Вы находитесь на странице: 1из 158

አማርኛ

የተማሪ መጽሐፍ
2ኛ ክፍል

አዘጋጆች

አበበች ተስፋዬ ዳምጤ


እሸቴ መብራት አንዳርጌ

አርታኢ
ሙሉሰው ከበደ ሰጋሁ

ሰዓሊ
አይናዲስ አምባው ምህረቴ

ዲዛይነር
ገነት አባተ መኮንን

የቡድን መሪ
ዶር. ማረው አለሙ ተሰማ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ


ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተመደበ በጀት በአብክመ ትምህርት
ቢሮና በምሁራን መማክርት ጉባዔ ትብብር ነው።

የመጽሐፉ ሕጋዊ የቅጂ ባለቤት © 2015 ዓ.ም. አብክመ ትምህርት ቢሮ ነው።

የምሁራን መማክርት ጉባዔ


ማውጫ

ጠቃሚ ምክር ለተማሪ ወላጅ/አሳዳጊ���������������������������������������������������������������������������������������� iv

ምዕራፍ 1 አልባሳት������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 1

ምዕራፍ 2 ወቅቶች������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 16

ምዕራፍ 3 ታሪኮች������������������������������������������������������������������������������������������������������������� 30

ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት�������������������������������������������������������������������������������������������������� 44

ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና������������������������������������������������������������������������������������������������� 58

ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ�������������������������������������������������������������������������������������������������� 71

ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር������������������������������������������������������������������������������������������ 87

ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት�������������������������������������������������������������������������������������������� 104

ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች�������������������������������������������������������������������������������������� 119

ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት������������������������������������������������������������������������������������������������ 134

ዋቢዎች������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������������ 150

iii አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ማውጫ ሐ


ጠቃሚ ምክር ለተማሪ ወላጅ/አሳዳጊ

መግቢያ
ይህ የተማሪ መጽሐፍ በፍኖተካርታውና በአገርአቀፍ ምዘናዎች ምክረሐሳቦች መሠረት በ2013 ዓ.ም
በተደረገው የሥርዐተትምህርት ለውጥ መነሻነት የተዘጋጀ ነው። በመሆኑም በመጽሐፉ ዝግጅት
የሚከተሉት ጉዳዮች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፤
1. የተማሪዎችን በጥልቀት የማሰብ፣ የመተንተን፣ የመጠየቅ፣ ችግር የመፍታት፣ የመወሰን፣
የመግባባትና የመገምገም ክህሎት የሚያሳድጉ ዓይነተብዙ ተግባራት ተካትተዋል፤

2. የተማሪዎችን አቀላጥፎ የማንበብ፣ የማዳመጥ፣ የመናገርና የመጻፍ ችሎታ የሚያጎለብቱ


ታሪኮችና ተዛማጅ ተግባራት እንዲኖሩ ተደርጓል፤

3. የትምህርቱ አቀራረብ ከይዘትተኮር ይልቅ ወደተግባርተኮር እንዲያመዝን ሆኗል፤

4. አገርበቀል እውቀቶች እንደአስፈላጊነታቸው በታሪኮች፣ በምንባቦችና በተግባራት ውስጥ


ተካትተዋል፤

5. የባሕላዊ ማንነትንና የአርበኝነትን ፋይዳዎች የሚያስገነዝቡ ታሪኮች፣ ምንባቦች፣


ሥነግጥሞችና ሥዕሎች እንደአስፈላጊነታቸው ተካትተዋል፤

6. ተማሪዎች በአብዛኛው በትብብር የሚማሩባቸው እድሎች ተመቻችተዋል፤

7. ለመማር የመማር ክህሎትን ለማጎልበት ሲባል፣ ተማሪዎች በየምዕራፎቹ አራቱን የቋንቋ


ክሂሎችና ሰዋስዋዊ ይዘቶች የሚማሩባቸው ዓይነተብዙ ብልሀቶች ተካትተዋል፤

8. የተማሪዎችን የፈጠራ ችሎታ ለማጎልበት ሲባል፣ ቋንቋውን ፈጥረው የሚጠቀሙባቸው


በርካታ እድሎች ተመቻችተዋል፤

9. ሥርዐተፆታንና አካቶ ትምህርትን ከግምት ለማስገባት በታሪኮች፣ በምንባቦች፣ በሥዕሎች፣


በተዛማጅ ተግባራት እንዲሁም በቋንቋው ትምህርት ይዘት አቀራረቦች ላይ ጥንቃቄ
ተደርጓል።

የተማሪ መጽሐፉ ዐቢይ ዓላማ የልጆችን በአማርኛ ቋንቋ የማዳመጥና የመናገር፣ የማንበብና የመጻፍ
ችሎታ ለማሳደግና በጥልቀት የማሰብና የመግባባት ብቃታቸውን ለማጎልበት ነው። መጽሐፉ በልጆች
የማንበብና የመጻፍ ስኬት ላይ የተሠሩ ምርምሮችን ግኝቶችና የአማርኛ ቋንቋን መሠረታዊ ባሕርያት
መነሻ አድርጎ የተዘጋጀ ነው።
የትምህርት ይዘቶቹ በአሥር ምዕራፎች የተደራጁ ናቸው፤ የመጀመሪያዎቹ ዐምስት ምዕራፎች
የትምህርት ይዘቶች በመጀመሪያው መንፈቀዓመት፣ ቀሪዎቹ ዐምስት ምዕራፎች ደግሞ በኹለተኛው
መንፈቀዓመት እንዲጠናቀቁ ሆነው የቀረቡ ናቸው። የአንድ ምዕራፍ የትምህርት ይዘቶች ደግሞ
በሦስት ሳምንታት እንዲጠናቀቁ ታስበው ነው የተደራጁት። የየምዕራፎቹ የትምህርት ይዘቶች
በአንድ ነጥብ በተለዩ ሦስት ቁጥሮች የተወከሉ ናቸው፤ የመጀመሪያው ቁጥር ምዕራፍን፣ ኹለተኛው
ቁጥር ሳምንትንና ሦስተኛው ቁጥር ቀንን የሚወክሉ ናቸው። ለምሳሌ፣ 1.1.1 የሚሉ ቁጥሮች
ምዕራፍ አንድን፣ ሳምንት አንድንና ቀን አንድን በቅደምተከተል ይወክላሉ፤ እንዲሁም 10.2.3
የሚሉ ቁጥሮች ምዕራፍ አሥርን፣ ሳምንት ኹለትንና ቀን ሦስትን በቅደምተከተል ይወክላሉ።

iv አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ጠቃሚ ምክር... መ


የተማሪ መጽሐፉ መሠረታዊ መርሆች የሚከተሉት ናቸው፤
„„ ልጆች እንግዳ ቃላትን ለማንበብና ቃላትን በተገቢ አሰዳደር አቀላጥፎ ለመጻፍ፣ የቋንቋው
ፊደላት የሚወክሏቸውን ድምፆች መማር ይጠበቅባቸዋል፤

„„ ልጆች አስቀድመው ቃላትን ቀጥሎም ዓረፍተነገሮችን ማንበብ አለባቸው፤ ቃላቱና


ዓረፍተነገሮቹም በተማሯቸው ፊደላት የተመሠረቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል፤

„„ ልጆች በፍጥነት፣ በትክክልና ያለችግር እንዲያነቡና ራሳቸውን በንግግርም ሆነ በጽሑፍ


በትክክልና በግልጽ ቋንቋ ለመግለጽ እንዲችሉ ማንበብንና መጻፍን በተከታታይ መለማመድ
አለባቸው፤

„„ ልጆች አዳዲስ ቃላትን ሲያዳምጡና ሲያነቡ የቃላቱንም ፍቺ አብረው መማር አለባቸው፤


የዚህም ዓላማ የሚያዳምጡትንና የሚያነቡትን መረዳት እንዲችሉ ነው፤ በተጨማሪም
ቋንቋውን በንግግርና በጽሑፍ በአግባቡ እንዲጠቀሙ ነው፤

„„ ልጆች ታሪኮችንና ምንባቦችን ሲያነቡ ሐሳቡን በትክክል ለመረዳት እንዲችሉ ዓይነተብዙ


የአንብቦ መረዳት ክሂሎችን ማዳበር አለባቸው።

የተማሪ ወላጅ/አሳዳጊ በቤት ውስጥ ልጆችዎን እንደሚከተለው ያግዙ፤

„„ ታሪኮችን ይተርኩላቸው፤

„„ ያዳመጧቸውን ታሪኮች መልሰው እንዲናገሩ ያበረታቷቸው፤

„„ ስለነገሯቸው ወይም ስላነበቡላቸው ታሪኮች ለሌሎች እንዲናገሩ ያበረታቷቸው፤ ይህም


አዳምጦ የመናገር ክሂሎቻቸውን እንዲያዳብሩ ያግዛቸዋል፤

„„ ታሪኮችን ዘወትር ያንብቡላቸው፤ ወይም ያስነብቡላቸው፤ ስለሚያነቡላቸው ታሪኮችም


ያወያዩዋቸው፤ ይህም ለማዳመጥ መልካም አጋጣሚ ይፈጥርላቸዋል፤ በራሳቸውም
ለማንበብ እንዲነሳሱ ይረዳቸዋል፤ ከልጆቹም ጋር ስለሚያነቡት ጽሑፍ ይወያዩ፤

„„ በሚያውቋቸው ወይም በተማሯቸው ፊደላት የተመሠረቱ ቃላትን ድምጽ እያሰሙ


እንዲያነቡ ያበረታቷቸው፤

„„ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉትን ወይም ለደራጃቸው የሚመጥኑ ሌሎች ታሪኮችን አዘውትረው
እንዲያነቡ ያበረታቷቸው፤ ለማንበብ የሚቸገሩባቸውን ቃላትና ዓረፍተነገሮች አርአያ
ሆነው በማንበብ እርስዎ እንዳነበቡት አድርገው እንዲያነቧቸው በአግባቡ ያግዟቸው፤

„„ ታሪኮችን በራሳቸው ተነሳሽነት እንዲያነቡ ያበረታቷቸው፤

„„ ለቤተሰብ አባላት ወይም ለጓደኞቻቸው ማስተላለፍ ስለሚፈልጓቸው መልዕክቶች


በራሳቸው እንዲጽፉ ያበረታቷቸው፤

v አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ጠቃሚ ምክር... ሠ


የትምህርቱ ይዘቶች

በመጽሐፉ የተካተቱት ዋና ዋና ይዘቶች በሚከተሉት ምልክቶች ተወክለዋል፤

የማዳመጥ ታሪክ ወይም ምንባብ


ይህ ምልክት የሚወክለው የትምህርት ይዘት የማዳመጥን ታሪክ ወይም ምንባብ ነው።

በክፍል ውስጥ ልጆች

„„ በመምህራቸው የሚነበበውን ታሪክ ወይም ምንባብ ያዳምጣሉ፤

„„ ርዕስንና ሥዕልን በማስተዋል ስለታሪኩ ወይም ስለምንባቡ ይገምታሉ፤

„„ የቅድመማዳመጥና የድኅረማዳመጥ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ፤

„„ ስለአዳመጡት ታሪክ ወይም ምንባብ ይወያያሉ።

የተማሪ ወላጅ/አሳዳጊ በቤት ውስጥ ልጆችዎን እንደሚከተለው ያግዙ

„„ ስለአዳመጡት ታሪክ ወይም ምንባብ የሚያስታውሱትን እንዲናገሩ ይጠይቋቸው፤ ሥዕሎቹ


ታሪኮቹን ለማስታወስ እንዴት እንደሚረዱ ይጠቁሟቸው።

አዲስ ወይም ተተኳሪ ፊደል


ይህ ምልክት በተለይም በአንደኛ ክፍል መጽሐፍ በመጀመሪያዎቹ ምዕራፎች ለትምህርት የቀረቡትን
አዳዲስ ወይም ተተኳሪ ፊደሎች ይወክላል፤

ማጣመር/መነጠል
ይህ ክፍል ቃላትን በማንበብና ወደተለያዩ ክፍሎች በመነጠል ወይም በማጣመር ላይ ስለሚያተኩር፣
ልጆቹ ቃላቱን እንዲያነቡና በተገቢ የፊደል አሰዳደር ሥርዓት እንዲጽፉ ያግዛቸዋል።

በክፍል ውስጥ ልጆች

„„ ቃላትን “ማጣመር”፡- ቃላቱ የተመሠረቱባቸውን ፊደሎች ወይም የቃላቱን የተነጣጠሉ


አሀዶች ለየብቻ ያነባሉ፤ መልሰውም አንድ ላይ ይሏቸዋል።

„„ ቃላትን “መነጠል”፡- ቃላቱን ያነባሉ፤ ቀጥለውም ወደፊደላት ወይም ወደአነስተኛ አሀዶች


ይነጥላሉ።

„„ ፍቺ ያላቸውን የቃላቱን አሀዶች ለይተው ያነባሉ።

vi አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ጠቃሚ ምክር... ረ


በክፍል ውስጥ ልጆች

„„ ያልተማሯቸውን ሞክሼና ውስብስብ ፊደላት ይማራሉ፤

„„ ፊደሎች በቃላት ውስጥ ያላቸውን ንበት (የድምጽ ውክልናቸውን) ይማራሉ፤

„„ በእያንዳንዱ ፊደል የሚጀምሩ ወይም የሚጨርሱ ቃላትን ለመለየት ይችላሉ፤

„„ ፊደላቱን በማየት የሚወክሏቸውን ድምፆች መጥራት ይለማመዳሉ፤

„„ የተማሯቸውን ፊደሎች ይለማመዳሉ።

ወላጅ/አሳዳጊ በቤት ውስጥ ልጆችዎን እንደሚከተለው ያግዙ

„„ ቀደም ብለው የተማሯቸውን ፊደላት እንዳይረሷቸውና አጣርተው እንዲለዩዋቸው ያግዙ፤

„„ የፊደሎቹን ስምና የሚወክሏቸውን ድምፆች የትኞቹ እንደሆኑ ይጠይቋቸው፤

„„ በተለያዩ ፊደሎች የሚጀምሩ ቃላትን አስበው እንዲናገሩ ይጠይቋቸው።

ማንበብ
ይህ ምልክት የሚነበቡ አዳዲስ ቃላትንና ተዘውታሪ ቃላትን፣ ዓረፍተነገሮችን፣ አጫጭር ታሪኮችን
ወይም ምንባቦችን የትምህርት ይዘቶች ያመላክታል።

በክፍል ውስጥ ልጆች

„„ ታሪኮችን ወይም ምንባቦችን አቀላጥፈው ያነባሉ፤ ወይም ለመረዳት ያነባሉ፤

„„ የድኅረንባብ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ፤

„„ ስለአነበቡት ታሪክ ወይም ምንባብ ይወያያሉ፤

„„ ስለአነበቡት ታሪክ ወይም ምንባብ ይጽፋሉ።

የተማሪ ወላጅ/አሳዳጊ በቤት ውስጥ ልጆችዎን እንደሚከተለው ያግዙ

„„ የየዕለቱን ትምህርት ታሪኮች ወይም ምንባቦች እንዲያነቡ ይጠይቋቸው፤

„„ በክፍል ውስጥ ያነበቧቸውን ታሪኮች ወይም ምንባቦች በቤት ውስጥ እንዲያነቡላችሁ


ያበረታቷቸው፤

„„ ለማንበብ የሚያስቸግሯቸውን ቃላት ደጋግመው እንዲያነቧቸው ያበረታቷቸው፤

„„ በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን ታሪኮች ስለመውደዳቸው ወይም ስለአለመውደዳቸው በምክንያት


እንዲገልጹ ይጠይቋቸው።

vii አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ጠቃሚ ምክር... ሰ


ቃላት
ይህ ምልክት የአዳዲስ ቃላትን ትምህርት ይዘት ያመለክታል።

በክፍል ውስጥ ልጆች

„„ ከመምህራቸውና ከሚያዳምጡት ታሪክ ወይም ምንባብ አዳዲስ ቃላትን ይማራሉ፤


„„ አዳዲስ ቃላትን ከሥዕሎች ወይም ከፍቻቸው ጋር ያዛምዳሉ፤
„„ ለቃላት ተመሳሳይና ተቃራኒ ይሰጣሉ፤
„„ ቃላቱን በዓረፍተነገር ውስጥ መጠቀም ይለማመዳሉ።

የተማሪ ወላጅ/አሳዳጊ በቤት ውስጥ ልጆችዎን እንደሚከተለው ያግዙ

„„ ቀደም ሲል በተማሯቸው ትምህርቶች ውስጥ ያሉ ሥዕሎችን ተመልክተው በሥዕሎቹ


የተወከሉትን ቃላት እንዲገልጹ ይጠይቋቸው፤
„„ ስለተማሯቸው ቃላት እንዲነግሩዎ ይጠይቋቸው።

መጻፍ
ይህ ምልክት ፊደላትንና ቃላትን የመጻፍ፣ እንዲሁም ሐሳብን በሥዕልና/ወይም በቃላት የመግለጽ
የትምህርት ይዘቶችን ያመላክታል፤

በክፍል ውስጥ ልጆች

„„ ፊደላትን መጻፍ ይለማመዳሉ፤


„„ በተማሯቸው ፊደላት ቃላትን ይጽፋሉ፤
„„ ቃላትን በተገቢ የፊደላት አሰዳደር መጻፍ ይለማመዳሉ፤
„„ አጫጭር የቃል ጽሕፈትና የፊደል አሰዳደር ሙከራዎችን ይሠራሉ፤
„„ ሀሳባቸውንና ግንዛቤያቸውን ለሌሎች ለማጋራት ዓረፍተነገሮችን ይጽፋሉ።

የተማሪ ወላጅ/አሳዳጊ በቤት ውስጥ ልጆችዎን እንደሚከተለው ያግዙ

„„ የእጅ ጽሕፈታቸውን እንዲያሻሽሉ ፊደላትንና ቃላትን በትክክል እንዲገለብጡ ይጠይቋቸው፤


„„ ቃላትን በተገቢ የፊደል አሰዳደር ሥርዓት በጽሑፍ እንዲለማመዱ ያድርጉ፤
„„ በሚሳሳቱበት ጊዜ በአግባቡ በመደገፍ ተግተው እንዲሠሩ ያበረታቷቸው፤
„„ አጫጭር ዓረፍተነገሮች እንዲጽፉ ያበረታቷቸው፤ ለቤተሰብ አባላት ወይም ለጓደኞቻቸው
አጫጭር መልዕክቶችን በጽሑፍ እንዲያስተላልፉ ያበረታቷቸው።

viii አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ጠቃሚ ምክር... ሸ


ምዕራፍ
አልባሳት
1
1.1.1 ማዳመጥ የጽዮን አዳዲስ ልብሶች

ቅድመማዳመጥ
የምታውቋቸውን የልብስ ዓይነቶች ዘርዝሩ።

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. በግራ በኩል የተደረደሩትን የልብስ ዓይነቶች ተናገሩ።

ለ. የጽዮን የደንብ ልብስ ምን ምን ይመስላችኋል?

ቃላት

1. ፊደላቱን ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. ሹ-ራ-ብ ሐ. አ-ባ-ቷ

ለ. ቀ-ሚ-ስ መ. ል-ብ-ስ

2. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. ጥቁር ኮት

ለ. ጥበብ ቀሚስ

ሐ. የደንብ ልብስ

መ. የበዓል ልብስ

1 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 1


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

የአክሊሉ ነጭ ሸሚዝ
አክሊሉ ነገ የልደቱ ቀን ነው። ታላቅ እህቱ በጧቱ ተነሳች። የአክሊሉን
ልብሶች ማጠብ ጀመረች። ነጩን ሸሚዝና አዲስ የተገዛውን ጥቁር ኮት
በሳፋ ውስጥ አደረገች። በኦሞና በዉኃ ዘፈዘፈቻቸው። ከጥቂት ደቂቃዎች
በኋላ ልብሶቹን በማሸት ልታጥብ ዝቅ አለች። ያየችውን ማመን አቃታት።
እናቷን ተጣራች። እናቷም ባዩት ነገር በጣም ተናደዱ። ወዲያውኑ አንድ
ሐሳብ መጣላቸው። ነጩን ሸሚዝ በሌላ ሳፋ በበረኪናና በኦሞ እንደገና
ዘፈዘፉት። ከአንድ ስዓት በኋላ አለቀለቁት። ሸሚዙ እንደድሮው ነጭ ሆነ።
እህቱና እናቱም ተቃቅፈው በደስታ ዘለሉ።

1.1.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ በጥንድ ተወያዩ።
ሀ. “ህልም እልም” ከሚለው ርዕስ ምን ትገምታላችሁ?
ለ. ልብስ ለመግዛት ገንዘብ ከየት ታገኛላችሁ?

“ህልም እልም”
አንድ አርሶአደር ብዙ የወተት ላሞች ነበሩት። አንድ ቀን ለልጁ በማሰሮ የሞላ
ወተት እንድትሸጥ ሰጣት። ወተቱንም ሸጣ ጫማ፣ ቲሸርት፣ ጉርድቀሚስና
ሸራጫማ እንድትገዛ ፈቀደላት። ልጅቷም በመንገድ እየሄደች ብዙ ነገሮችን
አሰበች።
“ነገ አዲስ ልብስ ለብሼ ወደትምህርትቤት እሄዳለሁ። ከሌሎች ልጆችም
የበለጠ ቆንጆ እሆናለሁ። ልጆችም አብረን እንጫወት ይሉኛል። እኔ ግን
ፊቴን እንዲህ አድርጌ እመልስባቸዋለሁ” ብላ አንገቷን መለስ አደረገች። ከራሷ
ላይ የነበረው ማሰሮ ተንሸራቶ በመውደቁ ተሰባበረ፤ ወተቱም የመንገዱን
ጠርዝ ይዞ ቁልቁል ፈሰሰ።

2 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 2


ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. አርሶአደሩ ለልጁ በማሰሮ ወተት የሰጣት ለምንድን ነው?

ለ. ማሰሮው ወድቆ የተሰባበረው ለምንድን ነው?

ሐ. ልጅቷን ብትሆኑ ኖሮ ምን ታደርጉ ነበር?

መ. በመጨረሻ ልጅቱ ምን የምታደርግ ይመስላችኋል?

የቃላት አጠቃቀም
ቃላቱን ከሥዕላዊ መግለጫዎቹ ጋር አዛምዱ።
“ሀ” “ለ”

1. ጥልፍቀሚስ ሀ.

2. ሹራብ ለ.

3. ሸሚዝ ሐ.

4. ቁምጣ መ.

5. ቲሸርት ሠ.

3 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 3


1.1.3 ማዳመጥ የጽዮን አዳዲስ ልብሶች

ቅድመማዳመጥ
ሥዕሉን ተመልከቱና ስለታሪኩ ገምቱ።

ድኅረማዳመጥ
የሚከተሉትን ቃላት/ሐረግ ፍቺ ተናገሩ።

ሀ. ከረቫት ለ. ኮት ሐ. ቲሸርት መ. የደንብ ልብስ

ቃላት

ፊደላቱን አጣምራችሁ ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. ተ - ሰ - ቅ - ለ - ዋ - ል ሐ. ተ - ደ - ር - ድ - ረ - ዋ - ል

ለ. ተ - ቀ - ም - ጠ - ዋ - ል መ. ተ - ን - ጠ - ል - ጥ - ለ - ዋ - ል

አቀላጥፎ ማንበብ
“የአክሊሉ ነጭ ሸሚዝ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

1.1.4 መጻፍ

1. ፊደላቱን ነጣጥላችሁ በትክክል አንብቡና ጻፉ።

ሀ. አንገቷን ለ. ሸራ ጫማ ሐ. ፈቀደላት

2. ፊደላቱን አጣምራችሁ ጻፉና አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. እ - ን - ድ - ት - ሸ - ጥ ሐ. ቁ - ል - ቁ - ል

ለ. እ - የ - ሄ - ደ - ች መ. እ - ን - ጫ - ወ - ት

3. የምታውቋቸውን የአልባሳት መጠሪያ ቃላት ዘርዝራችሁ ጻፉ።


ምሳሌ፡- ቀሚስ

4 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 4


4. ቃላቱን በብዙ ቁጥር ጻፉ።

ምሳሌ፡- ቀሚስ → ቀሚሶች

ሀ. ቀሚስ ለ. ልብስ ሐ. ሸሚዝ መ. ማሰሮ

5. መምህራችሁ የሚያነቡላችሁን ቃላት እያዳመጣችሁ በትክክል ጻፉ።

1.1.5 ክለሳ

1. የመነሻ ፊደሉን በሌላ ፊደል በመተካት አዲስ ቃል መሥርታችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ልብስ → ጥብስ

ሀ. ወረት ለ. ድርስ ሐ. ደመረ

2. በምሳሌው መሠረት መድባችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- በላይ የሚለበሱ → ሹራቦች

በውስጥ የሚለበሱ → የጡት ማስያዣዎች

ሱሪዎች ካልሲዎች የስፓርት ልብሶች

ጃኬቶች ቀሚሶች የውስጥ ሱሪዎች

ኮቶች የውስጥ ልብሶች የጡት ማስያዣዎች

3. በሚከተሉት ቃላት ብቻ ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ምሳሌ፡- እኔ የደንብ ልብስ አለኝ።

አዲስ ልብስ ቀይ ሽርጥ አለኝ

እኔ ሸሚዝ ቀሚስ ከድር ገዛች

ለበሰች ሥራነሽ ለበሰ የደንብ ልብስ

5 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 5


1.2.1 ማዳመጥ ቀኑብሽ በገና በዓል

ቅድመማዳመጥ
በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ።

ሀ. ሥዕሉ ስለምን እንደሚገልፅ ገምቱ?

ለ. በበዓል ቀን ምን ዓይነት ልብስ ትለብሳላችሁ?

ድኅረማዳመጥ
ሀ. ባለታሪኮቹ እነማን ናቸው?

ለ. የቀኑብሽ እናት ልጃቸውን “ቆንጆ ሆነሻል” ያሏት ለምንድን ነው?

ሐ. ቀኑብሽ ለእናቷ እግሯን ያሳየቻቸው ለምን ይመስላችኋል?

ቃላት

1. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ኩታ → ሰዎች በበዓል ቀን ኩታ ይለብሳሉ።

ሀ. ጥልፍ ሐ. የአንገት ልብስ

ለ. ጃኖ መ. የገና በዓል

2. ፊደላቱን በማጣመር ጽፋችሁ ድምጽ በማሰማት አንብቡ።

ምሳሌ፡- አ-ም-ሮ-ብ-ሻ-ል → አምሮብሻል

ሀ. ይ-ከ-በ-ራ-ል

ለ. ተ-ጫ-ም-ታ-ለ-ች

ሐ. ኩ-ታ-ቸ-ው-ን

6 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 6


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ተንኮለኛዋ አይጥ
አንድ ቀን አንዲት ተንኮለኛ አይጥ ከአንድ ቤት ሾልካ ገባች። ቀስ ብላ
በቁምሳጥኑ ውስጥ ተደበቀች። ፎጣውን፣ ሱሪውን፣ ጋቢውን፣ ሸሚዙን ፣
ኮቱንና ቀሚሶችን በጣጠሰቻቸው። በማግስቱ ባለቤቱ ወጥመድ አጠመደ።
አይጧ ተያዘች። ባለቤቱም ከወጥመድ በማላቀቅ ሊገላት ሲሞክር ድመቷ
እመር ብላ ያዘቻት።

1.2.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሥዕሉን ተመልከቱና ስለታሪኩ ገምቱ።

የልጁ መኝታቤት
ልጁ ከትምህርትቤት ሲመለስ ለመጫወት ይቸኩላል።
የደንብ ልብሱንና ቦርሳውን ባገኘበት ይጥላል። አንድ
ቀን እናቱ ወደመኝታቤት ገቡ። ቤቱ ተዝረክርኳል።
ልጁን ጠሩና “ጥፋትህን አውቀሃል?” አሉት። “አዎ
እማዬ! አሁን አስተካክላለሁ” አለ። ወዲያውኑ የደንብ
ልብሱን ካልጋው ራስጌ ባለው ቁምሳጥን አጣጥፎ ከተተ። ቦርሳውን
በመደርደሪያ ላይ አስቀመጠ። ጫማውን በአልጋው ሥር አኖረ።

(ምንጭ፤ አማርኛ እንደአፍ መፍቻ ቋንቋ ከ2ኛ የተማሪ መጽሐፍ፣ መጠነኛ ለውጥ ተደርጎ የተወሰደ)

7 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 7


ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።
ሀ. የልጁ መኝታቤት የተዝረከረከው ለምንድን ነው?
ለ. የልጁ እናት ወደልጁ መኝታቤት ለምን ገቡ?

