚባሉት ሩጫ፣ መሬትን መጫን፣ ወደ ላይ የመንሳፈፍ፣
የከፍታውን መሰናክል ማለፍና ወደ መሬት ማረፍ ናቸው፡፡
ተግባር የከፍታ ዝላይ

የእንቅስቃሴው ዓላማ፡- ከፍታን መጨመር እና ሸብረክ አስተራረፍን ማዳበር

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

በብዛት እግር ላይ ትኩረት ያደረገ የሰዉነት ማሟሟቂያ መሥራት፣

በመቆም ወደ ላይ መዝለል በዚህ ጊዜ ወደ ላይ ዘለን ስንመለስ የቁጢጥ አስትራረፍን


መለማመድ

በመቀጠልም ከተወሰነ መንደርደር በኋላ ያለ መሰናክል ወደ ላይ መዝለልን መለማመድ፣

በሁለት አግዳሚ በታሰረ ገመድ ላይ ከፍታው ከ50ሴንቲ ሜትር እሰከ 70 ሴንቲ


ሜትር የሚደርስን ከፍታ መዝለያ ከቆምንበት በመነሳት ማለፍ፣

በሂደት ከሁለት እርምጃ በኃላ የከፍታ መዝሊያ ገመዱን ማለፍን መለማመድ፣

በመንደርደር ከፍታውን ከፍ በማድረግ መዝለልና ወደ መሬት በምንመለስበት ጊዜ


ሽብርክ ማለትን መለማመድ፣

62
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ተግባር 2 በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ከላይ ያሉትን የአሰራር ቅደም ተከተሎች


በመከለስ ከፍታውን እያሳደግን እንቅስቃሴውን መለማመድ

ስዕል 4.4 የከፍታ ዝላይ

ማሰታወሻ
ዝላዩ የሚከናወነው ከሚዘለው አግዳሚ ትይዩ ከሚገኝ ቦታ ላይ ከ50 እስከ 70 ሴንቲ
ሜትር በመራቅ ይሆናል፡፡

የግምገማ ጥያቄ
የከፍታ ዝላይ ከቆምንበት በመነሳት አስተራረፉን ሰርታችሁ አሳዩ?

63
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ማጠቃሊያ
የአትሌቲክስ እንቅስቃሴዎች በአብዛኛው ተፈጥሮአዊ እንቅስቃሴዎች በመሆኑ
ለማንኛውም ዕድሜ ተስማሚ ነው፡፡ የአትሌቲክስ እንቅስቃሴዎች የመሮጥን፣
የመዝለልንና የመወርወርን ክህሎትን የሚያዳብር እነወቅስቃሴ ነው፡፡ ከዚህ
አኳያ የሰዉነትን ብርታት፣ ጥንካሬ፣ የመተጣጠፍ ችሎታና ሰዉነትን አስተባብሮ
የመስራት ብቃት የሚዳብር ነው፡፡

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የሩጫ ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች የተዘረዘሩ


ሲሆኑ የሩጫን ምንነትና ውጤታማነት መከናወን ያለዉ የእንቅስቃሴ ክህሎት
ተብራርተዋል፡፡ ከነዚህም በተጨማሪ የፍጥነት አሯሯጥና የሚያስገኘዉ ጥቅም
ተገጸል፡፡

የመወርወር ብቃትን ለማደራጀት ከባድ ኳሶችን፣ ተመሳሳይ ነገሮችን የመወርወር


እንቅስቃሴዎች እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡

የዝላይ ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች ከመሬት በመመንጠቅና በአየር


ላይ ለመንሳንፈፍ የሚያስችሉ ሁኔታዎች የሚታይባቸዉ ናቸው፡፡ እነዚህ
እንቅስቃሴዎች በዕለት ተዕለት ኑሮሯችን ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚገጥሙ
በመሆናቸው ጥቅማቸው የጎላ ነው ፡፡

ዝላይ ርቀትን ለመሸፈንና ከፍታን ለማስገኘት የሚከናወን ነው፡፡ ለዚህም


እንዲያገለግል ለክፍሉደረጃ የሚመጥን ነው ተብሎ የታመነበት የከፍታ ዝላይ
ላይ የማጠናከሪያ እንቅስቃሴ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

64
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የማጠቃለያ ጥያቄዎች
ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማንበብ ትክከለኛውን መልስ የያዘውን ፊድል ምረጡ

1. ከሚከተሉት ውስጥ የአትሌቲክስ ክፍል ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ውርወራ ለ. ዝላይ ሐ. ሩጫ መ. ወደ ፊት መንከባለል

2. --------- በመም የሚተገበር ተግባር ነው?

ሀ. ውርወራ ለ. ዝላይ ሐ. ሩጫ መ. ሁሉም

3. ሩጫን በፍጥነት ሮጦ ለመጨረስ የሚያስፈልገው የቱ ነው?

ሀ. የሩጫ አነሳስ ሐ. የላይኛው የሰዉነት ሁኔታ

ለ. የእጅና የእግር ቅንጅት መ. ሁሉም

4. የርዝመት ዝላይ ሂደት ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ መሮጥ ለ. ወደ ላይ መነሳት ሐ. ወደ ጎን መነሳት መ.ሁሉም

5. የከፍታ ዝላይ ሂደት የሆነው የቱ ነው?

ሀ መሬትን መጫን ለ.ወደ ላይ መንሳፈፍ ሐ. ወደ መሬት ማረፍ መ.ሁሉም

ለ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ

1. መሠረታዊ የአሯሯጥ ስልቶችን ዘርዝሩ?

2. የዝላይ ሂደቶችን ፃፉ?

3. ከባድ ዕቃን በመወርወር የምናገኘው ጥቅም ጥቀሱ?

65
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ምዕራፍ አምስት
ጅምናስቲክ
መግቢያ
ጅምናስቲክ በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቁት የውድደር ዓይነቶች አንዱ ነው፡፡
ጅምናስቲክ ማለት የተመረጠና የተደራጀ የአካል እንቅስቃሴ ሲሆን በነጠላ፣ በጥንድ
እና በህብረት እንዲሁም በመሳሪያና ያለ መሳሪያ የሚሰራ የእንቅስቃሴ ዓይነት ነው፡
፡ ጅምናስቲክ ሶስት ባህሪያት ሲኖሩት እነሱም ውድድራዊ፣ ትምህርታዊና ህክምናዊ
ባህሪያት ናቸው፡፡ ጅምናስቲክ በጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ውሰጥ የሚሰጠው
ጥቅም ጡንቻዎችን፣ መገጣጠሚያዎችን በተለይ ከወገብ በላይ ያለን የሰዉነት ክፍል
ጥንካሬን በማዳበር ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

በዚህ ምዕራፍ ስር የተለያዩ ክህሎት ተካተዋል፡፡ እነዚህም ያለ መሳሪያ የሚሰሩ


እንቅስቃሴዎች ማለትም ወደ ፊት መንከባለል፣ ወደ ኋላ መንከባለል እና በግንባር
መቆም ናቸው፡፡ በመሳሪያ ላይ የሚሰሩ አግዳሚ ሳጥን ላይ በመዝለል ወደ ፍራሽ
መገልበጥ፣ ፊትን ወደ አግዳሚ ወንበር በማዞር ወደ ኋላ መገልበጥ፣ ከአግዳሚ ወንበር
ላይ መዝለል እንዲሁም የፍሰት ምት ጅምናሲቲክ ቀርበዋል፡፡ ልዩ ፍላጎት ላላቸው
ለእነሱ የሚሆናቸውን ዓይነት እንቅስቃሴዎች በመምረጥ መሳተፍ አለባችሁ፡፡

የመማር ዉጤቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ


• ያለመሳሪያ የሚሰሩ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴን ይሰራሉ፣

• በዝቅተኛ ደረጃ በመሳሪያ የሚሰሩ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎችን ይሰራሉ፣

• የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎችን ጥቅም ይረዳሉ፣

• በመሳሪያ የሚሰሩ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎች የመስራት ግንዛቤን ያሻሽላሉ

66
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

5.1 ያለመሳሪያ የሚሰሩ የጅምናስቲክእንቅስቃሴዎች


አጥጋቢ የመማር ብቃቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• በተለያየ ዘዴ በግምባር ትቆማላችሁ፡፡

• ወደ ኋላ መንከባለልን በትክክል ትሰራላችሁ፡፡

• በተለያየ ሁኔታ ወደፊት ትንከባለላላችሁ፡፡

• ያለመሰሪያ የሚሰሩ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎችን ጥቅም ትገልፃላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


1. ያለ መሳሪያ የሚሰሩ የጅምናስቲክ ዓይነቶችን ጥቀሱ?

2. ያለ መሳሪያ ጅምንስቲክ ያለውን ጥቅም ዘርዝሩ?

ያለ መሳሪያ ጅምናስቲክ፡- ማለት የተቀናጀ፣ የተደራጀ እና የተመረጠ ያለምንም


መሳሪያ እገዛ የሚሰራ የጅምናስቲክ ዓይነት ነው፡፡

ያለ መሰሪያ የጅምናስቲክ ዓይነቶች የሚባሉት ወደ ፊት እና ወደ ኋላ መንከባለል፣


በመንሳፈፍ መንከባለል፣ በግንባር መቆም፣ በትከሻ መቆም፣ በእጅ መቆም፣ በግንባር እና
በእጅ መስፈንጠር ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ የሚሰጡት ጥቅምም የጡንቻ ብርታትና
ጥንካሬን፣ የመተጣጠፍ ችሎታን ለማሻሻል፣ ቅንጅትን ለማዳበር፣ ሚዛን መጠበቅን፣
በራስ የመተማመን ብቃትን ለማዳበር፣ ቅልጥፍናን ለማሻሻል እና የተስተካከለ የሰዉነት
ቁመና እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ በዚህ ክፍል ደረጃ የቀረቡት እንቅስቃሴዎች ወደፊት
መንከባለል፣ ወደኋላ መንከባለልና በግንባር መቆም ናቸው፡፡
ተግባር 1 ወደፊት መንከባለል

ወደ ፊት መንከባለል ያለ መሳሪያ የሚሰራ የጅምናስቲክ ዓይነት ሲሆን የመተጣጠፍ


ችሎታን፣ ቅንጅትን፣ ቅልጥፍናን እና ብርታትን ያሻሽላል፡፡
የአሰራር ቅደም ተከተል
• የሰዉነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ መስራት

• በመጀመሪያ ጉልበትን ወደ ደረት በማምጣት በእጅ ማሰርና ወደ ኃላና ወደ ፊት


መመላለስ፣

67
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ስዕል 5.1 ጉልበትን ወደ ደረት በማምጣት በእጅ ማሰርና ወደ ኋላና ወደ ፊት መመላለስ

• ፍራሽ ላይ በሆድ በመተኛት እጅና እግርን ዘርግቶ መንከባለል፣


• ግማሽ ጉልበትን ማጠፍና እጅን ወደ ፊት መዘርጋት መለማመድ፣

ስዕል 5.2 ወደ ፊት መንከባለል እግር በግማሽ ማጠፍ ቁጢጥ ማለት

68
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• ሁለት እግርን በሰፊው በመከፈት አንገትን በሁለት እግር መሀል በማስገባት ወደ