ሐ. ልጁን ብትሆኑ ኖሮ ምን ታደርጉ ነበር?

የቃላት አጠቃቀም
በምሳሌው መሠረት በልጁ መኝታቤት የሚታዩትን አልባሳት ጻፉ።
ምሳሌ፡- ካልሲ

1.2.3 ማዳመጥ ቀኑብሽ በገና በዓል

ቅድመማዳመጥ
የበዓላት ልብሶች መቼ መቼ የሚለበሱ ይመስላችኋል?

ድኅረማዳመጥ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።
ሀ. ቀኑብሽና ቤተሰቦቿ ወደየት ሄዱ?
ለ. የቀኑብሽ እናት “የፈራሁት አልቀረም” ያሉት ለምን ይመስላችኋል?

ሐ. ቀኑብሽ በእሩር መመታቷን እንዴት አወቃችሁ?

ቃላት

1. መምህራችሁ የሚያነቡላችሁን ቃላት እያዳመጣችሁ በትክክል ጻፉ።


2. የቃሉን የመሀል ፊደል በመግደፍና በሌላ ፊደል በመተካት ጻፉና ድምፅ
በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።
ምሳሌ፡- ደመቀ → ደበቀ፣ ደረቀ፣ ደቀቀ ….
ሀ. ለበሰ ለ. አጠበ ሐ. ወጠረ
8 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 8
አቀላጥፎ ማንበብ
“ተንኮለኛዋ አይጥ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

1.2.4 መጻፍ

1. ፈደላቱን ነጣጥላችሁ ጻፉና ድምፅ በማሰማት በትክክል አንብቡ።

ሀ. የ-ጥ-ል-ፍ-ቀ-ሚ-ስ ሐ. የ-ሴ-ት-ጫ-ማ

ለ. የ-አ-ን-ገ-ት-ል-ብ-ስ መ. የ-ጃ-ኖ-ጥ-ለ-ት-ኩ-ታ

2. ለሚከተሉት ሥዕሎች መጠሪያ ቃላት ጻፉ።

ሀ ለ ሐ መ
3. ቃላቱን ወይም ፊደላቱን በመግድፍና ቦታ በመቀያየር ሌሎች ቃላት
መሥርቱ።

ምሳሌ፡- የጥልፍ ቀሚስ፡- ቀስ፣ ጥል፣ ልጥ፣ ጥልፍ፣ ቀሚስ፣ ፍልጥ….

ሀ. የአንገት ልብስ ለ. ጃኖ ጥለት

4. የቃላቱን ቦታ በማስተካከል ዓረፍተነገር መሥርቱ።


ምሳሌ፡- በአልጋ ሥር ወድቋል ካልሲው፡-
ካልሲው በአልጋ ሥር ወድቋል።
ሀ. ጨዋታ እወዳለሁ መጫወት
ለ. ልብስ ነጭ እወዳለሁ መልበስ
ሐ. አከብራለሁ ከወላጆቼ ጋር በዓላትን

9 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 9


5. በልጁ ምኝታቤት ውስጥ የሚገኙትን ቁሶች ዘርዝራችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ቁምሳጥን

1.2.5 ክለሳ

1. የቃሉን የመነሻ ፊደል በመግደፍና ሌላ ፊደል በመተካት አዲስ ቃል


መሥርታችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ወረሰ → ጨረሰ፣ ደረሰ፣ ፈረሰ፣ አረሰ

ሀ. ደበቀ ለ. ቀጠረ ሐ. በለጠ

2. የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ አሟልታችሁ


ጻፉ።

የጥጥ
ነጭ

ልብስ

1.3.1 ማዳመጥ ተሸላሚው አብዱ

ቅድመማዳመጥ
በወላጆች ቀን፣ በትምህርትቤት መከፈቻ ቀን ወይም በሽልማት ሥርዓት
ምን ዓይነት ልብሶችን ትለብሳላችሁ? ለምን?

10 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 0


ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. አብዱ በጧቱ ተነስቶ ምን አደረገ?

ለ. አብዱ የተደሰተው ለምንድን ነው?

ሐ. የእናንተ የደንብ ልብስ ምን ዓይነት ቀለም አለው?

ቃላት

1. ቃላቱን በሹክሹክታ አንብቡ።

ሀ. ነጭ ሸሚዝ ለ. ጥቁር ሱሪ ሐ. ቢጫ ሹራብ

2. ፊደላቱን አጣምራችሁ አንብቡ።

ምሳሌ፡- መ-ል-ክ → መልክ

ሀ. ቁ-መ-ና ለ. ን-ጹ-ህ ሐ. አ-ጨ-በ-ጨ-ቡ

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

“ታጥቦ ጭቃ”
በአንድ ግቢ ውስጥ ሰው፣ ውሻና አህያ ይኖሩ ነበር። ሰውዬው ልብስ አጣቢ
ነው። አንድ ቀን የወለል ምንጣፍ፣ ብርድልብስ፣ በርካታ መጋረጃዎች፣
ስጋጃና የተለያዩ አልባሳትን በመያዝ ወደወንዝ ወርዶ ሲያጥብ ዋለ።
በመጨረሻ በአህያው ያልደረቁ ልብሶችን ጭኖ ወደቤት ተመለሰ። ውሻው
እርቦት ስለነበር እጥፍጥፍ ብሎ ተኛ። አህያው ጭነቱ እስከሚወርድለት
በአጥሩ ጥግ ቆመ። ሰውዬው ልብሶቹን አውርዶ በልብስ ማስጫ ገመዱ ላይ
ካሰጣ በኋላ ወደመኝታቤቱ ገብቶ ተኛ።

ባጋጣሚ እኩለሌሊት ላይ ሌባ ገባና የተሰጡትን ልብሶች ሲሰበስብ አህያው


በድንገት አናፋ። ሌባው ደንግጦ አጥሩን ዘሎ ሮጠ። ባለቤቱም በአህያው

11 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 01


ማናፋትና በሌባው ዳና ተደናግጦ ከእንቅልፉ ነቃና አየተደነባበረ ከቤት
ሲወጣ ውሻው ጥቅልል ብሎ ተኝቷል። የተሰጡት ልብሶች በመሬት ላይ
ወዳድቀዋል። ሰውዬውም ወይ “ታጥቦ ጭቃ” በማለት ለራሱ አጉረመረመ።

1.3.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በቃል መልሱ።
ሀ. ሥዕሉንና ርዕሱን በማስተዋል ስለታሪኩ ገምቱ?
ለ. “የቸኮለ አፍሶ ለቀመ” ማለት ምን ማለት ነው?

“የቸኮለ…..”
ቀኑ የመስከረም ዋዜማ ነው። የመንደሩ ወጣት
ወንዶች ተጠራሩና ወደወንዝ ወረዱ። ልብሳቸውን
አወላለቁ። ፎጣቸውን፣ ጃኬታቸውን፣ ካኔትራቸውን፣
የውስጥ ሱሪያቸውን፣ ቁምጣቸውን፣ ካልሲያቸውን፣
ጫማቸውን ባንድ ላይ ከመሩ። ከዚያም ወደወንዙ
እየዘለሉ ገቡ። ሲዋኙ፣ ሲዋኙ ዋሉ። ሰማዩ ዳመነ፤
ጉርምርምታ ተሰማ፤ የመብረቅ ብልጭታው ተደጋገመ። ወጣቶቹ ዋናቸውን
አቋረጠው ወደልብሳቸው እየተሯሯጡ ሄዱ። ያገኙትን ልብስ እያነሱ በችኮላ
መልበስ ጀመሩ።

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።
ሀ. ወጣቶቹ ተጠራርተው ወደወንዝ የወረዱት ለምንድን ነው?
ለ. ወጣቶቹ ዋናቸውን ያቋረጡት ለምንድን ነው?
ሐ. በአካባቢያችሁ በመስከረም ዋዜማ ወጣቶች ምን ያደርጋሉ? ለምን?
መ. የወጣቶቹ ስህተት ምንድን ነበር?
12 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 02
የቃላት አጠቃቀም
ለሥዕሎቹ መጠሪያ ቃላት ጻፉ።

ሀ ለ ሐ

1.3.3 ማዳመጥ ተሸላሚው አብዱ

ቅድመማዳመጥ
ለሚከተሉት ቃላት ፍቺ ጻፉ።

ሀ. ፈንጥቃለች ለ. ቁመና ሐ. አረፈ

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. በእናንተ ትምህርትቤት ተማሪዎች የሚሸለሙት ለምንድን ነው?

ለ. እናንተስ መሸለም ትፈልጋላችሁ? ለምን?

ሐ. አብዱ በመሸለሙ ምን የሚሰማው ይመስላችኋል?

ቃላት

1. አጣምራችሁ ድምፅ በማሰማት አንብቡና በትክክል ጻፉ።

ሀ. መ-ም-ህ-ሯ → መምህሯ ሐ. ብ-ር-ሀ-ኗ-ን

ለ. ጓ-ደ-ኞ-ቿ መ. እ-ስ-ክ-ር-ቢ-ቶ

13 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 03


2. ባለኹለት፣ ባለሦስትና ባለአራት ፊደል ቃላትን መሥርታችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ቢጫ፣ ሸሚዝ

ቁ ጓ ተ ሸ ይ ጣ

ዝ ጫ ሰ ሚ

ቢ ኛ ደ መ ቀ ና

አቀላጥፎ ማንበብ
“ታጥቦ ጭቃ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

1.3.4 መጻፍ

1. ፊደላቱን ድምፅ በማሰማት በትክክል አንብቡና አጣምራችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ጃ-ኬ-ታ-ቸ-ው-ን → ጃኬታቸውን

ሀ. ካ-ኔ-ት-ራ-ቸ-ው-ን ሐ. ካ-ል-ሲ-ያ-ቸ-ው-ን

ለ. ቁ-ም-ጣ-ቸ-ው-ን

2. የመድረሻ ፊደልን በመግደፍና በሌላ ፊደል በመተካት ቃላትን


መሥርታችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ዘለቀ → ዘለለ → ዘለፈ….

ሀ. ጠራ ለ. ወረደ ሐ. ዘመረ

4. በብዙ ቁጥር ቅርጽ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ቁምጣ → ቁምጣዎች

ሀ. ጫማ ለ. ካኔትራ ሐ. ፎጣ መ. ካልሲ

14 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 04


5. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ወደወንዝ ወረዱ

ሀ. ወደተራራ ለ. ወደመንደር ሐ ወደቤት

1.3.5 ክለሳ

1. ድምጽ በማሰማት በትክክል አንብቡና ጻፉ።

ሀ. ነጭ ሸሚዝ ለ. የውስጥ ሱሪ ሐ. ቁምጣ ሱሪ

2. የሚከተሉትን ቃላት በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ሸሚዝ → ነጭ ሸሚዝ፣ ሰፊ ሸሚዝ፣ ጠባብ ሸሚዝ

ሀ. ልብስ ለ. ፎጣ ሐ. ካልሲ መ. ጫማ

3. የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ አሟልታችሁ


ጻፉ።

ምሳሌ፡-

ይታጠባል ይለቀማል

ይሰጣል

ልብስ ይደርቃል ጥጥ

ይተኮሳል

ይለበሳል

15 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 1 አልባሳት 05


ምዕራፍ
ወቅቶች
2
2.1.1 ማዳመጥ ብልኋ ጉንዳን

ቅድመማዳመጥ
ስለጉንዳን የምታውቁትን ተናገሩ።

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ባለታሪኮቹ እነማን ናቸው?

ለ. ዘው ብሎ፤ የገባው ማን ነው? ለምን?

ሐ. የምስጥ አገባብ ትክክል ነው? ለምን?

ቃላት

1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት በትክክል አንብቡ።

ሀ. ጉንዳን ለ. ምስጥ ሐ. ጉድጓድ

2. ፊደላቱን በማጣመር አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. ሰ-ኔ ---- ሰኔ ሐ. ነ-ሐ-ሴ

ለ. ሐ-ም-ሌ መ. መ-ስ-ከ-ረ-ም

16 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች 06


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ዙሪያክብ ጨዋታ
ናሆም፣ ዘውዲቱ፣ ዘሃራና ሀሰን የአንድ ሰፈር ልጆች ናቸው። ዛሬ እለቱ
እሁድ ነው። ከእነዘውዲቱ ሰፈር ጠባብ ሜዳ አለ። ሜዳው ላይ ክብ ሰርተው
ይጫወታሉ። የመሀል ዳኛው ናሆም ነው።

ናሆም “ሰኞ”፤ ሲል ሁሉም ይቆማሉ። “ማክሰኞ” ሲል ሁሉም ይቀመጣሉ።


“ረቡዕ” ሲል ሁሉም ይተቃቀፋሉ። ከዚህ ውጭ ሌሎች ቀናት ሲጠሩ
ይንቀሳቀሳሉ። ጨዋታው ተጀመረ። ናሆም “ቅዳሜ” አለ። ከዘውዲቱ
በስተቀር ሌሎቹ ተቃቀፉ። ዘውዲቱ የጨዋታው አሸናፊ ሆነች።

(ከአማርኛ እንደአፍ መፍቻ ቋንቋ 2ኛ ከፍል መመማሪያ መጽሐፍ መጠነኛ ለውጥ ተደርጎ የተወሰደ)

2.1.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሀ. ሥዕሉንና ርዕሱን አስተውላችሁ ስለታሪኩ ገምቱ።

ለ. ከምች፤ ማለት ምን ማለት ነው?

ሐ. “ሰኞ ማክሰኞ” ለመጫወት ምን ምን ነገሮች ያስፈልጋሉ?

“ሰኞ ማክሰኞ”
ይቤላ፣ ሰሚራና አረጋ ከግቢው ወለል ላይ መስመር
አዘጋጁ። መስመሮቹ ተገጣጥመው ሰባት ክፍሎችን
ሠሩ። የመጀመሪያውን የመስመር ክፍል “ሰኞ”
አሉት። በመቀጠል እያንዳንዱን የመስመር ክፍል 1 2 3 4
5 6 7

ማክሰኞ፣ ረቡዕ፣ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜና እሁድ


ብለው በቅደምተከተል ሰየሙት። ተራው የይቤላ ነው። ከምቹን ሰኞ ላይ
አሳረፈች፤ ከዚያም ከማክሰኞ ጀምራ እየዘለለች ተጫወተች። በኹለተኛው

17 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች 07


ዙር ከምቹን ማክሰኞ ላይ አሳረፈችና ለመዝለል ሞከረች። ረቡዕ ላይ
መድረስ አቃታትና ወደቀች።

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. በጨዋታው የተሳተፉት ልጆች እነማን ናቸው?

ለ. ይቤላ ረቡዕ ላይ መድረስ ያቃታት ለምንድን ነው?

ሐ. ጨዋታውን ለማሸነፍ ምን ማድረግ ያስፈልጋል?

የቃላት አጠቃቀም
በሚከተሉት ሥዕሎች የልጆቹን ልብሶች መጠሪያ ቃላት ጻፉ።

5 6 7
1 2 3 4

2.1.3 ማዳመጥ ብልኋ ጉንዳን

ቅድመማዳመጥ
ስለምስጥ የምታውቁትን ተናገሩ።

ድኅረማዳመጥ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ባለታሪኮቹ እነማን ናቸው?

ለ. ጉንዳኗ ጉድጓዷን የደፈነችው ለምንድን ነው?

18 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች 08


ሐ. ጉንዳኗ የሠራችው ሥራ “መልካም ነው” ብላችሁ ታስባላችሁ? ለምን?

መ. ከጉንዳንና ከምስጥ የክረምት ወራት የሚመቸው ለማን ነው? ለምን?

ቃላት

1. ቃላቱን በትክክል እያነበባችሁ ጻፉ።

ሀ. ጉንዳን ለ. ሚያዝያ ሐ. ጉድጓድ መ. መግቢያ

2. ፊደላቱን በማጣመር በትክክል አንብቡ።

ሀ. እ-ሰ-ጥ-ሀ-ለ-ሁ ለ. ሁ-ለ-ታ-ች-ን-ም

አቀላጥፎ ማንበብ
“ዙሪያክብ ጨዋታ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

2.1.4 መጻፍ

1. ፊደላቱን አጣምራችሁ ድምጽ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡና ጻፉ።

ሀ. መ-ጀ-መ-ሪ-ያ → መጀመሪያ ሐ. አ-ሳ-ረ-ፈ-ች

ለ. ተ-ጫ-ወ-ች መ. እ-የ-ዘ-ለ-ለ-ች

2. በቃሉ መነሻ ላይ ፊደል በመግደፍና ሌላ ፊደል በመተካት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ሠራ → በራ፣ ጠራ፣ ፈራ፣ ደራ

ሀ. ክብ ለ. ሰፈረ ሐ. ጀመረ

3. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ሰኞ፣ ማክሰኞና ረቡዕ

ሀ. አራት ዐምስት ስድስት

ለ. ዘውዲቱ ናሆም ዘሀራ

19 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች 09


2.1.5 ክለሳ

1. ለሚከተሉት ቃላት ፍቺ ጻፉ።

ሀ. ወለል ለ. አሳረፈች ሐ. መሰየም መ. ተምች

2. “ሰኞ ማክሰኞ” የሚለውን ታሪክ በጥንድ እየተቀባበላችሁ በትክክል፣


በፍጥነትና በተገቢ አገላለፅ አንብቡ።

3. በሚከተሉት ቃላት ብቻ ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ሰሚራ፣ ምኒልክና ለምለም መስመር አዘጋጁ።

ሰሚራ ሮጡ አዘጋጁ አሰመሩ አብዱ

አሸናፊ ይቤላ መስመር ተጫወቱ ተማከሩ

አረፉ ሰላማዊት አስቀመጡ ሠሩ

ለምለም ምኒልክ ተቀመጡ

2.2.1 ማዳመጥ የዓመቱ ወቅቶች

ቅድመማዳመጥ
ሀ. ስለወቅቶች የምታውቁትን ተናገሩ?

ለ. ወቅቶች ስንት ናቸው?

ድኅረማዳመጥ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ምንጮች ኩልል ብለው የሚታዩት መቼ ነው? ለምን ይመስላችኋል?

ለ. የክረምት ወቅት ከሌሎቹ ወቅቶች በምን ይለያል?

ሐ. እህል በጎተራ ለመክተት ምን ምን ተግባራት ይከናወናሉ? ለምን?

20 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች !


ቃላት

1. ቃላቱን በጥንድ እየተቀባበላችሁ በትክክል አንብቡና ጻፉ።

ሀ. ክረምት ሐ. ጥቅምት

ለ. ግንቦት መ. መጋቢት

2. ፊደላቱን በማጣመር ድምጽ በማሰማት በትክክል አንብቡ።

ሀ. ይ-ዘ-ራ-ል → ይዘራል

ለ. ይ-ሰ-በ-ሰ-ባ-ል

ሐ. ይ-ጎ-መ-ራ-ል

መ. ያ-ሸ-ታ-ል

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

“በውድቅት ሌሊት”
ሌሊቱ ተጋምሶ ውድቅት ላይ ነው። ኃይለኛ ዝናብ ይዘንባል። “በዛብህ!
በዛብህ! ኧረ በዛብህ!” ተጣራች ባለቤቱ ማለፊያ። “ምን ሆንሽ?” አለ በዛብህ፤
“ምነው! አንተዬ አይታይህም እንዴ?” አለችው። “ምኑ?” በማለት ዙሪያውን
ሲመለከት፣ ቤቱ ውስጥ ጎርፉ ገብቶ ሞልቶታል። “ኧረግ! ኧረግ! እንዴት
ጉድ ተሠራን! በይ ነይ ተከተዪኝ! ‘ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ’ አለ ያገሬ
ሰው” አለና፣ ዝናብ እየመታቸው የጎርፉን ማፋሰሻ ቦይ መቆፈር ጀመሩ።

(ከአማርኛ እንደአፍ መፍቻ ቋንቋ 2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ ተሻሽሎ የተወሰደ)

21 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች !1


2.2.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሀ. ሥዕሉንና ርዕሱን በማስተዋል ታሪኩ ስለምን እንደሚገልጽ ገምቱ።

ለ. አደይ አበባ የሚያብበው በመቼ ወር ነው? ለምን ይመስላችኋል?

አደይ
ክረምቱ አልፎ መስከረም ጠብቷል። ልምላሜው
ቀልብን ይሠርቃል። የንፋሱ ሽውታ መንፈስን
ያድሳል። አበባ የዛሬዋን ቀን በጣም ናፍቃታለች።
ትምህርትቤት ከተዘጋ ኹለት ወራት አልፈዋል።
ሐምሌንና ነሐሴን ቤተሰቦቿን ሰትረዳ ከርማለች።
ዛሬ የትምህርትቤት መከፈቻ ቀን ነው። አበባ
የትምህርትቤት ልብሷን ለብሳ በጧቱ ከቤቷ ወጣች። ከሩቅ ጓደኛዋን አየቻት።

ሁለቱም እየሮጡ መጡና ተገናኙ፤ ተቃቀፉ፤ ተሳሳሙ። ናፍቆታቸውን


ሊወጡ፣ የትምህርት ሰዓት እስኪደርስ ከአንድ ዛፍ ሥር ተቀመጡ። ከፊት
ለፊታቸው የሚታየውን አደይ አበባ እያዩ፡-

“መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ፣


እንኳን ሰው ዘመዱን ይጠይቃል ባዳ”
የሚለውን ዘፈን ድምፅ በማሰማት አዜሙት።
(ከአማርኛ እንደአፍ መፍቻ ቋንቋ 2ኛ ከፍል መመማሪያ መጽሐፍ መጠነኛ ለውጥ ተደርጎ የተወሰደ)

ድኅረንባብ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።
ሀ. አበባ ቀኗን የናፈቀቻት ለምንድን ነው?
ለ. በመስከረም ወር ምን ዓይነት አበባዎች ይታያሉ?
ሐ. አበባ ቤተሰቦቿን ምን ዓይነት ሥራ ትረዳቸዋለች?
22 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች !2
የቃላት አጠቃቀም
በ“ሀ” ሥር ለቀረቡት ቃላት ተቃራኒ ከ“ለ” ሥር መርጣችሁ አዛምዱ።

“ሀ” “ለ”

1. ቅርብ ሀ. መለያየት
2. ክረምት ለ. መሸ
3. ዝግ ሐ. ክፍት
4. ጠባ መ. በጋ
5. መገናኘት ሠ. ሩቅ
ረ. መጥፋት

2.2.3 ማዳመጥ የዓመቱ ወቅቶች

ቅድመማዳመጥ
የሚከተሉትን ቃላት ፍቺ ተናገሩ።
ሀ. ወቅት ለ. ጸደይ ሐ. በልግ መ. በጋ ሠ. ክረምት

ድኅረማዳመጥ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ሰዎች በበጋ ወቅት ምን ምን ሥራዎችን ይሠራሉ?

ለ. በጸደይ ወቅት የሚዘሩ ሰብሎች ምን ምን ናቸው?

ሐ. በክረምት ወራት ብቻ የሚዘሩ ሰብሎች ምን ምን ናቸው?

23 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች !3


ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት እያነበባችሁ አጣምራችሁ ጻፉ።

ሀ. ገ-በ-ሬ-ዎ-ች ሐ. ወ-ቅ-ቶ-ች

ለ. ሰ-ብ-ሎ-ች መ. ም-ን-ጮ-ች

2. በምሳሌው መሠረት ተጣማሪ ቃላትን አዋቅራችሁ ጻፉ።

ምሰሌ፡- የጥቅምት እሸት

ሀ. የእህል ለ. የበጋ ሐ. የክረምት መ. የገበሬ

አቀላጥፎ ማንበብ
“በውድቅት ሌሊት” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

2.2.4 መጻፍ

1. ነጣጥላችሁ ጻፉና አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ምሳሌ፡- ጠብቷል → ጠ-ብ-ቷ-ል

ሀ. ተቃቀፉ ለ. ቤተሰቦቿ ሐ. ጓደኛዋ

2. በቃሉ መሀል ፊደል በመግደፍና በሌላ በመተካት ቃል መሥርቱና


ጻፉ።

ምሳሌ፡- አለፈ → አደፈ፣ አጠፈ፣ አቀፈ፣ አረፈ ….

ሀ. ጠየቀ ለ. በቀለ ሐ. ደረቀ

3. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. መስከረም ሐ. ጠየቀ

ለ. ፈነዳ መ. ልምላሜ

24 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች !4


2.2.5 ክለሳ

1. ለሚከተሉት ቃላት ፍቺ ጻፉ።

ሀ. ጠባ ለ. ዘመድ ሐ. መርዳት መ. መክረም

2. “አደይ” በሚለው ታሪክ ከመምህራችሁ ጋር እየተቀባበላችሁ በትክክል፣


በፍጥነትና በጥሩ አገላለፅ አንብቡ።

2.3.1 ማዳመጥ አስካልና ሄኖክ

ቅድመማዳመጥ
ሥዕሉን አስተውላችሁ ስለታሪኩ ገምቱ።

ድኅረማዳመጥ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ሔኖክ አስካልን ወደእርሻው ቦታ የወሰዳት ለምንድን ነው?

ለ. የበቆሎ እሸት ተጠብሶ ወይም ተቀቅሎ የሚበላው ለምንድን ነው?

ሐ. አስካልን ብትሆኑ ኖሮ ሄኖክን ምን ዓይነት ጥያቄ ትጠይቁት ነበር?

ቃላት

1. ሐረጋቱን ድምፅ በማሰማት በትክክል አንብቡ።

ሀ. የአክስት ልጅ ሐ. የጤፍ ቡቃያ

ለ. የበቆሎ እሸት መ. የእርሻ ቦታ

2. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- የአክስት ልጅ

ሀ. የጓሮ ለ. የገጠር ሐ. የሚጠበስ

25 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች !5


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ግጥም አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ክረምትና በጋ
የካቲት መውቂያ ነው/ ክምሩ ፈረሰ፣

ገለባው ተለየ /ነፋሱም ነፈሰ፣

መጋቢት መጣልን/ ዓመት ተጋመሰ፣

የበጋውም ወራት/ ሄደ እየቀነሰ።

ሚያዝያ ተተካ/ መጋቢት አለፈ፣

የበልጉ ዝናብም/ ጣለ አርከፈከፈ።

ሐምሌ ሊገባ ነው/ ደመናውን ጭኖ፣

ቀንና ሌሊቱን/ በዝናብ ጨፍኖ።

ነሐሴ ተተካ/ ኃይለኛው ክረምት፣

ያወርደው ጀመረ/ የዝናብ መዓት።

ዐምስት ዐምስት ቀን/ ሦስቱን ዓመታት፡

በአራተኛው ዓመት/ ስድስት ቀን ያላት፣

ዘመን አሻጋሪ /የጳጉሜ ወር ናት።

26 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች !6


2.3.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሥዕሉንና ርዕሱን አስተውሉና ታሪኩ ስለምን እንደሚገልጽ ገምቱ።

ወይ አለማስተዋል!
አንድ መንገደኛ ከገበያ ወደቤቱ ሲመለስ
ደከመውና ከሾላ ዛፍ ሥር ጋደም አለ።
ዙሪያውን በዓይኑ መቃኘት ጀመረ።
ባጋጣሚ ወደላይ ሲያንጋጥጥ የሾላ ፍሬ
አየ። ወደታች ሲያማትር ደግሞ በዱባው
ሐረግ ላይ ትልቅ የዱባ ፍሬ አየ። እጅግ
ተደነቀና ተፈጥሮን ወቀሰ።

ትንሽ እንደቆየ እንቅልፍ አሸለበው።


የበሰለችዋ የሾላ ፍሬ አፍንጫው ላይ
ወደቀች። ብንን ብሎ ተነሳ። “ይገርማል!
የዱባው ፍሬ ከላይ ተንጠልጥሎ ቢሆን
ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር?” አለ። ያሰበውን
ሁሉ እያሰታወሰ “ወይ አለማስተዋል!”
በማለት ራሱን ወቀሰ።

ድኅረንባብ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. መንገደኛው ከሾላ ዛፍ ሥር ጋደም ያለው ለምንድን ነው?

ለ. የዱባው ፍሬ ከላይ ተንጠልጥሎ ቢሆን ምን ይውጠኝ ነበር፤ ያለው


ለምንድን ነው?

ሐ. “ወይ አለማስተዋል!” ማለት ምን ማለት ነው?