ኋላ ለማየት መሞከርና ትከሻን በማስነካት መንከባለል፣ እንቅስቃሴውን ሶስት
ሶስት ጊዜ መለማመድ፣

• በእያንዳንዱ ልምምድ ጊዜ ደብተር በአገጭ በመያዝ ወደ ፊት መንከባለል፣

• በግማሽ ጉልበትን በማጠፍ እጅን ወደ ፍራሽ ማስቀመጥና ቀስ ብለን አንገትን


በሁለት ጭን መሀል በማስገባት ትከሻን መሬት በማስነካት መንከባለል ሁለት ጊዜ
መስራት፣

• በሁለት እግር መሀል ደብተር መያዝ እና ወደ ፊት መንከባለል፣

• በትክክለኛ አቋቋም በመቆም ለአንድ ጊዜ መንከባለልና ወደ ተራ በመመለስ ለሶስት


ጊዜ መደጋገም፣

• በትክክለኛው አቋቋም በመቆም ለሁለት ተከታታይ ጊዜ መንከባለልን በየተራ


ለሶስት ጊዜ ደጋግሞ መስራት፣

• በትክከለኛው አቋቋም በመቆም ለሶስት ተከታታይ ጊዜ መንከባለልን በየተራ ለሶስት


ጊዜ ደጋግሞ መስራት፣

• አቅጣጫ እየቀየሩ ለአራት ተከታታይ ጊዜ መንከባለል፣

• ለጓደኛ ሰርቶ ማሳየት

የአሰራር ስህተት
• ጭንቅላትን መሬት ወይም ፍራሽ በማስነካት መንከባለል፣

• ሰዉነትን በደንብ አለመጠቅለል፣

• ከተንከባለሉ በኋላ ሲነሱ መሬት መጫን ወይም መደገፍ፣

• መስመር ጠብቆ አለመገልበጥ፣

69
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ተግባር 2 ወደኋላ መንከባለል

ወደ ኋላ መንከባለልም ልክ እንደ ወደ ፊት መንከባለል የመተጣጠፍ ችሎታን፣


ቅንጅትን፣ ቅልጥፍናን እና ብርታትን ያሻሽላል፡፡

• የአሰራር ቅደም ተከተል

• በመጀመሪያ እግርን ወደ ደረት በማስጠጋት ማሰርና ወደ ኋላ ተወዛውዞ መመላለስ


ለአምስት ጊዜ መስራት፣

• ወደ ኋላ በመተኛት ወደ ኋላ ተወዛውዞ ከኋላ በኩል በእግር ጣት መሬት ነክቶ


መመለስ፣

• ሽብርክ(ቁጢጥ) ከማለት ወደ ኋላ መሬት ላይ እግር እንደታጠፈ ማረፍና


ተወዛውዞ ተመልሶ ቁጢጥ ማለት፣

• ወደ ኋላ መወዛወዝ፣ ከዚያም በመዳፍ ከትከሻ አጠገብ መሬትን እየነኩ ተመልሶ


ቁጢጥ ማለት፣

• እጅን ትከሻ አካባቢ ወደ ኋላ በመገልበጥ በድጋፍ ወደ ኋላ ተገልብጦ በጉልበት


መሬት መንካት፣

• በራስ ኃይል ተገልብጦ በጉልበት መሬት መንካት፣

• የእጅ ጣትንና መዳፍን በትከሻ በላይ ወደ ውጪ በማመልከት ዳሌ ከራስ ትክክል


ሲሆን ወዲያውኑ በእጅ በመግፋት ተገልብጦ ቁጢጥ ማለት፣

• በመደጋገም ወደ ኋላ ሁለት ጊዜና ሶስት ጊዜ መገልበጥ፣

• ወደ ፊትና ወደ ኋላ በማቀናጀት በመደጋገም መስራት፣

• ትክከለኛውን አሰራር ለጓደኛ ሰርቶ ማሳየት፣

70
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ስዕል 5.3 ወደ ኋላ መንከባለል

የአሰራር ስህተት
• ሁለት እጅን እኩል አለመጠቀም፣

• ኃይልን ወደ አንድ ጎን ማብዛት፣

• ክርንን ትይዩ በማድረግ ፋንታ ወደ ጎን መዘርጋት፣


ተግባር 3 በግንባር መቆም

የሰዉነት አንድ ሶስተኛውን ክብደት በግንባር ላይ ሁለት ሶስተኛውን ደግሞ በአጅ ላይ


እንዲያርፍ በማድረግ ሚዛን የመጠበቅ ችሎታን ማሻሻል ይቻላል፡፡ በግንባር መቆም
በከፍተኛ ደረጃ የሚያዳበረው ሚዛን መጠበቅንና የጡንቻ ጥንካሬን ነው፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል

• እግርን በትከሸ ስፋት ልክ በመክፈት በዚያው ስፋት ፍራሽ ላይ መንበርከክ፣

• ሁለት እጅን ከጉልበት መነሻ በማድረግ ሶስት መዓዘን መስራት

• የሁለቱ እጅ ጫፍ የተገናኘበት ቦታ ግንባርን ማስቀመጥ፣ የቀኝ ጉልበት


የተንበረከከበት ቦታ ቀኝ እጅን ማስቀመጥ፣ የግራ ጉልበት የተንበረከከበት ቦታ
የግራ እጅን ማስቀመጥ፣

• የተበረከከውን ጉልበት እግር ሳይንቀሳቀስ ቀጥ ማድረግ፣

71
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• ቀኝ ክርን ላይ ቀኝ እግርን፣ ግራ ክርን ላይ ግራ እግርን ቀስ አድርጎ መስቀልና


ለ10 ሰከንድ ሚዛን መጠበቅ (እንቅስቃሴው እስኪለመድ ድረስ ደጋግሞ መስራት)

• የላይኛውን እንቅስቃሴ ከሰራችሁ በኋላ ሁለት እግርን በሰው ድጋፍ ከከርን ትንሽ
ወደ ላይ ማንሳት፣

• ሁለት እግርን ያለምንም ድጋፍ ከፍ በማድረግና ለ10 ሰከንድ ሚዛን መጠበቅ፣

• ከክርን እግርን በመንሳት በሰው ድጋፍ ቀጥ በማድረግ ለ15 ሰከንድ ሚዛን


መጠበቅ፣

• ያለሰው ድጋፍ በራስ ሙከራ የላይኛውን እንቅስቃሴ መለማመድ፣

• እግር ከመሬት በቀጥታ ወደ ላይ ቀጥ በማድረግ ለ15 ሰከንድ ሚዛን መጠበቅ

ስዕል 5.4 በግንባር መቆም

72
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የአሰራር ስህተት
• በመሀል አናት መሬትን ወይም ፍራሽን መንካት፣

• እጅን ማጥበብ ወይም ማስፋት፣

• እጅን በጭንቅላት ትይዩ ማስቀመጥ፣

• ክብደትን ሙሉ ለሙሉ በግንባር ላይ ማሳተፍ

የግምገማ ጥያቆዎች
1. ወደ ፊት እና ወደ ኋላ መንከባለልን ሰርታችሁ አሳዩ?

2. በግንባር መቆምን በተለያየ ዘዴ ሰርታችሁ አሳዩ?

5.2 በመሳሪያ የሚሰሩ ጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎች


አጥጋቢ የመማር ብቃቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• በመሳሪያ የሚሰሩ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎችን ጥቅም ትገልጻላችሁ፣

• ትክክለኛዉን የመሳሪያ ጅምናስቲክ አጠቃቀምን ተግባራዊ ታደርጋላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


1. የመሳሪያ ጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎችን ጥቀሱ?

2. የመሳሪያ ጅምናስቲክ እንቅስቃሴ ጥቅሞችን ግለጹ?

በመሳሪያ የሚሰሩ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎች የመሳሪያ ጅምናስቲክ አንዱ የጅምናስቲክ


ዘርፍ ሲሆን የተለያዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም በተደራጀ መልኩ የሚሰራ እንቅስቃሴ
ነው፡፡

የመሳሪያ ጅምናስቲክ የሚባሉት፡


• ነጠላ አግዳሚ ዘንግ፡- ተንጠላጥሎ መወዛወዝ፣ ወደፊት መገልበጥ፣

73
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• ጥንድ አግዳሚ ዘንግ፡- የተለያዩ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎችን መስራት

• አግዳሚ ሳጥን፡- የተለያዩ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎችን መስራት

• አግዳሚ ወንበር ላይ ሚዛን መጠበቅ ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

የመሳሪያ ጅምናስቲክ መስራት የሚያስገኛቸው ጥቅሞች የመውጣት፣ የመንጠላጠል፣


የመወዛወዝና የመሳሪያ አያያዝን ለማሻሻል፣ድፍረትን እና በራስ መተማመንን
ለማዳበር፣የላይኛው የሰዉነት ክፍልን ለማጠንከር ይጠቅማል፡፡ በዚህ የክፍል ደረጃ
የቀረበላችሁ ክህሎት፡-

1. ከአግዳሚ ሳጥን በመዝለል ወደ ፍራሽ መገልበጥ፣

2. ፊትን ወደ አግዳሚ ወንበር በማዞር ወደ ኋላ መገልበጥና

3. ከአግዳሚ ወንበር ላይ መዝለል ናቸው፡፡


ተግባር 1 ከአግዳሚ ሳጥን/bar box/በመዝለል ወደ ፍራሽ መገልበጥ፣

ከአግዳሚ ሳጥን በመዝለል ወደ ፍራሽ መገለልበጥ በዋናነት በራስ የመተማመን


የሚያሻሽል፣ ድፍረትን የሚያዳብር፣ የእግር አስተራረፍን እና የሰዉነት መቀናጀትን
የሚጠይቅ የእንቅስቃሴ ዓይነት ነው፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል

• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት፣

• ያለምንም መሳሪያ ከቁጢጥ በሁለት እግር በመነሳት መዝለልና ሸብረክ ብሎ


ማረፍ

• አግዳሚ ሳጥን ላይ በእርምጃ መውጣት እና መውረድ፣

• አግዳሚ ሳጥን ላይ በመውጣት በሁለት እግር በመዝለል ከሳጥን መውረድና


ጉልበትን ሸብረክ አድርጎ የሰዉነት ክብደትን፣ ጉልበትን አጥፎ ተቆጣጥሮ መሬት
ላይ ማረፍ፣

• ከአግዳሚ ሳጥን ላይ ሸብረክ ብሎ ወደ ፍራሽ ዘሎ ማረፍ፣

• ከአግዳሚ ሳጥን ላይ ሸብረክ ብሎ ወደ ፍራሽ ዘሎ ማረፍና የእጅን መዳፍ ፍራሽ


ላይ ማሳረፍ(ለሁለት ጊዜ)

74
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• አግዳሚ ሳጥን ላይ ሸብረክ ብሎ ወደ ፍራሽ በፊት የእግር መዳፍ ዘሎ ማረፍ እና


የእጅን መዳፍ በመጠቀም ወደ ፊት በቀስታ መንከባለል (ለሶስት ጊዜ)

• አግዳሚ ሳጥን ላይ ሸብረክ ብሎ ወደ ፍራሽ በፊት የእግር መዳፍ ዘሎ ማረፍ እና


የእጅን መዳፍ በመጠቀም ፈጠን ብሎ ወደ ፊት መንከባለል(ለሶስት ጊዜ)

ስዕል 5.5 ወደ አግዳሚ ሳጥን ሲዘል

የግምገማ ጥያቄ
ከአግዳሚ ሳጥን ላይ በመዝለል ትክከለኛ አሰተራረፍን አሳዩ?
ተግባር 2 ፊትን ወደ አግዳሚ ወንበር በማዞር ወደ ኋላ መገልበጥ፣

ይህ እንቅስቃሴ መሳሪያ ላይ የሚከናወን ሲሆን በራስ መተማመንን፣ ድፍረትን፣ ሚዛን


መጠበቅን ጥንካሬን መተጣጠፍንና ቅልጥፈናን የሚያዳብር የጅምናስቲክ ዓይነት ነው፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል

• አግዳሚ ወንበር ላይ በመውጣት በጀርባ መተኛት

• አግዳሚ ወንበር ላይ ጉልበትን ወደ ደረት በመያዝ ወደ ኋላ እና ወደ ፊት


መወዛወዝ

• አግዳሚ ወንበር ላይ ሸበረክ በማለት እጅን ወደ ኋላ በመገልበጥ በድጋፍ ተገልብጦ

75
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

በጉልበት ወንበር መንካት

• በራስ ኃይል ወደ ኋላ ተገልብጦ በጉልበት ወንበር መንካት አለበት

• የእጅ ጣትንና መዳፍን ከትከሻ በላይ ወደ ውጪ በማመልከት ዳሌ ከራስ ትክክል


ሲሆን ወዲያውኑ በእጅ በመግፋት ተገልብጦ ወንበሩ ላይ ቁጢጥ ማለት፣

የግምገማ ጥያቄዎች
1. ከአግዳሚ ወንበር ወደኋላ መገልበጥን አሳዩ?

2. የእንቅስቃሴውን ጥቅም ምን እንደሆነ ግለፁ?


ተግባር 3 ከአግዳሚ ወንበር ላይ መዝለል፣

ከአግዳሚ ወንበር ላይ ለመዝለል ማተኮር ያለብን ወንበር ላይ አቋቋም፣እጅን ወደ ላይ


መዘርጋት፣ ሰፋ ባለ ሁኔታ መዝለል፣ ቀጥ ብሎ ወደ ፊት ለፊት መመልከት፣ ሰፋ
ባለ ሁኔታ ማረፍ እና እጆችን ወደ ጎን አግድም መዘርጋት ናቸው፡፡

የእንቅስቃሴ ዓላማ፡- በራስ መተማመን፣ ድፍረትን ማዳበር እና ሚዛን መጠበቅን


ማሻሻል ናቸው፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል


• መሬት ላይ በመሆን እጅን ወደ ላይ ማድረግንና ወደ አግድም መዘርጋትን
መለማመድ፣
• አግዳሚ ወንበር ላይ በመውጣት እግርን በትከሻ ስፋት ልክ በማድረግ እጅን ወደ
ላይ መዘርጋትን መለማመድ፣
• አግዳሚ ወንበር ላይ በመቆም ሰፋ ባለ ሁኔታ መዝለልና ማረፍ፣
• አግዳሚ ወንበር ላይ በመቆም ሰፋ ባለ ሁኔታ መዝለል፣ ማረፍ እና እጅን ወደ
አግድም መዘርጋት፣

76
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ስዕል 5.6 ከአግዳሚ ወንበር ላይ ዘሎ ወደ መሬት ማረፍ

የግምገማ ጥያቄ
ከአግዳሚ ወንበር ላይ መዝለል በትክክል ሰርታችሁ አሳዩ?

5.3 ተከታታይነት ያከው የጅምናሰቲቸ እንቅስቃሴ


ጅምናስቲክ
አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኃላ፡-

• ትክክለኛ ተከታታይነት ያለው የጅምናስቲክ እንቅስቃሴን ተግባራዊ


ታደርጋላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


ተከታታይነት ያለው የጅምናስቲክ ባህሪያትን ጥቀሱ?

ተከታታይነት ያለው ጅምናስቲክ በሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ውስጥ መሰጠቱ


ሚዛን መጠበቅን፣ የሰዉነት ፍሰት ምትንና የኪነ-ጥበብ ስሜትን እንድትረዱ ለማስቻል
ነው፡፡

77
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ተከታታይነት ያለው ጅምናስቲክ በሙዚቃ የፍሰትምተ ምት በመታገዝ እንደ መሸብለል፣


መጠማዘዝ፣ መሳሳብ እና ተመጣጣኝና ተመጣጣኝ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎችን በኳስ፣
በሪቫን ጨርቅ፣ በክብ ቦንዳ ብረት፣ የሚወረወር ዱላና ገመድ የሚተገበር የጥበብ
ዓይነት ነው፡፡ የፍሰት ምት ጅምናስቲክ በአለም አቀፍ ውድድር ላይ ሴቶች ብቻ
የሚወዳደሩት የወድድር ዓይነት ነው፡፡

መሳሳብ የአካል ክፍሎችን ከሰውነት ማዕከል ማራቅ ወይም መገጣጠሚያን እስከሚችለው


ድረስ ማንቀሳቀስ፣ እንቅስቃሴውን ለመጨመር እና ለመዘርጋት ማሳሳብ አስፈላጊ
ነው:: ትንሽ የህመም ስሜታ እስከሚሰማው ድረስ በተቻለ መጠን መጎተት፣ ሰዉነትን
ዘና ማድረግ ማሳሳብን ያሻሽላሉ፡፡

መጠማዘዝ የተመረጠውን የሰዉነት ክፍል በራሱ ዘንግ ዙሪያ ማሽከርከር ነው፡፡ በተቻለ
መጠን የሰዉነት ክፍልን በማጠማዘዝ በሌላው አቅጣጫ ማዞር እና ደጋፊ ክፍሎችን
አጥብቆ መያዝ መጠማዘዝን ያሻሽላል፡፡
ተግባራት

• በሆድ በመተኛት በእግር የኋላ ጭንቅላትን መንካት

• በሆድ በመተኛት ባሉበት መዋኘት

• ጉልበትን በግንባር መንካትና መመለስ

• በእጅ የእግር ጣትን መንካትና መመለስ

• አንገትን ማሽከርከር

• በመቀመጥ አንድ እግርን ወደ ላይ ማንሳት

• ቀጥ ባለ መስመር በእግር ጣት ሚዛን እየጠበቁ መንቀሳቀስ

ከላይ የተጠቀሱ እንቅስቃሴዎችን ቢያንስ ሶስት ክፍለ ጊዜ በመጠቀም በሙዚቃ ምት


እንቅስቃሴዎችን አቀናጅቶ በመስራት መለማመድ

78
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የምዕራፉ ማጠቃለያ
ጅምናስቲክ ማለት የተመረጠ የተደራጀ የአካል እንቅስቃሴ ሲሆን በነጠላ፣
በጥንድ እና በህብረት እንዲሁም በመሳሪያና ያለ መሳሪያ የሚሰራ የእንቅስቃሴ
ዓይነት ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የተጠቃለሉት፣ መሠረታዊ የጂምናስቲክ
እንቅስቃሴዎች ናቸው፡፡ የጂምናስቲክ እንቅስቃሴ ዘርፎች በጣም ብዙ ናቸው፡፡
ሆኖም በዚህ ክፍል ደረጃ እንደሚመጥኑ ታምኖባቸው የተመረጡት ያለመሳሪያና
በመሣሪያ ላይ እንዲሁም የፍሰት ምት ጅምናስቲክ የሚከናወኑ ተግባራት
ናቸው፡፡

ያለ መሳሪያ ጅምናስቲክ የሚያስገኛቸው ጥቅሞች የጡንቻ ብርታትና ጥንካሬን፣


የመተጠጣጠፍ ችሎታን ፣ቅንጅትንና ሚዛን መጠበቅን ወዘተ የመሳሰሉትን
ለማሻሻል ይጠቅማል፡፡

የመሳሪያ ጅምናስቲክ የጅምናስቲክ አንዱ ዘርፍ ሲሆን የተለያዩ መሳሪያዎችን


በመጠቀም በተደራጀ መልኩ የሚሰራ እንቅስቃሴ ነው፡፡ የሚያስገኛቸው
ጥቅሞችም የመውጣት፣ የመንጠላጠል፣ የመወዛወዝና የመሳሪያ አያያዝ
ለማሻሻል ድፍረትን እና በራስ መተማመንን ለማዳበር የላይኛው የሰዉነት
ክፍልን ለማጠንከር፣ መተጣጠፍን፣ መገለባበጥንና ብርታትን ለማሻሻል
ቅንጅትን ለማዳበር ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡

79
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የማጠቃለያ ጥያቄዎች
ሀ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጣቸው አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ
የያዘውን ፊደል ምረጡ

1. ከሚከተሉት ወስጥ የጅምናስቲክ ጥቅም የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ጡንቻዎችን ማጠንከር ሐ. የመሳሪያ አያያዝን ማሻሻልመሳሪያንክ

ለ. የመተጣጣፍ ችሎታን ማዳበር መ. ሁሉም መልስ ናቸው

2. ከሚከተሉት ወስጥ ነፃ ጅምናስቲክ እንቅስቃሴ ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. በግንባር መቆም ሐ. ወደ ፊት መንከባለል

ለ. አግዳሚ ወንበር ላይ ወደ ኋላ መንከባለል መ. ሁሉም

3. በግንባር መቆም ላይ የአሰራር ስህተት የሆነው የቱ ነው?

ሀ. በመሀል አናት መቆም ሐ. እጅን ማጥበብ

ለ. እጅን ከጭንቅላት ትይዩ ማድረግ መ. ሁሉም

4. የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ በምን ሊሠራ ይችላል?

ሀ. በጥንድ ሐ. በቡድን

ለ. በነጠላ መ. ሁሉም መልስ ናቸው

5. በከፍተኛ ደረጃ ሚዛን የመጠበቅ ችሎታን የሚጠይቅ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ የቱ


ነው?

ሀ. በግንባር መቆም ሐ. ወደ ኋላ መንከባለል

ለ. ወደ ፊት መንከባለል መ. ሁሉም መልስ ናቸው

6. ወደ ኋላ መንከባለል የአሰራር ሰህተት የሆነው የቱ ነው?

ሀ. እጅን በትከሻ ልክ መጠቀም ሐ. እጅን ዘርግቶ ሽብርክ ማለት

ለ. ኃይልን ወደ አንድ ጎን ማብዛት መ. ለ እና ሐ መልስ ናቸው፡፡

80
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

7. በግንባር መቆም አንድ ሶስተኛውን የሰውነት ክብደት የሚሆነው በየትኛው የአካል


ክፍል ነው?

ሀ. ግንባር ለ. ጭንቀላት ሐ. ትከሻ መ. ሁሉም

8. የመሳሪያ ጅምናስቲክ እንቅስቃሴ የሆነው የቱ ነው?

ሀ. በግንባር መቆም ሐ. ወደፊት መንከባለል

ለ. አግዳሚ ሳጥን ላይ መዝለል መ. ፍራሽ ላይ ወደ ጎን መንከባለል

9. አግዳሚ ወንበር ላይ ለመዝለል ማድረግ ያለብን?

ሀ. ሰፋ ባለ ሁኔታ መዝለል ሐ. ስናርፍ እጆችን ወደ ጎን መዘርጋት

ለ. ፊት ለፊት መመልከት መ. ሁሉም

10. የመሳሪያ ጅምናስቲክ መስራት በዋናነት የሚያዳበረው የቱ ነው?

ሀ. ድፍረትን ሐ. ፍረሃትን

ለ. በራስ መተማመንን መ. ሀ እና ለ መለስ ናቸው

ለ. የሚከተሉትን ጥያቁዎች መለሱ

1. የመሳሪያ ጅምናስቲከ እንቅስቃሴ ጥቅሞችን ዘርዝሩ?

2. የመሳሪያ ጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎችን ቢያንስ ሶስቱን ዘርዝሩ?

3. ወደ ፊት በመንከባለል ጊዜ የሚሰሩ የአሰራር ስህተቶችን ጥቀሱ?

81
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ምዕራፍ ስድስት
በኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ የማቀበል እና
የመቀበል ክህሎት
መግቢያ
የኳስ ጨዋታዎች መሠረታዊ ክህሎት መማር የሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርትን
አብይ አለማዎች ከግብ ለማድረስ ካለው ጠቀሜታ ባሻገር ትርፍ ጊዜያችንን ጤናማ
በሆነ መንገድ ለማሳለፍ በምንችለው የስፖርት ዓይነት በፍላጎት ተሳታፊ እንድንሆን
ያደርጋል፡፡ ከዚህ ባሻገር የኳስ ጨዋታ አላማዎች ውድድር የሚካሂድባቸው ኳስ
ጨዋታዎች ለመዝናኛነት፣ ጤናን ለመጠበቅ፣ ትርፍ ሰዓትን በጤናማ ቦታ ለማሳለፍ
ወዘተ ይጠቅማሉ፡፡

በዚህ የክፍል ደረጃ በሁሉም የኳስ ጨዋታ ዓይቶች የታወቁ ማቀበልና መቀበል
በሚል ርዕስ ተመርጦ ተካቷል፡፡ ማቀበልና መቀበል የሚዳብረው በአብዛኛው ጊዜ
በጨዋታ መልክ ነው፡፡

ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ባሉ መሰረታዊ ክህሎት


በሙሉ እንደ እቅስቃሴው ሁኔታ በማመቻቸት መሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡

የመማር ዉጤቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ


• በኳስ ጨዋታ ጊዜ መሰረታዊ የማቀበል ክህሎትን ትረዳላችሁ፣

• በመካከላቸዉ ያለዉን መልካም ግንኙነት ታሻሽላላችሁ፣

• በኳስ ጨዋታ ጊዜ ትክክለኛውን የማቀበል ክህሎት ታሳያላችሁ፣

82
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

6.1 የኳ ስአያያዝ
አጥጋቢ የመማር ብቃት፡ ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• የተሻሻለ የኳስ አያያዝ ዘዴ ትሰራላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄ


• የኳስ አያያዝ ዘዴዎችን ጥቀሱ?

ኳስ ለመጫወት የመጀመሪያው ተግባር በትክክል ኳስን መያዝ ነው፡፡ ይህ ተግባር


በቮሊቦል፣ በቅርጫት ኳስና በእጅ ኳስ ጎልቶ ይታያል፡፡ ኳስ በትክክል ለመያዝ የእጅ
እንነቅስቃሴ አቅጣጫ፣ የመጣውን ኳስ መቆጣጠር፣ የእጅ ጣቶች ሁኔታ ዋና ዋናዎቹ
ናቸው፡፡

ኳስ በትክክል ለመያዝ የምንከተላቸው ዘዴዎች


• ኳስን በሁለት እጅ መያዝ

• ኳስን በማየት መያዝ

• ኳሱን ከመያዛችን በፊት እጅን ተዘርግቶ መጠበቅ እና ጣቶችን ማስፋት


አለብን፡፡

• ኳሱን በምንይዝበት ሰዓት በጣቶች እንጂ በመዳፍ መንካት የለበትም፡፡

• ኳሱን ስንይዝ በትክክለኛው መሰረታዊ አቋቋም መሆን አለበት፡፡

የግምገማ ጥያቄ
የእጅ እና የቅርጫት ኳስ ለመጫወት የመጀመሪያው ተግባር ምንድን ነው?

83
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ሰዕል 6.1 የኳስ አያያዝ

6.2 ኳስ በአየር ማቀበል


አጥጋቢ የመማር ብቃቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• የቮሊቦል ክህሎትን ታሳያላችሁ፣

• ኳስን በመቆጣጠር የመቀበልና የማቀበል የተሻሻለ ዘዴ ትሰራላችሁ፣

• በጨዋታ ጊዜ የማቀበል ክህሎትን ተግባራዊ ታደርጋላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄ


ኳስ በአየር ላይ የማቀበል መሠረታዊ ነጥቦች ምንምን ናቸው?