27 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች !7


የቃላት አጠቃቀም
ስለሥዕሎቹ ምንነት ጻፉ።

2.3.3 ማዳመጥ አስካልና ሄኖክ

ቅድመማዳመጥ
የሚከተሉትን ቃላት ፍቺ ተናገሩ።

ሀ. አስጎበኛት ለ. ቡቃያ ሐ. አዘረዘረ

ድኅረማዳመጥ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ከጤፍ ሌላ በክረምት ወራት ምን ዓይነት ቡቃያዎች ይታያሉ?

ለ. የቡቃያና የእሸት ልዩነት ምንድን ነው?

ሐ. ክረምት ባይኖር ምን የሚከሰት ይመስላችኋል? ለምን?

ቃላት

1. ቃላቱን ድምጽ በማሰማት በትክክል አንብቡ።

ሀ. ያወርደው ለ. ዓመታት ሐ. ኃይለኛው

2. የቃላቱን የመሀል ፊደል በመግደፍ ሌሎች ቃላትን መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ቀነሰ → ቀደሰ፣ ቀመሰ፣ ቀወሰ፣ ቀለሰ….

ሀ. ከመረ ለ. ፈረሰ ሐ. ጠየቀ

28 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች !8


አቀላጥፎ ማንበብ
“ክረምትና በጋ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

2.3.4 መጻፍ

1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት በትክክል አንብቡና ጻፉ።

ሀ. የበሰለችው ለ. ይገርማል ሐ. እያስታወሰ

2. የቃላቱን ፊደላት በመግደፍ ሌሎች ቃላት መሥርቱ።

ምሳሌ፡- አሸለበው → አሸ፣ አለ፣ አለው፣ አበው፣ አሸው፣ አሸለበ…

ሀ. ሲያንጋጥጥ ለ. ሲያቀረቅር ሐ. አለማስተዋል

3. አጣምራችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ወደቀ - ች → ወደቀች

ሀ. አሰበ - ች ለ. ወቀሰ - ች ሐ. ተነሳ - ች

2.3.5 ክለሳ

1. በምሳሌው መሠረት ቃላት መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ወቃ - እየተወቃ

ሀ. ቆፈረ ለ. ቆረጠ ሐ. ደረቀ

2. የሚከተሉትን ወራት ከመስከረም ጀምራችሁ በቅደምተከተል


አስተካክላችሁ ጻፉና አንብቡ።

መጋቢት ሰኔ የካቲት ሃምሌ

ግንቦት ጥር መስከረም ሚያዝያ ጳጉሜ

ጥቅምት ኅዳር ነሐሴ ታኅሳስ

29 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 2 ወቅቶች !9


ምዕራፍ
ታሪኮች
3
3.1.1 ማዳመጥ የእንቆቅልሽ ጨዋታ

ቅድመማዳመጥ
ርዕሱን አስተውሉና ታሪኩ ስለምን እንደሚገልጽ ገምቱ።

ድኅረማዳመጥ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. በእንቆቅልሽ ጨዋታ ሂደት መላሾች መልስ ከጠፋቸው ምን ይቀጣሉ?

ለ. “ቀይ ዘንዶ በዋሻ ውስጥ ተጋድሞ” ለሚለው እንቆቅልሽ መልሱ “ምላስ”


የሆነው ለምን ይመስላችኋል?

ሐ. የእንቆቅልሽ ጨዋታ አጀማመሩ እንዴት ነው? የሚጨረሰውስ እንዴት


ተብሎ ነው?

መ. የእንቆቅልሽ ጨዋታ ለምን ይጠቅማል?

ቃላት

1. እንቆቅልሾችን በትክክል በማንበብ መልስ ጻፉ።

ሀ. ስሄድ አገኘኋት ስመለስ አጣኋት።

ለ. አባ ሲሏቸው ቆብ የላቸው።

ሐ. ትንሽ ምላጭ ሀገር ትላጭ።

30 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች V


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

“ብልጡ ቀበሮ”
አንድ ቀን አንዲት ድመት ከአንድ ነጋዴ ዓይብ ሠርቃ ትሄዳለች። በዚህ
ጊዜ አንድ ውሻ ያያታል። አይቡን ሊወስድባት ፈለገና ተጠጋት። ድመቷ
ግን የውሻውን ዓይን መቧጨር ጀመረች። ውሻው ደግሞ ይነክሳት ጀመር።
ድመቷ አላዋጣ ሲላት “ቀበሮ ይዳኘን” አለችው። ውሻውም ተስማማ። ቀበሮም
ጉዳያቸውን ካዳመጠ በኋላ “የማትረቡ ናችሁ!” አለና ዓይቡን ከኹለት እኩል
አካፈላቸው። ውሻው ግን “የእኔ ድርሻ አንሷል!” ብሎ ተቃወመ። ቀበሮም
“አዎ!... እውነትም” አለና ከድመቷ አንድ ጉርሻ ጎረሰለት። ድመቷም በተራዋ
እንዴ! የእኔ ድርሻ ቀንሷል! አለች። ቀበሮም “ልክ ነው፤ አንሷል”፤ አለና
ከውሻው ድርሻ ጎረሰለት። እንዲህ እያለ በየተራ የሁለቱንም ድርሻ እየጎረሰ
ባዷቸውን አስቀራቸው።

3.1.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሀ. ሥዕሉን አስተውሉና ስለታሪኩ ገምቱ።

ለ. ተኩላ ምን ዓይነት እንሰሳ ነው?

ሐ. ተኩላና ሰው ቢጣሉ ማን የሚያሸንፍ ይመስላችኋል?

መንገደኛውና ተኩላ
አንድ መንገደኛ ከዛፍ ግንድ ጋር የታሰረ ተኩላ
ያገኛል። ተኩላውም “እባክህ ፍታኝ” አለው።
መንገደኛውም “ምንገዶኝ” ብሎ ፈታው። በመቀጠል
ተኩላ “እበላሀለሁ” አለው። “በል ጦጢት ትፍረድና
ትበላኛለህ” አለው። ሁለቱም ተያይዘው ወደጦጢት

31 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች V1


ሄዱ። ጦጢትም ሰውዬውን “መጀመሪያ ተኩላን ስታገኘው እንዴት ነበር?
በድርጊት አሳየኝ” አለችው። ሰውዬውም አስሮ አሳያት። ጦጢትም “በል
ሰውዬ! ዱላ ከእጅህ! ተኩላ ከፊትህ!” እንግዲህ እወቅበት አለችው። ሰውዬውም
ተኩላውን በዱላው ቀጥቅጦ ገደለው።

ድኅረንባብ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. መንገደኛውና ተኩላው ጦጢትን ለዳኛነት የመረጧት ለምንድን ነው?

ለ. የጦጢት ፍርድ ትክክል ነው ትላላችሁ? ለምን?

ሐ. ከተኩላና ከሰውዬው ስህተት የማን የሚበልጥ ይመስላችኋል?

መ. መንገደኛውን ብትሆኑ ኖሮ ምን ታደርጉ ነበር? ለምን?

ሠ. ከታሪኩ ምን ተማራችሁ? ጠቃሚ ነው? ወይስ ጎጂ? ለምን?

የቃላት አጠቃቀም
በምሳሌው መሠረት ዓረፍተነገሮቹን አሟልታችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ተኩላ “እባክህ ፍታኝ!” አለ።

ሀ. ደብተር ስትዋሱ _______ ትላላችሁ።

ለ. መምህራችሁን ፈቃድ ስትጠይቁ _______ ትላላችሁ።

ሐ. ጓደኞቻችሁን መርዳት ስትፈልጉ _______ ትላላችሁ።

መ. ለታላላቆቻችሁ መቀመጫ ወንበር ስትለቁ _______ ትላላችሁ።

3.1.3 ማዳመጥ የእንቆቅልሽ ጨዋታ

ቅድመማዳመጥ
ሀ. የእንቆቅልሽን የአጨዋወት ቅደምተከተል ተናገሩ።

ለ. የእንቆቅልሽ ተጫዋቾች በቁጥር ስንት ናቸው? ለምን ይመስላችኋል?

32 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች V2


ድኅረማዳመጥ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. “እንቆቅልሽ የማሰብ ችሎታን ያሳድጋል” ቢባል ትስማማላችሁ? ለምን?

ለ. በእንቆቅልሽ ጨዋታ ርስበርስ መወዳደር ለምን የሚጠቅም ይመስላችኋል?

ሐ. በእንቆቅልሽ ጨዋታ አሸናፊ ወይስ ተሸናፊ መሆን ነው የሚመረጠው?

መ. በእንቆቅልሽ ጨዋታ የተሸናፊዎች ግዴታ ምንድን ነው? ለምን?

ቃላት

1. ነጣጥላችሁ አንብቡና ጻፉ።

ሀ. እንዲያውቁ ለ. እንዲገነዘቡ ሐ. እንዲመራመሩ

2. የቃላቱን የመሀል ፊደል በመግደፍና ሌላ ፊደል በመተካት ሌሎች


ቃላት መሥርታችሁ በትክክል ጻፉ።

ምሳሌ፡- ሰበረ → ሰከረ፣ ሰመረ፣ ሰፈረ

ሀ. ጠረበ ለ. ቀለመ ሐ. ቀበሮ መ. ደመረ

አቀላጥፎ ማንበብ
“ብልጡ ቀበሮ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

3.1.4 መጻፍ

1. ፊደላቱን አጣምራችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- መ-ን-ገ-ደ-ኛ → መንገደኛ

ሀ. ሰ-ው-ዬ-ው-ም ለ. ስ-ታ-ገ-ኘ-ው ሐ. ተ-ኩ-ላ-ው-ም

2. በሚከተሉት ቃላት የተሟሉ ዓረፍተነገሮች መሥርታችሁ ጻፉ።

ሀ. ተኩላ ለ. ስታገኘው ሐ. ሰውዬው መ. መንገደኛ

33 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች V3


3. አራት ነጥብን (።)፣ ቃለአጋኖን (!)፣ ጥያቄ ምልክትን (?) በመጠቀም
የተሟሉ ዓረፍተነገሮች መሥርቱ።

ምሳሌ፡- እናቴ እኮ! ትወደኛለች።

ጦጢት ምን አደረገች?

3.1.5 ክለሳ

1. የቃላቱን ቅደምተከተል በማስተካከል የተሟሉ ዓረፍተነገሮች ጻፉ።

ምሳሌ፡- ተጓዘ ብዙ መንገደኛው → መንገደኛው ብዙ ተጓዘ።

ሀ. ዳኛ ሆነች ጦጢት

ለ. ተንኮለኛ ነው ተኩላ እንስሳ

ሐ. የታሰረ ከግንድ ጋር ተኩላ አገኘ

መ. በል ሰውዬ ተኩላ ነው ከፊትህ

2. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- አንዱ ተቀማጭ ሌላው ተንቀጥቃጭ።

መልስ ምድብ
ተቀማጭ፡- ድንጋይ ሕይወት አልባ
ተንቀጥቃጭ፡- ቄጤማ ከአትክልት

ሀ. ሳታጠባ የምታሳድግ

ለ. ቀይ መነኩሴ፣ በትራቸው በትረ ሙሴ

ሐ. ሰው ፈረሱ፣ ጠፍር ልጓሙ

መ. አጠማጠሙ እንደቄስ፣ አላላሱ እንደውሻ

34 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች V4


3.2.1 ማዳመጥ የራበው ውሻ

ቅድመማዳመጥ
ሥዕሉን ተመልከቱና ስለታሪኩ ገምቱ።

ድኅረማዳመጥ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባደመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ውሻው ወደሰፈሩ እንዴት መሄድ ቻለ?

ለ. አራጁ ለውሻው ሳንባ የወረወረለት ለምንድን ነው?

ቃላት

1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት በትክክል አንብቡ።

ሀ. ኩሬ ለ. ጎረሰ ሐ. ቅርጫ መ. ክረምት

2. አጣምራችሁ በትክክል አንብቡ።

ሀ. ኩ-ር-ም-ት ለ. መ-ን-ደ-ር

ሐ. ደ-ፈ-ረ-ሰ መ. ወ-ረ-ወ-ረ-ለ-ት

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ቀበሮና ቁራ
አንዲት ቀበሮ ምግብ ፍለጋ ብዙ ተንከራተተች። በጣም ሰለደከማት ከዛፍ
ሥር ተቀመጠች። ቁራ፣ ሙዳ ሥጋ ባፉ ይዞ ከዛፍ ላይ አረፈ። ቀበሮ ድንገት
አየችው። ሆዷ በረሀብ ተላወሰ። ዘዴ ዘየደች። ድምጽዋን አለሰለሰችና “አንተ
ቁራ እንደመልክህ ድምጽህ ካማረ ንጉሥ ትሆናለህ!” አለችው። ቁራው
በሰማው ነገር በጣም ተደሰተ። ድምጹን ለማሰማት አፉን ሲከፍት ሙዳ
ሥጋው ወደቀ።

35 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች V5


3.2.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሀ. ሥዕሉንና ርዕሱን በትክክል በማስተዋል ስለታሪኩ ገምቱ።

ለ. ጎፈር፤ ማለት ምን ማለት ነው? የት የሚገኝ ይመስላችኋል?

ሐ. ሰዎች አንበሳን ሊያለምዱት የሚችሉ ይመስለችኋል? እንዴት?

“ብልኋ ሴት”
በባለቤቷ ባህርይ የተቸገረች አንዲት ሴት ነበረች። አንድ
ቀን የሴት አያቷን ምክር ጠየቀች። አያቷም የአንበሳ
ጎፈር እንድታመጣ መከሯት። አንበሳውን እንዴት
እንደምትቀርብ ስታወጣ ስታወርድ ሰነበተች። ከዚያም
ብዙ ሥጋ ይዛ ወደጫካ ሄደች። በመጀመሪያው ቀን
እጅግ ብዙ ሜትሮችን ርቃ ጉማጅ ሥጋ ወረወረችለት።
በሚቀጥለው ቀን ቀረብ ብላ ሥጋውን አስቀመጠች። በዚህ ዓይነት ሁኔታ
ርቀቷን እየቀነሰች ወደአንበሳው ተጠጋች። አንበሳውም ጠረኗንና ዳናዋን
እየለመደ መጣ። በመጨረሻም ይታከካት ጀመር።

ድኅረንባብ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።
ሀ. ስለታሪኩ ቀድማችሁ የገመታችሁት ትክክል ነበር? ለምን?
ለ. አያቷ የአንበሳ ጎፈር እንድታመጣ ያዘዟት ለምን ይመስላችኋል?
ሐ. አንበሳ ምን ዓይነት እንስሳ ይመስላችኋል? እንዴት አወቃችሁ?
መ. ሰዎች ከዱር እንስሳት ጋር መላመድ ይችላሉ? እንዴት?

36 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች V6


የቃላት አጠቃቀም
በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ቀረበ → እየቀረበች

ሀ. ቀነሰ ለ. ተጠጋ ሐ. ተቸገረ

3.2.3 ማዳመጥ የራበው ውሻ

ቅድመማዳመጥ
ለሚከተሉት ቃላት ፍቺ ስጡ።

ሀ. ቅርጫ ሥጋ ለ. ሳንባ ሐ. ኩሬ መ. ታከካት

ድኅረማዳመጥ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባደመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ኩሬው የደፈረሰው ለምን ይመስላችኋል?


ለ. ውሻው በእርግጥ በኩሬው ውስጥ ሌላ ውሻ አይቷል? እንዴት?
ሐ. ውሻው በመጨረሻ ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል? ለምን?

ቃላት

1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት በትክክል አንብቡና ጻፉ።

ሀ. ሳንባውን ለ. አራጁ ሐ. ፍለጋ

2. ድምፅ በማሰማት በትክክል አንብቡና አጣምራችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ሀ. አ-ጠ-ገ-ባ-ቸ-ው → አጠገባቸው

ለ. ባ-ጋ-ጣ-ሚ ሐ. ተ-መ-ለ-ከ-ተ መ. ሲ-ከ-ፋ-ፈ-ሉ

37 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች V7


አቀላጥፎ ማንበብ
“ቀበሮና ቁራ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

3.2.4 መጻፍ

1. ነጣጥላችሁ ድምጽ በማሰማት በትክክል አንብቡና ጻፉ።

ሀ. እንደምትቀርብ ለ. እንድታመጣ ሐ. በመጀመሪያው

2. በምሳሌው መሠረት ጻፉና በትክክል አንብቡ።

ምሳሌ፡- ለመደ፤ እየለመደ፣ እየለመደች፣ እየለመዳችሁ፣…..

ሀ. ጠየቀ ለ. አሰበ ሐ. ቀረበ መ. ለመደ

3. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- አንበሳ → ጎፈር

ሀ. ፈረስ ለ. ዶሮ ሐ. ጃርት መ. በሬ

3.2.5 ክለሳ

1. ሐረጋቱን አቀላጥፋችሁ አንብቡና በትክክል ጻፉ።

ሀ. ቅርጫ ሥጋ ለ. ሙዳ ሥጋ ሐ. ብልኋ ሴት

2. “ብልኋ ሴት” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

3.3.1 ማዳመጥ በቅሎ ለምን መካን ሆነች?

ቅድመማዳመጥ
ሀ. መካን፤ ማለት ምን ማለት ነው?

ለ. በቅሎ ምን አይነት እንስሳ ነች?

ሐ. በቅሎ ትወልዳለች? ለምን?

38 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች V8


ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።
ሀ. ታሪኩ የተፈፀመው መቼ ነው?

ለ. በቅሎ ለምን መከነች?

ሐ. ታሪኩ የተፈፀመው የት ነው?

መ. ድርጊቱ እንዴት ተፈፀመ?

ሠ. ድርጊቱ ለምን ተፈፀመ?

ቃላት

1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. ከመቅፅበት ለ. እምቢታዋን ሐ. እያጉረመረሙ

2. ፊደል በመግደፍና ቦታ በመቀያየር ቃላት መሥርቱ።

ምሳሌ፡- አለቀሰች → አለ፣ ሰቀለ፣ አለች፣ ቀለሰ፣ አለቀሰ

ሀ. ሊሰማሩ ለ. አበዛባቸው ሐ. ተመነጠቀ

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

የተዛባ ፍርድ
አንድ ቀን አንበሳ፣ ነብር፣ ጅብና አህያ ክፉ ቀን መጣባቸው። ተሰበሰቡ።
“የሠራነው ኃጢያት ነው” ለዚህ ያበቃን በማለት ኃጢያታቸውን ለመናዘዝ
ተስማሙ። የከፋ ኃጢያት የሠራውም ሊፈረድበት ውል ገቡ። በመጀመሪያ
አንበሳ ተነሳና “አንዲት ላም ከበረት ስትወጣ አግኝቼ በላኋት” አለ። እንስሳቱም
“ከበረት ማን ውጪ አላት? አንተ ጥፋተኛ አይደለህም!” አሉት። ቀጥሎ
ነብር፣ ተነሳና “በጫካ ውስጥ ፍየል አግኝቼ በልቻለሁ።” አለ። እነሱም
“ከእረኞች ማን አምልጪ አላት? አንተ ጥፋተኛ አይደለህም” አሉት።

39 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች V9


በሦስተኛ ደረጃ ጅብ ተነሳና “አንዲት በግ ላቷን በጐሮኖው ቀዳዳ አሹልካ
አግኝቼ በልቻለሁ” አለ። “ማን አሾልኪ አላት? ጥፋተኛ አይደለህም” ተባለ።
በመጨረሻም አህያ ተነሳችና “ጌታዬ በመንገድ ላይ ከሰው ጋር ሲያወራ
እንደተጫንኩ ሳር ነጭቻለሁ” አለች። “ጌታሽ ቆሞ ማን ሳር ነጪ አደረገሽ?
መዓት ያመጣሽብን አንቺ ነሽ” ብለው ተከፋፍለው በሏት።

(ፈቃደ አዘዘ። (1993፡38)። የስነቃል መመሪያ፤ መጠነኛ መሻሻል ተደርጎ የተወሰደ)

3.3.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ለሚከተሉት ቃላት ፍቺ ስጡ።

ሀ. ወረራ ለ. አርበኛ ሐ. መፋለም

የፍኖተሰላም ስያሜ
ጣሊያኖች ኢትዮጵያን በቅኝግዛት ለመያዝ አስበው በ1928 ዓ.ም ወረራ
አካሄዱ። የኢትዮጵያ አርበኞችም በዱር በገደሉ ተፋለሙ። ከዐምስት ዓመታት
በኋላ አርበኞች ጣሊያኖችን አሸነፉ። ጣሊያኖችም እግሬ አውጪኝ፤ ብለው
ወደሀገራቸው ተመለሱ። አፄ ኃይለሥላሤ በጦርነቱ ወቅት ወደውጪ
ሀገር ሄደው የዓለም መንግሥታት ወረራውን እንዲያወግዙ ሲጠይቁ ቆዩ።
ጣሊያኖች ተሸንፈው ሲወጡ አፄ ኃይለሥላሤ በሱዳን በኩል ወደሀገራቸው
ተመለሱ። ወደአዲስ አበባ ለመጓዝ “ወጀት” ከምትባል ከተማ አደሩ።
በማግስቱ ወደአዲስ አበባ ለመጓዝ ሲነሱ “በሰላም ወደሀገራችን ስለገባንና
የሰላም መንገድ ስለሆነልን “ወጀት” የምትባለውን ከተማ “ፍኖተሰላም” ትባል
ብለው ሰየሟት።

ድኅረንባብ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. አፄ ኃይለሥላሤ ወደውጪ ሀገር የሄዱት ለምንድን ነው?

ለ. ጣሊያኖች ወደሀገራቸው የተመለሱት ለምንድን ነው?


40 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች #
ሐ. ቅኝግዛት ማለት ምን ማለት ነው?

መ. ጣልያን ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ የፈለገችው ለምንድን ነው?

ሠ. አርበኞች በዱር በገደል የተፋለሙት ለምንድን ነው?

የቃላት አጠቃቀም
በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ፍኖተ - ሰላም → ፍኖተሰላም

ሀ. ደብረ - ማርቆስ ሐ. ደብረ - ታቦር

ለ. ደብረ - ብርሃን መ. ደብረ - ወርቅ

3.3.3 ማዳመጥ “በቅሎ ለምን መካን ሆነች?”

ቅድመማዳመጥ
ሀ. በቅሎዎች የሚራቡት እንዴት ነው?

ለ. በበቅሎና በፈረስ መካከል ያለው ልዩነትና ዝምድና ምንድን ነው?

ድኅረማዳመጥ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ታሪኩ የተፈፀመው የት ነው?

ለ. ታሪኩ ስለእንማን ይናገራል?

ሐ. ምንምን ድርጊቶች ተከናወኑ?

መ. ታሪኩ በምን ተጀመረ? በምንስ ተጠናቀቀ?

41 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች #1


ቃላት

1. አጣምራችሁ አንብቡና ጻፉ።

ሀ. እ-ም-ቢ-ታ-ዋ-ን ሐ. የ-ተ-ራ-ራ-ቁ-ት-ም

ለ. እ-ን-ስ-ሳ-ዋ

2. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ነጨ → ነጭቻለሁ

ሀ. አመለጠ ለ. በላ ሐ. አገኘ መ. ነጨ

አቀላጥፎ ማንበብ
“የተዛባ ፍርድ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

3.3.4 መጻፍ

1. አጣምራችሁ በማንበብ በትክክል ጻፉ።

ሀ. ኢ-ት-ዮ-ጵ-ያ

ለ. መ-ን-ግ-ስ-ታ-ት

ሐ. አ-ር-በ-ኞ-ች

መ. ሰ-የ-ሟ-ት

2. በሚከተሉት ቃላት በምሳሌው መሠረት ዓረፍተነገሮች መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ከተማ → በከተማ በርካታ ህዝብ ይኖራል።

በከተማ ብዙ ሸቀጦች ይሸጣሉ።

ሀ. አርበኛ ለ. ሰላም ሐ. ሀገር

42 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች #2


3. በምሳሌው መሠረት አጣምራችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- አዲስ - አበባ → አዲስአበባ

ሀ. አዲስ - ዘመን ሐ. ቀይ - ባሕር

ለ. ባሕር - ዳር

3.3.5 ክለሳ

1. በምሳሌው መሠረት ዐምስት ጥምር ቃላት በትክክል ጻፉ።

ምሳሌ፡- ሀ. ባሕርዛፍ

ለ. ደብረኤልያስ

2. “የተዛባ ፍርድ” የሚለውን ታሪክ በግላችሁ በትክክል፣ በፍጥነትና በጥሩ


አገላለጽ አንብቡ።

3. ስለምትወዷቸው የዱር እንስሳት አጭር አንቀጽ ጽፋችሁ አንበቡ።

43 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 3 ታሪኮች #3


ምዕራፍ
የጓሮ አትክልት
4
4.1.1 ማዳመጥ ሁለገቡ ፍራፍሬ

ቅድመማዳመጥ
ከዚህ በፊት የምታውቋቸውን የፍራፍሬ ዓይነቶች ተናገሩ።

ድኅረማዳመጥ
ሙዝን እንዴት መመገብ እንደሚቻል
በዝርዝር ጻፉ።

ምሳሌ፡- ሙዝ ተፈጭቶ ይበላል።

ቃላት

1. ፊደላቱን ድምጽ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. ፍ-ራ-ፍ-ሬ ሐ. የ-ሚ-ራ-ባ

ለ. ተ-ገ-ን-ፍ-ቶ መ. ተ-ፈ-ጭ-ቶ

2. በምሳሌው መሠረት ሌሎች ቃላት ጻፉና አንብቡ።

ምሳሌ፡- ፍራ - ፍሬ → ፍራፍሬ

ቅጠላ - ቅጠል → ቅጠላቅጠል

44 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት #4


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

እኔ ማን ነኝ?
ከፍራፍሬዎች እመደባለሁ። ቅርፄ ክብ ነው። ስበስል መልኬ ወደቢጫ
ያደላል። ተልጬ እበላለሁ። በውስጤ ከስምንት እስከ አሥር የሚደርሱ
ክፍልፋዮች አሉኝ። በየክፍልፋዮቹ ውስጥ ኹለት ወይም ከዚያ በላይ ዘሮች
አሉኝ። ሰዎች ሲመገቡኝ በጣም እጣፍጣለሁ። በውስጤ የያዘኩትም ዘር
በቅሎ ራሴን ይተካል። እኔ ማን ነኝ?

(ከ2ኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፍ መጠነኛ መሻሻል ተደርጎ የተወሰደ)

4.1.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሥዕሎቹን በማስተዋል ታሪኩ ስለምን እንደሚገልፅ ገምቱ።

“ሁለቱ ጓደኛሞች”
ሰላጣና ቆስጣ በጣም የሚዋደዱ አብሮ አደጎች ነበሩ።
ቆስጣ ለሰላጣ ከፍተኛ አክብሮት አለው። ሰላጣም
ቆስጣን እጅግ ይወደዋል። ሁለቱም በአፈር ውስጥ
ያሉ ማዕድናትን ይመገባሉ። ፀሐይን ይሞቃሉ፣
ዉኃም እኩል ይጠጣሉ። አንድ ቀን ሰዎች ቆስጣን ቀንጥሰው ወሰዱ።
ቆስጣም በጣም ተኩራራና በንቀት አየው።
“ሰዎች በየቀኑ እየቀነጠሱ ይወስዱኛል። አንተን ግን መጠቀም አልፈለጉም።
ለምን ይመስልሃል?” በማለት ሰላጣን ጠየቀው። ሰላጣም “አይ ጓደኛዬ!
አንተ መልክህ ጠቆር ቢልም ይፈልጉሀል። ስለዚህ ትበላለህ፤ እኔ ግን
መልኬ ፈካ ያለ ቢሆንም ለማባያነት ሎሚ/አቼቶ፣ ቃሪያ፣ ቲማቲም
ስለምፈልግ ወጪዬ ብዙ ነው” በማለት መለሰለት።

45 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት #5


ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ቆስጣን ቀንጥሰው የወሰዱት ለምንድን ነው?

ለ. ከሰላጣ ከቆስጣ ለምግብነት ለማዘጋጀት የሚቀለው የትኛው ነው?

የቃላት አጠቃቀም
ቆስጣንና ሰላጣን በማወዳደርና በማነጻጸር ጻፉ።

ቆስጣ አትክልት ሰላጣ


በስሎ ናቸው። በጥሬው
ይበላል። ይበላል።

4.1.3 ማዳመጥ ሁለገቡ ፍራፍሬ

ቅድመማዳመጥ
ሙዝ “ሁለገቡ ፍራፍሬ” የተባለው ለምን ይመስላችኋል?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. የሙዝ ልጣጭን በመጠቀም ፊታችንን እንዴት እናስውባለን?