ኳስ በአየር ላይ ማቀበል የመረብ ኳስ ጨዋታ መሠረታዊ ክህሎት ሲሆን በአብዛኛው


የሚተገበረው በጣት ሆኖ ከደረት በላይ የመጣችን ኳስ ለማቀበል ወይም ለመመለስ
የሚጠቅም ክህሎት ነው፡፡ ይህ ክህሎት የተጫዋቹን ትክከለኛነት፣ ኳስን ወደ ተፈለገው
አቅጣጫ ማድረስ እና ኳስ በእጅ በሚገናኝበት ጊዜ በትክክል መተግበርን ይፈልጋል፡፡

84
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

በትክክል ለማቀበል
• እግርን በትከሻ ስፋት ከፍቶ ወይም ሁለት እግርን ትይዩ በማድረግ መቆም

• እጅን ከራስ በላይ ሶስት ጎን መሥራት

• ጣትን ማስፋት (ጣት መታጠፍ የለበትም)

• ከትከሻ በላይ ክንድ ይታጠፋል

• ኳሱን በምናገኝበት ሰዓት እጅ ወደ ላይ ወይም ወደ ፊት መዘርጋት

• ኳስ በምናገኝበት ሰዓት የታጠፈውን እጅ መዘርጋት

• ኳስ ማየት፣ ጣትን እና አውራ ጣትን መጠቀም

• ኳስ የሚነካው የእጅ ክፍል የጣቶች ጫፍ መሆን አለበት

የአሰራር ቅደም ተከተል


• የእጅ እንቅስቃሴ የበዛበት የሰዉነት ማሟሟቂያ መስራት

• ኳስን መወርወርና መቅለብ መለማመድ፤ በተደጋገሚ ጊዜ መለማመድ

• ኳስን ወደ ላይ በመወርወር ሲነጥር ከጉልበት ሽብርክ በማለት በጣት መያዝ

• ኳስን በጣት መግፋት እና በጣት መያዝን በዝግታ መለማመድ አምስት ጊዜ


በሁለት ዙር

• ኳስን ከራስ በላይ በመጠኑ በመወርወር በጣት ወደ ላይ መምታትና መያዝ


አምስት ጊዜ በሁለት ዙር

• ኳስን በጣት በመግፍት ለጓደኛ ማቀበል እና በጣት መቀበልን ለሶስት ጊዜ


መለማመድ

• ኳሱን ወደ ግንባር በመወርወር በጣት ለጓደኛ ማቀበል እና በጣትመቀበል

• በመንቀሳቀስ በጣት ኳስ ማንቀርቀብ አምስት አምስት ጊዜ በሁለት ዙር

• በጣት ለጓደኛ በትክክል ማቀበል ሁለት ሁለት በመሆን እስከ አምስት ጊዜ


መቀባበል በሁለት ዙር

85
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ሰዕል 6.2 ኳስን በአየር ላይ በጣት ማቀበል

ማስታወሻ
ከላይ ያለውን እንቅስቃሴ በተደጋጋሚ ጊዜ ስንሰራ እግር እና እጅ መቀናጀት
አለባቸው፡፡

6.2.1- በአነስተኛ ጨዋታ ኳስ በአየር ላይ ማቀበል


• ሁለት ሁለት ሆኖ መቀባበል

• ሶስት ጎን በመስራት ለሶስት ኳሱን መቀባበል

• አራት ጎን በመስራት ለአራት ኳሱን መቀባበል

• ክብ በመስራት ኳሱን እንዳይወድቅ በጣት መቀባበል፤ የወደቀበት ወይም በትክክል


ያላቀበለ ከጨዋታው ውጪ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ መንገድ በአነስተኛ ሜዳ ላይ ገመድ በመዘርጋት ሶስት ሶስት በመሆን


በጣት መጫወት

86
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የግምገማ ጥያቄ
• ትክክለኛ ኳስ በአየር ላይ የማቀበል ዘዴን በመተግበር ሰርታችሁ አሳዩ?

6.3 በክንድ ኳስ ማቀበል


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-
• ኳስን በመቆጣጠር የመቀበልና የማቀበል የተሻሻለ ዘዴ ትሰራላችሁ፣

• ኳስን በተለያየ የማቀበል እንቅስቃሴ ጊዜ ሲሳተፉ ኃላፊነት የተሞላበት


የግንኙነትና ትብብር ክህሎትን ታሳያላችሁ፣

• በጨዋታ ጊዜ የማቀበል ክህሎትን ተግባራዊ ታደርጋላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


ኳስን በክንድ በትክክል ለማቀበል ወይም ለመመለስ መሠረታዊ ነጥቦችን አብራሩ?

በክንድ ኳስ የማቀበል ዘዴ
ከወገብ በታች ወይም ዝቅ ብሎ የመጣን ኳስ እና ፈጣን እና ጠንካራ ኳስን ለመመለስ
ወይም ለማቀበል የሚጠቅም ክህሎት ነው፡፡

በክንድ ማቀበልን በትክክል ለመሥራት


• አንዱን እግር ከሌላው ማስቀደምና ጉልበትን አጠፍ አድርጎ ከደረት ቀና ብሎ
መቆም፣

• አንድ እጅን ጨብጦ በመያዝ የሁለተኛውን እጅ አራት ጣቶችን በተጨበጠው እጅ


ላይ በመደረብ ሁለቱን አውራ ጣቶች ትይዩ በማድረግ መያዝ

• ኳስ በክንድ በሚመታበት ጊዜ ኳሱ ማረፍ ያለበት ከእጅ መታጠፊያ በላይና


ከክርን በታች ባለው የእጅ ክፍል መሆን አለበት

• አጅና እግር ከኳስ አቅጣጫ ጋር የተወሰነ ወደ ላይ መነሳትና ዓይናችን ወደ ኳስ


ማተኮር አለበት

87
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ስዕል 6.3 ኳስን በክንድ ማቀበል

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• ኳስ ወደ ላይ ለራስ በመወርወር መሬት ሳይነካ አንድ ጊዜ ብቻ ወደ ላይ መምታት


(ከአንድ ወደ ሁለት ከሁለት ወደ ሶስት ማሳደግ)

• ጓደኛ የወረወረውን ኳስ በክንድ ሰስት ጊዜ መምታት

• ኳስን በክንድ እየተንቀሳቀሱ እስከ አምስት ጊዜ ማንቀርቀብ

• ሁለት ሁለት ሆናችሁ በተወሰነ ርቀት ላይ በመቆም ኳስ በክንድ መቀባበል፡፡

• ኳስን በማሳጠርና በማስረዘም ለሁለት በክንድመጫወት

የግምገማ ጥያቄ
ትክክለኛ በክንድየማቀበል ዘዴን በመተግበር ሰርታችሁ አሳዩ?

88
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

6.3.1- በአነስተኛ ጨዋታ በክንድ ኳስ ማቀበል


የጨዋታው ዓላማ፡- በክንድ የመቀበልና የመመለስ ክህሎትን ለማሻሻል

• የላይኛውን እንቅስቃሴ በመከለስ ሁለት ሁለት ሆነው በክንድ መቀባበል

• በሁለት ሰልፍ ፊት ለፊት በመሰለፍ ኳስ በክንድ በመመለስ ኳስ ወደ ሄደችበት


አቅጣጫ በመሮጥ መሰልፍ፤

• አምስት በመሆን አራት ማዕዘን በመስራት ኳስን በክንድ ለጓደኛ እየሰጡ ወደ


ሰጡበት መሄድ እና ከኋላ መሰለፍ (ኳሱ የሚጀምርበት ማዕዘን ላይ ሁለት ሰው
መሆን አለበት) ለአስር ደቂቃ

• በክብ በመሆን ኳስ ሳይወድቅ በክንድ በመቀባበል መጫወት ለአስር ደቂቃ

• በአነስተኛ ሜዳ ገመድ ወይም መረብ በመዘርጋት ሶስት ሶስት ሆኖ በክንድ


መጫወት

የግምገማ ጥያቄ
• ኳስ በክንድ በመጫወት ያገኛችሁት ጥቅም ምንድን ነው?

6.4 ኳስ ማንሳት እና ማቀበል


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• ኳስን ማንሳትና ማቀበል በተሻለ ዘዴ ትሰራላችሁ፣

• በጨዋታ ጊዜ የሌሎችን ሀሳብ በመቀበል የኃላፊነት ሚና መወጣትን ታሳያላችሁ፣

• በጨዋታ ጊዜ የማንሳት ክህሎትን ተግባራዊ ታደርጋላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


ኳስ ማንሳትና ማቀበል ዓላማው ምንድን ነው?

በትክክል ኳስን ለማንሳት መሠረታዊ ነገሮችን ግለፁ?

89
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ኳስ ማንሳትና ማቀበል በመረብ ኳስ ጨዋታ አንዱ ክህሎት ሲሆን ለሚመታው


ወይም ለሚቀበለው ተጫዋች ኳሱን በትክክል አመቻችቶ የመስጠት ዘዴ ነው፡፡

ማቀበል ደግሞ ከላይ እንደተጠቀሰው ሁለት ዓይነት ነው፡፡ ኳስ ማንሳትና ማቀበል


በሁለቱም የማቀበል ዘዴ የሚቻል ሲሆን በአብዛኛው ጊዜ ግን የምንጠቀመው እና
ውጤታማ የመምንሆነው በጣት ማነሳትና ማቀበል ነው፡፡ አንዳንዴ ግን ኳሱ ዝቅ ብሎ
ሲመጣ በክንድ ማንሳትና ማቀበል ይቻላል፡፡

ስዕል 6.4 ኳስን ማንሳት እና ማቀበል

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• ያለ ኳስ ትክክለኛ በጣት የማቀበል የሰውነት ሁኔታን እጅና እግርን በማቀናጀት


መለማመድ፣

• እጅን ከራስ በላይ ሶስት ጎን በመስራት መዘርጋትና ማጠፍን መለማመድ፣

• ኳሱን ወደ መሬት በማንጠር ሲመለስ በጣት ወደ ላይ ማንሳት፣

• ኳሱን ከጓደኛ በመቀበል በትክክል በጣት ወደ ላይ ቀጥ አድርጎ ማንሳት፣

90
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• ትክሻን ከግድግዳ ትይዩ ወይም ከመረብ ትይዩ በማድረግ ኳሱን በጣት ግድግዳ
ወይም መረብ እንዳይነካ ቀጥ አድርጎ ማንሳትና በመደጋገም መለማመድ፣

• ልክ በጣት እንደተለማመዳችሁ በክንድ ኳሰ ማንሳትን መለማመድ፣

6.4.1- በአነስተኛ ጨዋታ ኳስን ማንሳትና ማቀበል


• ኳስን በጣት የማቀበል ዘዴን በመከለስ ሶስት ጎን በመስራት ለሶስት ኳሱን በየተራ
ማንሳት፣

• አራት ጎን በመሠራት ለአራት ኳሱን በየተራ ማንሳት

• ክብ በመስራት ኳሱን እንዳይወድቅ በጣት ማንሳት፤ የወደቀበት ወይም በትክክል


ያላቀበለ ከጨዋታው ውጪ ይሆናል፡፡ኳመስራትልስle

• በተመሳሳይ መንገድ በአነስተኛ ሜዳ ላይ ገመድ በመዘርጋት ሁለት ሁለት በመሆን


በጣት በማንሳት መጫወት፡፡

የግምገማ ጥያቄ
ኳስን ማንሳትና ማቀበልን ሰርታችሁ አሳዩ?

6.5 በዉስጥ የጎን እግር ኳስን ማቀበል


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• ኳስን በተለያየ የማቀበል እንቅስቃሴ ጊዜ ሲሳተፉ ኃላፊነት የተሞላበት


የግንኙነትና ትብብር ክህሎትን ታሳያላችሁ፣

• በጨዋታ ጊዜ የማቀበል ክህሎትን ተግባራዊ ታደርጋላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


በየትኛው የእግር ክፍል ኳስ መምታት ይቻላል?

ኳስን በውሰጥ የጎን እግር የማቀበል ጥቅሞችን ግለፁ?

91
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

በእግር ኳስ ጨዋታ ኳስ በውስጥ የጎን እግር መምታት በብዛት ጥቅም ላይ ከሚውሉት


የምት ዓይነቶች አንዱ ሲሆን ዒላማውን ጠብቆ ኳስ ለመምታት በጣም አመቺ የሆነ
የምት ዓይነት ነው፡፡ ይህ የማቀበል ዘዴ ቅርብ ላለ ጓደኛ ለማቀበልና ብዙ ጊዜ የፍፀም
ቅጣት ምት ለመምታት የሚያገለግል ነው፡፡ ምቱን በአግባቡ ለማከናወን፡-

1. የመቺው እግር መሰረታዊ አቋቋም

2. የሰዉነት አቋቋም

3. የመቺው እግር እንቅስቃሴ ወሳኝነት አላቸው፡፡

በዚህ መሠረት የመቺው እግር ጣቶች ከኳሷ በፊተኛው የሰዉነት ክፍል ትይዩ በመሆን
ከቆመ በኋላ መቺው የእግር ጫማውን ወደ ውጪ በማዞር ወደ ኋላ ተወስዶ ወደ
ፊት በመምታት በኳሷ አማካይ የሰውነት ክፍል ላይ ኃይል በማሳረፍ የሚከናወንበት
ተግባር ነው፡፡

ውጤታማ የሆነ ምት ለመምታት ከላይ የተዘረዘሩት መሠረታዊ ክህሎቶችን በአግባቡ


በመጠቀም መምታት አለብን፡፡ ሆኖም የመቺው እግር ኳሱን ሲመታ በተስተካከለ
ፍጥነት ኳሱ ከእግሩ እስኪርቅ ድረስ መሸኘት አለበት፡፡ ኳስ በውስጥ የጎን እግር
በሚመታበት ጊዜ የውስጥ የጎን እግርን ኳሱ ሙሉ ለሙሉ መንካት አለበት፡፡

ስዕል 6.5 ኳስን በውስጥ የጎን እግር ማቀበል

92
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የአሰራር ቅደም ተከተል

• የሰዉነት አቋቋምንና የእግር የመወንጨፍ እንቅስቃሴ ደጋግሞ መለማመድ

• ከቡድኑ አንድ ተማሪ ኳሱን በእጅ በመያዝ እንዳይንቀሳቀስ በመደገፍ የተሰለፉት


ተማሪዎች በመቆም ለአምስት ጊዜ በውስጥ የጎን እግር መንካትን መለማመድ

• ከላይ የተጠቀሰውን እንቅስቃሴ ከአንድ ወይም ከሁለት እርምጃ በኋላ መንካትን


መለማመድ፣

• ሁለት ሁለት በመሆን ከአምስት እስከ ሰባት ሜትር ርቀት ላይ በመቆም በውስጥ
የጎን እግር በመምታት መለማመድ

• ሁለት ሁለት በመሆን የምትንከባለልን ኳስ በተከታታይ ወይም ሳታቆሙ በውስጥ


የጎን እግር መምታትን መለማመድ፣

• ክብ፣ ረድፍ ወይም ሶስት ማዕዘን ወዘተ… በመስራት በውስጥ የጎን እግር እየመቱ
መቀባበልን መለማመድ፣

• የምትንከባለልን ኳስ በውስጥ የጎን እግር ወደ ግብ መምታትን መለማመድ

የግምገማ ጥያቄ
ኳስን በውስጥ የጎን እግር በትክክል ወደ ዒላማ አመታት በመስራት አሳዩ?

6.6 በዉጭየጎንእግርኳስንማቀበል
አጥጋቢ የመማር ብቃቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• ኳስን በመቆጣጠር ማቀበልን በተሻሻለ ዘዴ ትሰራላችሁ፣

• ኳስን በተለያየ የማቀበል እንቅስቃሴ ጊዜ ሲሳተፉ ኃላፊነት የተሞላበት


የግንኙነትና ትብብር ክህሎትን ታሳያላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄ


በውጭ የጎነ እግር ኳስን ለማቀበል መሰረታዊ ነገሮች ምን ምን ናቸው?

93
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ይህ ዓይነት ምት የሚከናወነው በውስጥ እግር ለመምታት አሰቸጋሪ ሆኖ ሲገኘ ነው::


ምቱ የሚከናወነው በውስጥ የጎን እግር መምታት ላይ ያለውን መሰረታዊ አቋቋም
የተጠበቀ ሆኖ የእግር ጣቶች ወደ ወስጥ በማዞር የሚከናወን ነው፡፡ ኳሱን በውጪ
የጎን እግር መምታት የሚጠቅመው ኳሱን በአጭር ለጓደኛ ለማቀበል ነው፡፡ ምቱን
በአግባቡ ለማከናወን፡-

• ኳሷ መሬት ከተቀመጠች በኋላ እግር ከኳሱ በመጠኑ ራቅ በማለት፣

• ከኳሷ የኋለኛውን ሰዉነት ክፍል ትይዩ በማድረግ የእግር ጣቶች በሚያርፉበት


ሁኔታ ተደርጎ የመቺው የእግር ጫማ ወደ ውስጥ ተጠማዝዞ በጫማው የውጪ
ክፍል በሚደረግ ንክኪ ኳሷ የምትመታበት ሁኔታ ነው፡፡

• ሰዉነት ወደ ፊት ዘንበል ማለት ይኖርበታል፡፡

ሰዕል 6.6 በውጭ የጎን እግር ኳስን ማቀበል


የአሰራር ቅደም ተከተል

• የሰዉነት ማሟሟቂያ በሚገባ መስራት

• ያለ ኳስ በውጭ የጎን እግር የአመታት ሁኔታን በመከተል የቀኝ እና የግራ እግር


ተራ በተራ ማወናጨፍ፣

• የቆመ ኳስን በውጭ የጎን እግር በሁለቱም እግር ተራ በተራ ነክቶ መመለስ

94
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• የቆመን ኳስ በውጭ የጎን እግር ከአንድ እርምጃ በኋላ ማቀበል (በቀኝና በግራ
እየቀያየሩ ማቀበል)

• ከሶስት እርምጃ በኋላ የቆመ ኳስን በውጭ የጎን እግር ተንደርድሮ ማቀበል
(በቀኝና በግራ እየቀያየሩ ማቀበል)

• ከጓደኛ የተሰጠችን ኳስ በውጭ የጎን እግር ማቀበል (በቀኝና በግራ እየቀያየሩ


ማቀበል)

• የቆመ ኳስን ከስድሰት እስከ ስምንት ሜትር ርቀት ወደ አለው ጓደኛ ወይም
ዒላማ ኳስን በውጭ የጎን እግር ማቀበል (በቀኝና በግራ እየቀያየሩ ማቀበል)

• ከጓደኛ የመጣን ኳስ ከስድሰት እሰከ ስምንት ሜትር ርቀት ላለ ጓደኛ ማቀበል


(በቀኝና በግራ እየቀያየሩ ማቀበል)

• ክብ፣ ረድፍ ወይም ሶስት መዓዘን ወዘተ በመስራት በውጭ የጎን እግር እየመቱ
መቀባበልን መለማመድ፣

የግምገማ ጥያቄ
ኳስን በውጭ የጎን እግር ማቀበልን የአሰራር ሁኔታን በመግለፅ ሰርታችሁ
አሳዩ?

6.7 በአነስተኛ ጨዋታ ጊዜ በውስጥ እና በውጭ


የጎን እግር አጨዋወት
አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• በጨዋታ ጊዜ የማቀበል ክህሎትን ተግባራዊ ታደርጋላችሁ፣

• በአዝናኝ ጨዋታ ጊዜ ተማሪዉ ለቡድኑ በሚያደርገው አሰተዋጽኦ


ትዝናናላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


በውስጥና በዉጭ የጎን እግር ጨዋታ ኳስን በማቀበል አንድነታቸውና
ልዩነታቸውን ግለፁ?

95
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ተግባር 1 መሀል ባልገባ

የጨዋታው ዓላማ ፡- በውሰጥና ውጭ የጎን እግር ኳስ የማቀበልን ክህሎት ማሻሻል


የአሰራር ቅደም ተከተል

• ስድስት ስድስት በመሆን መመዳደብና የመጫወቻ ከልል እንደ ቁጥራችሁ መጠን


መሥራት፣

• አንድ ሰው በእጣ መሀል ይገባል አንድ ሰው ደግሞ በእጣ ዳኛ ይሆንና አራታችሁ


መሀል የገባው ተጨዋች እንዳይነካባችሁ በውስጥና በውጪ የጎን እግር ብቻ
መቀባበል፡፡

• ከሁለቱ የጎን እግር ውጭ የነካ ተጨዋች እና ኳስ የተነካበት ከጨዋታው ውጭ


ይሆንና ዳኛ መሀል ይገባል፡፡

• መሀል የነበረው ወደ አራቱ ቡድን ይቀላቀላል፡፡ ይህን ሂደት በመከተል ቢያንስ


ለአስር ደቂቃ መጫወት፡፡
ተግባር 2 በሶስት ክፍት ጎሎች የማስገባት ጨዋታ

የጨዋታው ዓላማ ፡- በውሰጥና ውጭ የጎን እግር ኳስ የማቀበልን ክህሎት ማሻሻል


እና ዒላማ መጠበቅ
የአሰራር ቅደም ተከተል

• ጥንድ ጥንድ በመሆን አምስት ቡድን መመስረት

• በእጣ የሚገቡ አራት ቡድኖችን እና አንድ ጥንድ ዳኛ መለየት(ለአራቱ ጥንደች


አንድ አንድ ጎል መስጠት)

• በውስጥና በውጭ የጎን እግር እየተቀባበሉ ከሶስቱ ክፍት ወደ ሆነው ጎል ማስገባት

• የገባበት ጥንድ ወይም ከሁለቱ የጎን እግሮች ውጪ የተጫወተ ከጫወታው


ውጭ ይሆንና ይዳኛል፣ ዳኛ የነበረው ተጨዋች ይሆናል፡፡ ይህን ሂደት በመከተል
ቢያንስ አስራ ሁለት ደቅቃ መጫወት፣

የግምገማ ጥያቄ
ከላይ ባሉት ሁለት ጨዋታዎች የተሰማችሁን ስሜት ግለፁ? በጨዋታው ምን
ሚና ነበራችሁ? ምንስ ጥቅም አገኛችሁ?

96
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

6.8 ኳስ በደረት ማቀበል


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• ኳስን በደረት ትይዩ በመቆጣጠር የመቀበል፣የመያዝና የማቀበል የተሻሻለ


ዘዴ ትሰራላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


1. ኳስን በደረት ትይዩ የማቀበል ዘዴ በየትኛው የጨዋታ ዓይነት ጎልቶ
ይታያል?

2. የተሻለ በደረት የማቀበል ዜዴን ለመስራት መተኮር ያለብን ዋና ዋና ነገሮችን


ዘርዝሩ?

ኳስ በደረት ትይዩ የማቀበል ዘዴ በቅርጫት ኳስ ጨዋታ ጎልቶ የሚታይ የማቀበል


ዘዴ ነው፡፡ ይህ የማቀበል ዘዴ ቅርብ ላለ ጓደኛ ለማቀበል የሚጠቅም ሲሆን ፈጣን
የማቀበል ዘዴ ነው፡፡ ኳስ በደረት ትይዩ ለማቀበል ዋና ዋና ነጥቦች ኳስን በጣት
መያዝ፣ ኳስ ደረት አካባቢ ማድረግ፣ ክርንን ቀጥ ማድረግ፣ ኳስን እጅ በመዘርጋት
መሸኘት እና ኳስን ከተቀባዩ ደረት አካባቢ ማድረስ ይጠበቅብናል፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል

• ያለ ኳስ እጅን በመዘርጋትና እግር ወደ ፊትን ወደ ኋላ አንድ ላይ በማድረግ


በማመላለስ ከእግር ጋር አቀናጅቶ መስራት፣

• ኳስን በትክክል በመያዝ ደረት አካባቢ አልሞ መወርወር

• አራት ሜትር ርቀት ላለ ጓደኛ በደረት ትይዩ ማቀበልና መቀበልን መለማመድ

• አራት ሜትር ርቀት ላለ ጓደኛ በደረት ትይዩ በማቀበል ወደ አቀበለበት አቅጣጫ


በመሮጥ ከኃላ መሰለፍ

• እንቅስቃሴውን ደጋግሞ በመስራት ማሻሻል ይቻላል፡፡

97
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ስዕል 6.7 ኳስን በደረት ትይዩ መቀባበል

6.8.1 በጨዋታ ጊዜ ኳስን በደረት ትይዩ ማቀበል


ተግባር በተቀማጭ ቅርጫት ውስጥ ኳስን መክተት

የጨዋታው ዓላማ ፡- በደረት ትይዩ የማቀበል ዘዴ ማሻሻልና የተፈለገበት ቦታ ማድረስ

የአሰራር ቅደም ተከተል

• ጥንድ ጥንድ በመሆን አምስት ቡድን መመስረት

• አራት ተቀማጭ ቅርጫቶችን በተለያዩ አቅጣጫዎች ማስቀመጥ

• በእጣ የሚገቡ አራት ቡድኖችን እና አንድ ጥንድ ዳኛ መለየት(ለአራቱ ጥንደች


አንድ አንድ ቅርጫት መስጠት)

• በደረት ትይዩ እየተቀባበሉ ከሶስቱ ክፍት ወደ ሆነው ተቀማጭ ቅርጫት ማስገባት

• ከገባበት ጥንድ/ቡድን/ ወይም ከደረት ትይዩ ውጭ የተቀባበለ ከጨዋታ ውጭ


ይሆንና ይዳኛል፣ ዳኛ የነበሩት ተጨዋች ይሆናሉ፡፡ ይህን ሂደት በመከተል
መጫወት፣

• በቀጣይ የተጫዋች ቁጥርን በመጨመር የላይኛውን መጫወት፡፡

98
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የግምገማ ጥያቄ
• በደረት ትይዩ ኳስን ማቀበልን በተግባር አሳዩ?

6.9 በእጅ ኳስ እና በቅርጫት ኳስ ጨዋታ ጊዜ


ኳስን በማንጠር ማቀበል
አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• ኳስን በማንጠር የማቀበል እንቅስቃሴ ጊዜ ሲሳተፉ ኃላፊነት የተሞላበት


የግንኙነትና ትብብር ክህሎትን ታሳያላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


ይህን የማቀበል ዘዴ መቼ ልንጠቀመው እንችላለን? በየትኛው የኳስ ጨዋታ
ዓይነት?