ለ. ከሙዝ ፍሬ ለጥቅም የማይውለው የትኛው ክፍል ነው? ለምን?

ቃላት

1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንበቡ።

ሀ. ተልጦ ለ. ተቀቅሎ ሐ. ተፈጭቶ መ. ተቆርጦ

46 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት #6


2. የፊደሎቹን ቅደምተከተል በማስተካከል ቃላት መሥርቱ።

ምሳሌ፡- መቀልቀ → መቀቀል

ሀ. መደመብ ለ. መባራት ሐ. መገንድ መ. መላብት

አቀላጥፎ ማንበብ
“እኔ ማን ነኝ?” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

4.1.4 መጻፍ

1. ነጣጥላችሁ ጻፉና አንብቡ።

ምሳሌ እየቀነጠሱ → እ-የ-ቀ-ነ-ጠ-ሱ

ሀ. ይመስልሀል ለ. ለማባያነት ሐ. የሚዋደዱ

2. የሚከተሉትን ቃላት በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡-

ቆስጣ፡- ይቀነጠሳል → ይታጠባል → ይከተፋል → ይሠራል → ይበላል።

ሀ. ሰላጣ ለ. ካሮት ሐ. ጥቅል ጎመን

3. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ቆስጣ ይቀነጠሳል፤

ሀ. ቆስጣ ለ. ዛፍ ሐ. ጥጥ መ. አበባ

4. ስለሙዝና ስለብርቱካን ልዩነትና ተመሳስሎ ጻፉ።

ሙዝ ብርቱካን
ይበላሉ።
ልጣጩ ፊትን ብዙ ክፍሎች
ያስውባል። አሉት።

47 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት #7


4.1.5 ክለሳ

1. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ብርቱካን ለ. ሰላጣ ሐ. ቆስጣ መ. ሙዝ

2. እንደሰላጣና ቆስጣ ጓደኛ በመሆን ጭውውት አቅርቡ።

3. የሚከተሉትን ቃላት በምሳሌው መሠረት መድቧቸው።

ብርቱካን እንቁላል ሰላጣ ትርንጎ ጥቅል ጎመን

ቆስጣ ዓሳ ድንች ቀይሥር ካሮት

ምሳሌ፡- በስለው የሚበሉ → ዓሳ

በጥሬያቸው የሚበሉ → ሰላጣ

4.2.1 ማዳመጥ ፈጣኗ ሯጭ

ቅድመማዳመጥ
ሀ. ሰዎች ደስተኛና ጤነኛ የሚሆኑት እንዴት ነው?

ለ. ሥዕሉን ተመልክታችሁ ስለታሪኩ ገምቱ።

ድኅረማዳመጥ
የሥዕሎቹን መጠሪያ ቃላት ተናገሩ።

ሀ ለ ሐ መ

48 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት #8


ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. አ-ት-ክ-ል-ት ለ. እ-ሰ-ራ-ለ-ሁ ሐ. እ-መ-ገ-ባ-ለ-ሁ

2. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- የሽሮ + ወጥ → የሽሮ ወጥ

ሀ. የፓፓያ ለ. የሙዝ ሐ. የጤፍ

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

“ወይ አለማወቅ!”
“ተረኛ! ተረኛ!” አለ ነርሱ። ወይዘሮ ታሪኳ “አቤት!” ብለው የኹለት
ዓመት ልጃቸውን ይዘው ገቡ። “ምኑን ነው ያመመው?” ዶክተሯ ጠየቁ።
“አያዩትም! ጠጉሩ ሳስቷል፣ ሆዱ ተነፍቷል፤ ድዱም ይደማል” አሉ
ወይዘሮ ታሪኳ ልጃቸውን በአዘኔታ እየተመለከቱ።

ዶክተሯም መረመሩና “በጣም ያሳዝናል፤ እንደዚህ ያደረገው የተመጣጠነ


ምግብ አለማግኘቱ ነው። አሁንም ወተት፣ የተፈጨ ሥጋ፣ እንቁላል፣
ማር፣ ጥራጥሬ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ይመግቡት። ቶሎ ይሻለዋል።
ለአሁኑ ግን መድሃኒት አዝለታለሁ” በማለት አስረዷቸው። ወይዘሮ
ታሪኳም “ወይ አለማወቅ! ልጄን በምግብ እጥረት ገድዬው ነበር” በማለት
ተፀፀቱ።

(ከ2ኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፍ መጠነኛ መሻሻል ተደርጎ የተወሰደ)

49 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት #9


4.2.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሥዕሉን በመመልከት የተረዳችሁትን ግለጹ።

“የጓሮ አትክልትን ማልማት በብልሃት”


የጓሮ አትክልት ለማልማት ሰፊ ቦታና ብዙ
የእርሻ መሣሪያዎች አያስፈልጉም። ትንሽ
መቆፈሪያ፣ አካፋ፣ ባልዲ፣ የዉኃ ማጠጫና
የመሳሰሉትን መጠቀም ይቻላል። የመኖሪያ
ግቢያችን ሰፊ ባይሆን እንኳ አፈርን በተለያዩ
ጎድጓዳ ቁሳቁሶች በማድረግ አትክልት ማልማት ይቻላል። በተለይ በቶሎ
የሚደርሱ አትክልትና ፍራፍሬን በትንሽ ቦታ በማምረት ለምግብነት ማዋል
ይቻላል። ለምሳሌ ሽንኩርት፣ ሰላጣ፣ ቆስጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ ቲማቲም፣
ቃሪያ በማምረት መጠቀም ብልህነት ነው።

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።
ሀ. በግቢያችሁ/በጓሯችሁ ምን ዓይነት አትክልትና ፍራፍሬ በቅለዋል?
ለ. በጠባብ ቦታ በምን ዓይነት ዕቃዎች አትክልትን ማምረት ይቻላል?
ሀ. የታሪኩን ሐሳብ አጠር አድርጋችሁ ለክፍል ጓደኞቻችሁ ንገሯቸው።
ለ. የታሪኩን ሐሳብ በአንድ ዓረፍተነገር ግለጹ።

የቃላት አጠቃቀም
በምሳሌው መሠረት ሌሎች ቃላት ጻፉ።

ምሳሌ፡- አትክልት → ጎመን

ፍራፍሬ → ብርቱካን

50 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት $


4.2.3 ማዳመጥ ፈጣኗ ሯጭ

ቅድመማዳመጥ
ፈጣን ሯጭ ለመሆን ምን ያስፈልጋል፤ ብላችሁ ታስባላችሁ።

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ባለታሪኳ ማን ናት?

ለ. ባለታሪኳ ፈጣን ሯጭ የሆነችው እንዴት ነው?

ሐ. እናንተ ፈጣን ሯጭ መሆን ትፈልጋላችሁ? ለምን?

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. የ-ተ-ወ-ለ-ድ-ኩ-ት ሐ. የ-ም-መ-ገ-በ-ው

ለ. የ-ም-ት-ነ-ግ-ረ-ን መ. የ-ም-ሠ-ራ-ው

2. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- የሥጋ - ወጥ  የሥጋ ወጥ

ዱባ ሥጋ ሽሮ ክክ ድንች ምሥር

አቀላጥፎ ማንበብ
“ወይ አለማወቅ!” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

4.2.4 መጻፍ
1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት አንብቡና ጻፉ።

ሀ. መሣሪያዎች ለ. መቆፈሪያዎች ሐ. አካፋዎች

51 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት $1


2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ባልዲ ዉኃ ለመቅዳት ያገለግላል።

ሀ. ባልዲ ለ. ቃሪያ ሐ. ማዳበሪያ መ. አካፋ

4.2.5 ክለሳ

1. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ጠባብ ለ. ብልህ ሐ. ቁሳቁስ መ. ማዳበሪያ

2. ስለተለያዩ የጓሮ አትክልት ጥቅም ጻፉ።

3. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ጠጉሩ ሳስቷል።

ሀ. ጠጉሩ ለ. ሰውነቱ ሐ. ድዱ መ. ሆዱ

4. ሥዕሎችን በመጠቀም በምሳሌው መሠረት ዓረፍተነገሮች መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ባቄላ እንቁላልና ዓሣ መመገብ ጤናማ ያደርጋል።

52 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት $2


4.3.1 ማዳመጥ የጓሮ አትክልት ቦታ አዘገጃጀት

ቅድመማዳመጥ
ለሚከተሉት ቃላት ፍቺ ጻፉ።

ሀ. ማለስለስ ለ. ማፋሰሻ ቦይ ሐ. መመንጠር

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. የጓሮ አትክልት ቦታ ለማዘጋጀት ምን ምን ያስልጋል?

ለ. ቤተሰቦቻችሁ የጓሮ አትክልት ሲተክሉ ምን ያደርጋሉ?

ቃላት

1. አጣምራችሁ ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. ማ-ዘ-ጋ-ጀ-ት → ማዘጋጀት ሐ. ማ-ፋ-ሰ-ሻ

ለ. መ-ም-ረ-ጥ መ. መ-ቆ-ፈ-ር

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ማለስለሰ ለ. ስፍራ ሐ. ቦይ መ. መቆፈር

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

የሐና አመጋገብ
ሐና የኹለተኛ ክፍል ተማሪ ናት። አንድ ቀን የሳይንስ መምህራቸው
“ሁሉንም የምግብ ዓይነቶች በተመጣጠነ መልኩ መመገብ ያስፈልጋል፤
የተመጣጠኑ ምግቦች ለሰውነታችን ጥንካሬ ይሰጣሉ፤ የአስተሳሰብ እድገት
ያመጣሉ። አልፎ ተርፎም ውበትን ይጠብቃሉ። በተለይ አትክልትና
ፍራፍሬን መመገብ ጤናማ እንድንሆን ትልቅ አስተዋፅኦ አላቸው” በማለት
53 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት $3
አስተማሯቸው። ሐናም ከትምህርትቤት ስትመለስ ለቤተሰቦቿ “ከዛሬ ጀምሮ
ይሄን ምግብ አልወድም፤ ያንን እወዳለሁ ብዬ አልመርጥም፤ እናንተንም
አላስቸግርም አለቻቸው።”

(አማርኛ እንደአፍ መፍቻ 2ኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፍ ተሻሽሎ የተወሰደ)

4.3.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሥዕሉን ተመልክታችሁ ታሪኩ ስለምን እንደሚገልጽ ገምቱ።

ዝንጀሮና የአፕል ፍሬ
በወንዝ አጠገብ የበቀለች አፕል በአካባቢዋ ላሉ
እንስሳት ሲሳይ ነች። ዝንጅሮም የአፕል ፍሬ
እየተመገበች እምቡጥ ፅጌረዳ መስላ ትኖራለች።
አንድ ቀን ዝንጀሮ ለመዝናናት አፕሏን ይዛ
ወደወንዝ ወረደች። በወንዙ ዳር ዐዞ አገኘች።
ስለደነገጠች ቶሎ ብላ አፕሏን በዐዞው አፍ
ውስጥ ከተተችው። ዐዞውም እያጣጠመ ተመገበ።
ለእርሷም እንዲያመጣላት ሚስቱ ጠየቀችው።
ዝንጀሮን አመሰግኖ ወደቤቱ ሄደ። ለባለቤቱም ስለውሎው ነገራት።
በማግስቱ ዝንጀሮዋ ብዙ አፕል ይዛ መጣች። ዐዞውም ዝንጀሮዋን ወደቤቴ
ልውሰድሽ ብሎ በጀርባው አዝሎ ወደቤቱ ጉዞ ጀመሩ። ከወንዙ መሀል
ሲደርሱ “ባለቤቴ ልብሽን ትፈልገዋለች” አላት። ዝንጀሮም “ውይ! ከአፕሉ
ዛፍ ላይ ትቼው ነው የመጣሁት፤ መልሰኝና አውርጄ ልስጥህ” አለችው።
ዐዞም ልቧን ለመቀበል ጓጉቶ ወደወንዙ ዳር መለሳት።

54 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት $4


ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. ከዝንጀሮ ሌላ በዛፍ ላይ የሚኖሩ እንስሳት እነማን ናቸው?

ለ. ዐዞ ምን ዓይነት እንስሳ ይመስላችኋል?

ሐ. ዝንጀሮዋ በመጨረሻ ምን የምታደርግ ይመስላችኋል?

መ. እንደዝንጀሮ ያለ ሁኔታ ቢያጋጥማችሁ ምን ታደርጋላችሁ?

የቃላት አጠቃቀም
በምሳሌው መሠረት ሌሎች ሐረጋት ጻፉ።

ምሳሌ፡- የአፕል ፍሬ

4.3.3 ማዳመጥ የጓሮ አትክልት ቦታ አዘገጃጀት

ቅድመማዳመጥ
ከርዕሱ ምን ተረዳችሁ?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ቤተሰቦቻችሁ የጓሮ አትክልት ሲያዘጋጁ ምን ምን አስተውላችኋል?

ለ. ፍሎችን ለማፍላት ምን ዓይነት ቅድመዝግጅት ያስፈልጋል?

ሐ. የታሪኩን ድርጊቶች በቅደምተከተል ተናገሩ።

55 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት $5


ቃላት

1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. መመንጠር ለ. ማፍላት ሐ. መትከል

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ቦታ ለ. ስፍራ ሐ. ማጤን መ. ፍል

አቀላጥፎ ማንበብ
“የሐና አመጋገብ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

4.3.4 መጻፍ

1. ፊደላቱን ድምፅ በማሰማት አንብቡና አጣምራችሁ ጻፉ።

ሀ. አ-መ-ሰ-ገ-ነ ሐ. የ-አ-ፕ-ል-ፍ-ሬ

ለ. ከ-ተ-ተ-ች-ው መ. በ-ማ-ግ-ስ-ቱ

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. አዘለ ለ. አፕል ሐ. ወረደች መ. ፅጌረዳ

3. “ዝንጀሮና የአፕል ፍሬ” በሚለው ታሪክ መሠረት የዝንጀሮንና የአፕል


ዛፍን ልዩነት ግለፁ።

ምሳሌ፡-

ዝንጀሮ የአፕል ዛፍ

ብዙ ጠጉር አላት። ብዙ ቅጠሎች አሉት።

56 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት $6


4.3.5 ክለሳ

1. ዓረፍተነገሮቹን አስተካክላችሁ ጻፉ።

ሀ. አታለለችው ዐዞን ዝንጀሮ

ለ. አፍ ውስጥ በዝንጀሮው ከተተችው አፕሉን

ሐ. አፕሉን ወደወንዝ ይዛ ወረደች ዝንጀሮ

2. የምታውቋቸውን ታሪኮች/ተረቶች ለክፍል ጓደኞቻችሁ በቃል ተናገሩ።

3. ጅምር ዓረፍተነገሩን በመጠቀም “ዝንጀሮና የአፕል ፍሬ” የሚለውን


ታሪክ በራሳችሁ አገላለጽ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ዐዞም ወደወንዙ ዳር መለሳት።…

57 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 4 የጓሮ አትክልት $7


ምዕራፍ
የአካባቢ ንጽህና
5
5.1.1 ማዳመጥ ንፅህና ለጤና

ቅድመማዳመጥ
የአካባቢያችሁን ንፅህና ለመጠበቅ ቤተሰቦቻችሁ ምን ያደርጋሉ?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ኮቪድን (ኮረናን) ለመከላከል ሰዎች ምን ያድርጋሉ?

ለ. ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ስለሚያጋልጡ ልማዳዊ ክንዋኔዎች ተናገሩ።

ቃላት

1. ነጣጥላችሁ ጻፉና ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. ማጠራቀሚያ ለ. መትፋት

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ሳሙና ሐ. ማቃጠል

ለ. ጉድጓድ መ. መሸፈን

58 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና $8


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

“በቁማችን ሞተናል!”
አቶ አግማሴ “እትትት….. ውይ! ወይኔ! ራሴ!” እያሉ ይጮሃሉ።
ጎረቤታቸው አቶ አያሌው፣ “ምን ሆነሃል? ያችወባ ተነሳችብህ እንዴ?
ይገርማል! በገዛ እጃችን የበሽታ ጎሬ እንሁን!” አሉ አቶ አግማሴ ጥርሳቸውን
እያፋጩ፣ “እስቲ ተመልከት! በዙሪያችን ያለው ዉኃ አረንጓዴ ሠርቶ!
የቆሻሻው ሽታስ አፍንጫችንን በጥሶ ሊጥለው አይደል!?” አሉ። አቶ
አያሌውም “እኛማ በቁማችን ሞተናል እኮ! ነገ ማህበረሰቡን ሰብስቤ
የፅዳት ዘመቻ አውጃለሁ” አሉና እጃቸውን አወናጨፉ።

(አማርኛ እንደአፍ መፍቻ 2ኛ ከፍል መማሪያ መጽሐፍ ተሸሽሎ የተወሰደ)

5.1.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ርዕሱን በማንበብ ታሪኩ ስለምን እንደሚገልፅ ገምቱ።

በሽታን መከላከል
በንፅህና ጉድለት የሚመጡ በሽታዎችን መከላከል ያስፈልጋል። ለምሳሌ
ጠጉርን፣ ገላንና እጅን በመታጠብ፣ ልብስን በማጠብ የተስቦ በሽታን
እንከላከላለን። ቆሻሻን ሰብስቦ በማቃጠልና በመፀዳጃቤት በመጠቀም
የተቅማጥ፣ የዓይንማዝና የጉንፋን በሽታዎችን መከላከል ይቻላል።
በክረምት የሚያቁሩ ኩሬዎችን በማፋሰስና በማድረቅ የወባ ትንኝ እንዳትራባ
በማድረግ የወባ በሽታን መቀነስ ይቻላል።

59 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና $9


ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።
ሀ. አንዳንድ ሰዎች በበሽታ የሚጠቁት ለምን ይመስላችኋል?
ለ. ምንባቡን አጠር አድርጋችሁ ለጓደኞቻችሁ በቃል ተርኩ።
ሐ. ራሳችንና አካባቢያችንን ባናፀዳ ምን እንሆናለን?

የቃላት አጠቃቀም
የአካባቢ ንፅህናን ለመጠበቅ ስለሚያስችሉ አራት ተግባራት ጻፉ።
ምሳሌ፡- ቆሻሻን ሰብስቦ ማቃጠል።

5.1.3 ማዳመጥ ንፅህና ለጤና

ቅድመማዳመጥ
ለቃላቱ/ሐረግ ፍቺ ስጡ።
ሀ. መፀዳጃቤት ለ. ኮረና ሐ. ተላላፊ በሽታዎች

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።
ሀ. የታሪኩን ሐሳብ በቃል ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተናገሩ።
ለ. የተከናወኑ ድርጊቶችን በቅደምተከተል ግለጹ።

ቃላት

የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ አሟልታችሁ ጻፉ።

መፀዳጃ

ቤት

60 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና %


አቀላጥፎ ማንበብ
“በቁማችን ሞተናል!” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

5.1.4 መጻፍ

1. ድምፅ በማሰማት አንብቡና ጻፉ።

ሀ. መ-ከ-ላ-ከ-ል

ለ. የ-ዓ-ይ-ን-ማ-ዝ

ሐ. የ-ወ-ባ- በ-ሽ-ታ

መ. ተ-ቅ-ማ-ጥ

2. ሥርዓተነጥቦችን በመጠቀም ዓረፍተነገሮችን እንደገና ጻፉ።

ሀ. ዓይንማዝ ተቅማጥና አሜባ ተላላፊ በሽታዎች ናቸው

ለ. አቤት የቆሻሻው ሽታ አፍንጫን ይሰነፍጣል

ሐ. የአካባቢ ንፅህናችንን እንዴት እንጠብቅ

3. የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጁና አሟልታችሁ ጻፉ።

የግል ንፅህና የአካባቢ ንፅህና

እጅንና ፊትን መታጠብ ቆሻሻን ማቃጠል

61 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና %1


5.1.5 ክለሳ

1. በሚከተሉት ቃላት ብቻ ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ምሳሌ፡- የአካባቢ ንፅህና መጠበቅ ያስፈልጋል።

አሜባ የግል ንፅህና የአካባቢ ቆሻሻ

መጠበቅ ተገቢ ያስፈልጋል ነው ጉድጓድ

2. “የቆሻሻው ሽታ አፍንጫዬን በጥሶ ሊጥለው ነው” ሲሉ ምን ማለታቸው


ነው?

5.2.1 ማዳመጥ “የወፏ ትዝብት”

ቅድመማዳመጥ
ስለቆሻሻ መጣል በአካባቢያችሁ ምን ምን ታዘባችሁ?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ወፏ የእነአብርሃምን ግቢ የወደደችው ለምንድን ነው?

ለ. ወፏ በአካባቢው ማረፊያ ያጣችው ለምንድን ነው?

ሐ. ከታሪኩ ምን ተረዳችሁ?

ቃላት

1. ሐረጋቱን ድምፅ እያሰማችሁ አንብቡ።

ሀ. የሞቱ እንስሳት ሐ. በየቦታው የወደቁ

ለ. በአካባቢያችሁ መ. በየሜዳው የተጣሉ

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ማረፊያ ለ. መጥፎ ጠረን ሐ. መታዘብ

62 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና %2


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

“ታሞ ከመማቀቅ…”
ድመትና ውሻ በአንድ ቤት ውስጥ ተረዳድተው ይኖራሉ። አካባቢያቸውን
በማፅዳት ግን ፍጹም አይግባቡም።
ድመት፣ እባክህ የአካባቢያችን ንፅህና በመጓደሉ ዝንቦችና ጉንዳኖች/
ዘመሚቶች አላስቀምጥ አሉን፤ አለችው።
ውሻ፣ ይህ የሆነው በአንቺ ምክንያት ስለሆነ ራስሽን ጠይቂ።
ድመት፣ ምነው… እኔማ ጽዳትን በመጠበቅ በኩል እታወቃለሁ፤
ዓይነምድሬንም ሆነ ሽንቴን ጉድጓድ ቆፍሬ እቀብራለሁ።
ውሻ፣ እኔም የምችለውን ሠርቻለሁ።
ድመት፣ አንተ እኮ! ዓይነምድርህንም ሆነ ሽንትህን በአገኘህበት ቦታ
ትፅዳዳለህ። ‘ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ’ እንደሚባለው
ጥንቃቄ ያስፈልጋል፤ አለችው።
ውሻ፣ እውነት ብለሻል ትኩረት ባለመስጠቴ አካባቢውን በክዬዋለሁ፤
ለወደፊቱ አስተካክላለሁ፤ አለ።

5.2.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ርዕሱን በማንበብ ስለምን እንደሚገልጽ ገምቱ።

መተባበር ለመልካም ተግባር


አሚናት፡- ሃሎ! ሃሎ…
የሺዋስ፡- አቤት …. ሃሎ እንደምንዋልሽ አሚናት?
አሚናት፡- ፈጣሪ ይመሰገን በጣም ደህና ነኝ፤ ለምን ከሥራ ቀረህ?
የሺዋስ፡- ከሥራ የቀረሁት የአካባቢያችንን ሰዎች ሳስተባብር ነው።

63 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና %3


አሚናት፡- ለምን ጉዳይ?
የሽዋስ፡- በዚህ ክረምት ወቅት አካባቢያችን በተለያዩ ቆሻሻዎች ስለተበከለ
መፍትሄ ለመስጠት ነው።
አሚናት፡- ታዲያ ምን አደረጋችሁ?
የሽዋስ፡- የዉኃ ማፋሰሻ ቦዮችን አፀዳን፤ ደረቅ ቆሻሻዎችን ሰበሰብንና
በቆፈርነው ጉድጓድ አቃጠልነው።
አሚናት፡- መተባበር ለመልካም ተግባር ነው። ትልቅ ሥራ ሠርታችኋል።

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. በአካባቢያችሁ የፅዳት ዘመቻ ይደረጋል? ለምን?

ለ. የሺዋስ ከሥራ የቀረው ለምንድን ነው?

ሐ. የስልኩ ንግግር በምን ዓይነት ንግግር ይጠናቀቅ ይመስላችኋል? ለምን?

የቃላት አጠቃቀም
አካባቢን የሚበክሉ ነገሮችን ዘርዝራችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- የዉኃ ፕላስቲክ

5.2.3 ማዳመጥ የወፏ ትዝብት

ቅድመማዳመጥ
ሥዕሉን በመመልከት የተረዳችሁትን ተናገሩ።

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. አብርሃም ከወፏ ጋር ሊያወራ የፈለገው ለምንድን ነው?

ለ. እናንተ ወፏን ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?

64 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና %4


ቃላት

1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. እየለመደ ለ. ያዳምጣል ሐ. ስትቃርም

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. የተበከለ ለ. እየለመደ ሐ. ቋንቋ

አቀላጥፎ ማንበብ
“ታሞ ከመማቀቅ...” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

5.2.4 መጻፍ

1. ድምፅ በማሰማት አንብቡና አጣምራችሁ ጻፉ።

ሀ. አ-ቃ-ጠ-ል-ን ለ. አ-ፀ-ዳ-ን ሐ. ሰ-በ-ሰ-ብ-ን

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ሥራ ለ. ወራት ሐ. መተባበር

3. በምሳሌው መሠረት ስለሰላምታ አቀራረብ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ዓለሙ፡- “እንደምን አደርሽ?”

ፋጡማ፡- “ፈጣሪ ይመስገን።”

ዓለሙ፡- “___________?”

ፋጡማ፡- “በጣም ደህና ነኝ።”

ፋጡማ፡- “አመሰግናለሁ በሰላም ዋል።”

ዓለሙ፡- ___________

65 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና %5


5.2.5 ክለሳ

1. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ቆሻሻ ለ. ፅዳት ሐ. መበከል

2. ስለትምህርትቤታችሁ ንፅህና አጠባበቅ ጭውውት አቅርቡ።

3. የሰላምታ ዓይነቶችን ከነምላሻቸው በቡድን ሆናችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ጠያቂ፡- እንደምን አደርክ? → መላሽ፡- ፊጣሪ ይመሰገን።

5.3.1 ማዳመጥ “ውርሳችሁ ምክሬ ነው”

ቅድመማዳመጥ
ሥዕሉን አስተውላችሁ ስለታሪኩ ገምቱ።

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል
መልሱ።

ሀ. ልጆቹ ሚስጢሩን ለማወቅ የጓጉት ለምን


ይመስላችኋል?

ለ. አርሶአደሩ ቆሻሻውን ከአፈሩ ጋር የሚቀላቅለው ለምንድን ነው?

ቃላት

1. ድምጽ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. አ-ስ-ጠ-ራ-ቸ-ው ሐ. የ-ሚ-በ-ሰ-ብ-ሱ

ለ. እ-ቀ-ብ-ራ-ለ-ሁ መ. እ-ለ-ያ-ቸ-ዋ-ለ-ሁ

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ጤነኛ ለ. ቆሻሻ ላስቲክ ሐ. የቤት ጥራጊ

66 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና %6


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ጣናን እንከባከብ
የጣና ሐይቅ ከባሕር ዳር ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ ይገኛል። ሐይቁ
በየጊዜው ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጠ ነው። ከችግሮቹ መካከል አንደኛው
በሐይቁ አካባቢ ያሉ ኗሪዎች ልብሳቸውን ያጥቡበታል፤ ሰውነታቸውን
ይታጠቡበታል። ሌሎች ቁሳቁሶችንና ተሽከርካሪዎችን ያፀዱበታል።

ኹለተኛው የእነዚህ ቆሻሻዎች መጠራቀም በሐይቁ ዙሪያ የእንቦጭ አረም


እንዲራባ ምቹ ሁኔታን ፈጥረውለታል። የአረሙ መብዛት ደግሞ ሐይቁን
በማድረቅ ወደመሬትነት ቀይሮታል። ስለዚህ ሐይቁ በጥንቃቄና በንፅህና
ካልተያዘ ጉዳቱ የከፋ ይሆናል።

5.3.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ከርዕሱ ምን ተረዳችሁ?