በማንጠር የማቀበል ዘዴ በቅርጫት ኳስና በእጅ ኳስ ጨዋታ በአንድና በሁለት እጅ


የሚተገበር የማቀበል ዘዴ ነው፡፡ ይህ የማቀበል ዘዴ በመሀከላችን ተከላካይ ወይም
ተቃራኒ ቡድን ካለ እና ሌሎች የማቀበል ዘዴዎችን ማቀበል ካልቻልን ይህን የማቀበል
ዘዴ መተግበር ግድ ይላል፡፡

ዋና ዋና ነጥቦች
• በሁለት እጅ ከሆነ የኳሱ መነሻ ከደረት ዝቅ ማለት አለበት፣

• ኳሱን ስናነጥር በመካከላችን ባለው 2/3 (ሁለት ሶስተኛው) ርቀት ላይ ነው፡፡

• የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• ያለ ኳስ እጅን ከደረት ዝቅ በማድረግ አንድ እግርን ወደ ፊት ወደ ኋላ ከእጅ ጋር


ማመላለስ

• በመቆም ኳስን በሁለት እጅ አንጥሮ ለጓደኛ ማቀበል

• አንድ እግርን ወደ ፊት ከእጅ ጋር በማቀናጀት አንጥሮ ማቀበል

99
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• እጅን ከእግር ጋር በማቀናጀት 2/3 (ሁለት ሶስተኛው) ርቀት በአንድ ወይም


በሁለት እጅ አንጥሮ ማቀበል

• ተከላካይ መሀል በቆመበት አንጥሮ ለጓደኛ ማቀበል

• የላይኛውን እንቅስቃሴ በመተግበር ወደ አቀበሉበት አቅጣጫ መሮጥና ከኋላ


መሰለፍ

ሰዕል 6.8 ኳስ በማንጠር ማቀበል

6.9.1 ኳስ በማንጠር የማቀበል ጨዋታ


ተግባር ፡- ኳስ በማንጠር የማቀበል ጨዋታ

የጨዋታው ዓላማ፡- አንጥሮ የማቀበል ከህሎትን ለማሻሻል

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• የሰዉነት ማሟሟቂያ መስራት

• አቀብሎ መሮጥን ለሶስት ደቂቃ መስራት

100
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

• በአራት ማዕዘን በተሰመረ ትንሽ ስፋት ባለው ቦታ ሁለት ለሁለት ሆኖ በአንድ


ወይም በሁለት እጅ አንጥሮ የማቀበል ጨዋታ ለአምስት ደቂቃ መጫወት

• በአራት ማዕዘን በተሰመረ ትንሽ ስፋት ባለው ቦታ ሶስት ለሶስት በሁለት ወይም
በአንድ እጅ አንጥሮ የማቀበል ጨዋታ ለሰባት ደቂቃ መጫወት፣

• በአራት ማዕዘን በተሰመረ ትንሽ ስፋት ባለው ቦታ አራት ለአራት በሁለት ወይም
በአንድ እጅ አንጥሮ የማቀበል ጨዋታ ለስምንት ደቂቃ መጫወት፣

የግምገማ ጥያቄ
ኳስን አንጥሮ በመስጠት ጊዜ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነገሮችን ዘርዝሩ?

6.10- አነስተኛ ጨዋታ


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• በአዝናኝ ጨዋታ ጊዜ ተማሪዎች ለቡድኑ በምታደርጉት አሰተዋጽኦ


ትዝናናላችኑ፡፡

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


በየትኛው የኳስ ጨዋታ መሳተፍ ትፈልጋላችሁ?

በመጀመሪያ የምትፈልጉትን የጨዋታ ዓይነት መምረጥ

ለምሳሌ፡- የእግር ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የመረብ ኳስና የቅርጫት ኳስ

የመረብ ኳስ፡- ለምትፈልጉ የመረብ ኳስ ጨዋታን በቡድን መጫወት

የእግር ኳስ፡- ለምትፈልጉ የእግር ኳስ ጨዋታን በቡድን መጫወት

የቅርጫት ኳስ፡- ለምትፈልጉ የቅርጫት ኳስ ጨዋታን በቡድን መጫወት

የእጅ ኳስ፡- ለምትፈልጉ የእጅ ኳስ ጨዋታን በቡድን መጫወት

ማስታወሻ ጨዋታው ማቀበል እና መቀበልን ዓላማ ያደረገ መሆን አለበት

101
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የምዕራፉ ማጠቃለያ
ኳሶችን በእጅ ወይም በእግር አማካኝነት በመጠቀም በተፈለገው አቅጣጫ
እየተቆጣጠሩ ወደ ፊት በማምራት ነጥብ ለማስቆጠር የሚቻልበት ሂደት ነው::
ኳሶችን ተቆጣጥሮ ለመንቀሳቀስ በመጀመሪያ ኳሶቹን መቆጣጠር ከዚያ ወደ
ተፈለገው ግብ መላክ ያስልጋል፡፡ ኳስ በትክክል ለመያዝ የእጅ እንቅስቃሴ
አቅጣጫ፣ የመጣውን ኳስ መቆጣጠር፣ የእጅ ጣቶች ሁኔታ ዋና ዋናዎቹ
ናቸው፡፡ በክንድኳስ የማቀበል ዘዴ ከወገብ በታች ወይም ዝቅ ብሎ የመጣን
ኳስ፣ ፈጣን እና ጠንካራ ኳስን ለመመለስ፣ ለማቀበል የሚጠቅም ክህሎት ነው::
ኳስ ማንሳትና ማቀበል በሁለቱም የማቀበል ዘዴ የሚቻል ሲሆን በአብዛኛው
ጊዜ ግን የምንጠቀመው እና ውጤታማ የምንሆነው በጣት ማንሳትና ማቀበል
ነው፡፡

በውስጥ የጎን እግር የማቀበል ዘዴ ቅርብ ላለ ጓደኛ ለማቀበልና ብዙ ጊዜ


የፍፀም ቅጣት ምት ለመምታት የሚያገለግል ነው፡፡ ምቱን በአግባቡ ለማከናወን
የመቺው እግር መሰረታዊ አቋቋም፣ የሰዉነት አቋቋም እና የመቺው እግር
እንቅስቃሴ ወሳኝነት አላቸው፡፡

ኳሱን በውጪ የጎን እግር መምታት የሚጠቅመው ኳሱን ቅርብ ላለ ጓደኛ


ለማቀበል ነው፡፡ በማንጠር የማቀበል ዘዴ በመሀከላችን ተከላካይ ወይም ተቃራኒ
ቡድን ካለ እና ሌሎች የማቀበል ዘዴዎችን ማቀበል ካልቻልን ይህን የማቀበል
ዘዴ መተግበር ግድ ይላል፡፡ ስለሆነም ለዚህ ክፍል ደረጃ የማቀበልና የመቀበል
ክህልቶች አይተናል፡፡ ማቀበልና ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ ኳስን ማድረስ ሲሆን
መቀበል ደግም ኳስን በቁጥጥር ስር ማድረግ ነው፡፡

102
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የማጠቃለያ ጥያቄዎች
ሀ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጣቸው አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ
የያዘውን ፊደል ምረጡ

1. ከሚከተሉት ውስጥ ከደረት በላይ የመጣችን ኳስ ለማቀበል የሚጠቅም ዘዴ ነው?

ሀ. በክንድማቀበል ለ. በአየር ላይ ማቀበል ሐ. በእግር ማቀበል

2. ኳስ በክንድየማቀበል ዘዴ በየትኛው የኳስ ጨዋታ ይከናወናል?

ሀ. በእግር ኳስ ለ. በቅርጫት ኳስ ሐ. በመረብ ኳስ

3. ከሚከተሉት ውስጥ ኳስን በክንድ የማቀበል ጥቅም የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ከደረት በላይ የመጣን ኳስ ለመመለስ

ለ. ጠንከር ያለ ኳስን ለመመለስ

ሐ. ቀለል ያለ ኳስን ለመመለስ

4. ኳስ ማንሳትና ማቀበል በእግር ኳስ ጨዋታ ይዘወተራል?

ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

5. ከሚከተሉት ውስጥ ቅርብ ላለ ጓደኛና ፍፁም ቅጣት ምት ለመምታት የሚያገለግለው


የምት ዓይነት የቱ ነው?

ሀ. በውስጥ የጎን እግር ለ. በውጭ የጎን እግር ሐ. በፊት ለፊት እግር

6. ኳስ በአየር ላይ በመግፋት ጊዜ ከኳሷ ጋር የሚገናኘው የእጅ ክፍል የቱ ነው?

ሀ. የመዳፍ ጀርባ ለ የእጅ ጣቶች ሐ. ክንድ

ለ. በ ሀ ስር ከተዘረዘሩት በ ለ ስር ካሉት ጋር አዛምዱ

ሀ ለ

1. በውጭ የጎን እግር ማቀበል ሀ. በጣትና በክንድየሚከናወን

2. ኳስ በደረት ትይዩ ማቀበል ለ. ኳስን ከመሬት ጋር በማጋጨት የሚከናወን

3. ኳስን በማንጠር ማቀበል ሐ. የእግር ጣቶችን ወደ ውስጥ በማዞር የሚከናወን

4. ኳስን ማንሳትና ማቀበል መ. ፈጣን በእጅ የማቀበል ዘዴ


103
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ምዕራፍ ሰባት
በአዲስ አበባ ደረጃ የሚገኙ የኢትዮጵያ ባህላዊ
እንቅስቃሴዎች እና ጨዋታዎች
መግቢያ
ማንኛውም ዛሬ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚከናወኑ ዘመናዊ ስፖርቶች ሁሉ የመነጩት
ከባሕላዊ ስፖርት እንቅስቃሴ ነው፡፡ባህላዊ ጨዋታዎች በጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ
ትምህርት ውስጥ ተካተው እንዲማሩ መደረጋቸው በሌሎች ነባር ይዘቶች ጠቀሜታ
ባሻገር ለማሳደግ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን እና ስፖርቱን ለማስፋፋት ከሚደረጉ
ጥረቶች አንዱና ዋናው አካል ስለሆነ ነው፡፡ እነዚህ ባሕላዊ ስፖርቶች ይዘታቸው
ሲጠና ጥንካሬን፣ ብርታትን፣ ቅልጥፍናንና የመንፈስ ጥንካሬን የመሳሰሉትን ብቃቶች
በማሳደግ ረገድ ያላቸው ሚና በጣም ከፍተኛ ነው፡፡

አዲስ አበባ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች መገኛ ከተማ እንደመሆኗ መጠን የተለያዩ
የባህል እንቅስቃሴዎች እና ባህላዊ ጨዋታዎች የሚከናወኑባት ከተማ ናት፡፡ በዚህ
የክፍል ደረጃ በኢትዮጵያ የሚገኙ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችና ጨዋታዎች ተካተው
ቀርበዋል፡፡

የመማር ዉጤቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ


• በአዲስ አበባ ደረጃ የሚገኙ ባህላዊ አንቅስቃሴዎችና ጨዋታዎችን ታሳያላችሁ፣

• በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችንና ጨዋታዎች ለተማሪዎች


ጤናማ ህይወት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ታደንቃላችሁ፣

• በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ባህላዊ እንቅስቀሴዎችና ጨዋታዎች በመሥራት


አካላችሁን ታዳብራላችሁ፣

104
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

7.1. ባህላዊ እንቅስቃሴዎች


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• በአዲስ አበባ ደረጃ የሚገኙ የኢትዮጵያ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን ቢያንስ


5 ትገልጻላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን
የምታውቋቸውን ግለፁ?

አገራችን የበርካታ ብሔረሰቦች ስብጥር እንደመሆኗ መጠን የብዙ ባህሎችም ባለቤት


ናት፡፡ ይህ የብዙ ብሔረሰቦች ስብስብ የሀገሪቷን አንድነት እኩልነት ወዘተ እንዲመሰርቱ
ያደርጋቸዋል፡፡ አንዱ ባህል ከሌላው አለመብለጡንና አለማነሱን መገንዘብ ይኖርብናል::
በአዲስ አበባ የተለያዩ ብሔረሰብ ባህላዊ እንቅስቃሴዎች የሚንፀባረቅባት ከተማ ናት::
ይህም የሆነበት ምክንያት የሁሉም ብሔረሰብ መናኽሪያ እና ዋና ከተማ በመሆኗ
ነው፡፡

ባህላዊ እንቅስቃሴ ማለት በልዩ ልዩ የህዝብና የሀይማኖት በዓላት እንዲሁም


በሠርግና በሀዘን ጊዜ የሚደረጉ አካላዊ እንቅስቃሴዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- አማርኛ፣
ጉራግኛ፣ ወላይትኛ፣ ትግርኛ፣ ስልጤኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሱማሌኛ፣ አፋርኛ፣ ጉምዘኛ፣
በርታኛ፣ አገውኛ ወዘተ… የመሳሰለት አካላዊ እንቅስቃሴዎች ናቸው፡፡ እነዚህን
ባህላዊ እንቅስቃሴዎች በመንቀሳቀስ የባህል ልውውጥ ማድረግን፣ የአንድነት መንፈስ
መፍጠርንና በእንቅስቃሴዎች የአካል ብቃት ማዳበርን ያስገኛሉ፡፡

የግምገማ ጥያቄ
የኢትዮጵያ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን ቢያንስ አምስት ዘርዝሩ?

105
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

7.2. በአዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ የተወሰኑ


የኢትዮጵያ ባህላዊ እንቅስቃሴዎች (ክፍልአንድ)
አጥጋቢ የመማር ብቃቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ትምህርት ከተማራችሁ በኃላ፡-

• በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያ ባህላዊ እንቅስቃሴዎች


ትዝናናላችሁ፣

• በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችን


ትሰራላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄዎች


• የትኛው ባህላዊ እንቅስቃሴ የትኛውን የአካል ክፍል ያሳትፋል?

በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያ ባህላዊ እንቅስቃሴዎች ከወገብ በላይ፣ ዳሌንና
ከወገብ በታች በአብዛኛውን የሚያንቀሳቅሱ ባህላዊ እንቅስቃሴዎች እንደሚከተሉት
ቀርበዋል፡፡

ከወገብ በላይ በብዛት የሚያንቀሳቅሱ፡- ጎንደርኛ፣ ጎጃምኛ፣ወሎ፣ ሰቆጣ፣ትግረኛ ወዘተ


በመንቀሳቀስ ከወገብ በላይ የሚገኙ የአካል ክፍሎችን የሚያሳትፉ ባህላዊ እንቅስቃሴዎች
ናቸው፡፡

ከወገብ በታች እና ዳሌ አካባቢ በብዛት የሚያንቀሳቅሱ፡- አገውኛ፣ ከፋኛ፣ ወለይታ፣


ኦሮሚኛ፣ ጉራግኛ፣ አፋርኛ፣ ሱማልኛ፣ ስልጢኛ ወዘተ በመንቀሳቀስ ከወገብ በታችና
ዳሌ አካባቢ የሚገኙ የአካል ክፍሎችን የሚያሳትፍ ባህላዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡ በዚህ
የክፍል ደረጃ በዋናነት ዳሌና ከወገብ በታች ያሉት የአካል ክፍሎችን የሚየሳትፍ
ባህላዊ እንቅስቃሴ፡፡

106
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ማስታወሻ
ባህላዊ እንቅስቃሴዎች እንደየ አካባቢው ሁኔታ የሚጨፈሩ ቢሆንም አብዛኛዎቹ ግን
መላ አካልን የሚያንቀሳቅሱ ናቸው፡፡

ሀ የአገው፣ የወለይታን እና የከፋ ብሔረሰብ ባህላዊ እንቅስቃሴ


የእንቅስቃሴው ዓላማ፡- ወገብና ዳሌ አካበቢ የሚገኙ የአካል ክፍሎች ማንቀሳቀስ

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• ወገብ እና ዳሌ አካባቢ ያለውን የሰዉነት ክፍል በደንብ ማሟሟቅ እና ማሳሳብ


• ከላይ የተጠቀሰውን ባህላዊ እንቅስቃሴዎች በቡድን መለማመድ
• አንዱ ቡድን የሰራውን ለሌሎች ቡድን ማቅረብ
• እየተቀያየሩ ሁሉንም ባህላዊ እንቅስቃሴ መለማመድ

ስዕል 7.1 (ከወገብ በታችና ዳሌ አካባቢ የሚያንቀሳቅሱ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ
እንቅስቃሴዎች)

107
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የግምገማ ጥያቄ
1. የአገው፣ የወላይታና የከፋ ባህላዊ እንቅስቃሴ በመንቀሳቀስ ምን ጥቅም
አገኛችሁ?

2. የኦሮሚኛ፣ የጉራጊኛ፣ የአፋርኛ፣ የሱማልኛ፣ የስልጢኛ

የእንቅስቃሴው ዓላማ፡- መላ አካልን ማንቀሳቀስ


የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

• ከወገብ በታች ያለውን የሰዉነት ክፍል በደንብ ማሟሟቅ እና ማሳሳብ

• ከላይ የተጠቀሱትን ባህላዊ እንቅስቃሴዎች በቡድን መለማመድ

• አንዱ ቡድን የሰራውን ለሌሎች ቡድን ማቅረብ

• እየደጋገማችሁ እንቅስቃሴውን መለማመድ

• እየተቀያየራችሁ ሁሉንም ባህላዊ እንቅስቃሴዎች መለማመድ

ከላይ የተጠቀሱትን ባህላዊ እንቅስቃሴዎች በማሟሟቂያ ክፍለ ጊዜና በዋናው ክፍለ


ጊዜ መምህሩ/ሯ በሚያዘጋጁላችሁ ትምህርት መሳተፍ እና እንቅስቃሴ ማድረግ ባህላዊ
እንቅስቃሴዎችን ለማሳደግ ጤንነት ለመጠበቅ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርባችኋል::

ስዕል 7.2 (መላ አካልን የሚያንቀሳቅሱ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ እንቅስቃሴዎች)

108
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የግምገማ ጥያቄ
የምትችሉትን ከወገብ በታች የሚገኙ የአካል ክፍሎችን የሚያሳትፉ ከባህላዊ
እንቅስቃሴዎች ውስጥ አንድ ሰረታችሁ አሳዩ?

7.3. ባህላዊ ጨዋታዎች


አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• በአዲስ አበባ ደረጃ የሚገኙ የኢትዮጵያ ባህላዊ ጨዋታዎችን ቢያንስ 5


የሚሆኑትን ትገልጻላችሁ፣

• በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያ ባህላዊ ጨዋታዎችን


ታደንቃላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄ


በአካባቢያችሁ የሚገኙ ባህላዊ ጨዋታዎችን ጥቀሱ?

ባህል ማለት አንድ ብሔረሰብ በጋራ የሚጠቀምበት አንድ ወጥ የሆነ ስነ ስርዓት


ማለት ነው፡፡ የአንድ ህብረተሰብ እምነት አምልኮ፣ የማምረቻ ዓይነቶች፣ እደ ጥበብ፣
በዓላት፣ አመጋገብና አለባበስ በአንድነት ባህል ይባላሉ፡፡ የተለያዩ ህዝቦች የተለያየ
ባህል አላቸው፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥም የተለያዩ ባህሎች አሉ፡፡ ማንኛውም ባህል
እኩል ነው፡፡ አንዱ ባህል ከሌላው አይበልጥም አያንስም፡፡ የባህል እኩልነት ካለና
ከተረጋገጠ ደግሞ ከሌሎች ጋር መቀራረብን ይፈጥራል፡፡

ባህላዊ ጨዋታዎች የምንላቸው በህብረተሰቡ ውስጥ ተወልደው አደገው አሁንም


በስራ ላይ ያሉ የጨዋታ ዓይነቶች ናቸው፡፡ እነዚህም በተለያዩ አካባቢዎች
የየካባቢዎችቡሚዘወተሩ እንደ ገና ጨዋታ፣ ፈረስ ግልቢያ፣ ትግል፣ ገበጣ፣ ሻህ፣
ቡብ፣ ኩርቦ፣ ሁርቤ ወዘተ የመሳሰሉት ሲሆኑ እነዚህ ባህላዊ ጨዋታዎች የራሳቸው
የሆነ ሕግና ደንብ ኖሯቸው ህብረተሰቡ የሚሳተፍባቸው ናቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ
የአካባቢያችን የባህል ጨዋታዎች ሲከናወኑ የነበረው በበዓላት ቀናት ሲሆን አሁን
ግን ከበዓላት ውጭም ይከናወናሉ፡፡

በአጠቃላይ ባህል የሚጫወተው ሚና በጤናና ሰዉነት ማጎልማሻ ትምህርት ውስጥም


ሰለሚካተቱ የሁለቱን የጠበቀ ግንኙነት በቀላሉ ለመገንዘብ ይረዳናል፡፡

109
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የግምገማ ጥያቄዎች
1. በአዲስ አበባ የሚገኙ የኢትዮጵያ ባህላዊ ጨዋታዎች ዘርዝሩ?

2. ባህል ማለት ምን ማለት ነው?

7.4 በአዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ የተወሰኑ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጨዋታዎች

አጥጋቢ የመማር ብቃቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-

• •በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያ ባህላዊ ጨዋታዎችን


ታደንቃላችሁ፣
• በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያ ባህላዊ ጨዋታዎችን
ትሰራላችሁ፣

የመነሻና የማነቃቂያ ጥያቄ


የገበጣ ምን ዓይነት ጨዋታ ነው?

የባለ 18 ጉድጓድ የስሉስ ገበጣ ባህላዊ ጨዋታ ምንነት

ባህላዊ የገበጣ ጨዋታ አጀማመር የረዥም ጊዜ ታሪክ ያለው የጨዋታ ዓይነት ነው::
ከክርስቶስ ልደት በፊት በ6ኛውና በ7ኛው ክፍለ ዘመን በፊት ጨዋታው በሀገራችን
ይዘወተር እንደነበር የሚያመለክት መረጃ ተገኝቷል፡፡

ከዚህ በፊት በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት እንግሊዛዊያን


መካከል የአፄ ቴዎድሮስ የቅርብ ጓደኛ የነበረው ዋልተር ፕላውዶን በሪፖርቱ
እንደገለፀው በበጌ ምድር በራስ አሉላ ካምፕ ውስጥ የነበሩት ወጣቶች በከፍተኛ ሰሜት
የገበጣ ጨዋታ ይጫወቱ እንደነበር ያስረዳል፡፡ በተጨማሪም በ1890 ዓ.ም. ወደ
ኢትዮጵያ ከገቡት የውጭ ሀገር ሰዎች መካካል ኮምዋልሳ ሀሪስ የተባለው እንግሊዛዊ
በወቅቱ በፃፈው ሪፖርት ላይ የሸዋ መሳፍንትና መኳንንት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት
ገበጣ የሚባል ጨዋታ በመጫወት ነው የሚል ይገኝበታል፡፡ ይህ እንግዲህ የሚያሳየን
የገበጣ ጨዋታ በንጉሳዊያን ቤተሰቦች ጭምር ይዘወተር እንደነበር ያስገነዝበናል፡፡

110
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ለሱልስ ገበጣ መስፋፋት እትጌ ጣይቱ ብጡል እጅግ
ከፍተኛ ሚና ነበራቸው፡፡ ይኸውም የሆቴል አገልግሎትና ጥቅም በማይታወቅበት
ዘመን እትጌይቱ በስማቸው ሆቴል አሰርተው ስለነበር የሆቴል ጥቅምን ለማስተዋወቅ
የገበጣ ጨዋታ ውድድር ያካሂዱ ነበር፡፡ ጨዋታው በይበልጥ በቤተ-መንግስት አካባቢ
ባሉ ሹማምንቶች በከፍተኛ ሁኔታ ይዘወተር ነበር፡፡

ከላይ ባየናቸው መረጃዎች መሰረት የገበጣ ጨዋታ በኢትዮጵያ ከከርስቶስ ልደት በፊት
ጀምሮ ይዘወተር የነበረና በመካከለኛው ክፍለ ዘመን እድገት እያሳየ መጥቶ በመሳፍንቱና
በመኳንንቱ ዘመን በቤተ-መንግስትና በአደባባይ በከፍተኛ ስሜት የሚዘወተር ባህላዊ
ጨዋታ እንደነበር ታሪክ ያረጋግጣል፡፡ ዛሬም ይህ አኩሪ የባህል ጨዋታ በመላው
ኢትዮጵያ በመዘውተርና በመስፋፋት የውድድር ስፖርት በመሆን ያገለግላል፡፡

የስሉስ ገበጣ ውድደር በሁለት ቡድን ተወዳዳሪ ተጨዋቾች መካከል የመጫወቻ


ገበጣው በመካከላቸው በማስቀመጥ ሕጉ በሚፈቅደው አጨዋወት መሠረት ከራሳቸው
ቤት እኩል ጠጠር አፍሰው በመነሳትና በመዘርዘር ውግ በመውጋት ጠጠሮችን
በውግ ላይ በማከማቸትና ተጋጣሚውን ከጨዋታ ውጪ በማድረግ አሸናፊ ለመሆን
የሚከናወን ባህላዊ ጨዋታ ነው፡፡

የመጫወቻ ገበጣ አዘገጃጀት


ለስሉስ ገበጣ ጨዋታ የሚያገለግል ባለ 18 ጉድጓድ ገበጣ በአካባቢው በሚገኙ ነገሮች
ማዘጋጀት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ወፍራም የሆነን ጣውላ በመቦርቦር፣ ሲሚንቶና አሸዋ
በአንድ ላይ አብኩቶና ከጭቃ አስተካከሎ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡

የመጫወቻ ጠጠሮች አዘገጃጀት


የመጫወቻ ጠጠሮች በአካባቢው ከሚገኙ ነገሮች በክብ ወይም በድቡልቡል ቅርፅ
ማዘጋጀት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ፣ ከወንዝ ከሚገኙ ጠጠሮች፣ ከብይና ከብረት መሰል
ነገሮች አስተካክሎ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡

የመጫወቻ ገበጣ መጠንና ይዘት


የገበጣው ርዝመቱ ቢያንስ 96 ሴ.ሜ ቢበዛ 100 ሴ.ሜ ሲሆን ወርዱ ደግሞ ቢያንስ
34 ሴ.ሜ ቢበዛ 38 ሴ.ሜ ነው፡፡

የገበጣው ጉድጓዶች አቀማመጥ በሶስት ረደፍ 6፣6፣6 ጉድጓዶችን በመያዝ ሲሆን

111
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

በጠቅላላው 18 ጉድጓዶች በተርታ እና በትይዩ ሆነው የተሰሩ መሆን አለባቸው::


የመጫወቻ ጉድጓዶች ዲያሜትር 6 ሴ.ሜ ጥልቀታቸው 2 ሴ.ሜ ነው፡፡ የጠጠር
ማከማቻው ጉድጓዶች ስፋት 12 ሴ.ሜ ጥልቀታቸው 2 ሴ.ሜ ነው፡፡ የጠጠር ማከማቻ
ጉድጓዶች ከመጫወቻ ጉድጓዶች ያላቸው ርቀት 5 ሴ.ሜ ነው፡፡ ጉድጓዶች በሁለት
ዓይነት ቀለም በመቀባት መለየት አለብን ማለትም ዘጠኙን አንድ ዓይነት ዘጠኙን ሌላ
ዓይነት ቀለም መቀባት አለበት፡፡