“ሁሉም ቢተጋገዝ”
ጊዜው ክረምት ነው። ከላይ ዶፍ ዝናብ ይዘንባል። ጎርፉ ከየቤቱ የሚወጣውን
ቆሻሻ በዉኃ ማፋሰሻ ቦይ ይጨምራል። ኗሪዎችም ዝናቡን ተገን አድርገው
በማዳበሪያ ያጠራቀሙትን ቆሻሻ በየቱቦው ይጥላሉ። ዝናቡ ማባራት ጀመረ።

ኗሪዎቹ ከየቤታቸው ወጡ። ቆሻሻው በየቱቦው ተቀርቅሮ፣ በየመንገዱ


ወዳድቆ ይታያል። ጎርፉም መሄጃ ስላጣ መንገዱን አጥለቅልቆታል። ቆሻሻ
ፌስታሎች፣ አሮጌ ጨርቆች፣ ቆሻሻ ወረቀቶችና ሌሎችም ቆሻሻዎች በጎርፍ
በተጥለቀለቀው መንገድ ላይ ተንሳፈዋል። የአካባቢው ሰዎች ስህተታቸው
ስለገባቸው ራሳቸውን ወቀሱ። አካፋና ዶማ ይዘው የዉኃ ማፋሰሻ ቦዩንና
በየመንገዱ ላይ ያሉትን ቆሻሻዎች ማፅዳት ጀመሩ።

67 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና %7


ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።
ሀ. በጎርፉ ላይ የተንሳፈፉት ነገሮች ምን ምን ናቸው?
ለ. ኗሪዎች ቆሻሻውን በየቱቦው መልቀቃቸው ትክክል ነው? ለምን?
ሐ. ጎርፉ መሄጃ ያጣው ለምንድን ነው?
መ. የታሪኩን ድርጊቶች በቅደምተከተል ጻፉ።

የቃላት አጠቃቀም
ለቃላቱ ተመሳሳይ ፍቺ ጻፉ።

ሀ. ማጥለቅለቅ ለ. ስህተት ሐ. መዝነብ መ. መጨመር

5.3.3 ማዳመጥ “ውርሳችሁ ምክሬ ነው”

ቅድመማዳመጥ
ለቃላቱ ተመሳሳይ ጻፉ።

ሀ. ፅዳጅ ለ. ማሳ ሐ. ውርስ መ. ሚስጢር

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።
ሀ. አርሶአደሩ ልጆቹን ያስጠራቸው ለምንድን ነው?
ለ. የአርሶአደሩን ምክር ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተናገሩ።
ሐ. እናንተስ ወላጆቻችሁ ምን ዓይነት ምክር ይመክሯችኋል?

ቃላት
ለቃላቱ ተመሳሳይ ፍቺ ጻፉ።

ምሳሌ፡- መራባት → መዋለድ


ሀ. ምቹ ለ. ችግር ሐ. መብዛት መ. መቀየር
68 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና %8
አቀላጥፎ ማንበብ
“ጣናን እንከባከብ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

5.3.4 መጻፍ

1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት አንብቡና ጻፉ።

ሀ. አጥለቀለቀው ለ. ያጠራቀሙት ሐ. ይጨምራል

2. የሚከተሉትን ቃላት በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ጨመረ → ይጨምራል

ሀ. ደከመ ለ. ቆሸሸ ሐ. ዘነበ መ. ለቀቀ

3. በቃላቱ ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ዶፍ ለ. ተገን ሐ. አባራ

4. ወደአፈርነት የሚቀየሩና የማይቀየሩ ቆሻሻ ነገሮችን ዘርዝራችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡-
ቆሻሻ

ወደአፈርነት የሚቀየሩ ወደአፈርነት የማይቀየሩ

ወረቀት ፌስታል

69 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና %9


5.3.5 ክለሳ

1. “ሁሉም ቢተጋገዝ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

2. በአካባቢያችሁ፣ ከቆሻሻ ጋር በተያያዘ ያስተዋላችሁትን ነገር ለክፍል


ጓደኞቻችሁ ተናገሩ።

3. ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ አሟልታችሁ ጻፉ።

መንስኤ ውጤት

ዝናብ ዘነበ። ጎርፍ ተከሰተ።

ቆሻሻዎች በየቱቦው ተጣሉ።

ጎርፉ መሄጃ አጣ።

ሰዎች በመሳሳታቸው

70 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 5 የአካባቢ ንጽህና &


ምዕራፍ
ባህላዊ ሙዚቃ
6
6.1.1 ማዳመጥ ባህላዊ ዘፈኖች

ቅድመማዳመጥ
ሀ. በአካባቢያችሁ ምን ዓይነት በዓላትን ታከብራላችሁ?

ለ. በበዓላት ወቅትስ ምን ዓይነት ዘፈኖችን ትዘፍናላችሁ?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ባህላዊ ዘፈኖች የሚዘፈኑት ለምንድን ነው?

ለ. ሰዎች በኅብረት ሲሠሩ ስለሚያዜሟቸው ዜማዎች ተናገሩ።

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. አርሶአደሮች

ለ. ቃላዊ ሀብቶች

ሐ. ባህላዊ ዘፈኖች

2. የባህላዊ ዘፈኖች ዓይነቶችን በስም ዘርዝራችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- የሠርግ

71 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ &1


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ግጥም አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

የሠርግ ዘፈኖች
የሠርግ ቤት ከዋዜው ጀምሮ በሠርግ ዘፈኖችና በእልልታ ይደምቃል።
በሙሽራዋ ቤት ከሚዘፈኑ ዘፈኖች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው።

የሙሽራይቱ እናት ከላይ ይቀመጡ፣

የሙሸራይቱ አባት ከላይ ይቀመጡ፣

አሳድገዋታል እያቆላመጡ።

የእኛ ሙሽራ ዘመናይ፣

አበራች እንደፀሀይ።

የእኛ ሙሽራ ኩሪ ኩሪ፣

ወሰደሽ አስተማሪ።

ከሙሽራው ቤት ከሚዘፈኑት ዘፈኖች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።

የሙሽራው ማማር የሚዜው ውበት፣

አነሁልሎኝ ሄደ እንዳልሠራ ቤት።

እኔ ለሙሽራው ደስ ይበለው ብዬ፣

እዘፋፍናለሁ ይሉኝታዬን ጥዬ።

ወንድምዬ... ወንድም አበባ፣

ይዘህ በጊዜ ግባ። በማለት ሠርጉን ያደምቁታል።

72 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ &2


6.1.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ርዕሱን አንብቡና የተረዳችሁትን በቃል ግለጹ።

እረኛውና ዋሽንቱ
አንድ ቀን እረኛው በጧት ተነሳ:: ዋሽንቱን ያዘና ወደግጦሽ ቦታ ወረደ።
ከብቶቹን አሰማራ። ከዚያም ዋሽንቱን እየነፋ፡-

“ከብቶቼን እያገድሁ ስጫወት ዋሽንቴን፣

በደስታ ፈዝዤ አያታለሁ እሷን።”

እያለ በዋሽንቱ ማዜም ጀመረ። በድንገት አንድ በሬ ከበቆሎ ማሳ ገባበት።


እረኛው ቢሮጥ አልደርስበት አለ። በሬውን ለመምታት ዋሽንቱን ወረወረው።
በሬው ደንብሮ ሲሮጥ በዋሽንቱ ላይ ቆመበት። እረኛው በሬው የሠራውን
አይቶ ኩርምት ብሎ ተቀመጠ። ጓደኛው የዋሽንቱ ድምፅ ሲጠፋባት እየሮጠች
ወደእረኛው መጣች። እረኛውም በምልክት አሳያት። “በቃ አትዘን ከእኛ ጓሮ
የሸንበቆ ተክል አለ። እንሂድና እናዘጋጅ፤ አለችው።

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. እረኛው ዋሽንቱን መወርወሩ ትክክል ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? ለምን?

ለ. እረኛው ለጓደኛው በምልክት ያሳያት ምንድን ነው? እንዴት አወቃችሁ?

የቃላት አጠቃቀም
በምሳሌው መሠረት ሌሎችን አገላለጾች አሟልታችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ዋሽንት --- ይነፋል።

ሀ. ክራር ሐ. አታሞ

ለ. ማሲንቆ መ. ደወል

73 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ &3


6.1.3 ማዳመጥ ባህላዊ ዘፈኖች

ቅድመማዳመጥ
የሚከተሉትን ጥያቄዎችን በቃል መልሱ።

ሀ. እርሻ ሲታረስ ምን ዓይነት ዜማዎች ይዜማሉ?

ለ. ልደት ሲከበር ምን ዓይነት ዘፈኖች ይዘፈናሉ?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ከባህላዊ ዘፈኖች መካከል የምታውቁትን ለመምህራችሁ ተናገሩ።

ለ. በዘመን መለወጫ በዓል ምን ዓይነት ዘፈኖች ይዘፈናሉ?

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. ክንዋኔዎች ለ. ዘመን መለወጫ ሐ. ቃላዊ ሀብቶች

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ባህል ለ. ዋዜማ ሐ. ማዜም

አቀላጥፎ ማንበብ
“የሠርግ ዘፈኖች“ የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

6.1.4 መጻፍ

1. ነጣጥላችሁ ድምፅ በማሰማት አንብቡና ጻፉ።

ሀ. ዋሽንት ለ. አሰማራ ሐ. እናዘጋጅ

74 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ &4


2. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ዋሽንት ለመሥራት ሸንበቆ ያስፈልጋል።

ሀ. ዋሽንት ለ. ከበሮ ሐ. ማሲንቆ መ. ክራር

3. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. አሳያት ለ. ጀመረ ሐ. ምልክት መ. ድምፅ

4. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- በዓል ይከበራል።

ሀ. ሙሽራ ለ. ቀለበት ሐ. ሠርግ መ. ልደት

6.1.5 ክለሳ

1. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. አሳደጓት ለ. ዘፈኑ ሐ. አረሱ መ. አረሙ

2. ጅምር ሐሳቡን ጨርሳችሁ ጻፉ።

ራሔል፡- እንደምን አደርሽ ሀና?

ሀና፡- ፈጣሪ ይመስገን ደህና ነኝ።

ራሔል፡- የት ልትሄጂ ነው?

ሀና፡- ወደዓመት በዓል?።

ራሔል፡- ____________

ሀና፡- ____________

3. “የሠርግ ዘፈኖች” የሚለውን ታሪክ አቀላጣፋችሁ አንብቡ።

75 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ &5


4. በ“ሀ” ክፍል ላሉት ቃላት ተቃራኒ ከ“ለ” ክፍል መርጣችሁ አዛምዱ።

“ሀ” “ለ”

1. አቆላመጠ ሀ. ጥንታዊ
2. ወሰደ ለ. ውበቷ ጠፋ
3. ዘፈነ ሐ. አዋረደ
4. ዘመናዊ መ. መለሰ
ሠ. አለቀሰ

6.2.1 ማዳመጥ “የማሲንቆና የፈረስ ጓደኝነት”

ቅድመማዳመጥ
ሀ. ሥዕሉን አስተውሉና ስለታሪኩ ገምቱ።

ለ. ስለምታውቋቸው የባህል ሙዚቃ


መሣሪያዎች ተናገሩ።

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. የማሲንቆ ክር ከምን የሚሠራ ይመስላችኋል? እንዴት አወቃችሁ?

ለ. የፈረስ ጭራ ለምን ለምን የሚያገለግል ይመስላችኋል?

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. አማከረቻቸው ለ. ተበጠሰባት ሐ. ስትገዘገዢ

2. የክር የሙዚቃ መሣሪያዎችን ዘርዝራችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ማሲንቆ

76 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ &6


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

“የከበሮ አዘገጃጀት”
ከበሮ ከምት የሙዚቃ መሣሪያዎች መካከል አንዱ
ነው። ከበሮን ለማዘጋጀት የከብቱ ቆዳ በዉኃ ይነከራል፤
በመቀጠል በችካል ይወጠራል፤ ከጠጉሩ ጀርባ ያለው አካል
ይፋቃል፤ ከዚያም ይለፋል። ለቆዳ መወጠሪያ የሚሆነው
ወፍራም የዋንዛ እንጨት ይጠረባል። ውስጡ ደግሞ
ይቦረቦርና ክፍት ይሆናል። እንጨቱ ሞላላ ቅርፅ ሆኖ ታቹ ጠባብ፣ ላዩ
ሰፊ ክብ ቅርጽ ይኖረዋል። ተለፍቶ የተዘጋጀው ቆዳ በተጠረበው እንጨት
ከላይና ከታች ባለው ቀዳዳ ላይ ተደርጎ በጠፍር እየተጠላለፈ ይወጠራል።
ከበሮው ጥሩ ድምጽ እንዲኖረው የእምቧይ ፍሬ በየጊዜው እየተቀባ ፀሐይ
ይሞቃል።

6.2.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
በበዓል ወቅት በአካባቢያችሁ ምን ዓይነት ባህላዊ ዘፈኖች ይዘፈናሉ?

ሆያ ሆዬ
የቡሄ በዓል በሚከበርበት ዕለት የሚዜም ባህላዊ ዜማ ነው። ልጆች የበዓሉ
ዕለት ከየሰፈሩ ተጠራርተው በመገናኘት በአንድ ላይ እያሸበሸቡ፡-
ሆያ ሆዬ፣ ሆያ ሆዬ፣
የእኔማ ጌታ የሰጡኝ ሙክት፣
ከግንባሩ ላይ አለው ምልክት።
ሆያ ሆዬ የኔማ ጉዴ

77 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ &7


ጨዋታ ነው ልማዴ።
ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ
የእኔማ እመቤት የፈተለችው፣
የሸረሪት ድር አስመሰለችው።
በማለት በዜማ ከጨፈሩ በኋላ ሙልሙል ዳቦ ወይም እንደአካባበቢው
ባህል የተለያየ ስጦታ ይሰጣቸዋል። ከዚያም ለማመስገን
ዓመት ዓውደዓመት ድገምና፣
ዓመት፣ ድገምና፣
የማምዬ ቤት ወርቅ ይፍሰስበት፣
ዓመት፣ ድገምና ዓመት ድገምና፣
ክበር በስንዴ ክበር በጤፍ፣
ጠላትዎት ሁሉ ይርገፍ፤
በማለት እየጨፈሩ መርቀው ይሄዳሉ።

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. “ሆያ ሆዬ” ባህላዊ ጨዋታ የሚዜመው መቼ ነው?

ለ ልጆቹ “ሆያ ሆዬን” እያዜሙ ምን ያደርጋሉ? በቅደምተከተል ግለጹ።

ሐ. “ሆያ ሆዬ” ጨዋታን መነሻ በማድረግ ሌሎች ባህላዊ ጨዋታዎችን


በቡድን ሆናችሁ በመዘጋጀት በክፍል ውስጥ አዚሙ።

የቃላት አጠቃቀም
በቃላቱ ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ሙክት ለ. ምልክት ሐ. ልማድ

78 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ &8


6.2.3 ማዳመጥ “የማሲንቆና የፈረስ ጓደኝነት”

ቅድመማዳመጥ
ሀ. ማሲንቆና ፈረስ እንዴት ጓደኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግለጹ?

ለ. የፈረስ ጭራ ለምን ለምን ጥቅም ይውላል?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. የማሲንቆው ክር የተበጠሰባት ለምን ይመስላችኋል?

ለ. ማሲንቆ ከሌሎች የሙዚቃ መሣሪያዎች በተለየ እነክራርን ጓደኛ


ያደረገው ለምን ይመስላችኋል?

ሐ. እናንተስ ጓደኞቻችሁን የምትመርጡት እንዴት ነው? ለምን?

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት ነጣጥላችሁ አንብቡ።

ሀ. ማ-ን-ጎ-ራ-ጎ-ር ለ. መ-ግ-ረ-ፊ-ያ ሐ. ት-በ-ጠ-ሻ-ለ-ሽ

2. በ“ሀ” ክፍል ላሉት ቃላት ተመሳሳይ ከ“ለ” ክፍል መርጣችሁ አዛምዱ።

“ሀ” “ለ”

1. ተበሳጨች ሀ. አወያየች

2. ትቆረጫለሽ ለ. ተናደደች

3. አማከረች ሐ. የተፈተለ

4. ይነካኩናል መ. ትበጠሻለሽ

5. የተገመደ ሠ. ይዳስሱናል

ረ. ትስተካከያለሽ

79 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ &9


አቀላጥፎ ማንበብ
“የከበሮ አዘገጃጀት” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

6.2.4 መጻፍ

1. ስንኞቹን በዜማ አንብቡ።

“ሆያ ሆዬ፣ ሆያ ሆዬ

ሆያ ሆዬ፣ የኔማ ጉዴ

ጨዋታ ነው ልማዴ።”

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ሙልሙል ለ. ልማድ ሐ. ጨዋት

3. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- በቡሄ ዕለት ሙልሙል ዳቦ ይጋገራል።

ሀ. በገና ዕለት

ለ. በኢድአልፈጥር ዕለት

6.2.5 ክለሳ

1. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ከበሮ ለ. ማሲንቆ ሐ. ክራር መ. ዋሽንት

2. “የከበሮ አዘገጃጀት” የሚለውን ታሪክ በተጋርቶ አንብቡ።

3. ስለምታውቁት የሙዚቃ መሣሪያ አዘገጃጀት ለክፍል ጓደኞቻችሁ ግለጹ።

80 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ W


4. በ“ሀ” ክፍል ላሉት ቃላት ተቃራኒ ከ“ለ” ክፍል መርጣችሁ አዛምዱ።

“ሀ” “ለ”

1. ጀርባ ሀ. ዝግ
2. ላይ ለ. ፊት
3. መወጠር ሐ. ታች
4. ክፍት መ. መፍታት
5. ማሰር ሠ. ማላላት
ረ. መቀጠል

6.3.1 ማዳመጥ እስክስታ

ቅድመማዳመጥ
ሀ. ባካባቢያችሁ የሚከናወኑትን ባህላዊ ውዝዋዜዎች ግለጹ?

ለ. ባህላዊ ዘፈኖች መቼ መቼ ይዘፈናሉ?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ወንዶችና ሴቶች ባህላዊ ዘፈኖችን ሲዘፍኑ በምን ይለያያሉ?

ለ. እስክስታ ራስን ከማዝናናት አልፎ ለምን ይጠቅማል?

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. እስክስታ ሐ. ባህላዊ ጭፈራ

ለ. ውዝዋዜዎች መ. የአካል ጥንካሬ

81 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ W1


2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ትከሻ ለ. መቀነት ሐ. ነጠላ መ. አንገት

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ቀረርቶና ፉከራ
ቀረርቶና ፉከራ የህብረተሰቡ ቃላዊ ሀብቶች ናቸው። ሰዎች ስሜታቸውን
በዜማና በውዝዋዜ ይገልፃሉ። በመጀመሪያ አቅራሪዎች በአንድ ጆሯቸው
ላይ ጣታቸውን ይሰኩና ከወዲያ ወዲህ እየተንጎራደዱ ያቅራራሉ።
ለምሳሌ፡- አባት የሞተ ዕለት ባገር ይለቀሳል፣
እናት የሞተች ዕለት ባገር ይለቀሳል፣
ሀገር የሞተችለት ወዴት ይደረሳል።
ሀገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ ፣
የሞተልሽ ቀርቶ የበደለሽ በላ።
ጎበዝ ወይዛዝርቱ ኢትዮጵያን ጠብቁ፣
ሁሉም በሀገር ነው አልማዝና ወርቁ።
ምኒልክ ተነስቶ ባያነሳ ጋሻ፣
ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ ሀበሻ።
ማረሻው ምንሽር መጎልጎያው ጓንዴ፣
ያማራዎች መኩሪያ ወልቃይት ጠገዴ።

ከዚህ በኋላ ፎካሪዎች ስሜታቸው ይነሳሳል፤ ከወዲያ ወዲህ እያሉ ዱላቸውን


ወይም ጠመንጃቸውን ከፍ ዝቅ በማድረግ እየተንበረከኩ፣ እየተነሱ ይፎክራሉ።
ከሚፎክሯቸው ግጥሞች መካከልም የሚከተሉት ይገኙባቸዋል።

82 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ W2


ውረድ እንውረድ አባይ ካለቱ፣
እንገንባውና ይብራ መብራቱ።
አርሶ መሸመትና ተኩሶ መሳት፣
ይለበልባል እንደእግር እሳት።

6.3.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
የሥዕሎቹን መጠሪያ ቃላት ተናገሩ።

ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች

በአማራ ክልል የሚገኙ ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ብዙ ዓይነት ናቸው።


ክራር፣ በገናና ማሲንቆ የክር የሙዚቃ መሣሪያዎች ናቸው። መለከት፣
ዋሽንትና ጥሩንባ የትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያዎች ናቸው። ሌሎች ነጋሪት፣
ከበሮ፣ አታሞ፣ ደወል፣ ቃጭልና ፅናፅል የምት የሙዚቃ መሣሪያዎች
ናቸው።

የክር ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ከእንጨት፣ ከበግ፣ ከፍየልና ከከብት


ቆዳ፣ ጅማቶች፣ ከፈረስ ጭራ ወዘተ ይሠራሉ። የትንፋሽ ባህላዊ የሙዚቃ
መሣሪያዎች ከቀርቅሃ፣ ከቅል፣ ከሸንበቆ ወዘተ አንደየዓይነታቸው ሊሠሩ
ይችላሉ። የምት ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ደግሞ ከዋንዛ እንጨት፣
ከከብት ቆዳ፣ ከጠፍር፣ ከፈረስ ጭራ እንደየዓይነታቸው ሊሠሩ ይችላሉ።

83 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ W3


ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።
ሀ. የክር ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያ ከምት የሙዚቃ መሣሪያ በምን ይለያሉ?
ለ. ከብረት ብቻ የሚሠሩ የሙዚቃ መሣሪያዎች ምን ምን ናቸው? ለምንስ
አገልግሎት ይውላሉ?
ሐ. የቤት እንስሳት ለሙዚቃ መሣሪያዎች የሚሰጡት ጠቀሜታ ምንድን
ነው?
መ. የምታውቋቸው ዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ምን ምን ናቸው?

የቃላት አጠቃቀም
የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ አሟልታችሁ ጻፉ።

ክራር

የክር

ባህላዊ
የሙዚቃ
መሣሪያዎች

6.3.3 ማዳመጥ እስክስታ

ቅድመማዳመጥ
ለቃላቱ ተመሳሳይ ፍቺ ስጡ።

ሀ. እስክስታ ለ. ዘፈን ሐ. ውዝዋዜ

84 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ W4


ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ባህላዊ ውዝዋዜዎች መቼ ይከናወናሉ?

ለ. በባህላዊ ውዝዋዜ ተወዛዋዦች የሚለብሷቸውን አልባሳት ግለጹ።

ሐ. እስክስታ የትኛውን የአካል ክፍላችንን ያጠነክራል ብላችሁ ታስባላችሁ?

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. ወ-ገ-ባ-ቸ-ው-ን ሐ. ማ-ን-ቀ-ሳ-ቀ-ስ

ለ. ው-ዝ-ዋ-ዜ-ዎ-ች መ. ት-ክ-ሻ-ቸ-ው-ን

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ጨፈረ ለ. ለመደ ሐ. አገዘ መ. ባህል

አቀላጥፎ ማንበብ
“ቀረርቶና ፉከራ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

6.3.4 መጻፍ

1. አጣምራችሁ አንብቡና ጻፉ።

ሀ. ጥ-ሩ-ን-ባ ለ. ነ-ጋ-ሪ-ት ሐ. በ-ገ-ና

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ደወል ለ. ቃጭል ሐ. ከበሮ

3. ቃላቱን ወደብዙ ቁጥር ለውጣችሁ ጻፉ።

ሀ. ክራር ለ. ዋሽንት ሐ. ቃጭል መ. ደወል

85 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ W5


6.3.5 ክለሳ

1. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።


ምሳሌ፡- የፈረስ ጭራ
ሀ. የፈረስ ሐ. የበሬ ለ. የዋንዛ መ. የከብት
2. ዓረፍተነገሮቹን አስተካክላችሁ ጻፉ።
ሀ. የፍየል ጠፍር ቆዳ ይሆናል።
ለ. አዋጅ ነጋሪት ሲታወጅ ይጎሰማል።
ሐ. ፅናፅልና ቃጭል መሣሪያዎች የሙዚቃ ናቸው።
3. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።
ምሳሌ፡- ፎካሪ ይፎክራል።
ሀ. አቅራሪ ለ. ዘፋኝ ሐ. አልቃሽ መ. ጨፋሪ

86 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 6 ባህላዊ ሙዚቃ W6


ምዕራፍ
መልካም ሥነምግባር
7
7.1.1 ማዳመጥ ዘሀራ

ቅድመማዳመጥ
ሀ. ልጆች “ጥሩ ሥነምግባር አላቸው” ተብሎ የሚታሰበው ምን ምን
ሲያደርጉ ነው?

ለ. ታላላቆቻችሁን፣ ጓደኞቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ታከብራላችሁ?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ዘሀራ ታላላቆቿን እንዴት የምታከብር ይመስላችኋል?

ለ. በክፍሉ ውስጥ መምህሩ ያላስተዋሉት ነገር ምን ነበር?

ሐ. ከታሪኩ ምን ተማራችሁ?

ቃላት

1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. ዓይነሥውር ሐ. ታናናሾቿ

ለ. ሥነምግባር መ. ታላላቆቿ

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. መለሰች ለ. ጠየቀች ሐ. አዳመጡ

87 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር W7


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

“ይቅርታ ጠይቂ!”
“አባዬ! አባዬ! ኧረ አባዬ!” ኤልሃና ተጣራች። “ምን ሆነሽ ነው? ኤልሃና
በጧቱ የምትጣሪው” አሏት አባቷ። ቢጃማቸውን እየቀየሩ ከመኝታቤታቸው
ሆነው ተጣሩ። “እየውልህ አባዬ ኤልሳ የእኔን ጫማዎች እያደረገችብኝ”
ብላ አለቀሰች። አባቷ ሮጠው ከልጆቻቸው መኝታቤት ገቡ። ሁለቱም
እህትማማቾች ጫማዎችን ይዘው ይታገላሉ። ወዲያው አባታቸውን እንዳዩ
ኤልሳ ጫማዎቹን ለቀቀቻቸው። ኤልሃናም ጫማዎቿን ለአባቷ እያሳየች
እንባዋን ጠራረገች። አባታቸውም “ኤልሳ በይ አሁን እህትሽን ይቅርታ
ጠይቂ! የአንቺ ያልሆነን ነገር ካልተፈቀደልሽ በስተቀር አትንኪ!” አሏት።
ኤልሳም ዝቅ ብላ እህቷን ይቅርታ ጠየቀች። ኤልሃናም “ይቅር ብዬሻለሁ”
አለቻትና ተቃቅፈው ተሳሳሙ።

7.1.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ርዕሱን አንቡበና ታሪኩ ስለምን እንደሚገልጽ ገምቱ።

መስጠትና መቀበል
ኤደን፣ ናትናኤልና ዘቢባ የኹለተኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው። አንድ
ቀን ለእረፍት እንደወጡ ዘቢባ “ዶሮ እንቁላል ይጥላል” ብላ ጠየቀቻቸው
ናትናኤልም፣ “አሁን ይሄ ጥያቄ ነው?” ብሎ ሳቀባት። ኤደንም፣ “አንተ
ደግሞ ሁልጊዜ ራስህን ከፍ አድርገህ ታያለህ!” አለችው። ናትናኤልም፣
“አይ!... ማየት ሳይሆን እንቁላል የማይጥል ዶሮ ያለ ይመስል ገርሞኝ
እኮ ነው!” አለ። ኤደንም “ይኼውልህ መልሱ ዶሮ እንቁላል ሊጥልም፣
ላይጥልም ይችላል ነው” አለችው። ዘቢባም “ተመልከት ሁልጊዜ አውቃለሁ

88 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር W8


አትበል እውቀትህን ለሌሎች መስጠት ብቻ ሳይሆን መቀበልንም ተማር”
ብላ ገሰፀችው።

(ከ2ኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፍ መጠነኛ መሻሻል ተደርጎ የተወሰደ)

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን ታሪኩን መሠረት በማድረግ በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. ናትናኤል በዘቢባ ጥያቄ የሳቀው ለምንድን ነው?

ለ. የኤደን መልስ ትክክል ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? እንዴት?

ሐ. እናንተ ናትናኤልን ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?

መ. ናትናኤል የዘቢባን ተግሳፅ መቀበል ይገባዋል ወይስ አይገባውም?

ሠ. ከታሪኩ የተማራችሁትን ለመምህራችሁ ንገሩ።

የቃላት አጠቃቀም
በምሳሌው መሠረት ጥያቄና መልስ ያለው ምልልሳዊ ጽሑፍ አዘጋጁ።

ምሳሌ፡- ናትናኤል፡- እባክሽ ትርፍ እስክርቢቶ ካለሽ አውሺኝ?