በአጠቃላይ ለስሉስ ገበጣ የሚያስፈልጉት ጠጠሮች ብዛት 60 ሲሆኑ በእያንዳንዱ


ጉድጓድ ሶስት ሶስት ጠጠር ይቀመጥና ስድስቱ ከጉድጓድ ውጪ ተጠባባቂ ይሆናሉ፡፡
ውድደሩ በሁለቱም ፆታዎች በአንድ አንድ ሰው ይካሄዳል፡፡ አንድ ዋና ዳኛ እና አንድ
ነጥብ መዘጋቢ ዳኛ ይኖረዋል፡፡

የጨዋታው አጀማመር ሂደት


• ሁለት ተጋጣሚ ተጨዋቾች የመጫወቻ ገበጣውን በተመቻቸ ሁኔታ በመካከላቸው
በማድረግ ፊት ለፊት ትይዩ በመሆን ይቀመጣሉ፡፡

• ተጨዋቾችም እያንዳንዳቸው 9.9 (ዘጠኝ ዘጠኝ) የመጫወቻ ጉድጓድና 1.1 (አንድ


አንድ) የጠጠር ማከማቻ ጉድጓድ ይካፈላሉ፡፡

• የጠጠር አጣጣል ስርዓቱ የሚከናወነው ከግራ ወደ ቀኝ ይሆናል፡፡

• አንድ ተጨዋች ከግራ ወደ ቀኝ ጠጠሮቹን በየጉድጓዱ እየጣለ ሲሄድ ወደ ራሱ


9ኛ ቤት ላይ ሲደርስ ወደ ተጋጣሚው 1ኛ ቤት፣ በተጋጣሚው 9ኛ ቤት ላይ
ሲደርስ ወደ ራሱ 1ኛ ቤት ታጥፎ ጨዋታውን መቀጠል እንጅ በቀጥታ ፊት
ለፊት ተሻግሮ መጫዎት የለበትም፡፡

• ጨዋታውን የሚጀምረው በዳኛው አማካኝነት ሁለቱም ተጋጣሚዎች ከፈለጉበት


ከየራሳቸው ጉድጓድ ውስጥ እኩል ጠጠሮችን በማፈስ ይጀምራሉ፡፡

• ከሁለቱ አንደኛው ተጨዋች ጠጠሮቹን በፍጥነት በየቤቱ እየጣለ በመጫዎት


ቀድሞ በባዶው ቤት ያደረ ወይም ያረፈ ከሆነ የሚቀጥለውን የጨዋታ ሂደት
ይቀጥላል፡፡ ከዚያ በኋላ በየተራቸው እንዲሄዱ ይደረጋል፡፡

• በዚህ የክፍል ደረጃ ቀለል ያለ የገባጣ ጨዋታን መምህሩ/ሯ በሚያሳያችሁ መሠረት


ልምመድ እንድታደርጉ ቀርቦላጭኋል፡፡ ሙሉ ጨዋታውን ግን ስድሰተኛ ክፍል
በምዕራፍ ሰባት በሰፊው ታገኙታላችሁ፡፡

112
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ስዕል 7.3 (ባለ 18 ጉድጓድ ገበጣ መጫወቻ ቁስ)

የግምገማ ጥያቄዎች
1. የገበጣ ጨዋታ አጀማመርንና አጨዋወቱን አብራሩ?

2. ባለ 18 ጉድጓድ የገበጣ ጫወታ ለምን ስሉስ ተባለ?

113
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የምዕራፉ ማጠቃለያ
አንድን ሀገር ልዩ ከሚያደርጉት ዋና ዋና ነገሮች አንዱ ባሕልና ልማድ ነው::
ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ብሔረሰቦችና ህዝቦች አገር እንደ መሆኗ መጠን
ብዛት ያላቸው ባሕሎች ወግና ልማዶች አሏት፡፡ ከባሕል ቅርሶቻችን ውስጥ
አንዱ ጨዋታዎችና ጭፈራዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ዘርፈ ብዙ ጨዋታዎችና
እንቅስቃሴዎች የህብረተሰቡን አባላት በተለያዩ እንቅስቃሴዎች በማሳተፍ ረገድ
ዓይነተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት በአንድ በኩል
እንቅስቃሴዎቹ አካልንና አእምሮን ከማበልፀግ አኳያ ያላቸው ሚና ከፍተኛ
ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ተማሪዎቹ በራሳቸው ባሕላዊ እንቅስቃሴዎች ሲሳተፉ
ደስታን ከማግኘታቸውም በላይ የኔነትን ስሜት አዳብረው ባህላቸውን ለማሳደግ
አመቺ ሁኔታ ስለሚፈጥር ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የተለያዩ የባህል እንቅስቃሴዎች እና ባህላዊ


ጨዋታዎች የሚከናወኑባት ከተማ ስትሆን በዚህ የክፍል ደረጃ በኢትዮጵያ
የሚገኙ እንቅስቃሴዎችና ባህላዊ ጨዋታዎች ወስጥ የተለያዩ ብሔረሰብ አካላዊ
እንቅስቃሴና ባለ 18 ጉድጓድ ገበጣ ምንነት እና የአጨዋወት ሂደት ለማየት
ተችሏል፡፡

114
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የማጠቃለያ ጥያቄዎች፡-
ሀ. የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች በማንበብ ትክከል የሆነውን እውነት ስህተት የሆኑትን
ሐሰት በማለት መልሱ

1. ዘመናዊ ስፖርት የመጣው ከባህላዊ ጨዋታዎች ነው፡፡


2. አንድ ባህል ከሌላ ባህል ይበላለጣል፡፡
3. ባህል ማለት አንድ ብሔረሰብ የሚጠቀምበት ወጥ የሆነ ስነ-ስረዓት ነው፡፡
4. በድሮ ጊዜ የባህል ጨዋታዎች የሚከናወኑት በበዓላት ቀናት ነበር፡፡
5. አፄ ሚኒልክ ለስሉስ ገበጣ መስፋፋት ከፍተኛ ሚና ነበራቸው፡፡

ለ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማንበብ ትክከለኛውን መልስ የያዘውን ፊድል ምረጡ

1. ከሚከተሉት ውስጥ ባህላዊ እንቅስቃሴን በመስራት የሚገኝ ጥቅም ነው?


ሀ. የባህል ልውውጥ ለ. የአንድነት መንፈስ
ሐ. የአካል መዳበር መ. ሁሉም

2. የባህል መገለጫ ያልሆነው የቱ ነው?


ሀ. ቋንቋ ለ. ሃይማኖት ሐ. ግጭት መ. አለባበስ

3. የኢትዮጵያ ባህላዊ ጨዋታ ያልሆነው የቱ ነው?


ሀ. ገበጣ ለ. ገመድ ጉተታ ሐ. ገና መ. ሻህ

4. ከሚከተሉት ውስጥ ዳሌ አካባቢን የሚያሳትፍ ባህላዊ እንቅስቃሴ የቱ ነው?


ሀ. ስልጤኛ ለ. ጉራግኛ ሐ. አገውኛ መ. ሱማሌኛ

5. የስሉስ ገበጣ ጨዋታ በባለ ስንት ጉድጓድ ይጫወታሉ?


ሀ. 12 ለ. 18 ሐ. 9 መ. 16

6. ከሚከተሉት ውስጥ እግርን የሚያሳትፍ ባህላዊ እንቅስቃሴ የቱ ነው?


ሀ. ወላይተኛ ለ. አገውኛ ሐ. ጉራግኛ መ. ሁሉም

7. የስሉስ ገበጣ ጨዋታ በስንት ጠጠሮች ይጫወታሉ?


ሀ. 60 ለ. 56 ሐ. 48 መ. 50

8. የስሉስ ገበጣ ጨዋታ በአንድ ጉድጓድ ስንት ጠጠሮች ይቀመጣሉ?

ሀ. 3 ለ. 4 ሐ. 5 መ. 6
115
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

የቁልፍቃላትፍቺ
ጤና፡- ከበሽታ ነፃ መሆን ብቻ ሳይሆን የአካል፣ የአዕምሮና የማህበራዊ ግንኙነትን
ደህንነት ነው፡፡

ስፖርት፡- የተቀናጀ ውድደራዊ ጨዋታ

ነርቭ፡- ለአዕምሮ መልዕክት የሚያደርስና የሚመልስ የአካል ክፍል ነው፡፡

ኦሎምፒክ፡- በአራት ዓመት አንድ ጊዜ የመደረግ አለም አቀፍ ውድድር

እ.ኤ.አ. ፡- እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር

የሰረገላ ውድድር፡- በፈረስ የሚጎተት ክፍት ተሸከርካሪ

ማህበራዊ፡- በመሰባሰብ የአንድነት መገለጫ ነው

መረጃ፡- ጽሁፋዊ ወይም ቃላዊ ማረጋገጫ

ጥምረት፡-ሁለትና ከዚያ በላይ ሆነው መግባባት

ስሜት፡- አውነታዊ እና አሉታዊ የሰው ልጅ ባህሪ የሚገለጽ

የአካል ብቃት፡- የሰውነት ችሎታ ማለት ሲሆን እንቅስቃሴ ወይም ውድድር


ያለምንም ድካም ወይም ችግር የማከናወን ችሎታ

ጤና ተኮር፡- ከጤና ጋር የሚዛመድ እንቅስቃሴዎች የሚያካትት

ውድድር ተኮር ፡- ከውድድር ጋር የሚዛመድ

ቅልጥፍና፡- በተለያዩ አቅጣጫዎች የመዞር

የጡንቻ ብርታት፡- ጡንቻ ለረጅም ሰዓታት መስራት

አበረታች ቅመሞች፤- ሃይል የሚሰጡ አነቃቂ ንጥረ ነገር

መም፡- ለመሮጫ የሚያገለግል መስመር

መመንጠቅ፡- ወደ ላይ መነሳት ማለት ነው

ሽቅብ፡- ወደ ላይ መነሳት

116
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

አሎሎ፡- ከብረት የሚሰራ ዱቡልቡል የውርወራ መሳሪያ

ዲስከስ፡- ከእንጨትና ከነሐስ የሚሰረራ ጠፍጠጣፋ የውርወራ መሳሪያ

ጅምናስቲከ፡- በዓይን የሚታይ የትበብ ዓይነት

የመሳሪያ ጅምናስቲከ፡- በመሳሪያ በመታገዝ የሚሰራ የጅምናስቲክ ዓይነት

ሚዛን መጠበቅ፡- የሰውነት ስበትን ማመጣጠን

ሪቫን፡- ከጨርቅ የተሰራ ተውለብላቢ ነገር

አግዳሚ ወንበር፡- ሚዛንን ለመጠበቅ የሚሰራበት ቁስ

ማቀበል፡- ኳስን ለጓደኛ በአየር ወይም በመሬት በትክክል መስጠት

መቀበል፡- ከጓደኛ የመጣን ኳስ በቁጥጥር ስር ማዋል

ክንድ፡- በሁለት ክርን እና እጅ መገጣጠሚያ መሀል የሚገኝ የእጅ ከፍል

ባህል፡- የአንድ ብሔረሰብ ወጥ የሆነ ስነ-ሰረዓት

ስሉስ፡- ሶስት ማለት ነው፡፡

ገበጣ፡- ከተለያዩ ቁሶች የሚሰራ የባህል መጫወቻ ዕቃ ነው

117
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

ዋቢመጻሕፍ
1. BTEC Level 2 First in sport Oxford New York Rob Commons, Michala Swales
2010 first edition

2. Concepts of physical fitness Charles B. Corbin Lindsey, gerg welk active life style
10th edition

3. Ethiopian Natinal Anti Doping Office (2018)

4. IAAF Kids Athletics practical gude 2002 first edition

5. International Olympic Committee (2020)Olympic charter

6. LA84 Fundation 2012 track and field coching manual

7. Modern Text Book of Physical education Health and sports second revised edioion
2003 acording to Panjab Universty Chandigarh

8. Physical education students text book grade 10 Addis Ababe, 2005 revised edition

9. Physical education students text book grade 11 Addis Ababe, 2005 revised edition

10. Physical education students text book grade 12 Addis Ababe, 2005 revised edition

11. Physical education students text book grade 9 Addis Ababe, 2005 revised edition

12. Royal Navy track and filed 2008 coching manual

13. Social Emotional Learning Resource Guide 1st Edition 2019-2020 www.casel.org
or https://schoolguide.casel.org

14. World Anti Doping Agency (2015) Anti Doping policies and regulations code

15. የ5ተኛ፣ የ6ተኛ፣ የ7ተኛና የ8ተኛ ክፍል የሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት


የመምህሩ መምሪየ አዲስ አበባ 2009 ዓ.ም

16. የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች የውድድር ህግ

17. https://en.wikipedia.org/wiki/KenenisaBekele

18. https://en.wikipedia.org/wiki/Gezahegne_Abera

19. https://en.wikipedia.org/wiki/Gymnastics

20. https://en.wikipedia.org/wiki/Olympic_Games

118
የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ አምስተኛ ክፍል የተማሪ መፅሐፍ

119

Вам также может понравиться