ኤደን፡- “እሺ ጻፍና መልስልኝ።

ናትናኤል፡- “አመሰግናለሁ።”

7.1.3 ማዳመጥ ዘሀራ

ቅድመማዳመጥ
የሚከተሉትን ቃላት ፍቺ ተናገሩ።

ሀ. ይቅርታ ለ. አላስተዋልኩም ሐ. አመሰግናለሁ

89 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር W9


ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ታሪኩ የተፈፀመው የት ነው? ባለታሪኮችስ እነማን ናቸው?

ለ. የዘሀራ አስተማሪ የደነገጡት ለምንድን ነው?

ሐ. ዘሀራ ጥያቄው አልተነበበልኝም ያለችው ለምንድን ነው?

ቃላት

1. በብዙ ቁጥር ቅርጽ ጻፉና አንብቡ።

ምሳሌ፡- ተማሪ - ዎች → ተማሪዎች

ሀ. ጥያቄ ለ. አሳዳጊ ሐ. ሁኔታ መ. አጋጣሚ

2. በነጠላ ቁጥር ቅርጽ ጻፉና አንብቡ።

ምሳሌ፡- ወላጆች → ወላጅ

ሀ. ታላቆች ለ. ታናሾች ሐ. መልሶች መ. ቀኖች

አቀላጥፎ ማንበብ
“ይቅርታ ጠይቂ!” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

7.1.4 መጻፍ

1. ቃላቱን አንብቡና ጻፉ።

ሀ. ይኼውልህ ለ. ጠየቀቻቸው ሐ. ተመልከት

2. ለሚከተሉት ቃላት ተቃራኒ ፍቺ ጻፉ።

ምሳሌ፡- መስጠት → መቀበል

ሀ. ሁልጊዜ ለ. መጣል ሐ. መገሰፅ

90 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር (


3. በምሳሌው መሠረት ጽፋችሁ አንብቡ።

ምሳሌ፡- ምክር መስጠት ያስደስተኛል።

አስተያየት መቀበል ያስደስተኛል።

4. የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ አሟልታችሁ


ጻፉ።

ምግባር

ሥነ

7.1.5 ክለሳ

1. ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. አ-ድ-ር-ገ-ሀ-ል ሐ. ተ-መ-ል-ከ-ት

ለ. መ-ቀ-በ-ል-ን መ. አ-ው-ቃ-ለ-ሁ

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ሳቀ ሐ. መጠየቅ

ለ. ረፍት መ. ይቅርታ

91 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር (1


3. የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ በሚከተሉት
ቃላት/ሐረጋት አሟልታችሁ ጻፉ።

መሳደብ መቆጣት መታመን

መከባበር ሃላፊነትን መተው ስህተትን ማመን

ራስን መውደድ ጓደኛን መውደድ

ጥሩ መጥፎ
ሥነምግባር ሥነምግባር

“የመልካም ሥነምግባር
7.2.1 ማዳመጥ
መገለጫዎች”
ቅድመማዳመጥ
ወላጆቻችሁን ወይም ታላላቆቻችሁን ለማስደሰት ምን ታደርጋላችሁ?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. በቤተሰብ ወይም በትምህርትቤት የተሰጣችሁትን ኃላፊነት እንዴት


ትወጣላችሁ?

ለ. የሀቀኝነትና የታማኘነት መገለጫዎች ምን ምን ናቸው?

92 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር (2


ቃላት

1. ድምፅ በማስማት አንብቡ።

ሀ. ታ-ማ-ኝ-ነ-ት ሐ. ኃ-ላ-ፊ-ነ-ት

ለ. ሀ-ቀ-ኝ-ነ-ት መ. መ-ከ-ባ-በ-ር

2. በምሳሌው መሠረት ቃላት መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ታማኝ -ነት → ታማኝነት

ሀ. ኃላፊ ለ. ወጣት ሐ. ልጅ መ. ሰው

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ታላላቆቻችሁን አክብሩ
አንድ ቀን አንድ አዛውንት ብዙ ዕቃ በትከሻቸው ተሸክመው ይሄዳሉ።
ከኋላቸው ነጂምና ሐና ከትምህርትቤት ወደቤታቸው ሲመለሱ አዛውንቱን
ከሩቅ አዩዋቸው። አዛውንቱ ትንሽ ሄደው ይቀመጣሉ፤ አሁንም ትንሽ
ሄደው ይቀመጣሉ። ሐናም “ነጂም አባባን አየሃቸው?” “ውይ! ሐና እኔም
ላሳይሽ ስል ነው የቀደምሽኝ። ሮጠን እንድረስባቸው?” አለ ነጂም። ሐናም
“አዎ! የአማርኛ መምህራችን ታላላቆቻችሁን አክብሩ፣ ከራሳችሁ ይልቅ
ለሌላ ሰው ቅድሚያ ስጡ አላሉንም?” አለችው። ነጂምም “ልክ ብለሻል
በይ ቶሎ እንድረስባቸውና ሸክማቸውን ተቀብለን እንሸኛቸው” አላትና
እየተሯሯጡ ሄዱ።

(ከ2ኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፍ መጠነኛ መሻሻል ተደርጎ የተወሰደ)

93 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር (3


7.2.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሥዕሉን አስተውሉና ስለታሪኩ ገምቱ?

ኃላፊነትን መቀበል
ወይኒቱና ከማል የኹለተኛ ክፍል ተማሪዎች
ናቸው። ዛሬ በትምህርት ቤታቸው የፅዳት ዘመቻ
ይካሄዳል። መምህራቸው የክፍሉን ተማሪዎች
በስምንት ቡድን መደቧቸው። ወይኒቱና ከማልም
የየራሳቸውን የስራ ድርሻ ተቀበሉ። የእነወይኒቱ
የሥራ ድርሻ የመማሪያ ከፍሎችን አካባቢ
ማፅዳት ነበር። እነከማል ደግሞ የቢሮዎችንና
የሰንደቅዓላማ አካባቢዎችን ማፅዳት ነበር። ድንገት ከማል “መምህር” አለ።
“አቤት! ከማል ችግር አለ?” አሉት መምህሯ። “ለእኛ የተሰጠን ሥራ
ከእነወይኒቱ ይበልጣል” በማለት አጉረመረመ። መምህሯም “ሁላችሁም
የምታፀዱት የትምህርትቤታችሁን ግቢ ነው አሉት። ወይኒቱም “ከማል እኛ
ቶሎ ከጨረስን እናግዛችኋለን” አለችው።

(ከ2ኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፍ መጠነኛ መሻሻል ተደርጎ የተወሰደ)

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. መምህሯ ተማሪዎችን በስምንት ቡድን የከፈሏቸው ለምንድን ነው?

ለ. ከከማልና ከወይኒቱ ኃላፊነትን የተቀበለው ማን ነው?

ሐ. እናንተ ከማልን ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር?

94 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር (4


የቃላት አጠቃቀም
በሳምንቱ ውስጥ በትምህርትቤታችሁ የሠራችኋቸውን ተግባራት በቡድን
በመወያየት ዘርዝራችሁ ጻፉና ለክፍል ጓደኞቻችሁ አንብቡ።

ምሳሌ፡- የመማሪያ ክፍሌን አፅድቻለሁ።

የክፍሌን ሥነሥርዓት ጠብቄያለሁ።

“የመልካም ሥነምግባር
7.2.3 ማዳመጥ
መገለጫዎች”

ቅድመማዳመጥ
ለቃላቱ ተመሳሳይ ፍቺ ጻፉ።

ሀ. ሀቀኝነት ለ. ታማኝነት ሐ. ኃላፊነት

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ከቤተሰብ ትዕዛዝ ውጪ በልታችሁ ታውቃላችሁ? ለምን?

ለ. በክፍላችሁ ውስጥ መጥፎ ሥነምግባር ያላቸው ተማሪዎች ቢኖሩ ምን


ታደርጋላችሁ? ለምን?

ቃላት

1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. እንሸኝላቸው

ለ. እንድረስባቸው

ሐ. እንቀበላቸው

መ. እናግዛቸው

95 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር (5


2. በ“ሀ” ክፍል ላሉት ቃላት ተቃራኒ ከ“ለ” ክፍል መርጣችሁ አዛምዱ።

“ሀ” “ለ”

1. ማክበር ሀ. መረገም

2. መሸከም ለ. መቀበል

3. መቀመጥ ሐ. መናቅ

4. መመረቅ መ. ማውረድ

ሠ. መቆም

አቀላጥፎ ማንበብ
“ታላላቆቻችሁን አክብሩ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

7.2.4 መጻፍ

1. ሐረጋቱን ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡና ጻፉ።

ሀ. የሥራ ድርሻ ሐ. የሰንደቅዓላማ

ለ. የምታፀዱት መ. የትምህርትቤታችሁን

2. ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ አሟልታችሁ ጻፉ።

መምህር 1. መምህር ማክበር

ማክበር

96 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር (6


3. ዓረፍተነገሮቹን አስተካክላችሁ ጻፉ።

ሀ. አዛውንቱን ረዳኋቸው በሥራ

ለ. አባባን አገዝኳቸው ሮጬ

ሐ. የተሰጠንን መወጣት ኃላፊነት ተገቢ ነው

4. የጥያቄ ምልክት (?)፣ ትዕምርተአንክሮ (!)፣ አራት ነጥብ (።) በመጠቀም


ዓረፍተነገሮች መሥርቱ።

ምሳሌ፡- አቤት! ናሆም የት ሄድህ?

7.2.5 ክለሳ

1. ቃላቱን በማጣመር ሐረግ መሥርቱና ጻፉ።

ምሳሌ፡- የሥራ - ድርሻ → የሥራ ድርሻ

ሀ. የፅዳት - ዘመቻ ሐ. የሰንደቅ - ዓላማ

ለ. የትምህርት - ቤት

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. አፀዱ ሐ. ጠረጉ

ለ. አቃጠሉ መ. ሰበሰቡ

3. በሳምንቱ ውስጥ ያከናወናችኋቸውን በጎተግባራት በቡድን ሆናችሁ


በዝርዝር ጻፉና ለክፍል ጓደኞቻችሁ አንብቡ።

ምሳሌ፡- ወላጆቼ ያዘዙኝን ተግባር አከናወንኩ።

የግቢያችንን አትክልት ዉኃ አጠጣሁ።

97 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር (7


7.3.1 ማዳመጥ “ርህራሄን መማር”

ቅድመማዳመጥ
ሥዕሉን አስተውሉና ስለታሪኩ ገምቱ።

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ልጆቹ እንቁራሪቷን የተተናኮሏት ለምን ይመስላችኋል?

ለ. ልጆቹ በእንቁራሪቷ ላይ ድንጋይ መወርወራቸው እንቁራሪቷን ጠቀማት?


ወይስ ጎዳት? እንዴት?

ሐ. አህያዋ በእንቁራሪቷ ጎን ቀስብላ ያለፈችው ለምንድን ነው?

ቃላት
1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. አይቻታለሁ ሐ. ሊተናኮሏት

ለ. እንቁራሪቷ መ. ማሳደዳችንን

2. በ“ሀ” ክፍል ላሉት ቃላት ተቃራኒ ከ“ለ” ክፍል መርጣችሁ አዛምዱ።

“ሀ” “ለ”

1. መመለስ ሀ. መርሳት
2. ማሳደድ ለ. ደግነት
3. ክፋት ሐ. መሄድ
4. ማግኘት መ. መንከባከብ
5. ማለፍ ሠ. ማጣት
ረ. መውደቅ

98 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር (8


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ውሸታሙ እረኛ
በጫካ አጠገብ የሚኖር አርሶአደር ነበር። የሚያረባቸውን በጎች ቀበሮዎች
እየበሉበት ተቸገረ። በጎችን የሚጠብቅ እረኛ ቀጠረ። እረኛውንም መከረው።
“በጎችን ቀበሮ ሊበላ ሲመጣብህ ጩህ” ጩኸትህን ስንሰማ ተሯሩጠን
እንመጣለን” አለው።

አንድ ቀን እረኛው “ኡ! ኡ! ቀበሮ! ቀበሮ!” እያለ ጮኸ። የመንደሩ ሰዎች


እየተሯሯጡ ደረሱ። እረኛው እየሳቀ “ቀለድኩባችሁ! ውሸቴን ነው!” አለ።
በጎችን ሲመለከቱ የጎደለ የለም። ሰዎችም እየተናደዱ ተመለሱ። በሌላ ቀን
እረኛው “ኡ! ኡ! ቀበሮ! ቀበሮ!” እያለ ደጋግሞ ጮኸ። ጩኸቱ የውሸት
መስሏቸው አንድም ሰው ብቅ አላለም። ቀበሮዎችም ብዙ በጎችን በሉ።
የበጎቹ ባለቤት ማታ ላይ የበጎቹ ቁጥር ቀንሶ አገኘው። የሆነውን ከተረዳ
በኋላ እረኛውን በመጥፎ ሥነምግባሩ ከቤቱ አባረረው።

7.3.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
እስከአሁን ካነበባችኋቸው መጻሕፍት የምትወዷቸውን ተናገሩ?

መጽሐፌ መካሪዬ
ያቺ መጸሐፌ/ የምወዳት፡
ብዙ ምክሮች/ በውስጧ አሏት፣
የማልሰለቻት/ ሁሌ አዲስ ናት።
ስለርህራሄ/ ትነግረኛለች፣
ስለዕውቀትም/ ታወራኛለች።

99 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር (9


ስለምትሰጥ/ ጥሩ ትምህርት፣
መጽሐፌ/ ሁሌ አዲስ ናት።
ስለእምነት/ ታስረዳለች፣
ስለዕውቀት/ ትገልጻለች፣
ስለእውነት/ ትነግራለች።
ስለምትሰጥ/ ጥሩ ትምህርት፣
መጸሐፌ/ ሁሌ አዲስ ናት።
መጽሐፌ/ የታነፀች፣
በሥነምግባር/ የተሞላች፣
መጸሐፌ/ የኔ መሣሪያ፣
ሆናኛለች/ የእውቀት ገበያ።
መጸሐፌ የእኔ መምህር፣
የምትነግረኝ/ መልካም ምግባር፣

ሁሌም አለች/ ዕውቀት ስትዘከር።

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በግጥሙ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. ባለታሪኩ መጽሐፉን የሚወዳት ለምንድን ነው?

ለ. ባለታሪኩ መጽሐፉን “መካሪዬ” ያላት ለምን ይመስላችኋል?

ሐ. መጽሐፏ ምን ዓይነት ምክሮችን ትመክራለች?

የቃላት አጠቃቀም
በምሳሌው መሠረት በግጥሙ ውስጥ የተገለፁትን ጠቃሚ ምክሮች ጻፉ።
ምሳሌ፡- ትዕግስት

100 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር )


7.3.3 ማዳመጥ “ርህራሄን መማር”

ቅድመማዳመጥ
ለቃላቱ ተመሳሳይ ፍቺ ጻፉ።

ሀ. ርህራሄ ለ. መገሰፅ ሐ. መገንዘብ

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ከአህያዋ ተግባር ምን ተማራችሁ?

ለ. እናንተ ልጆቹን ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር?

ሐ. ታሪኩ ስለእነማን ይናገራል? የትኛውን ባለታሪክ ወደዳችሁ? ለምን?

ቃላት

1. አቀላጥፋችሁ እያነበባችሁ ጻፉ።

ሀ. እየወረወሩባት ሐ. ሩህሩህነት

ለ. ሊተናኮሏት መ. ማሳደዳችንን

2. የቃላቱን ፊደል በመግደፍ ወይም ቦታ በማቀያየር ቃላት መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ልትቆምበት → ትል፣ ባት፣ ልት፣ ምት፣ ልቆም፣….

ሀ. እንቁራሪት ሐ. እንዳትረግጣትም

ለ. ተመለከትካት

አቀላጥፎ ማንበብ
“ውሸታሙ እረኛ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

101 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር )1


7.3.4 መጻፍ

1. በምሳሌው መሠረት አዲስ ቃል መሥርታችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ነገር → ነገረኛ

ሀ. ተንኮል ለ. ትዕቢት ሐ. ትዕግስት መ. ቅናት

2. ሐረጋቱን ድምፅ በማሰማት አንብቡና ጻፉ።

ሀ. ያቺ መጽሐፌ ሐ. ብዙ ምክሮች

ለ. በጣም የምወዳት መ. ከእሷ አላጣም

3. አጣምራችሁ ጻፉና አንብቡ።

ሀ. ሥነ-አዕምሮ ሐ. ሥነ-ሕይወት

ለ. ሥነ-ምግባር መ. ሥነ-ጽሑፍ

4. በ“ሀ” ክፍል ላሉት ቃላት/ሐረግ ተመሳሳይ ከ“ለ” ክፍል መርጣችሁ


አዛምዱ።

“ሀ” “ለ”

1. መታነፅ ሀ. ማውሳት
2. ውሸት ለ. ማፍቀር
3. ትዕግስተኛ ሐ. መገንባት
4. መልካም ምግባር መ. ሀሰት
5. ሩህሩህነት ሠ. ችኩል ያልሆነ
6. መውደድ ረ. አዛኝነት
ሰ. ጥሩ ባህርይ

102 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር )2


7.3.5 ክለሳ

1. ለተሰመረባቸው ቃላት አውዳዊ ፍቺ ጻፉ።

ሀ. መጽሐፌ ብዙ ምክሮች አሏት።

ለ. አንድም ሰው ብቅ አላለም።

ሐ. መጽሐፌ የዕውቀት ገበያ ሆናለች።

መ. እንቁራሪቷን ሊተናኮሏት ፈለጉ።

2. “መጽሐፌ መካሪዬ” የሚለውን ግጥም እየተቀባበላችሁ በሐረግ በሐረግ


ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

3. በምሳሌው መሠረት አጫጭር ምልልሳዊ ታሪኮችን አዘጋጁና በክፍል


ውስጥ አቅርቡ።

ምሳሌ፡- ኤደን፣ “እባክህ አቤል መጽሐፍ አውሰኝ?”

አቤል፣ “የአንቺ መጽሐፍ ምን ሆኖብሽ ነው?”

ኤደን፣ “በእሱ ርዕስ የተጻፈ አጋዥ መጽሐፍ የለኝም።”

አቤል፣ “ኦ! በጣም ይቅርታ! ለዛሬ አውስሻለሁ።”

ኤደን፣ “በጣም አመሰግናለሁ፤ መጽሐፉን በጥንቃቄ አንብቤ


እመልሳለሁ።”

አቤል፣ “ጠንቃቃ እንደሆንሽ አምናለሁ።”

103 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 7 መልካም ሥነምግባር )3


ምዕራፍ
የምግብ አዘገጃጀት
8
8.1.1 ማዳመጥ አተር

ቅድመማዳመጥ
ስለምታውቋቸው የምግብ ዓይነቶችና አዘገጃጀት ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተናገሩ።

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. አተር ለምግብነት እንዴት ይዘጋጃል?

ለ. አተር እንዴት ይመረታል?

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. ይ-ለ-ቀ-ማ-ል ሐ. ይ-ከ-ካ-ል

ለ. ይ-ፈ-ጫ-ል መ. ይ-ታ-ጠ-ባ-ል

2. የቅመም ዓይነቶችን ዘርዝራችሁ ጻፉና አንብቡ።

ምሳሌ፡- ኮረሪማ

104 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )4


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

የምግብ አቀራረብ
ቀኑ እሁድ ነበር። ወይዘሮ የዛብነሽ ምሳ ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ ይላሉ።
ሥራቸውን እንደጨረሱ ያዘጋጇቸውን ምግቦች መደርደር ጀመሩ። በአንድ
በኩል ዳቦ፣ እንጀራ፣ ሥጋ ወጥ፣ ጥብስ፣ ምንቸት አብሽ ደረደሩ። በሌላ በኩል
የወተት ተዋፅኦዎችን (እርጎና አይብ) አቀረቡ። ከአትክልትና ፍራፍሬዎች
ደግሞ አበሻ ጎመን፣ ጥቅል ጎመን፣ ቀይሥርና ካሮትን በቅደምተከተል
አስቀመጡ። ከዚህም በተጨማሪ ሙዝና ብርቱካን በአንድ ጎን ደረደሩ፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሽሮወጥ፣ ምሥርወጥና ክክወጥ በጎድጓዳ ሳህን አቀረቡና
ለአፍታ ያህል ቃኘት በማድረግ ሳቅ አሉ።

(ከ2ኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፍ መጠነኛ መሻሻል ተደርጎ የተወሰደ)

8.1.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሰላጣ ምን ዓይነት ምግብ ይመስላችኋል?

የሰላጣ አዘገጃጀት
ሰላጣ የአትክልት ዓይነት ነው። በጥሬ ከሚበሉ የቅጠላቅጠል ዓይነቶች
ይመደባል። ሰላጣን በምግብነት ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብኣቶች አሉ፤
እነሱም፡- ሰላጣ፣ ሎሚ/አቼቶ፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ቃሪያ፣ ጨውና
የአትክልት ዘይት ናቸው።

ሰላጣን ለማዘጋጀት በቅድሚያ ሰላጣው ይታጠባል፤ ይቀነጠሳል፣ ሽንኩርት


ተልጦ ይከተፋል፤ ቃሪያም ተሰንጥቆ ይከተፋል፤ ቲማቲምም ይከተፋል።
ከዚያ በኋላ ሰላጣው፣ ሽንኩርቱ፣ ቃሪያውና ቲማቲሙ ባንድ ላይ በጎድጓዳ
ሳህን ይደባለቃሉ። ለማጣፈጫ ዘይትና ጨው ይደረጋል። በመጨረሻም

105 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )5


የሎሚ ጭማቂ ወይም አቼቶ ይደረግና ሁሉንም በማቀላቀል ለምግብነት
ይውላል። ሰላጣን ለመመገብ ዳቦ ወይም እንጀራ በማባያነት ይቀርባል።

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ልክ እንደሰላጣ በጥሬያቸው የሚበሉ ምግቦች ምን ምን ናቸው? እንዴት


አወቃችሁ?

ለ. የሰላጣን አዘገጃጀት በቅደምተከተል ግለጹ።

ሐ. ሰላጣ በጥሬው የሚበላው ለምን ይመስላችኋል?

መ. በጣም የምትወዱትን ምግብ መርጣችሁ አዘገጃጀቱን ተናገሩ።

የቃላት አጠቃቀም
በሥዕሎቹ መጠሪያ ቃላት ዓረፍተነገሮች መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ሰላጣ በጥሬው ይበላል።

8.1.3 ማዳመጥ አተር

ቅድመማዳመጥ
ለሚከተሉት ቃላት ፍቺ ስጡ።

ሀ. መከካት ለ. ጣዕም ሐ. እሸት

106 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )6


ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. አተር ከወጥ በተጨማሪ በምን መልክ ለምግብነት ይውላል?

ለ. ለምግብነት የሚውሉ የጥራጥሬ እህሎች ምን ምን ናቸው?

ሐ. የታሪኩን ሐሳብ ባጭሩ ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተናገሩ።

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. ጥ-ራ-ጥ-ሬ ሐ. ይ-ደ-ር-ቃ-ል

ለ. ይ-በ-ጠ-ራ-ል መ. ዝ-ን-ጅ-ብ-ል

2. የጥራጥሬ ዓይነቶችን ዘርዝራችሁ ጸፉ።

ለምሳሌ፡- አተር

አቀላጥፎ ማንበብ
“የምግብ አቀራረብ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

8.1.4 መጻፍ

1. ቃላቱን አንብቡና ጻፉ።

ሀ. አዘገጃጀት ለ. ይመደባል ሐ. ይከተፋል

2. ፊደል በመግደፍ ወይም ቦታ በማቀያየር ቃላት መሥርቱና ጻፉ።

ምሳሌ፡- ቀላቀለ → ቀላ፣ ላቀ፣ ላላ፣ ቀቀለ፣ ለቀቀ ….

ሀ. ይቀነጣጠሳል ለ. ይሰነጣጠቃል

3. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ሎሚ ለ. ቲማቲም ሐ. ቃሪያ መ. ዘይት

107 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )7


4. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ወተት → ይታለባል → ይረጋል → ይሰበቃል → ይናጣል →


ቅቤ ይወጣል።

ሀ. የዶሮ ወጥ ለ. እንጀራ

8.1.5 ክለሳ

1. ሐረጋቱን ድምፅ በማሰማት አንብቡና ጻፉ።

ሀ. የምግብ ዓይነቶች ሐ. የተላጠ ሽንኩርት

ለ. ጎድጓዳ ሳህን መ. የአትክልት ዘይት

2. የሐሳብ ማደራጃ ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ በሚከተሉት


ቃላት አሟልታችሁ ጻፉ።

እርጎ ሥጋ ወጥ አይብ ፓፓያ ክክወጥ

አበሻ ጎመን ሎሚ ቅቅል አሬራ ጥብስ ብርቱካን

ሽሮወጥ ቀይሥር አፕል

ምሳሌ፡-

የእንስሳት ተዋጽኦ የእፅዋት ተዋጽኦ

እርጎ ፓፓያ

3. በመመሪያው መሠረት በቡድን ሆናችሁ ስለአንድ ምግብ አዘገጃጀት


በመወያየት ጻፉና ለክፍል ጓደኞቻችሁ አንብቡ።

108 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )8


8.2.1 ማዳመጥ የዶሮ ወጥ አሠራር

ቅድመማዳመጥ
የዶሮ ወጥ እንዴት እንደሚሠራ ታውቃላችሁ? እስኪ ተናገሩ?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. በበዓላት ቀን የሚዘጋጁ የምታውቋቸው የምግብ ዓይነቶችን ዘርዝሩ።

ለ. የዶሮ ወጥ ለመሥራት የፈላ ዉኃ የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. እ-ን-ዲ-ላ-ቀ-ቁ ሐ. ይ-ገ-ሸ-ራ-ል

ለ. ይ-ለ-በ-ለ-ባ-ል መ. ይ-በ-ለ-ታ-ል

2. ከሚከተሉት ቃላት መርጣችሁ ዓረፍተነገሮቹን አሟልታችሁ ጻፉ።

ይለበለባል ይበለታል ይቁላላል

ይነፋል ይወጣል ይዘፈዘፋል

ሀ. የታረደው ዶሮ በቀሰም ________።

ለ. ዶሮው በጭድ ወይም በገለባ ________።

ሐ. የተለበለበው የዶሮ ሥጋ ከታጠበ በኋላ ________።

መ. ሽንኩርት፣ ዘይትና በርበሬው ________።

ሠ. የተበለተው ሥጋ በሎሚና በጨው ________።

ረ. የዶሮውን ወጥ ጨው በማስተካከል ________።

109 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )9


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

የምግብ ዝግጅት ውድድር


የምግብ ዝግጅት ውድድሩ ተጀምሯል። የምግብ ባለሙያዎቹ ከወዲያ
ወዲህ ሽርጉድ ይላሉ። አለምነሽ የሥጋ ወጥ በሸክላ ድስት ሠራች።
አትክልቱን ደግሞ በብረትድስት ሠራች። አለምነሽ የሽሮ ወጥ ለመሥራት
አሰበች። ለሽሮ ወጥ መሥሪያ ተጨማሪ ሸክላ ድስት አጣች።

ጓደኛዋን ጠየቀችው። “ውድድር መሆኑን ረሳሽው እንዴ?” አላት።


አለምነሽም “ምን አለበት?” አለችው። ጓደኛዋም “ሸክላድስቴን ላንቺ ሰጥቼ
እኔ በምን ልሠራ ነው?” አላት። “ልክ ነህ! መጀመሪያ ማቅረብ ነበረብኝ”
አለችው። ጓደኛዋም “ሠርገኛ መጣ! በርበሬ ቀንጥሱ ሆንሽብኝ እኮ!”
አላት። “አይምሰልህ ችግር ብልሃትን ይፈጥራል፤ የሽሮ ወጡን በመጥበሻ
እሠራዋለሁ” አለችና ከልቧ ሳቀች።

(ከ2ኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፍ ተሻሽሎ የተወሰደ)

8.2.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ርዕሱን አንብባችሁ ስለታሪኩ ገምቱ።

“የፈሰሰ ዉኃ…”
የዶሮ ወጡና የበጉ ጥብስ ጣት ያስቆረጥማል። እንዲሁም አይብ፣ እርጎና
በቅቤ የራሰ ክትፎ ተደርድረዋል። ጠላውና ጠጁ በጠርሙስና በብርሌ
በጠረጴዛ ላይ ቀርበዋል። ወይዘሮ ዘርፌ እንግዶቻቸው ዘግይተውባቸው
ወጣ ገባ ይላሉ። ድንገት ከወደኋላቸው የኳኳታ ድምፅ ሰሙ።

110 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )0


አንዲት ድመት እመር ብላ ባጠገባቸው አለፈች። ዞር ሲሉ ልጃቸው ሰይፉ
ዱላ ይዞ ሲሮጥ ተጋጩ። “ምንድን ነው ጉዱ?” አሉ ወይዘሮ ዘርፌ “እማዬ
እይው እስኪ!” ብሎ ሲያሳያቸው በጠረጴዛው ላይ ያለው እርጎ ተደፍቷል።

(ከ2ኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፍ ተሻሽሎ የተወሰደ)

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. በጠረጴዛው ላይ ያለው እርጎ የተደፋው ለምን ይመስላችኋል?

ለ. ሰይፉ ዱላ ይዞ የሮጠው ለምን ይመስላችኋል?

ሐ. ወይዘሮ ዘርፌ በመጨረሻ ምን የሚያደርጉ ይመስላችኋል?

መ. ከታሪኩ ምን ተረዳችሁ?

የቃላት አጠቃቀም
ሠንጠረዡን በደብተራችሁ አዘጋጁና አሟልታችሁ ጻፉ።

ምግቦች መጠጦች
ምሳሌ፡- የበግ ጥብስ ጠላ

8.2.3 ማዳመጥ የዶሮ ወጥ አሠራር

ቅድመማዳመጥ
የቃላቱን ተመሳሳይ ፍቺ ተናገሩ።

ሀ. መበለት ለ. መንጨት ሐ. ቀሰም መ. መቀንጠስ

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ከዶሮ ወጥ ውስጥ ቅመማቅመም የሚጨመረው ለምንድን ነው?

111 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )01


ለ. የዶሮው ሥጋ በሎሚና በጨው የሚዘፈዘፈው ለምንድን ነው?

ሐ. የዶሮ ወጥ ለመሥራት የሚከናወኑ ተግባራትን በቅደምተከተል ተናገሩ።

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. ማ-ስ-ተ-ካ-ከ-ል ሐ. እ-ን-ዲ-ላ-ቀ-ቁ

ለ. ተ-ቀ-ቅ-ለ-ው መ. በ-መ-ጀ-መ-ሪ-ያ

2. የሚከተሉትን ቃላት በዶሮ ወጥ አሠራር ሂደት ቅደምተከተል ጻፏቸው።

ይሠራል ይለበለባል ይታረዳል ይገዛል


ይገሸራል ይበለታል ይዘፈዘፋል ይወጣል

አቀላጥፎ ማንበብ
“የምግብ ዝግጅት ውድድር” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

8.2.4 መጻፍ

1. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት አንብባችሁ ጻፉ።

ሀ. ተደርድረዋል ሐ. እንግዶቻቸው

ለ. ተንቆርቁሯል መ. ይበረብራል

2. በሥዕሎቹ ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ምሳሌ፡- የዶሮ ወጥ በሸክላድስት ይሠራል።

112 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )02


3. በምሳሌው መሠረት ዓረፍተነገሮቹን አሟልታችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- እንጀራ በሳህን ይበላል።

ሀ. ፓስታ ____ ይበላል። ሐ. ወተት ____ ይጠጣል።

ለ. መኮረኒ ____ ይበላል። መ. ጠላ ____ ይጠጣል።

4. የምግብ መሥሪያ ዕቃዎችን በዝርዝር ጻፉ።

ምሳሌ፡- ድስት

8.2.5 ክለሳ

1. ሐረጋቱን ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. እማዬ እይው እስኪ! ሐ. ባጠገባቸው አለፈች።

ለ. ተንቆርቁረው ቀርበዋል። መ. ምንድን ነው ጉዱ!

2. “የፈሰሰ ዉኃ….” የሚለውን ታሪክ በቡድን በመሆን አንብቡና አጠቃላችሁ


ጻፉ።

8.3.1 ማዳመጥ ምግብና ጥቅሙ

ቅድመማዳመጥ
ምግብ ለሰዎች ምን ጥቅም ይሰጣል?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ስትጫወቱ ጉልበት (ኃይል) የምታገኙት ከምንድን ነው?

ለ. በሽታ እንዳይዘን ምን ማድረግ ይኖርብናል?

ሐ. በታሪኩ ውስጥ ያልተገለጹትን የምግብ ዓይነቶች ተናገሩ።

113 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )03


ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. ሰ-ው-ነ-ታ-ች-ን ሐ. እ-ና-ድ-ጋ-ለ-ን

ለ. ተ-መ-ጣ-ጣ-ኝ መ. እ-ን-ጫ-ወ-ታ-ለ-ን

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱና አንብቡ።

ሀ. እንቁላል ለ. ብርቱካን ሐ. ድንች መ. ስኳር

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

አሸናፊ ማነው?
ላም፣ በግ፣ ፍየልና ጎመን ለክርክር ከበሬ ዘንድ ቀረቡ። ላም “የሰው ልጆች
ሥጋዬን፣ እርጎዬንና ቅቤዬን ይመገባሉ። ወተቴን፣ አሬራዬንና አጓቴንም
ይጠጣሉ” አለች። በግ “እኔም ለሰው ልጅ ብዙ ጥቅም እሰጣለሁ፤ ክርክሩ
ስለምግብ ስለሆነ ሥጋዬ ለጥብስ፣ ለቅቅል፣ ለምንቸት አብሽ፤ ለአሮስቶና
ለመሳሰሉት ያገለግላል” አለች።

ፍየልም በተራዋ “ሦስታችንም ሥጋችንን ለምግብነት ሲውል፤ የእኔ ግን


ቅጠላቅጠሎችን ከየቁጥቋጦው ሰለምመገብ የሰው ልጆች ሲመገቡኝ እጅግ
ጤናማ ይሆናሉ” አለች። ጎመን ተነሳና “የሁላችሁም መሠረት አትክልትና
ፍራፍሬ ነን” አለ። በዚህ ጊዜ የመሀል ዳኛው በሬ “ሁላችሁም ትክክል
ናችሁ፤ በናንተ መካከል አሸናፊም ተሸናፊም የለም አለ።

114 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )04


8.3.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ከርዕሱ ምን ተረዳችሁ?

ምግቦች በበዓል ቀን
የተለያዩ እምነቶች ያሏቸው ሰዎች በበዓላት ወቅት የተለያዩ ምግቦችን
ያዘጋጃሉ። ለምሳሌ፣ በእስልምና እምነት በኢድአልፈጥር ዕለት ለቁርስ
በአብዛኛው ገንፎ ይገነፋል። ገንፎው ከገብስ፣ ከስንዴ ከመሳሰሉት ሊዘጋጅ
ይችላል። ለምሳ ደግሞ ሥጋወጥ፣ ጥብስ፣ ክትፎና የመሳሰሉት ከለስላሳ
መጠጦች ጋር ተዘጋጅተው ይቀርባሉ።

በኦርቶዶክስ የክርስትና እምነት ደግሞ በፋሲካ በዓል የጸሎተሐሙስ ዕለት


ጉልባን ይዘጋጃል፤ ዓርብ ዕለት ደግሞ የሚሻሚሾ ቂጣ ይጋገርና በርበሬና
ዘይት ተቀብቶ ልጆች ይመገባሉ። ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ በዘጠኝ
ሰዓት ጀምሮ ዶሮወጥ በእንጀራ ይበላል። በቁርስ ሰዓት ቡና ይፈላል፤ እርድ
ይታረዳል። የተለያዩ መጠጦች ይቀርባሉ። እንደየባህሉ ጥብስ፣ ክትፎና
የመሳሰሉት ምግቦች ይቀርባሉ።

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. በእናንተ አካባቢ በበዓል ቀን ምን ዓይነት ምግቦች ይዘጋጃሉ?

ለ. ለስላሳ መጠጥ የሚባሉት ምን ምን ናቸው?

ሐ. የታሪኩን ሐሳብ በአጭሩ ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተናገሩ።

115 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )05


የቃላት አጠቃቀም
በ“ሀ” ክፍል ካሉት ቃላት ጋር የሚዋቀሩ ከ“ለ” ክፍል መርጣችሁ አዛምዱ።

“ሀ” “ለ”

1. ገንፎ ሀ. ይጠመቃል
2. ቂጣ ለ. ይጠበሳል
3. ጥብስ ሐ. ይጣላል
4. ወጥ መ. ይጋገራል
5. ጠላ ሠ. ይገነፋል
ረ. ይሠራል

8.3.3 ማዳመጥ ምግብና ጥቅሙ

ቅድመማዳመጥ
ለቃላቱ ተመሳሳይ ፍቺ ስጡ።

ሀ. ጤናማ ለ. መጠበቅ ሐ. መገንባት

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ልዩ የሆነውን ምግብ ለዩና ለምን በአካባቢያችሁ እንዳልተገኘ ግለጹ።

ለ. ምግብ ለሰውነታችን ምን ምን ጥቅም ይሠጣል?

ቃላት

መምህራችሁ የሚያነቡላችሁን ሐረጋት ጻፉና አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

አቀላጥፎ ማንበብ
“አሸናፊ ማነው?” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

116 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )06


8.3.4 መጻፍ

1. ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡና ጻፉ።

ሀ. ሚ-ሻ-ሚ-ሾ ሐ. ፀ-ሎ-ተ-ሀ-ሙ-ስ

ለ. ኢ-ድ-አ-ል-ፈ-ጥ-ር መ. በ-አ-ላ-ቸ-ው

2. በሚከተሉት ቃላት በምሳሌው መሠረት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ገንፎ ከገብስ፣ ከስንዴና ከበቆሎ ዱቄት ይዘጋጃል።

ሀ. እንጀራ ለ. ጠላ ሐ. ዳቦ መ. ጠጅ

3. “ምግቦች በበዓል ቀን” የሚለውን ታሪክ በትክክል፣ በፍጥነትና በጥሩ


አገላለጽ አንብቡ።

4. ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ አሟልታችሁ ጻፉ።

ምግብ

ጉልበት ሰጪ ገንቢ ከበሽታ ተከላካይ

ƒƒ ዳቦ ƒƒ ሥጋ ƒƒ ጎመን

ƒƒ ƒƒ ƒƒ

117 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )07


8.3.5 ክለሳ

1. በምሳሌው መሠረት ወደብዙ ቁጥር ለውጣችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- የዱር እንስሳ - የዱር እንስሳት

ሀ. የምግብ ዓይነት ሐ. የመሀል ዳኛ

ለ. የሰው ልጅ መ. የጓሮ አትክልት

2. መምህራችሁ የሚያነቡላችሁን ሐረጋት እያዳመጣችሁ ከጻፋችሁ በኋላ


በትክክል አንብቡ።

3. “ምግቦች በበዓል ቀን” የሚለውን ታሪክ ድምፅ በማሰማት በየግላችሁ


በትክክል፣ በፍጥነትና በጥሩ አገላለጽ አንብቡ።

4. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ሥጋ ተጠብሶ ይበላል።

ሀ. ሙዝ ለ. ወተት ሐ. እንቁላል መ. ብርቱካን

118 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 8 የምግብ አዘገጃጀት )08


ምዕራፍ
ዲጂታል መሣሪያዎች
9
9.1.1 ማዳመጥ ሬዲዮና ቴሌቪዥን

ቅድመማዳመጥ
ሀ. ሥዕሎቹን አስተውሉና ስለታሪኩ ገምቱ።

ለ. ስለሬዲዮና ስለቴሌቪዥን የምታውቁትን


ተናገሩ።

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ሬዲዮና ቴሌቪዥን በሳሎን የሚቀመጡት ለምን ይመስላችኋል?

ለ. በሬዲዮ /በቴሌቪዥን ለልጆች ምን ዓይነት መልእክት ይተላለለፋል?

ሐ. ሬድዮና ቴሌቪዥን ልዩነታቸው ምንድን ነው?

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. ሬ-ዲ-ዮ ሐ. አ-ድ-ማ-ጮ-ች

ለ. ቴ-ሌ-ቪ-ዥ-ን መ. ታ-ዳ-ሚ-ዎ-ች

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ዘፈን ለ. ድራማ ሐ. ሬዲዮ መ. ታዳሚ

119 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )09


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

የወንድሜ ስልክ
ወንድሜ የአስራ ኹለተኛን ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈትኖ ወደዩኒቨርሲቲ
የሚያስገባ ውጤት አመጣ። ሁላችንም በጣም ተደሰትን። ወንድሜም ጎንደር
ዩኒቨርሲቲ ተመደበ። ለወትሮው ተለይቶን ስለማያውቅ እጅግ ግራ ተጋባን።
ምንም እንኳ የምንኖረው በገጠር ቢሆንም ስለስልክ ምንነት በመጠኑም ቢሆን
እናውቃለን። ስለዚህ ኹለት ስልኮች ገዛን። የወንድሜ ስልክ በጣም ያምራል።
በውስጡ ብዙ ነገሮችን ይዟል። ፎቶ ያነሳል፣ ከበይነመረብ/ኢንተርኔት የተለያዩ
መረጃዎችን ይቀበላል፣ ይልካል። ወንድሜ ሙዚቃዎችን፣ ፊልሞችን በስልኩ
ጭኖ ያዳምጣል፣ ይመለከታል። የወንድሜ ወደዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን
ሲደርስ ሁላችንም በስልኩ ፎቶ ተነሳን።

9.1.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ከሥዕሉ ምን ትረዳላችሁ?

“የመጀመሪያዋ ቀን”
አንዲት የገጠር ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአጎቷ ጋር
ወደከተማ ሄደች። ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከተማ ደረሱ።
ከተማው በመብራቶች አሸብርቋል። ልጅቷ እጇን
አፏ ላይ አድርጋ በዝምታ ታያለች። አጎቷም ግራ
እንደተጋባች አውቆ“ ከተማችንን አየሽው?” አላት።
“አዎ! ጋሼ! ምኑ ነው እንዲህ የሚንቀለቀለው?” አለችው። “ይሄውልሽ ይህ
በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠራ መብራት ነው። በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ
ብዙ ዓይነት መሣሪያዎች አሉ።
ለምሳሌ ስልክ፣ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ የዉኃ
ማጣሪያ ማሽን፣ የምግብ ማብሰያ ማሽን፣ የምግብ ማቀዝቀዣ ማሽን፣ የሻሂ
120 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )!
ማፍያ ማሽን፣ ካሜራና ሌሎችም የሚሠሩት በኤሌክትሪክ ኃይል ነው”
አላት። ልጅቷም “አሁን የጠራሃቸው ዕቃዎች ሁሉ በቤትህ ውስጥ አሉ?”
አለችው። “አዎ! ከቤት ስንደርስ ሁሉንም አሳይሻለሁ” አላት።

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።
ሀ. ልጅቷ እጇን አፏ ላይ አድርጋ በዝምታ የምታየው ለምን ይመስላችኋል?
ለ. ኤሌክትሪክ ባይኖር በኑሯችን ላይ ምን ችግር የሚፈጠር ይመስላችኋል?

ሐ. የታሪኩን የድርጊት ቅደምተከተሎች ከመነሻ እስከመድረሻ ግለጹ።

የቃላት አጠቃቀም 1

በሥዕሉ የተመለከቱት ቁጥሮች


}
2 3
የሚወክሏቸውን ቃላት ጻፉ። }
4
5 6

9.1.3 ማዳመጥ ሬዲዮና ቴሌቪዥን

ቅድመማዳመጥ
የሚከተሉትን ቃላት ፍቺ ተናገሩ።
ሀ. ድራማ ለ. ፊልም ሐ. ታዳሚ

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።
ሀ. የተሸላ ሐሳብ የሚቀርብበት ሬድዮ ወይስ ቴሌቪዥን ይመስላችኋል?
ለ. በመጨረሻስ ልጅቱ ምን የምትል ይመስላችኋል? ለምን?
ሐ. ከቴሌቪዥንና ከሬዲዮ በቀላሉ ከቦታ ወደቦታ አንቀሳቅሶ ለመጠቀም
የሚመቸው የትኛው ነው? ለምን?

121 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )!1


ቃላት

መምህራችሁ የሚያነቡላችሁን ቃላት እያዳመጣችሁ ጻፉ።

አቀላጥፎ ማንበብ
“የወንድሜ ስልክ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

9.1.4 መጻፍ

1. በ“ሀ” ክፍል ላሉት ሥዕሎች መጠሪያ ቃላት ከ“ለ” ክፍል መርጣችሁ


አዛምዱ።
“ሀ” “ለ”

1. ሀ. ሬዲዮ

2. ለ. ቴሌቪዥን

3. ሐ. ስልክ

4. መ. ባትሪ

5. ሠ. ካሜራ

122 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )!2


2. በምሳሌው መሠረት አሟልታችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- የልብስ ማጠቢያ ማሽን

ሀ. የዉኃ ______ ማሽን መ. የሊጥ ______ ማሽን

ለ. የምግብ ______ ማሽን ሠ. የዜና ______ ቴሌቪዥን

ሐ. የዳቦ ______ ማሽን ረ. የዜና ______ ሬድዮ

3. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ካሜራ ሐ. ማብሪያ ማጥፊያ

ለ. ስልክ

9.1.5 ክለሳ

1. መምህራችሁ የሚያነቡላችሁን ቃላት ጽፋችሁ አንብቡ።

2. “የመጀመሪያዋ ቀን” የሚለውን ታሪክ ጥንድ ጥንድ በመሆን በተጋርቶ


አንብቡ።

3. የሚከተለውን የስልክ ጥሪ ምልልስ አሟልታችሁ ጻፉ።

ከድር፤ ሄሎ! ... ሄሎ!

ኤልሃና፤ አቤት! አቤት! ማን ልበል?

ከድር፤ ይቅርታ! ከድር እባላለሁ?

ኤልሃና፤ ________

ከድር፤ ________

ኤልሃና፤ ________

ከድር፤ ስለትብብርሽ አመሰግናለሁ።

123 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )!3


4. በሚከተሉት ቃላት/ሐረግ ዓረፍተነገሮቹን አሟልታቸሁ ጻፉ።

ቴሌቪዥን ባትሪ ስልክ ሬዲዮ የኤሌክትሪክ ምድጃ

ሀ. _______ ከሌላ ሰው ጋር በቀጥታ በድምፅ ለመገናኘት ያገለግላል።

ለ. _______ መረጃዎችን በማየትና በማዳመጥ ለመከታተል ያስችላል።

ሐ. _______ መረጃዎችን በድምፅ ብቻ ያቀርባል።

መ. _______ ብርሃን ብቻ ለመስጠት ያገለግላል።

ሠ. _______ ምግቦችን ለማብሰል ይጠቅማል።

9.2.1 ማዳመጥ የኮምፒዩተር ክፍለጊዜ

ቅድመማዳመጥ
ሥዕሉን አስተውሉና ስለታሪኩ ገምቱ።

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን ባዳመጣችሁት ታሪክ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ድረስ የመረጃ ግንኙነት (አይሲቲ) ክፍለጊዜ እስከሚደርስ የሚቸኩለው


ለምን ይመስላችኋል?

ለ. ድረስ የመጠቆሚያዋ ስያሜ የሚገርመው ለምን ይመስላችኋል?

ቃላት

1. ነጣጥላችሁ ድምፅ በማሰማት አንብቡ።

ሀ. ኮ-ም-ፒ-ዩ-ተ-ር

ለ. መ-ጠ-ቆ-ሚ-ያ

ሐ. የ-ኮ-ም-ፒ-ዩ-ተ-ር-ሰ-ሌ-ዳ

መ. መ-ተ-ግ-በ-ሪ-ያ
124 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )!4
2. ቃላቱን ድምፅ በማሰማት አንብቡና ጻፉ።

ሀ. ኮምፒዩተር ሐ. የኮምፒዩተር ሰሌዳ

ለ. መጠቆሚያ መ. መተግበሪያ

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ዓይነሥውሩ ተማሪና ስልኩ


ዓይነሥውሩ ተማሪ አዳሪ ትምህርትቤት ከገባ ጥቂት ቀናትን አሳልፏል።
የትምህርትቤቱ አስተዳደር ሀላፊ አነስተኛ መጠን ያላት ቴፕና የተለያዩ
ትምህርቶች የተቀረፀባቸውን ካሴቶች ሰጠችው። አጠቃቀሙን በሚገባ
አሰለጠነችው፤ ማስታወሻም በብሬሉ ጻፈ። ከአንድ ዓመት በኋላ ስልክ
ተሰጠው። ለስልኩ መተግበሪያ (ጃውስ) ተጫነለት።

ቁጥሮችን በዳበሳ እንዴት እንደሚጠቀም ሰለጠነ። የተደወለለትን ስልክ ሲቀበል


በስልኩ የተመዘገበ ከሆነ የደዋዮችን ስም ይጠራለታል። ካልተመዘገበ የስልክ
ቁጥሩን በድምጽ ይነግረዋል። ለመደወል ከፈለገ ደግሞ እንደማንኛውም
ሰው ቁጥሮችን በመነካካት ወይም መደወያ ቁልፉን በመጫን ይደውላል።

9.2.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሀ. “ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል” ከሚለው ሐሳብ ምን ትረዳላችሁ?

ለ. በችኮላ የሚሠራ ሥራ ችግር የሚያስከትል ይመስላችኋል?

“ሲሮጡ የታጠቁት...”

አብዲ የፍኖተጥበብ ትምህርትቤት ተማሪ ነው። ችኩል ከመሆኑ የተነሳ ብዙ


ንብረቶች ይበላሹበታል። ሰዓቱ፣ የሒሳብ ማሽኑ፣ የራሱ ስልክ እየወደቁ
ተሰባብረዋል።

125 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )!5


የዛሬው ግን የተለየ ነው። አብዲ በጧቱ ወደኳስ ሜዳ ለመሄድ የእናቱን
ስልክ አነሳ፤ አስራ ኹለት ሰዓት ሆኗል። የስፓርት ልብሱን በፍጥነት
ለመልበስ ሲል ስልኩ ከእጁ አምልጦት ወደቀ። በጣም ደነገጠ። ስልኩን ይዞ
እየተቻኮለ ከቤት ወጣ። የስልክ መጠገኛ ሱቆች በር ሲደርስ ዝግ ናቸው።
ኹለት ስዓት ሲሆን በስልክ ጥገና የታወቀችው መልካም መጣች። ስልኩን
ሰጣት። “ኦ! መስታወቱ ተሰብሯል፣ የባትሪ ማቀፊያውም ከጥቅም ውጭ
ሆኗል ለማስተካከል ጊዜ ስለሚወስድ ነገ ና” አለችው።

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. አብዲ የሚቸኩለው ለምን ይመስላችኋል?

ለ. አብዲ ሱቆች በር ላይ የተቀመጠው ለምን ይመስላችኋል?

ሐ. እናንተ አብዲን ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር? ለምን?

የቃላት አጠቃቀም
የሥዕሎቹን መጠሪያ ቃላትና የአገልግሎት ልዩነታቸውን ጻፉ።

12
11 1
10 2

9 3

8 4
7 5
6

9.2.3 ማዳመጥ የኮምፒዩተር ክፍለጊዜ

ቅድመማዳመጥ
ለቃላቱ ተመሳሳይ ፍቺ ስጡ።

ሀ. ጠርዝ ለ. ሌባ ጣት ሐ. መጠቆሚያ

126 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )!6


ድኅረማዳመጥ
ሀ. የሥዕሎችን ተግባርና አገልግሎት በታሪኩ መሠረት ግለጹ።

ለ. ድረስ በመረጃ ክፍል ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባራት በቅደምተከተል


ጻፉ፡

ቃላት

1. የሚከተሉትን ጻፉና አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. መጫን ለ. ግራ ጠርዝ ሐ. ትራወጣለች

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. መክፈት ለ. መዝጋት ሐ. መጠቆም

አቀላጥፎ ማንበብ
“ዓይነሥውሩ ተማሪና ስልኩ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

9.2.4 መጻፍ

1. ድምፅ በማሰማት አንብቡና በትክክል አጣምራችሁ ጻፉ።

ሀ. ን-ብ-ረ-ቶ-ች ሐ. የ-እ-ጅ-ሰ-ዓ-ት

ለ. የ-ሒ-ሳ-ብ-ማ-ሽ-ን መ. የ-ስ-ል-ክ-መ-ጠ-ገ-ኛ

2. በሚከተሉት ሐረጋት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. የእጅ ሰዓት ለ. የሒሳብ ማሽን ሐ. የስልክ መጠገኛ

127 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )!7


3. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- በስልክ → ይደወላል፤ ፈልም ይታያል፤ ዘፈን ይደመጣል፤


መረጃ ይተላለፋል….

ሀ. በሒሳብ ማሽን ለ. በሰዓት ሐ. በቴሌቪዥን

4. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- በስልክ ሙዚቃ፣ መዝሙር፣ ፎቶግራፍ፣ ፊልም፣ መጽሐፍ


ወዘተ. ይጫናሉ።

ሀ. በካሴት ለ. በካሜራ

9.2.5 ክለሳ

1. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- የስልክ ቁጥር

ሀ. መደወያ ለ. የኮምፒዩተር ሐ. የመረጃ

2. እናንተስ ልክ እንደአብዲ ያጋጠማችሁን ወይም ሌሎች ሲናገሩ


የሰማችሁትን ገጠመኝ በክፍል ውስጥ ተናገሩ።

3. የዲጂታል መሣሪያዎችን በዝርዝር ጻፉ።

ምሳሌ፡- ስልክ

9.3.1 ማዳመጥ መገናኛ ብዙኃን

ቅድመማዳመጥ
መገናኛ ብዙኃን ምን ማለት ነው?

128 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )!8


ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ሌሎች ተማሪዎች ምን ዓይነት ርዕስ የደረሳቸው ይመስላችኋል?

ለ. እነሂሩት መገናኛ ብዙኃን መሥሪያቤት ሲደርሱ ምን ምን የሚያዩ


ይመስላችኋል?

ሐ. ስለመገናኛ ብዙኃን የተረዳችሁትን ተናገሩ?

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. መ-ል-ዕ-ክ-ት ሐ. ማ-ስ-ተ-ላ-ለ-ፊ-ያ

ለ. ማ-ሰ-ራ-ጫ መ. ባ-ለ-ሙ-ያ

2. ቃላቱን በብዙ ቁጥር ቅርጽ ጽፋችሁ አንብቡ።

ሀ. መልእክት ሐ. ርዕስ

ለ. ድርጅት መ. መገናኛ

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ምልልሳዊ ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

የተሳሳተ የስልክ ጥሪ
ደዋይ “ሄሎ!”

ተቀባይ “ጤና ይስጥልኝ! ማን ልበል?”

ደዋይ “ዛሬ ደግሞ እንዴት ዓይነት ሰላምታ ነው? እባክሽi”

ተቀባይ “ይቅርታ! ማንን ፈልገው ነው?”

ደዋይ “ወይጉድ! ቀልዱን ተይውና አድምጪኝ።”

ተቀባይ “ስልኩን ልዘጋው ነው?” መልእክቱ ተቋረጠ።

129 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )!9


ደዋይ መልሶ ይደውላል። “የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም።”

ይንቆራጠጥና መልሶ ይደውላል። “የደወሉላቸው ደንበኛ ከአገልገሎት ውጪ


ናቸው።”

ጥቂት እንደማሰብ ይልና ስልኩን እንደገና አንስቶ ቁጥሩን ይመለከታል።


ባየው ነገር ተደናግጦ ዝም አለ።

9.3.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ርዕሱን አስተውሉና ታሪኩ ስለምን እንደሚገልጽ ገምቱ።

“የማስጠንቀቂያ ደወል”
በቃሉ የድራማና የሥነፅሁፍ አስተባባሪ
ነው። በጧቱ ተነስቶ መቅረፀድምፁን
በሰንደቅዓላማ ማክበሪያ ቦታ አዘጋጀው።
የመዝናኛ ሙዚቃዎችን የያዘውን ካሴት
በመቅረፀ ድምፁ አስገባና ከፈተው።
ተማሪዎች በሙዚቃው እየተነቃቁ
ወደሰንደቅዓላማው ቦታ ተመሙ።

የትምህርትቤቱ ርዕሰመምህር በመሰለፊያው


መድረክ ላይ ንግግር ለማድረግ ሲዘጋጁ፣
በቃሉ የድምፅ ማጉያውን መናገሪያ
አቀበላቸው። ርዕሰመምህሩም “ተማሪዎች በየክፍሎቻችሁ የኤሌክትሪክ
ማብሪያዎችንና ማጥፊያዎችን እንዳትነኩ፤ የተላጠ የኤሌክትሪክ ገመድ
ስለሚኖር ለአደጋ ትጋለጣላችሁ” አሉ።

130 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )V


ድህረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. በቃሉ የመዝናኛ ሙዚቃዎችን የከፈተው ለምንድን ነው?

ለ. ተማሪዎች ወደሰንደቅዓላማው ቦታ የተመሙት ለምንድን ነው?

ሐ. “የማስጠንቀቂያ ደወል” የሚለውን ታሪክ በቃል በክፍል ውስጥ ተርኩ።

የቃላት አጠቃቀም
በትምህርትቤታችሁ በሰልፍ ላይ በድምፅ ማጉያ የሚተላለፉ ትዕዛዛዊ
መልእክቶችን በቡድን ሆናችሁ በዝርዝር ጻፉ።

ምሳሌ፡- ሀ. የቤት ስራ መስራት አለባችሁ።

ለ. እጃችሁን መታጠብ አለባችሁ።

9.3.3 ማዳመጥ መገናኛ ብዙኃን

ቅድመማዳመጥ
ለቃላቱ ተመሳሳይ ፍቺ ስጡ።

ሀ. ማሠራጫ ለ. ማብሪያ ሐ. መልእክት

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. እናንተ ወደመገናኛ ብዙኃን ድርጅት ብትሄዱ ባለሙያውን ምን ምን


ልትጠይቁ ትችላላችሁ?

ለ. እነሂሩት ያላነሱት ጥያቄ ምንድን ነበር?

ሐ. መገናኛ ብዙኃን የሚባሉት ምን ምን ናቸው?

131 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )V1


ቃላት

ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ አሟልታችሁ ጻፉ።

ዓይነት
ምሳሌ፡-

የመገናኛ ብዙኃን

አቀላጥፎ ማንበብ
“የተሳሳተ የሰልክ ጥሪ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

9.3.4 መጻፍ

1. አጣምራችሁ ጻፉና አቀላጥፋችሁ አንበቡ።

ሀ. ሥ-ነ-ጽ-ሑ-ፍ ሐ. ድ-ም-ፅ-ማ-ጉ-ያ

ለ. መ-ዝ-ና-ኛ

2. ቢጋሩን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ አሟልታችሁ ጻፉ።

ጽሑፍ

ሥነ

132 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )V2


3. በስልክ፣ በመብራት፣ በሒሳብ ማሽን፣ በቴሌቪዥንና በመሳሳሉት
መሣሪያዎች የምንጠቀምባቸውን ተቃራኒ ተግባራት በቃላት ግለጹ።

ምሳሌ፡- ማብራት → ማጥፋት

9.3.5 ክለሳ

1. መምህራችሁ የሚያነቡላችሁን ቃላት በትክክል ጻፉና አቀላጥፋችሁ


አንብቡ።

2. ለአንድ ለማታውቁት ሰው ስልክ ደውላችሁ መልዕክት ተለዋወጡ።

(ጥንድ ጥንድ እየሆናችሁ ጭውውቱን አቅርቡ።)

3. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ዘጋ ሐ. ደወለ

ለ. ደነገጠ መ. ተቀበለ

4. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡-

ትዕግስት የሌለው ትዕግስት ያለው

ƒƒ ስልኩን ዘጋሁብህ! ƒƒ ይቅርታ! ማን ልበል!

ƒƒ ዝምበል! ምን ታመጣለህ! ƒƒ እስኪ ልሞክር።

133 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 9 ዲጂታል መሣሪያዎች )V3


ምዕራፍ
የዱር እንስሳት
10
10.1.1 ማዳመጥ ጉልበት ወይስ ብልሃት

ቅድመማዳመጥ
ሀ. ጉልበት ምንድን ነው? ብልሃትስ?

ለ. ከጉልበትና ከብልሃት የትኛው ይሻላል? ለምን?

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ጥንቸል “አሸንፋለሁ” ብላ የተማመነችው እንዴት ነው?

ለ. የጥንቸል ስህተት ምን ነበር?

ሐ. ዔሊ ያሸነፈችበት ምክንያት ምንድን ነው?

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡና ጻፉ።

ሀ. ጉ-ል-በ-ት ሐ. መ-ሮ-ጫ-ው

ለ. ብ-ል-ሃ-ት መ. ው-ድ-ድ-ር

2. የቃላቱን የመነሻ ፊደል በመግደፍና በሌላ በመተካት አዳዲስ ቃላት


መሥርቱ።

ምሳሌ፡- ኹለት → ዱለት፣ አለት፣ ስለት፣ ዕለት፣ ጥለት ……

ሀ. ቀረቡ ለ. ዞረ ሐ. ሥር

134 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )V4


አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

የሌሊት ወፍ
በድሮ ጊዜ ቀን ቀን የሌሊት ወፍ የጓደኞቿን ምግብ እየተበደረች ትበላ ነበር።
ከጊዜ በኋላ ብድሯን መክፈል ሲያቅታት ከሌሎች ወፎች ለመሰወር ወሰነች።
ከጉጉት ጋርም በሌሊት መኖር ጀመረች። የድሮ ሰዎች “በዚህ የተነሳ ሌሊት
እንጂ ቀን አትበርም” ይላሉ። ያም ሆነ ይህ የሌሊት ወፍ ከሌሎች ወፎች
በእጅጉ ትለያለች። እንደሰው አጥቢ ናት። ቀን ቀን በተቦረቦረ ዛፍ ውስጥ፣
ጨለምለም ባለ ቦታ ወይም በዋሻ ውስጥ ታሳልፋለች። ስትተኛም ክንፏን
በማጠፍ ራሷን ዘቅዝቃ ነው። ልጆቿንም በድምጻቸው ትለያለች። የሌሊት
ወፍ ለስልሳ ቀናት ያህል ሳታቋርጥ ልጆቿን ትመግባለች። በአማካይ
ለዐምስት ዓመታት በሕይወት ትኖራለች።

10.1.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሥዕሉን አስተውሉና ታሪኩ ስለምን እንደሚገልጽ ገምቱ።

ነብርና ድኩላ
ነብርና ድኩላ በአንድ ላይ ተስማምተው ለመኖር
ተማማሉ። በአንድ ላይ ሲኖሩ የድኩላ አካሉ
እየሞላ፣ ሰውነቱ እየጨመረ፣ እያብረቀረቀ ይታይ
ጀመር። ነብርም ይህንን አይቶ መሀላውን ሊያፈርስ
ከጀለና ተቅበጠበጠ። አንድ ቀን ለሽርሽር ራቅ ወዳለ ቦታ ሄዱ። ነብርም
“ድኩላን መሃላ ቢፈርስ ምን ይሆናል?” ብሎ ጠየቀው። ድኩላም “በልጅ
ይደርሳል” አለው። ነብርም “አሃ! እንደዚህ ከሆነማ! ብሎ በድኩላው አካል
ላይ ተከመረበት። ድኩላም ባልሞት ባይ ተጋዳይነት ሲፈራገጥ ቀንዱ
በነብሩ ሆድ ላይ ተሰካ። ነብርም እያቃሰተ ‘መሃላ የሚደርስ በልጅ ነው’

135 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )V5


ብለኸኝ አልነበር” አለው። ድኩላም “ምናልባት አባትህ ምሎ ከድቶ እንደነበር
ማን ያውቃል?” አለው።

(ከበደ ሚካኤል፡- ታሪክና ምሳሌ 2ኛ መጽሐፍ ተሻሽሎ የቀረበ)

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. ከነብርና ከድኩላ የትኛው ኃይለኛ ይመስላችኋል? ለምን?

ለ. ነብር መሃላውን ሊያፈርስ የተቅበጠበጠው ለምንድን ነው?

የቃላት አጠቃቀም
“ነብርና ድኩላ” በሚለው ታሪክ ላይ ያለውን ሥዕል በማስተዋል በነብርና
በድኩላ መካከል ያሉትን ልዩነቶች ግለጹ።

ምሳሌ፡-

ነብር ድኩላ

መልኩ ዥንጉርጉር ነው። መልኩ ግራጫ ነው።

10.1.3 ማዳመጥ ጉልበት ወይስ ብልሃት

ቅድመማዳመጥ
ለቃላቱ ተመሳሳይ ፍቺ ስጡ።

ሀ. መሃላ ለ. ማፍረስ ሐ. ጉልበት መ. ብልሃት

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. ዔሊ ምን ዓይነት እንስሳ ትመስላችኋለች?

ለ. ጥንቸልስ ከዔሊ በምን ትለያለች?

136 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )V6


ሐ. ከተረቱ ምን ተማራችሁ?

ቃላት

ሀ. መምህራችሁ የሚያነቡላችሁን ቃላት ጻፉና አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ለ. ዔሊን አሸናፊ ያደረጋት ዘዴ ምን ነበር?

አቀላጥፎ ማንበብ
“የሌሊት ወፍ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

10.1.4 መጻፍ

1. ቃላቱን አቀላጥፋችሁ አንብቡና በደብተራችሁ ላይ በትክክል ጻፉ።

ሀ. እየተቅበጠበጠ ለ. እያብረቀረቀ ሐ. እየሞላ

2. ለቃላቱ ተመሳሳይ ፍቺ ስጡ።

ሀ. መከጀል ለ. ተቅበጠበጠ ሐ. አጣጣረ

3. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. መንፈራገጥ ለ. ሽርሽር ሐ. ማቃሰት

4. ሠንጠረዡን በደብተራችሁ አዘጋጁና በሚከተሉት ቃላት/ሐረግ


አሟልታችሁ ጻፉ።

ርግብ የሌሊት ወፍ ዐዞ ዝንጀሮ

ዓሳ እንቁራሪት ጉጉት

የሚያጠቡ እንቁላል የሚጥሉ

ƒƒ የሌሊት ወፍ ƒƒ ዓሳ

137 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )V7


10.1.5 ክለሳ

1. የአዕዋፍ ዓይነቶችን ዘርዝራችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ጉጉት

2. ስለዱር እንስሳት ታሪክ ወይም ገጠመኝ አስታውሱና ለክፍል ጓደኞቻችሁ


ተርኩላቸው።

3. “ነብርና ድኩላ” የሚለውን ታሪክ በየተራ ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተርኩ።

4. ጥያቄዎቹን በጽሑፍ መልሱ።

የምትኖረው የት ነው?

የምትተኛው እንዴት የምትበረው መቼ


የሌሊት ወፍ
ነው? ነው?

ከሌሎች ወፎች ለምን ተለየች?

10.2.1 ማዳመጥ ዋልያና ቀይ ቀበሮ

ቅድመማዳመጥ
ስለብርቅዬ የዱር እንስሳት የምታውቁትን ተናገሩ።

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ሥዕሉን አስተውሉና በዋልያና በቀይ ቀበሮ መካከል ያለውን ተመሳስሎና


ልዩነት ግለጹ።

ለ. ከዋልያና ከቀይ ቀበሮ የትኛው ያስደስታችኋል? ለምን?

138 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )V8


ቃላት

1. አቀላጥፋችሁ አንብቡና በትክክል ጻፉ።

ሀ. መሰሎቻቸውን ለ. የዱር እንስሳት ሐ. ቅጠላቅጠሎች

2. በምሳሌው መሠረት ነጥላችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- እንደቀጭኔ → እንደ - ቀጭኔ

ሀ. እንደዋልያ ሐ. እንደዝሆን

ለ. እንደአይጥ መ. እንደከበሮ

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ዶልፊንና ዐዞ
በዉኃ ውስጥ ከሚኖሩ እንስሳት መካከል
ዶልፊንና ዐዞ ይጠቀሳሉ። ሁለቱም የተለያየ
አፈጣጠርና ባህርይ አላቸው። ዶልፊኖች
ልክ እንደሰው፣ ሰዎችን የሚንከባከቡ፣
የሚወዱና የማይተናኮሉ ናቸው። ዐዞዎች ግን ሰዎችን በሹል ጥርሳቸው
የሚቀረጥፉ አደገኛ ፍጡሮች ናቸው። ዶልፊኖች እንደሌሎች አጥቢዎች
መሰላቸውን በመውለድ ይራባሉ። ዐዞዎች ደግሞ እንቁላል በማስፈልፈል
ይራባሉ። ዶልፊን በአንድ ጊዜ አንድ በመውለድና በማጥባት ታሳድጋለች።
ዐዞ ግን እስከአስራ ዐምስት እንቁላሎች በዉኃ ዳር በሚገኝ አሸዋ ውስጥ
ትጥልና ትቀብራለች። ጊዜው ሲደርስ አሸዋውን ትምሳለች። የሚፈለፈሉት
ዐዞዎች እንቁላሎቻቸውን ከውስጥ ሆነው በመስበር ይፈለፈላሉ። ከዚያም
እየተሯሯጡ ወደወንዙ ወይም ወደሐይቁ ይገባሉ።

139 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )V9


10.2.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ጉንዳንና ዋኔ ምን ዓይነት እንስሳት ይመስሏችኋል?

ጉንዳንና ዋኔ
ከዕለታት በአንድ ቀን ጉንዳን ለመሻገር ወደአንድ ጅረት አመራ። ወደወንዙ
ሲገባ የወንዙ ማዕበል ክፉኛ አንገላታው። ዋኔ በአፏ የቅጠል ዝንጣፊ ይዛ
በጅረቱ አናት ላይ ትበራለች። ዋኔዋም ጉንዳኑ ከወዲያ ወዲህ ሲንገላታ
አየችው። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ማዕበሉ እንደሚያሰጥመው ተረዳች። ዋኔዋ
በጉንዳኑ ትይዩ ዝቅ ብላ በመብረር የያዘችውን ዝንጣፊ ቅጠል ቁልቁል
ወረወረችለት። ጉንዳኑም በዝንጣፊው ቅጠል ላይ በመሆን ራሱን አዳነ። በሌላ
ቀን አንድ ልጅ ዋኔዋን በወጥመድ ያዛት። ዋኔዋም ለማምለጥ ስትፈራገጥ
ጉንዳኑ አያት። ቀስ ብሎ ተጠጋና የልጁን እግር ክፉኛ ነከሰው። ልጁ
ደንግጦ የወጥመዱን ገመድ ለቀቀው።

ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. ዋኔዋ ዝቅ ብላ በጉንዳኑ ትይዩ የበረረችው ለምንድን ነው?

ለ. ጉንዳኑ የልጁን እግር ክፉኛ የነከሰው ለምን ይመስላችኋል?

ሐ. በመጨረሻ ዋኔዋ ምን የምትሆን ይመስላችኋል? እንዴት አወቃችሁ?

የቃላት አጠቃቀም
በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ማዕበል ለ. ጅረት ሐ. ወጥመድ

140 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )#


10.2.3 ማዳመጥ “ዋልያና ቀይ ቀበሮ”

ቅድመማዳመጥ
ዋልያና ቀይ ቀበሮ ምን ዓይነት እንስሳት ይመስሏችኋል?

ድኅረማዳመጥ
ሀ. በምሳሌው መሠረት ጻፉ።

ምሳሌ፡- ቀይ ቀበሮ ቡችሎችን ትወልዳለች።

ዋልያ ዝሆን አንበሳ ድመት

ለ. ታሪኩ ዋልያን ከፍየል ጋር ያመሳሰላት ለምንድን ነው?

ሐ. ዋልያና ቀይ ቀበሮ ብርቅዬ የዱር እንስሳት የተባሉት ለምን ይመስላችኋል?

ቃላት

1. ቃላቱን አቀላጥፋችሁ አንብቡና ጻፉ።

ሀ. ብሔራዊ ሐ. ሥርዓት

ለ. ብርቅዬ መ. አመጋገብ

2. ቃላቱን በነጠላ ቁጥር ቅርጽ ጻፏቸው።

ምሳሌ፡- ቀበሮዎች → ቀበሮ

ሀ. ዋልያዎች ሐ. እንስሳዎች

ለ. ቡችላዎች መ. አጥቢዎች

አቀላጥፎ ማንበብ
“ዶልፊንና ዐዞ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

141 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )#1


10.2.4 መጻፍ

1. አጣምራችሁ ጻፉና አንብቡ።

ሀ. ቁ-ል-ቁ-ል ሐ. ሲ-ን-ገ-ላ-ታ

ለ. ዝ-ን-ጣ-ፊ መ. ስ-ት-ፈ-ራ-ገ-ጥ

2. በምሳሌው መሠረት መድረሻ ፊደሉን እየገደፋችሁ አዲስ ቃል ጻፉ።

ምሳሌ፡- ተረዳችው → ተረዳች → ተረዳ

ሀ. አየችው ሐ. ነከሰው

ለ. ያዘችው መ. ለቀቀው

3. ለቃላቱ ተቃራኒ ፍቺ ስጡ።

ሀ. ቁልቁል ለ. መንገላታት

ሐ. መወርወር መ. መንከስ

4. ቢጋሮቹን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ አሟልታችሁ ጻፉ።

አንበሳ ቀጭኔ

ስጋ ዕፅዋት
የሚመገቡ የሚመገቡ

142 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )#2


10.2.5 ክለሳ

1. መምህራችሁ የሚያነቡላችሁን ቃላት እያዳመጣችሁ ጻፉና አንብቡ።

2. የጉንዳንና የዋኔን ታሪክ ለክፍል ጓደኞቻችሁ በቃል ተርኩ።

3. በሚከተሉት ዓረፍተነገሮች መነሻነት ተገቢ ሥርዓተነጥቦችን በመጠቀም


አጭር አንቀፅ ጻፉ።

ƒƒ አንበሳ በጠና ታመመ።

ƒƒ አንበሳ ወደውስጥ ግቢ አላት።

ƒƒ ጦጣ ተጠራች።

ƒƒ ጦጣዋ ወደቤቷ ተመለሰች።

4. ጉንዳንና ዋኔ ያደረጉትን ትብብር በቅደምተከተል ግለጹ።

10.3.1 ማዳመጥ ይህን ታውቁ ኖሯል?

ቅድመማዳመጥ
ሥዕሉን አስተውሉና ስለታሪኩ ገምቱ።

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ዝሆን ግዙፍ አጥቢ እንስሳ የተባለው ለምንድን


ነው?

ለ. ዝሆኖች ከሌሎች እንስሳት በምን የሚለዩ ይመስላችኋል?

ሐ. የዝሆንን ታሪክ ባጭሩ ለጓደኞቻችሁ ተርኩ።

143 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )#3


ቃላት

1. አቀላጥፋችሁ አንብቡና ጻፉ።

ሀ. ኢ-ት-ዮ-ጵ-ያ ሐ. አ-ፍ-ሪ-ካ

ለ. ዓ-ለ-ማ-ች-ን መ. ኩ-ን-ቢ-ያ-ቸ-ው

2. በ“ሀ” ክፍል ላሉት ቃላት ተስማሚ የሆኑትን ከ“ለ” ክፍል መርጣችሁ


አዛምዱ።

“ሀ” “ለ”

1. ዝሆን ሀ. አፍንጫ

2. ቀጭኔ ለ. ስንጥብ

3. ዓሣ ሐ. ኩምቢ

አቀላጥፎ ማንበብ
የሚከተለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ቀጭኔ
ቀጭኔዎች በአፍሪካ አህጉር በብዛት የሚገኙ የዱር
እንስሳት ናቸው። እንደዝሆኖች ጡት አጥቢዎች ናቸው።
ሽሆናቸው ደግሞ እነደቀንድ ከብቶች መሀሉ ስንጥቅ
ነው። በምድር ላይ ከሚገኙ እንስሳት በርዝመታቸው
አንደኛ ናቸው። ወንዱ ቀጭኔ ከሴቷ ትንሽ ይረዝማል።
ቀጭኔዎች አንገታቸው እጅግ ረዥም ከመሆኑ የተነሳ
ከረዣዥም ዛፎች ቅጠላቅጠልንና ፍራፍሬን በመቀንጠስ
ይመገባሉ። የቀጭኔዎች ምላስም በጣም ረዥም ስለሆነ ጆሯቸውን ለማፅዳት
ያስችላቸዋል።

144 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )#4


10.3.2 አንብቦ መረዳት

ቅድመንባብ
ሠንጠረዡን በደብተራችሁ አዘጋጁና ስለጥርኝ የምታውቁትንና ማወቅ
የምትፈልጉትን በተመለከተ አሟልታችሁ ጻፉ።

ምሳሌ፡- ምን አውቃለሁ? ምን ማወቅ እፈልጋለሁ?


ƒƒ ሥጋ በል እንስሳ ናት ƒƒ የጥርኝን ጥቅም
ƒƒ ƒƒ

ጥርኝ
ጥርኞች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አጥቢ እንስሳት ናቸው። ጥርኞች ሥጋ
በል ከሆኑ እንስሳት ይመደባሉ። በአማካይ ከአንድ እስከአራት ቡችሎችን
በጉድጓድ ውስጥ ይወልዳሉ። የጥርኝ ቡችሎች በተወለዱ በዐምስት ቀናቸው
መራመድ ይችላሉ። ጥርኞች ከሰውነታቸው የሚያመነጩት ዝባድ የሚባል
ፈሳሽ አላቸው። ቡችሎቹ ከተወለዱ ከዐምስት ወራት ጀምሮ ዝባድ ያመነጫሉ።
ዝባዱ ደስ የሚል ጠረን አለው። ዝባዱን የሚይዙት ከመፀዳጃቸው ጥግ ባለ
ከረጢት መሰል አካላቸው ውስጥ ነው። ዝባዱ በመጀመሪያ ቢጫ የመሰለ
ቅባት ሲሆን እየቆየ ሲሄድ ይጠጥርና ጥቁር ቡናማ መልክ ይኖረዋል።
ሰዎች የጥርኝን ዝባድ ለማግኘት ጥርኞችን በየቤታቸው ያረቧቸዋል።
ዝባዱም ከሌሎች ንጥረ ነገሮች ጋር ተቀምሞ ሽቶ ይሆናል።

145 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )#5


ድኅረንባብ
ጥያቄዎቹን በታሪኩ መሠረት በጽሑፍ መልሱ።

ሀ. ሠንጠረዡን በደብተራችሁ አዘጋጅታችሁ በታሪኩ መሠረት አሟልታችሁ


ጻፉ።

ምን ተማርኩ?
ƒƒ ጥርኝ የምታመነጨው ፈሳሽ ዝባድ ይባላል።
ƒƒ
ƒƒ

ለ. ልክ እንደጥርኝ ለሰው ልጆች ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኙ የዱር እንስሳትን


ዘርዝሩና ጥቅማቸውንም ግለጹ።

ሐ. ሠንጠረዡን በደብተራችሁ አዘጋጁና አሟልታችሁ ጻፉ።

ከሰውነታቸው የሚወልዱት ቡችሎቹ መራመድ


ዓይነት የሚመገቡት
የሚያመነጩት ቡችላ ብዛት የሚጀምሩት
ጥርኝ

የቃላት አጠቃቀም
ሥዕሎቹን በማስተዋል ልዩነታቸውንና ተመሳስሏቸውን ግለጹ።

146 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )#6


10.3.3 ማዳመጥ ይህን ታውቁ ኖሯል?

ቅድመማዳመጥ
ለቃላቱ ፍቺ ስጡ።

ሀ. ዝርያ ለ. ኩምቢ ሐ. ባህርይ

ድኅረማዳመጥ
ጥያቄዎችን በታሪኩ መሠረት በቃል መልሱ።

ሀ. ሴቷ ዝሆን ለስንት ዓመታት ያህል በእርግዝና ትቆያለች?

ለ. ከዝሆን የተረዳችሁትን ጥሩና መጥፎ ባህርያት ግለጹ።

ሐ. ስለዝሆኖች ባህርይ የተገለፀው በየትኛው የታሪክ ክፍል ነው?

ቃላት

1. ድምፅ በማሰማት አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

ሀ. በ-ር-ዝ-መ-ታ-ቸ-ው ሐ. ጆ-ሯ-ቸ-ው-ን

ለ. አ-ን-ገ-ታ-ቸ-ው መ. ያ-ስ-ች-ላ-ቸ-ዋ-ል

2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. መተንፈስ ለ. መሸከም ሐ. ማሽተት

አቀላጥፎ ማንበብ
“ቀጭኔ” የሚለውን ታሪክ አቀላጥፋችሁ አንብቡ።

10.3.4 መጻፍ

1. ቃላቱን አቀላጥፋችሁ አንብቡና በትክክል ጻፉ።

ሀ. መፀዳጃ ለ. ዝባድ ሐ. ጥርኝ መ. ቡችሎች

147 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )#7


2. በሚከተሉት ቃላት ዓረፍተነገር መሥርቱ።

ሀ. ጥርኝ ለ. ቅባት ሐ. ሽቶ

3. ቃላቱን በነጠላ ቁጥር ለውጣችሁ ጻፉ።

ሀ. ጥርኞች ሐ. ከረጢቶች

ለ. ቡችሎች መ. እንስሶች

4. በ“ሀ” ክፍል ላሉት ቃላት ተቃራኒ ከ“ለ” ክፍል መርጣችሁ አዛምዱ።

“ሀ” “ለ”

1. ሴት ሀ. ድፍን

2. ትልቅ ለ. የቆሸሸ

3. ረዥም ሐ. ወንድ

4. የፀዳ መ. ትንሽ

5. ስንጥቅ ሠ. አጭር

ረ. ከባድ

5. ዝሆንና ቀጭኔን በማወዳደርና በማነጻጸር ግለጹ።

የዱር
ዝሆን ቀጭኔ
እንስሳት
በኩምቢው በአፍንጫዋ
ናቸው።
ይተነፍሳል። ትተነፍሳለች።

148 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )#8


10.3.5 ክለሳ

1. መምህራችሁ የሚያነቡላችሁን ሐረጋት እያዳመጣችሁ ጻፉ።

2. “ጥርኝ” የሚለውን ታሪክ ድምፅ በማሰማት በየግላችሁ በትክክል፣


በፍጥነትና በጥሩ አገላለጽ አንብቡ።

3. የምትወዱትን ተረት በክፍል ውስጥ ተርኩ።

4. በሚከተሉት ነጥቦች መሠረት በቡድን ሆናችሁ አጭር አንቀጽ ጻፉ።

ƒƒ ምንነት

ƒƒ አፈጣጠር

ƒƒ ጥቅም

ƒƒ ከሌሎች እንስሳት የሚለይበት ባህርይ

5. በዚህ ምዕራፍ ካነበባችኋቸው ታሪኮች አንዱን መርጣችሁ ዋና ዋና


ሐሳቦችን በመለየት ጻፉና አንብቡ።

149 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ምዕራፍ 10 የዱር እንስሳት )#9


ዋቢዎች

ስዩም ታደሰ። (1998)። ተረት ተረት አንደኛ መጽሐፍ። አዲስ አበባ።

ትምህርትና ስነ ጥበብ ሚኒስቴር። (1959)። ለማ በገበያ። አዲስ አበባ።

ትምህርትና ስነ ጥበብ ሚኒስቴር። (1959)። ታሪክና ምሳሌ 1ኛ መጽሐፍ። አዲስ አበባ።

ትምህርትና ስነ ጥበብ ሚኒስቴር። (1959)። ታሪክና ምሳሌ 3ኛ መጽሐፍ። አዲስ አበባ።

ትምህርት ሚኒስቴር። (2006)። አማርኛ እንደአፍ መፍቻ ቋንቋ የተማሪ መጽሐፍ። አዲስ አበባ።

ትምህርት ሚኒስቴር። (2006)። አማርኛ እንደአፍ መፍቻ ቋንቋ የመምህር መጽሐፍ። አዲስ አበባ።

ትምህርት ሚኒስቴር። (1975)። የአማርኛ መማሪያ 2ኛ ክፍል። አዲስ አበባ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ። (1996)። የአማርኛ 2ኛ ክፍል መማሪያ
መጽሐፍ። ባሕር ዳር።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ። (1996)። የአማርኛ 3ኛ ክፍል መማሪያ
መጽሐፍ። ባሕር ዳር።

አቢ ደስታ። (2005)። አፌን በዳቦ አብሱ። አዲስ አበባ። ዜድ ኤ ማተሚያ ቤት።

አቢ ደስታ። (2004)። ተረቴን መልሱ። አዲስ አበባ

አስክንድር ስዩም። (2008)። አንበሳውና ዳክዬዎች። አዲስ አበባ። ኤች.ኬ.ኃላ/የተ/የግ/ማህበር።

እንዳለ ጌነቦ። (2011)። የተረት ሙዳይ። አዲስ አበባ።

ዘሪሁን አስፋው። (1992)። የሥነ ጽሑፍ መሠረታውያን። አዲስ አበባ። ንግድ ማተሚያ ድርጅት

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ። (2011)። እንቆቅልሽ ጨዋታ። ጎንደር።

150 አማርኛ 2ኛ ክፍል ~ የተማሪ መጽሐፍ ~ ዋቢዎች )$

Вам также может понравиться